tgoop.com/nahuseman25/755
Last Update:
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_3
#ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ጥብርያዶስ
➯ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደ ሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው:: "ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ ለምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት።" "ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው::" ንጉሡም እመቤታችንን "ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት።" ቤተሰቦቹንም "ማርያምን ከእርሱ ቤት መኖርዋን ለማንም እንዳይነግሩ አስጠነቀቃቸው።" ሄሮድስ ግን በብዙ አገሮች እየዞረ ቢፈልጋት ሊያገኛት አልቻለም፡፡ ሄሮድስ እንዲህ ይል ነበር ማርያምን ምድር ዋጠቻትን።
➯ሄሮድስ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ያደረገው ጥረት የደከመው ድካም እጅግ ብዙ ነው። ያለውን ኃይል አሟጦ ተጠቅሟል የሚፈልገውን አለማገኘቱ ደግሞ ድካሙን ውጤት አልባ አድርጐታል።
➯ከብዙ ቀናት በኋላ ሄሮድስ ጥብርያዶስ በሚባል አገር እመቤታችን መኖርዋን ሰማ፡፡ እመቤታችን ወደ አለችበት ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ መልእክተኛ ላከ፡፡ ሄሮድስ የጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል "ንጉሥ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል #ማርያምን_ከነልጅዋ ያዝልኝ ብዙ ወርቅ እና ብር እሰጥሃለሁ በእኔ እና በአንተ መካከል ጽኑ ፍቅር ይሆናል።" ንጉሡም የሄሮድስን ደብዳቤ አንብቦ በጣም ተገረመ። እንዲህም አለ "ማርያም በእኔ ቤት መኖርዋን ለሄሮድስ ማን ነገረው መቼም ሰው አልነገረውም ሰይጣን ነግሮታል እንጂ።" የእመቤታችን ዘመድ የሆነው ንጉሥም ሄሮድስ የላከውን መልእክት ለእመቤታችን ነገራት። እመቤታችንም በጣም ደነገጠች።
➯ንጉሡም "እኔ ከሞትኩ ትሞቻለሽ እኔ ከዳንኩ ትድኛለሽ አትፍሪ ለሄሮድስ አሳልፌ አልሰጥሽም አላት፡፡" "ወትቤ ማርያም ዘፈቀደ አምላከ እስራኤል ለይኩን /ማርያምም የእስራኤል አምላክ የፈቀደው ይሁን አለች፡፡"
➯በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ "ሲነጋ ይህን አገር ለቀሽ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂጂ አላት፡፡ በዚያም እኔ መጥቼ ተነሺ እስክልሽ ድረስ ተቀመጪ አላት።" በነጋ ጊዜ መልአኩ የነገራትን ለንጉሡ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ደስ ብሎት የሦስት ቀን መንገድ እስከ ዛብሎን እና እስከ ንፍታሌም ድረስ ሸኛት። ከዚህ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡
#ክፍል_አራት_ይቀጥላል.....
BY ናሁ ሰማን(Nahu seman)
Share with your friend now:
tgoop.com/nahuseman25/755