Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 6

ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ።የዓለም ሁሉ መድኃኒት ዛሬ ተወለደ።አንድም ስለሁሉ ዓለም ዛሬ ተወለደ ይላል።ዓለም
በጭንቅ የነበረበት ዘመን ዘመነ ብሉይ ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ በመባል ይታወቃል።ምንም እንኳ ጻድቃንን የሲኦል እሳት በጸጋ እግዚአብሔር ባያገኛቸውም ይኖሩ የነበሩት ግን በሲኦል ነበር።ቅዱሳን ነቢያት ጽድቃችን እንደመርገም ጨርቅ ሆነ ብለዋል።ምንም ጽድቅ ቢሰሩ መግቢያቸው ሲኦል ነበርና እንዲህ
በምሳሌ ተናገረው።ስለዚህ ሰውን ሁሉ ለማዳን የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ።በኀዘን ለነበረው ሰው መልአኩ ለእረኞች ወይም ለኖሎት እንደነገራቸው በሉቃስ ወንጌል እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘይከውን ለክሙ ዓቢየ ፍሥሓ ብሎ ታላቅ ደስታ የሚሆንላችሁ እነሆ መድኃኒት ተወልዶላችኋል።ብሎ በሥቃይ በኀዘን የነበሩ ሰዎች በክርስቶስ ልደት እንደተደሰቱ ይናገራል። የተደሰቱትም መላእክትም ጭምር ናቸው ምክንያቱም መላእክት እንደ ታላቅ ወንድም ናቸውና የእኛ መዳን ቢያስደስታቸው።ስብሀት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ ብለው አመስግነዋል።በአንድ ኃጥእ በንሥሓ መመለስ በመላእክት ዘንድ ደስታ ይሆናል ይላል።በኃጥእ አዳም ወደ ገነት መመለስ ተደስተዋልና ነው።ይሁንና አዳነን ስንል ምን ማለታችን ነው ስንል በመዳን ሂደት ውስጥ የእግዚአብሔር ድርሻ አለ።ከእኛም የሚጠበቅ ድርሻ አለ። በእግዚአብሔር በኩል ያለው የመዳን ሂደት ሙሉ በሙሉ ተደረገ ማለት ነው።ከዚህ በኋላ የእኛ ድርሻ ይጠበቅብናል።ድርሻችንንም ራሱ እንዲህ እንዲህ አድርጉ እያለ ነግሮናል።ለምሳሌ ያልተጠመቀ አይድንም ተብለናል ስለዚህ መጠመቅ የእኛ ፈንታ ነው ማለት ነው።ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ህይወት የለውም ብሏል ስለዚህ ሥጋውን ደሙን መቀበል የእኛ ፈንታ ነው ይህንና ይህን የመሳሰሉ ከእኛ የሚጠበቁ ድርሻዎች አሉ።እነዚህን ሳናደርግ ብንቀር ችግሩ ከእኛ እንጂ እግዚአብሔር አላዳነንም ተብሎ ሊተረጎም አይገባም።ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ። የደስታችን ምንጭ ዛሬ ተወለደ ስለዚህ ሰብአ ሰገል ሄደው አይተው ተደሰቱ።መላእክት አመሰገኑ እረኞች አይተው ደስ አላቸው።ስለዚህም ሊቃውንቱ በማኅሌት ርእይዎ ኖሎት
አእኮትዎ መላእክት..... አንፈርአጹ ሰብአ ሰገል እያሉ በቅዱስ ያሬድ ማህሌት ደስታቸውን ይገልጻሉ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 16 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 7
      ©የመጨረሻ ክፍል©
ተወለደን ተጸነሰ ይቀድመዋል።ተጸነሰን ደግሞ በቅድምና ነበረ የሚለው ይቀድመዋል።ጌታ ሰው ሲሆን ሥጋን ከሰማይ ይዞ ወረደ አንልም ከእመቤታችን ነሳ እንላለን እንጂ።ከሰማይ ይዞት ከወረደማ ከእመቤታችን ተወለደ አያሰኝም ስለዚህ ከሰማይ ሥጋን ይዞ ወረደ የሚለው አያስኬድም።አምላክ ሰው ሆነ ሰው
አምላክ ሆነ ስንል ተዋሕዶው እንዴት ነው ቢሉ።በምሳሌ ዘየሐጽጽ እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ ነው።ሰው ነፍስና ሥጋ ቢኖሩትም አንድ ሰው ይባላል እንጂ ሁለት አይባልም።ሰው መባል የሁለቱ ተዋሕዶ ውጤት ነው።ይህንንም ሰፋ አድርገን ስንመለከተው ለምሳሌ የሚራብ የሚጠማ ሥጋችን ነው ወይስ
ነፍሳችን? ነፍሳችን ነው እንዳይባል።የሰው ልጅ በነፍሱ
እንደመላእክት እንደሚኖር ተገልጹዋል መላእክት ደግሞ አይበሉም።ስለዚህ ነፍስ አትበላም ማለት ነው። ሥጋ ነው
የሚራብ የሚጠማ እንዳንል።ነፍስ የተለየችው ሥጋ አይራብም አይጠማም።ስለዚህ የተራበው የተጠማው ማን ነው ስንል? ሰው ነው።ይህንንም የቃል እና የሥጋ ተዋሕዶ በዚህ አምሳል ነው።ቃል በሥጋ ተራበ ተሰቀለ እንላለን።ሥጋ በቃል ረቀቀ መላ
እንላለን ከተዋሕዶ በኋላ ለያይተን አንናገርም።እንግዲህ ልደት ሲነሳ የወለደችው እናቱም ትነሳለች።ማርያም ግን በልቧ ትጠብቀው ነበር ይላል።የሚደረገውን ምስጢር እያየች
እንደዘመናችን ሰው ልናገረው አትልም ነበር።በልቧ ትጠብቀው ነበር ብሎ ወንጌላዊ ሉቃስ ገልጾልናል።ጌታን ከእመቤታችን የበለጠ የሚያውቀው ሰው የለም።እናቱ ናት አንዳንዶች እናቱን
ሲሳደቡ ያሳዝናሉ በእውነት።እናት እና አባትህን አክብር ብሎ ሕግን የሰራ ጌታን እናቱን ካከበረ መናፍቃን ግን እርሷን
መጥላታቸው።የእምነታቸውን መሰረት ሰይጣናዊነት ከማስረዳት ውጭ ሌላ አያስገነዝበንም።

ጌታ እኔን ምሰሉ ብሎ እርሱን እድንመስል ሕግን እየሰራ አሳይቶናል።ስለዚህ እናቱንም እንወዳታለን እርሱንም እንወደዋለን እንጂን አንዱን ጥለን አንዱን አንጠልጥለን አንሄድም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
ጥቅምት 16 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
ስለ ትዳር ክፍል 1
እሷን ለማግባት መሠረታዊ ምክንያቱ "መልክ" ከሆነ በእሳት አደጋ ወይም በመኪና አደጋ ወይ በሌላ ምክንያት ፊቷ ቢበላሽ ወይም አካሏ ቢጎድል ይፈታታል።ወይም እርሷን ለማግባት መሠረታዊ ምክንያቱ "ገንዘብ/ሀብት" ከሆነ በተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ አደጋ ንብረቷ ቢጠፋ ይፋታታል።ወይም ደግሞ እውቀቷን አይቶ ቢያገባት ይህም ቢሆን እውቀት ጸጋ ስለሆነ በእርጅና በሕመም ሊጠፋ ይችላል። ስለዝህ እውቀቷ ሲጠፋ ይፋታታል።

ታድያ ምንን አይተን እንጋባ?
በእርግጥ መጀመሪያውንም ትዳርን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሲሰጥ ዋና እና መሠረታዊ ምክንያቱ 3 ነው። ይኽውም ዘር ለመተካት፥ ለመረዳዳት፥ እና አንድ ለአንድ ተወስኖ የፈቲው ጾርን ለማሸነፍ ነው።የሰው ልጅ ሲፈጠር ብዙ ዓይነት ፍላጎቶች እንዲስማሙት ተደርጎ ነው የተፈጠረው።ለምሳሌ የመብላት ፍላጎት አለው።ለዚህ ፍላጎቱ ምግብ ተሰርቶለታል።ሴት ከወንድ ወንድ ከሴት በመኝታ አንድ የመሆን ፍላጎት አለው።ለዚህ ፍላጎቱ ደግሞ ትዳር ተሠርቶለታል።ለሁሉም ፍላጎቶቻችን ደግሞ ድንበር ሥርዓት ተሠርቶልናል። ይኸውም ለትዳር አንድ ሴት ለአንድ ወንድ ነው።ሌላው ለመረዳዳት ነው። የሰው ልጅ በብዙ ረገድ ፍጹም ስላልሆነ ረዳት ያስፈልገዋል።ከአንድ ሁለት ይሻላል። አንድ ሊቅ፦

ሐንካስ በእግረ እውር ሖረ።
እውርኒ በዓይነ ሐንካስ ነጸረ።
ወበክልኤሆሙ ወይንየ ተመዝበረ።

ብለዋል ምስጢሩ መተባበርን ለመግለጽ ነው።አንካሳ በእውር እግር ሄደ።እውር ደግሞ በአንካሳ ዓይን አይቶ በጋራ ሆነው ሥራ መስራት እንደቻሉ ያሳያል። ስለዚህ ለመጋባት ተፈጥሯዊ የሴት እና የወንድ መሳሳብ፥ እንዲሁም በሃይማኖት አንድ መሆን፥ በእድሜ ተቀራራቢ መሆን፥ በቂ ነው። ሌላው እና ዋናው ግን እስከ ሞት የሚዘልቅ ፍቅር ሊኖረው ይገባል።

ብትነጫነጭበት፥ ብትቀማጠልበት፥ ብትሸራከት፥ ብትሰድበው፥ ወዘተ ከሌላ ወንድ ጋር እስካልተኛች ድረስ ይህንን ገራገር ሆኖ በትእግስት እየወደዳት እንክብካቤ እያደረገላት እስከ መጨረሻው ሊቀጥሉ ይገባል።ሚስትም ለባሏ ይህንኑ ማድረግ አለባት። ንብረታቸው ቢጠፋና ጎዳና ቢያድሩ፥ በተለያየ ምክንያት በጦርነት በሕመም በቦታ ቢለያዩ እስካሉ ድረስ ሊለያዩ አይገባም። ሌላው ግን አንዱ ሠራተኛ አንዱ ተቀማጭ መሆን የለባቸውም። በተቻለ መጠን ራሳቸውን ለማኖር ጠንክረው መስራት እና ልጆቻቸውን በጥሩ አስተዳደግ ማሳደግ አለባቸው።

ጌታ ምእመናንን እንዴት እንደሚወዳቸው ምእመናንን ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እንደሚወዳት ለመግለጽ በሙሽራ እና በሙሽራይቱ መስሎ ተናግሮታል።ይህም የሚያሳየን ትዳር ሁለት ሰዎች አንድ የሚሆኑበት ነው።

ክፍል 2 ይቀጥላል።
ትዳር ክፍል

በቁርባን ያልተደረገ ጋብቻ ቁጥሩ ከዝሙት ነው እንጂ እንደ ትዳር አይቆጠርም።እጮኝነት የዝግጅት ጊዜ ነው።በእጮኝነት ጊዜ ምንም ዓይነት የመኝታ ግንኙነት ሊኖር አይገባም። እጮኝነት የልቤ ንግሥት፥ የኔ ማር የሚባባሉበት ሳይሆን ስለወደፊት ሕይወት በጥልቀት የሚወያዩበት ጊዜ ነው። ከትዳር በፊት የሚደረግ ግንኙነት ቁጥሩ ከዝሙት ነው። ድንግልናቸውን ጠብቀው ለሚያገቡ ሰዎች ሥርዐተ ተክሊል ተደርጎላቸው ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ይጋባሉ። ነገር ግን የሰው ልጅ ብዙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎች ስላሉበት ከትዳር በፊት ግንኙነት ያደረጉ ሰዎች ካሉ ደግሞ ንሥሓ ገብተው ጸሎተ መዓስባን ተደግሞላቸው ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ይጋባሉ። ከተጋቢዎች አንዱ ድንግል አንዱ ደግሞ ድንግል ካልሆነ ደግሞ ድንግል ለሆነው ተክሊል ተደርጎለት ድንግል ላልሆነው ሳይደረግለት ሥርዐቱ ይከናወናል። ከሠርግ በፊት ባልና ሚስት ትዳራቸው ይባረክላቸው ዘንድ 40 ቀን መጾም አለባቸው።

ያለ ቁርባን መጋባት የመጣው ከግራኝ መሐመድ መነሳት ወዲህ እንደሆነ ይነገራል።ነገር ግን ያለ ቁርባን የሚደረግ ሠርግ እና ጋብቻ ቁጥሩ ከዝሙት ስለሆነ ይህንን ነገር ካህናት ተገንዝበው በገጠርም በከተማም ማንኛውም ክርስቲያን የሆነ ሰው በቁርባን እንዲያገባ ሊያደርጉ ይገባል። ይህንን ባያደርጉ ግን በፈጣሪ ዘንድ ተጠያቂ ይሆናሉ።ሌላው በትዳር ጊዜ እድሜ ለሴት ቢያንስ 15 ዓመት ሊሆናት ይገባል።ለወንዱም ቢያንስ 22 ዓመት ሊሆነው ይገባል። በፍትሐ ነገሥቱ መሰረት ይህ ምናልባት ተመችቷቸው ያደጉ ሴቶች ካሉ ቢያንስ 12 ዓመት ወንዱ ደግሞ 18 ዓመት ሊሆን እንደሚገባ ፍትሐነገሥት አንቀጽ 24 በሰፊው ይገልጻል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጎይታይ በጃካ ንጸሎተይ ተመልከቶ
ስለ ትዳር ክፍል 4

እሷ ወይም እሱ  ሩካቤ ማድረግ የማይችል/የማትችል ከሆነ ቢፋቱ ይቻላል ነውርነት የለውም።  ሚስቱ ጽንሷ ከታወቀ በኋላ ሩካቤ የሚያደርግ ወንድ የተጸነሰው ወንድ ቢሆን ግብረ ሰዶም ሴት ብትሆን ደግሞ ከልጁ እንደ ደረሰ ይቆጠራል።በወር አበባ ጊዜ፣ በጽንስ ጊዜ፥ በአጽዋማት ጊዜ፥ በዐበይት በዓላት ጊዜ፥ ሥጋውን ደሙን ከመቀበላቸው በፊት እና በኋላ ባሉት 3/3 ቀናት፥ በአራስነቷ ጊዜ፥ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም። ካህናት ሁለተኛ ካገቡ ብዙ ቀኖና ተሰጥቷቸው ከክህነታቸው ይሻራሉ። ሦስተኛ ካገቡ ግን ከክርስቲያንነታቸው ተወግዘው ይለያሉ። ክህነት የሌለው ምእመን አንድ ካገባ በኋላ በሞት ወይም በዝሙት ምክንያት ሌላ ሚስት ያገባል።ይህች ሁለተኛ ሚስቱም በዝሙት ወይም በሞት ብትለየው ታላቅ ቀኖና ተሰጥቶት ሦስተኛ እንዲያገባ ይፈቀዳል።ከሦስትኛ ሚስቱ በላይ አራትኛ ጊዜ ካገባ ግን ይወገዛል።

ከተጫጩ በኋላ ምናልባት ሴቲቱ ወይም ወንዱ የማግባት ሐሳቡን ቢቀይር እስካልተጋቡ ድረስ ነውር የለበትም። ሌላ ማጨትም ይችላል።ልመንኩስ ካለም መመንኮስ ይችላል። ነገር ግን ከተጋቡ በኋላ በዝሙት ካልሆነ በስተቀር ሊፋቱ አይገባም።ምናልባት አንዱ ልመንኩስ የሚል ሀሳብ ቢያቀርብ ባለቤቷ/ባለቤቱ ካልፈቀደችለት አይችልም። ባልና ሚስት ተመካክረው እንመንኩስ ቢሉ ወይም አንዱ ለአንዱ ከፈቀደለት ግን ይችላል።

የተፈቀደ ፍቺ
ባሏን ወይም ሚስቱን ሌላ ሰው ሊገድለው/ላት እንዳቀደ ሰምቶ ወይም ሰምታ ካልነገረችው ወይም ካልነገራት ይፋቱ ይላል ፍትሐነገሥት።በተጨማሪም ከላይ እንደገለጽኩት ሴቲቱ ወይም ወንዱ ሩካቤ ማድረግ የማይቻለው ወይም የማይቻላት ከሆነ ትዳር ይፈርሳል።መፋታት ይችላሉ።
ትዳርና የወሊድ መቆጣጠሪያ ክፍል 5
......ባለቤቴ እና እኔ ኑሯችን ከእጅ ወደ አፍ ነው።እንኳን ልጅ ወልደን ማሳደግ ራሳችንንም ማኖር እየከበደን ነው።ስለዚህ ጥሩ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ የወሊድ መቆጣጠሪ እንጠቀማለን።ይህ አይፈቀድም ወይ...... የሚል ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይነሳል። በነገራችን ላይ የወሊድ መቆጣጠሪያ ካደረገች ሴት ጋር ሩካቤ ማድረግ ማለት በኮብል ስቶን ላይ ጤፍ እንደመዝራት ያለ ነው። ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ እንዲህ ይላል "ሚስቱ እንዳትወልድ መድኃኒትን ያደረገ ሰው ታላቅ በደልን በደለ" ይላል።መነኩሴ ሲመነኩስ ታላቅ የፍትወት ፈተና እንደሚያጋጥመው እውነት ነው። ስለዚህ ይህንን ለመዋጋት የስነ ልቡና ዝግጅት አድርጎ ነው የሚገባው።ወደ ትዳርም ሲገባ ልጅ እንደምትወልድ ቤት እንደምትሰራ በደንብ አስበህ የምትገባበት ነው።ስለዚህ ላለመውለድ የወሊድ መቆጣጠሪያን እንደ አማራጭ መያዝ ሳይሆን ብዙ ልጅ እንደምትወልድ አስበህ እንዴት እንደምታኖራቸው ማሰቡ ላይ ትኩረት ማድረግ የተሻለ ነው።

እንጂማ.... ሰው ፍትወት የማይነሳበት ቢሆን ኖሮ ሁሉም መነኩሴ በሆነ ነበር። ማስተዳደር አይሆንልኝም ካልክ አለማግባት እና መመንኮስ ነው።አይ ፍትወትን ማሸነፍ አልችልም ካልክ ደግሞ ልጆች ይወለዱ ለፍተህ ግረህ እየሰራህ አሳድጋቸው።በመነኮሳትምኮ ታላቅ የሆነ የፍትወት ፈተና አለባቸው።ነገር ግን በጾም በጸሎት ያለ እንቅልፍ በትጋህ ሌሊቱን ሙሉ በስግደት እያደሩ ፍትወቱን ለማጥፋት እስከ እለተ ሞታቸው ይታገሉታል። በትዳር ያለው ፈተና ደግሞ ልጅን ለማሳደግ ሙሉ ኃላፊነትን መሸከም ነው።ስለዚህ ይህንን ለማድረግ ደግሞ እስከ እለተ ሞትህ እየጣርክ እየሰራህ መኖር ነው።

ሌላው ግን የሰውን ልጅ የሚመግብ እግዚአብሔር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።የሚያኖርም ነፍስን ከሥጋ የሚለይም እግዚአብሔር ብቻ ነው። ክረምትንና በጋን እያፈራረቀ የሰውን ልጅ የሚመግብ እግዚአብሔርን በፍጹም ልንጠራጠረው አይገባም።ትዳር በብዙ መንገድ ሊፈተን ይችላል።ስለዝህ አእምሯዊ የስነ ልቡና ዝግጅት አድርገን ነው ልንገባበት የሚገባው። እስከ መጨረሻው ላለመለያየት ልዩ ፍቅር እስከ ሞት ድረስ ሊኖረን ይገባል።
ትዳር እና አለመተማመን

አንዴ አባ ጳውሊ ሲሰራ ሲሰራ ውሎ ከሥራ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱን ከአገልጋያቸው ጋር አልጋ ላይ ተኝታ አገኛት።እና እርሱም ተረጋግቶ በቃ አንተም ለእርሷ መልካም ሁንላት አንቺም ለእርሱ መልካም ሁኝለት ብሎ መንኖ ገዳም ገባ ይባላል።በባልና በሚስት መካከል አለመተማመን ከነገሠ አደገኛ ነው።ባልና ሚስት አንድ አካል ስለሆኑ ፍጹም ግልጸኛ መሆን አለባቸው። ችግራቸውንም በግልጽ በመነጋገር መፍታት አለባቸው።እንዳው ቢቻል በባልና በሚስት ጉዳይ ሌላ ሦስተኛ አካል በጭራሽ ሊገባ አይገባም። እናትህም ትሁን አባትህም ይሁን አብሮ አደግ ጓደኛህም ይሁን ብቻ ማንም ቢሆን በእናንተ መካከል ሊገባ አይገባም።

ለምሳሌ እናትህ ሚስትህን ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ አገኘኋት ብላ ብትነግርህ ተረጋግተህ ሄደህ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝተሽ ሰዎች አየናት ብለውኛል ይህ ነገር እውነት ነወይ ብለህ ጠይቃት።አይ አይደለም ካለችህ ልታምናት የሚገባህ ሚስትህን ነው።አንተ እስካላየሀት ድረስ የሰው ነገር ሰምተህ ሚስትህን መጥላት አይገባም።ሌሎች ነግረውህ ሳይሆን በራስህ መንገድ አረጋግጠህ ጥፋተኛ ሆና ካገኘሀት ብቻ የራስህን ውሳኔ መወሰን እንጂ ሌላ ሰው በጭራሽ እንዳትሰማ ተጠንቀቅ።ሴትም ብትሆኝ እንዲሁ።በመካከላችሁ ምንም ዓይነት የጥርጣሬ ስሜት እንዳይገባ።

ውርጃ
ጽንስን ማስወረድ አይገባም።ጌታን ያጠመቀው እና ሴቶች ከወለዱት እርሱን የሚበልጠው የለም የተባለው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በጽንስ ደረጃ እያለ ነበር ለጌታችን የሰገደ።ሉቃ.1 ላይ አንፈርዐጸ እጓል በውስተ ከርሣ እንዲል። ስለዚህ ምንም እንኳ ከቤተሰብ ፈቃድ ውጭ ሥጋዊ ፈቃድ አነሳስቶን በሕገ ወጥ መንገድ ጸንሰን ብንገኝ ቤተሰብን ወይም የሰፈርህን ሰዎች ስድብ እና አሽሙር በመፍራት ጽንስ እንዳታስወርዱ። ላጠፋነው ጥፋት ይቅር ባይ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን ንሥሓ ገብተን ስድብን ተቋቁመን ልጁን ልናሳድገው ይገባል።
2025/01/01 03:53:08
Back to Top
HTML Embed Code: