Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
እንኳንም ዱኒያ ሆንሽ ...
ምን ብታምሪ ዱኒያ ነሽ ብለን ባንብቃቃ ኑሮ በዱኒያ ከፍና ዝቅ ልባችን እጅጉን ባዘነች እጅግ በተከፋችብን ነበር ....
ያረቢ ዱኒያ ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው አንተ ጋር ያለው ግን ቀሪ ነው 💛
ለዱኒያ ብዙ ሳንጨነቅ ብዙም ሳንደክምላት ምንኖርበትን.....
ወደ አንተ ምንቀርብበትን... ሪዝቅ ብቻ ስጠን🤲🏼

https://www.tgoop.com/muslimprincess2024
ልባቹ ንፁህ ብትሆን ከ ጌታቹ ቃል( ቁርአን ) ባልጠገባቹ ነበር ።
🔘ዑስማን ኢብኑ አፋን ረዲየላሁ አንሁ
የተባረከው የረመዳን ወር ከደጅ ቆሟል! አንቺስ ተዘጋጅተሻል?

ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿أتاكم شهرُ رمضانَ شهرٌ مباركٌ فرض اللهُ عليكم صيامَه، تفتحُ أبوابُ السماءِ، وتغلقُ فيه أبوابُ الجحيمِ، وتغلُّ فيه مردةُ الشياطينِ، للهِ فيه ليلةٌ خيرٌ من ألفِ شهرٍ من حرمَ خيرَها فقد حُرِم.﴾

“የረመዳን ወር መጣላችሁ፤ የተባረከው ወር። አላህ በናንተ ላይ እንድትፆሙ ግዴታ ያደረገባችሁ፤ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት፣ ሸይጣኖች የሚታሰሩበት። በዚህ ወር ውስጥ ከአንድ ሺህ ሌሊት ብልጫ ያላት ሌሊት አለች፤ የሷን መልካም ነገር የተነፈገ በርግጥም መልካም ከሆነ ነገር ተንፍጓል።”

📚 ነሳዒ ዘግበውታል: 4/129
የሚረዝቀኝ በዒባዳየ ልክ ቢሆን ኖሮ አንዲት ጉርሻ እንኳ ባልደረሰኝ ነበር!!
እዝነትህ ቀና አረገኝ ያረብ!!
Forwarded from ابن ابي حبيب(መርከዝ አቡ ሙስሊም) (ابو مسلم حبيب بن سعيد الحبشي)
ቆንጆ ብትሆኚ ገዳይ በውበትሽ
ታምሪያለሽ እያሉ ሺ ወንዶች ቢያንደንቁሽ

እወቂ የኔ እህት
ጸባይዲን ከሌለሽ
በኒቃብጂልባብ በደንብ ካልተሸፈንሽ
ሲም የሌለው ቀፎ ቁመና ብቻ ነሽ።

ቻናል:-www.tgoop.com/habibseidabumuslim
📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለ ረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዿን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዷንን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዷን
የኔ ዉድ ኢስላም የሰጠሽን ቦታ ታውቂዋለሽ?
መልስሽ አዎ ወይም አይ ሊሆን ይችላል
ዛሬ እኔ የሰማሁትን ልነግርሽ ነውና በትኩረት አዳምጪኝ
→በኢስላም በስምሽ አንድ ሱራ ተጠርቷል
→አንቺ ነሽ የመጀመሪያዋ ሸሂድ!
→ነብዩም ሰ.አ.ወ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ አደራ በመልካም ያዙአቸው ያሉት አንቺን ነው
→የማህበረሰቡ ግማሽ ነሽ ይላሉ ነገር ግን ፈፅሞ ያላንቺ አይሞሉም!!
ውዴ ምን አተለቀው ደረጃሽ?
አንቺ እናት ነሽ!!
አንቺ ሚስት ነሽ!!
አንቺ እህት ነሽ!!
ባጠቃላይ ሙሉ ማህበረሰብ ነሽ!!
→አንቺ በህፃንነትሽ የወላጆችሽ ጀነት ነሽ
→ትዳር ስትይዢ የባልሽ ግማሽ ኢማን ነሽ
→እናት ስትሆኚ ጀነት በእግርሽ ስር ናት
ሴትን አታከብሩም የተከበራቹ ብትሆኑ እንጂ
ሴትን አታዋርዱም የተዋረዳቹ ብትሆኑ እንጂ
ረሱል ሰ.አ.ወ
እና ውዴ እድለኛ አይደለውም ብለሽ ታስቢያለሽን? አልሀምዱሊላህ በይስኪ እህቴ ይሄን ሁሉ ኒዕማ ለሰጠሽ ጌታ!!!!

https://www.tgoop.com/muslimprincess2024
ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أتاكم شهرُ رمضانَ شهرٌ مباركٌ فرض اللهُ عليكم صيامَه، تفتحُ أبوابُ السماءِ، وتغلقُ فيه أبوابُ الجحيمِ، وتغلُّ فيه مردةُ الشياطينِ، للهِ فيه ليلةٌ خيرٌ من ألفِ شهرٍ من حرمَ خيرَها فقد حُرِم.﴾

“የረመዳን ወር መጣላችሁ፤ የተባረከው ወር። አላህ በናንተ ላይ እንድትፆሙ ግዴታ ያደረገባችሁ፤ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት፣ ሸይጣኖች የሚታሰሩበት። በዚህ ወር ውስጥ ከአንድ ሺህ ሌሊት ብልጫ ያላት ሌሊት አለች፤ የሷን መልካም ነገር የተነፈገ በርግጥም መልካም ከሆነ ነገር ተነፍጓል።”

ነሳዒ ዘግበዉታል 4/129

https://www.tgoop.com/muslimprincess2024
﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد
ሰበር
======
የረመዷን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ቅዳሜ የካቲት 22, 2017 E.C. የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።


አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዷን ሙባረክ!
አላህ ሆይ!
የዚህን ዓመት ረመዳን ካለፉት ዓመታት የተለየ አድርግልን። ከእንቅልፍና ከገፍላ አንቃን።
በሞተው የቀልባችን ሬሳ ውስጥ ሩኅ ዝራበት። ወንጀላችንን ማረን። ጭንቀታችንንም ገላግለን!
አሚን!
💎 የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
“ ከናንተ አንዳችሁ ወደ በርሃ ሲጓዝ ስንቁን ተሸከማ (የነበረች) ግመሉ (የጠፋበትን ስንቅ ተሸክማ) (ድንገት) ብትመለስ ከሚደሰተው በላይ አላህ አንድ ባሪያው ወደርሱ በንስሓ
በሚመለስበት ጊዜ በጣም ይደሰታል።»

📚ቡኻሪና ሙስሊም
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“ለፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት። ደስታዎችም፦ ማታ ሲያፈጥር በማፍጠሩ የሚደሰተውና በአኼራ ጌታውን ሲገናኝ በፆሙ የሚደሰተው ነው።”
ጾም ሆድን ከምግብ ብቻ ሳይሆን አእምሮን ከሐሳብ፣ ምላስን ከውሸት፣ አይንን ከመጥፎ እይታ መጠበቅ ነው።"
ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ)
ሰላትን ሳይሰግድ ረመዳንን የሚጾም ሰው አላህ ከሱ ያለመብላትና ያለመጠጣት ጉዳይ የለውም።
2025/03/03 11:42:56
Back to Top
HTML Embed Code: