tgoop.com/news_et/19
Create:
Last Update:
Last Update:
" በአሜሪካ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን " ሌኒ ዮሮ
የማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ሌኒ ዮሮ በዛሬው የወዳጅነት ጨዋታ ባሳየው እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆኑን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።
" ዛሬ ባደረግኩት እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ በዚህ እንደምቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ " ያለው ሌኒ ዮሮ " የቡድኑ ስሜት ደስ ይላል እሮብ አሜሪካ ሄደን ሶስት ጨዋታዎች እናደርጋለን ፣ ሁሉንም ለማሸነፍ የቻልነውን እናደርጋለን " ብሏል።
ማንችስተር ዩናይትድ በአሜሪካ ቆይታው ከአርሰናል፣ ሪያል ቤቲስ እና ሊቨርፑል ጋር በተከታታይ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል።
BY Et News

Share with your friend now:
tgoop.com/news_et/19