Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1020 - Telegram Web
Telegram Web
+++ የጀማሪ ጠባይ +++

መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።"

ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?" እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
5
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት መንፈሳዊ ምግባራት የሆኑትን አምስቱ የስጦታ ዓይነቶች ምጽዋት፣መባዕ፣ሰእለት፣ አሥራት እና በኩራት መሀል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ምፅዋት፦ ምጽዋት መስጠት ከገንዘብ፣ ከዕውቀት፣ ከንብረት…ከመሳሰሉት ላይ ለእግዚአብሔር ቤት እና ለችግሮኞች መለገስ ነው፡፡ 

መባዕ፦ ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር ከሚቀረበው የስጦታ ዓይነቶች አንዱ ሲሆን መባዕ ማቅረብ የተገዥነት መገለጫ በመሆኑ በረከት የሚያስገኝ ምግባር ነው፡፡ 

ስእለት፦ ስእለት  ሰው በፈቃዱ አንድ ነገር ለእግዚአብሔር ለማድረግ  /ደስታውን ለመግለጥ/ ቃል የሚገባበት ሥርዓት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አማላጅነት በማመንና በመማጸን “ይህ ቢደረግልኝ ይህን አደርጋለሁ” በሚል አገላለጽ ቃል የሚገቡት የስጦታ ዓይነት ነው፡፡

በኩራት፦ በኩር ማለት መጀመሪያ ማለት ሲሆን የበኩራት ስጦታ ከልጅ ፣ ከንብረት … ከመሳሰለው የመጀመሪያውን መስጠት ነው ሲሆን ይህንንም ከመጀመሪያው ምርታችን ከመጀመሪያ ደመወዛችን የመጀመሪያ (ቦነስ) ጭማሪዎችን ለእግዚአብሔር ቤት በመስጠት የተናገረውን ከማያስቀረው አምላካችን በረከት አንደምናገኝ ፈፅሞ በማመን ነው።

ዐስራት፦ ዐስራት አንድ አሥረኛ ማለት ነው፡፡ ከሚያገኙት ገቢ አንድ ዐሥረኛውን ለእግዚአብሔር ቤት  መስጠትን ያመለክታል፡፡ ከሙሴ በፊት በዘመነ አበው የተጀመረ የእግዚአብሔር ሕግ ነው፡፡ ዐሥራት መክፈል አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሚገልጽበት ተግባር አንዱ መሆኑን ከተገነዘብን አከፋፈሉንም በማስተዋል ልንፈጽም  ያስፈልጋል፡፡
ዐሥራት ከገቢ/ከደመወዝ/ ከዐሥር አንዱን በየወሩ ለቤተክርስቲያን  በመምህረ ንስሐ በኩል ወይም በቀጥታ በመሔድ በየወሩ ወይንም አጠራቅመን የምንከፍለው ነው።
2👍1
Audio
​​* ሁሉን ተውኩት *

ሁሉን ተውኩት እናቴ ሁሉን ለአንቺ
መገፋቴን መውደቄን ተመልከቺ
ልመናዬን ድንግል ሆይ ሳትሰለቺ

ቢሆንም ባይሆንም ቢሞላም ባይሞላም
ለዚህ ከንቱ ዓለም እኔ አልጨነቅም
ሁሉን ትቼዋለሁ ከእግሮችሽ በታች
ደካማ ልጅሽን ድንግል ተመልከቺ

      አዝ======

መልካም ያልኩት ጓዴ ክፉ ሲሆንብኝ
አይቻለሁ በአይኔ ፊቱን ሲያዞርብኝ
የተወጋው ልቤ በአንቺ እንዲፈወስ
በመድኃኒት እጅሽ ሁሌ ይዳሰስ

      አዝ======

ጎጆዬን አትርሻት ደሳሳዋ ቤቴን
ዘይት የሌለውን ባዶ ማድጋዬን
አንቺ ከነገርሽው ልጅሽ ያዝንልኛል
ጎዶሎዬን ሞልቶ ፀጋን ያለብሰኛል

      አዝ======

የዋህ ሩህሩህ ነሽ አዛኝ ለፍጥረት
ትችይበታለሽ ማሰጠት ምሕረት
የልቤን ፍላጎት ሳልነግርሽ ታውቂአለሽ
እንዳትዘገዪ አዛኝቷ ስልሽ

              መዝሙር
   በዘማሪ ዲያቆን ብሩክ ሌራ

"የአስጨናቂዎችሽም ልጆች
አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ
የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ"
            ኢሳ፷፥፲፬
9👍2
[   የሰማዩ ~ መንገደኛ   ]

የአመነ ሰው ከክርስቶስ ዙፋን የሰማያዊውን ደጅ በንሰሃ ለመምታት የምትሄድባቸው አምስቱ የንሰሃ መንገዶች፦

1፡ ሀጢያትን ማሰብ
የመጀመሪያው መንገድ የሰራነውን ሀጢያትን ማሰብ/ማሰላሰል/፡፡ ሀጥያተኛነትህን የምታስበው እና የምታሳስበው ከሆነ እግዚአብሔር ይቅር ሊልህ ታማኝ ነው። ሀጥያተኛነትህን ስታስበው ደግመህ አትበድልም። ህሊናህ ሲከስህ መንፈስ ቅዱስ ሲወቅስህ እንጂ በጌታ ዙፋን ፊት ሌላ አካል እስኪከስህ አትጠብቅ።

"እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።" (መዝሙር 51:3)

2፡ የሌሎችን ጥፋት መርሳት
ሁለተኛው መንገድ ንሰሃ ከመግባትህ በፊት የሌሎችን በደል ይቅር በላቸው። ይህም ስሜትን መቆጣጠር እና ሌሎች ሰዎች በአንተ ላይ ያደረጉትን ሀጢያት ይቅር ማለት አለብህ። ሌሎችን ይቅር ስትል ጌታ ይቅር ይልሃል።

"ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅርብለናልና፤" (የሉቃስ ወንጌል 11:4  )

3፡ ፀሎት
ፀሎት ሶስተኛው መንገድ ሲሆን። ይቅር ይለኛል ብለህ አምነህ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከህ ስለሀጢያትህ ፀልይ እርሱንም እጠበኝ ቆሽሻለሁ፣ አንፃኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ በለው። መለወጥ እና በሰውና በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኜ እንድኖር መንፈስህ ይቆጣጠረኝ በለው። ስትጨርስም ስለምህረቱ የምስጋናን ፀሎት አምጣ።

"በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል። ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ!" (መዝሙር 51:7-10)

4፡ ደግነት
መንገድ አራት ምህረትና ፍቅሩን ለመለመን በፊቱ ስትቆም ከሚሰጥና ደግ በሆነ ልብ ይሁን። ደግነትህ ብዙ እንድትቀበል ያደርግሃል። መካስ ባትችልም እንደ ካሳ ግን የተቀበልከውን ፍቅር ለብዙ ስጠው።

5፡ ትህትና
አምስተኛው መንገድ ትህትና ። በማስመሰል ሳይሆን በእውነት ትህትና የአንተ ክብር ምንም መልካምነት እንደሌለው እና ትከሻህ በሀጥያት ሸክም እንደጎበጠ በእግዚአብሔር ፊት ሁን። እግዚአብሔርም በምህረት ከባዱ ሸክምህን ከላይህ ላይ አራግፎ ሀጢያትህን በደሙ እያነፃ ፍቅሩን በልብህ ያሳዝልሃል።

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" (ማቴዎስ 11:2)

የሰማዩ መንገደኛ ሆይ በትንሹ አንደኛውን መንገድ ገንዘብህ አድርገው። አንዱ አንዱን ይስበዋልና።እግዚአብሔር ትግላችንን/ተጋድሎአችንን መንገዳችንን ይባርክልን።
👍5🥰3
‹በእግዚአብሔርን በሚያምን ሁሉ አጠገብ ጠባቂ መልአኩ አለና ስለዚህ ንስሐ ይግባ› በማለት ከንስሐ ሕይወት ጋር  አያይዞ ያሳስበናል፡፡ ሊቁ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያም ሰው ብቻውን ሆኖ እንኳን ቢጸልይ ጠባቂ መልአኩ ከእርሱ ጋር አብሮት እንደሚሆን የሚናገር ሲሆን ፤ ሊቁ ጠርጠሉስም ብዙውን ጊዜ በምንዘናጋበት በግል ጸሎታችን ጊዜ አብሮን ለምስጋና ከሚቆመው መልአክ ክብር የተነሣ መቼም ቢሆን ቁጭ ብለን እንዳንጸልይ ይመክራል፡፡


አበው ቅዱሳን እንደሚያስተምሩት ጸሎት እና ቃለ እግዚአብሔርን ከሚወድ ሰው ጋር እኒህ ጠባቂ መላእክት ዘወትር የማይለዩ ቢሆንም ፤ ኃጢአትን ባደረገ ጊዜ ግን ከእርሱ ያርቃቸዋል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ‹በክፉ ሥራዎቻችን እስካላሸሸናቸው ድረስ መላእክት ከእኛ መቼም ቢሆን አይርቁም፡፡ ጭስ ንቦችን ፣ክፉም ሽታ ርግቦችን እንደሚያባርር እንዲሁ የሚከረፋው ኃጢአታችን ሕይወታችንን የሚጠብቁትን መላእክት ያርቃቸዋል› ሲል መልካሙን ባለማድረግ በኃጢአታችን ክፉ መዓዛ ጠባቂ መላእክቶቻችንን እንዳርቃቸው ያስጠነቅቀናል፡፡ ገነተ አበውም (Paradise of the holy fathers) ላይ አንድ የበቃ የእግዚአብሔር ሰው ያየው ራእይ ይህን በመሰለው ጉዳይ በቂ ዕውቀት የሚያስጨብጠን ነው፡፡ ‹በአንድ ወቅት አበው መነኮሳት ተሰብስበው ስለ ምናኔ ሕይወት መልካምነት ሲወያዩ ሳለ ከመካከላቸው ከነጽሮት [መላእክትን ከማየት] የደረሰ አንድ አረጋዊ ፤ ቅዱሳን መላእክት እኒህን አባቶች ረበው ሲበሩ ተመለከተ፡፡ ነገር ግን ወደ ሌላ ከንቱ ርእስ (ሥጋዊ) በተሸጋገሩ ጊዜ ዓሣሞች በዙሪያቸው ከበዋቸው በአረንቋ (ጭቃማ) ላይ ሲንከባለሉ ታየው፡፡ ዳግመኛም እኒሁ አባቶች ጨዋታቸውን ወደ መንፈሳዊ ወግ በማምጣት ባደሱት ጊዜ መላእክቱ ተመልሰው እግዚአብሔርን ሲያከብሩ ተመልክቷል›፡፡

በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ ክፉ በሠራን እና በአምላካችን ላይ ባመጽን ጊዜ የሚሸሹን መላእክት ወዴት ይሄዱ ይሆን? ብለን ከጠየቅን መጽሐፈ መነኮሳት ይመልስልናል፡፡ ተጠባቂው ሰው ጌታውን በምግባር አሳዝኖ፣ በሃይማኖት ክዶ የሆነ እንደሆነ ዑቃቢ መልአኩ ከእርሱ ይሸሽና ሌላ አንድን ጻድቅ ወደሚጠብቅ ወዳጁ መልአክ ፍቅሩ ስቦት ይሄዳል፡፡ ይህንንም ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት አንዱ የሆነው ማርይስሐቅ ‹ያንዱ መልአከ ዑቃቢ ወዳንዱ የሄደ እንደሆነ፤ ያንዱ መልአከ ዑቃቢ ተከትሎት ይሄዳልና ‹እስመ በአሐዱ ፍቅር ይሰሐብ ካልዑ›/‹በአንዱ ፍቅር ሁለተኛው ይሳባል› እንዲል› በማለት ይገልጸዋል (ማርይስሐቅ. ገጽ 35)፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ጠባቂ አድርጎ የሰጠን መላእክቶቻችን እንዳያዝኑብን እንጠንቀቅ፡፡ የኃጢአታችንም ክፉ ሽታ እንዳያርቃቸው በንስሓ እንባ ነፍሳችንን እንጠብ፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በተለይ እንደነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት፣ ቅዱስ አውግስጢኖስ ያሉ አባቶች ከሰው ልጆችም ውጪ እንደ ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና ሌሎችንም ፍጥረታት የሚጠብቁ መላእክት እንዳሉ በዮሐንስ ራእይ ላይ የተጠቀሱትን ‹የውኃውም መልአክ›፣ ‹አራት መላእክት አየሁ እነርሱም…አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ›፣ ‹በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ› የሚሉትን የመጽሐፍ ክፍሎች በመጥቀስ ያስተምራሉ(ራእይ 7:1፣ 14:18 ፣ 16:5)፡፡ ለአገርም [ለሕዝብም] ቢሆን ጠባቂ መልአክ እንደሚሾም "ሚካኤል አንተ ለያዕቆብ ኖላዌ ዘርዑ" ‹ለያዕቆብ እና ለዘሩ ጠባቂ [እረኛ] ሚካኤል አንተ ነህ› የሚለው ቃል የሚያስረዳን ሲሆን አንድ ሊቅ ደግሞ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ያለውን ለቅዱስ ጳውሎስ በራእይ በመቄዶንያ ሰው አምሳል ተገልጦ "ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን" ያለውን መልአክ የመቄዶንያ ሀገር ጠባቂ መልአክ (shepherd angel) እንደሆነ ይናገራል (ሐዋ 06.9)፡፡ ታዲያ በዚሁ ተመሳሳይ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ፊሊጶስን ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ላይ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ እንዲያገኘው የነገረው መልአክ የኢትዮጵያ ሀገር [ሕዝብ] ጠባቂ መልአክ ይሆንን? (ሐዋ 8:26)::
👍6🙏2
ጸሎት ምስጋናና ልመና ነው፤እግዚአብሔር ስላደረገልን፣ ስለሚያደርግልንም እንዲሁም ለሚያስብልንም ነገር የምናመሰግንበት መንገድ ጸሎት ነው፡፡ የቤተክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ንጹሕ ልቡና እንዲሰጠን ከክፋት፣ ከተንኮልና ከምቀኝነት እንዲጠብቀን ጥበብና ማስተዋሉንም እንዲሰጠን፣ ቅን ልቡና እንዲፈጥርልን ልዩነትንና ክፋትን ከመካከላችን እንዲያጠፋልን እና እውነተኛ ፍቅር እንዲሰጠን መጸለይ ያስፈልጋል፡፡በአሁን ጊዜ በዓለማችን በሀገራችንና በቤተክርስቲያን እውነተኛ ሰላም ጠፍቷልና እርሱ ሰላምን እንዲሰጠን ልንጸልይ ይገባል፤ጌታችን‹‹ወደፈተናእንዳትገቡትጉናጸልዩ።›› ብሎ ያስተማረን ለዚህ ነው፡፡

ጸሎት ኃጢያተኛን ወደ ንስሐና ወደ አምላኩ ረድኤት እንዲገባ የሚረዳ በር ነው፡፡ ማር ይስሐቅ ስለዚህ ነገር ሲናገር “ከጸሎት በቀር ንስሐ መግቢያ በር አለ ብሎ የሚናገር ቢኖር እርሱ በሰይጣን የተታለለ ነው፡፡” ይላል ታዲያ ምን ትጠብቃለህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ጸልይ በንስሐ ወደ ክርስቶስ ቅረብ እርሱ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም።” ብሏልና፡፡ (ዮሐ 15፥5) ስለዚህ ኃጥያት የከበደው የተጨነቀ ሰው “መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።” ይበል:: (ኤር 31፥18)

የማይጸልይ ሰው እግዚአብሔርን አላወቀውም:: የሚጸልይ ግን ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የፈለገና የቀደመው ክፉ ሴራው እየታወሰው በትሕትና የተሰበረ ልብ ያለው ነው። ስለዚህ ለጸሎት “ጊዜ የለኝም።” ማለት ጊዜያትን ባርኮ ቀድሶ የሚሰጠንን እግዚአብሔርን ማሳዘን ነው በእውነት፡፡

አንድ አገልጋይ (ባሪያ) “ጌታዬን የማነጋገሪያ ጊዜ የለኝም።” ቢል እንዴት ያለ ድፍረት ይሆን? ፍጡርስ ከፈጣሪው ጋር ለመነጋገር ጊዜ የለኝም። ቢል እንዴት ያለ የእግዚአብሔርን የቸርነቱን ነገር መናቅ ይሆን? ከንቱና መጥፎ ለሆኑ በርካታ ነገሮች ግን ጊዜ እናገኛለን። ከዚህ የምንረዳው ችግሩ የጊዜ ሳይሆን የፍላጎት እንደሆነ ነው፡፡ የመጸለይ ፍላጎት ያለው ጊዜ ስለማግኘቱ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ስለዚህም ጸሎት የምትመካበት፣ ያለእርሱ መኖር የማትችል እንደሆንክ የምታረጋግጥበት ነውና ስለጸሎት የምታስበውን ሐሳብ ሁሉ ዛሬውኑ መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ይህን አረጋግጥና ፀሎትን እንደመንፈሳዊ መንገድ ተቀብለህ እምነትህን ጣልበት፡፡ አንተ የምትጸልየው ጸሎት እንደመልካም መዓዛ በወርቁ ጽንሀ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያርጋል፡፡

ጸሎት እግዚአብሔርን የናፈቀ ልብ ሲቃ ነውና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ይለካበታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክህን የምትወድ ከሆነ ትጸልያለህ፡፡ ከጸለይክ ደግሞ ፍቅረ እግዚአብሔር በውስጥህ ያድጋል፡፡ እስቲ በዚሁ ፍቅር የተቀጣጠለና ልብ የሚነካውን የዳዊትን ጸሎት አስተውል፡፡ “ዋልያ ወደውሃ ምንጮች እንደሚናፍቅ አቤቱ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች፣ ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፡፡ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?”(መዝ 41፥1-2) በእውነት ዝናምን እንደምትናፍቅ ደረቅ መሬት እግዚአብሔርን መናፈቅና መጠማት ይህ አይደለም ?

ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ጸሎትህ በፍቅር የተቀመመና የጣፈጠ ይሁን፤ ውሱን ፍጡር ሆነህ ሳለህ ለማይወሰነው አምላክ ያለህን ናፍቆት የምትገልጽበት መንፈሳዊ መንገድህ ስለሆነ፤ ውስጣዊት ነፍስህ ወደመገኛዋና እረፍቷ የምትጠማው ጥማት ስለሆነ በተሰበረ መንፈስና በትሁት ልቦና ከጌታህ ጋር ተነጋገር።

“ዕሹ ታገኛላችሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኙማላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል”። (ማቴ.7፥7) በእውኑ ላይሰጥ ለምኑ፤ ላይገለጥ ዕሹ ይላል?!!
                
ŜĤÃŘÊ ~ @nshachannel ~ ĴÔÎÑ
                 
👍2
👉🏾👉🏾👉🏾ምስጢራተ #ቤተክርስቲያን


ምስጢር የሚለው ቃል ግሪክ ነው፤ በግእዝና በአማርኛም እንዳለ ተወስዷል፤ ትርጓሜውም የማይታይ ረቂቅ ማለት ነው፤ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ማለት በሚታይ ምልክት የማይታይ ጸጋ የሚሰጥባቸው በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸሙ ሥርዓታት ማለት ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና በግዙፍ ምልክት የሚሠሩ ነገር ግን በእምነት ዓይን ብቻ የሚታዩ ረቂቃን የሆኑ ነገሮች ሁሉ ምሥጢራት ይባላሉ።

ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በቁጥር ሰባት ናቸው ፤ እነርሱም ጥምቀት፣ ሜሮን፣ ቅዱስ ቁርባን፣ ክህነት፣ ንስሓ፣ ተክሊል ፣ ቀንዲል ናቸው። ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን ሁሉ የሚያስፈልጉና የማያስፈልጉ አሉ፤ ጥምቀት ሜሮን ቅዱስ ቁርባንና ንስሓ ለሁሉም ያስፈልጋሉ። ክህነት ቀንዲልና ተክሊል ግን ለሁሉም ግድ አያስፈልጉም።

ከሰባቱ ምሥጢራት መካከል የማይደገሙና የሚደገሙ አሉ፤ ጥምቀት ፣ ሜሮን ክህነትና ተክሊል አይደገሙም። የቀሩት ግን ይደገማሉ፤ ይልቁንም ይዘወተራሉ። ከሰባቱ ምሥጢራት መካከል ክህነት በጳጳስ ወይም በቀሳውስት ሊሰጡ ይችላሉ።

1. ምሥጢረ ጥምቀት

ጥምቀት ማለት መጥለቅ ፣ መነከር ፣ ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር በውሃ ውስጥ መግባት ማለት ነው። ከሰባቱ ምሥጢራት ሁሉ መጀመሪያው ጥምቀት ነው።ጌታችን “ማንም ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይችልም” ብሎ በተናገረው መሠረት ጥምቀት ወደ ቤተ ክርስቲያንና ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር መግቢያ በር ነው።

ጥምቀት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተመሥርቷል፤ ጌታችን ጥምቀትን በተግባርና በትእዛዝ መሥርቶታል፤ በተግባር ማለት፦ ራሱ ጌታችን በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቋል። በትእዛዝ ማለት ፦ ከትንሣኤ በኋላ “ሂዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው” ብሎ ደቀ መዛምርቱን አዝዟቸዋል።

በምሥጢረ ጥምቀት የሚገኝ ጸጋ፦  በምሥጢረ ጥምቀት የውርስ ኀጢአትና ከጥምቀት በፊት የተሠሩ ኀጢአቶች ሁሉ ይሰረያሉ። መንፈሳዊ ልደትና ሐዲስ ህይወት ይገኛሉ፤ ድኀነት ይገኛል። ንጽሐ ጠባይዕ ያደፈባቸው ወይም የጥንተ አብሶ ውርስ ያለባቸው ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት አይችሉምና በውሃ የሚፈፀም ክርስቲያናዊ ጥምቀት ብቻ ሰውን በአዲስ ልደት እንዲወለድ በማድረግ ይህን የጥንተ አብሶ ውርስን ያስወግዳል። ስለዚህ ሰው ሁሉ ለመዳን ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ አለበት።

-    ምሥጢረ ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ አይደገምም። ሥጋዊ ልደት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ መንፈሳዊ ልደትም አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

-    ህፃናት ከተወለዱ በኋላ ወንዶችን በ40 ቀናቸው ሴቶችን በ80 ቀናቸው እንዲጠመቁ ይደረጋል። ለሕፃናት ጥምቀት ያስፈለገበትም ምክንያት የጥንተ አብሶ ውርስ ስላለባቸው ከዚያ ለመንጻት እንዲችሉ ነው። ሕፃናት ከጥንተ አብሶ ውርስ በስተቀር የገቢር ኃጢአት ስለሌለባቸው በሚጠመቁበት ጊዜ ንስሓ አያስፈልጋቸውም።

-    የሕፃናት ጥምቀት በወላጆቻቸው ወይም በአሳዳሪዎቻቸው ወይም በክርስትና አባትና እናታቸው እምነት ይፈጸማል። የአንዱ እምነትም ሌላውን እንደሚጠቅም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወላጆቻቸው ወይም በአሳዳሪዎቻቸው እምነት ለበሽተኞች ተአምራትን ያደርግና ይፈውሳቸው ነበር።

ተጠማቂው ትልቅ ከሆነ በቅድሚያ ትምህርተ ክርስትናን መማር፣ በሚጠመቅበት ጊዜ እምነቱን ማሳወቅ፣ ንስሐውን መግለጥ አለበት።

2. ምሥጢረ ሜሮን

ሜሮን ማለት ቅብዓት ማለት ነው፤ ምስጢረ ሜሮን አዲሱ ተጠማቂ በመንፈሳዊ ሕይወቱ እንዲያድግና እንዲበረታ ፀጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ምሥጢረ ቤተክርስቲያን ነው። ሜሮን ከዘይት (ወይራ) ከበለስና ከተለያዩ እፅዋት በጳጳሳት ይወጣል።

በሚስጢረ ሜሮን የሚገኝ ጸጋ  ፦ ተጠማቂው ሜሮን በሚቀባበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ይቀበላል። የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በሜሮን ይረጋገጣል፤ ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ዕድገትና ኃይልን ያገኛል። ለዚህ ሁሉ ምሥጢረ ሜሮን እንደ ማሕተም ነው።

3. ምሥጢረ ቁርባን

ቁርባን ማለት መባዕ ሆኖ የሚቀርብ የሚሰጥ ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ስለኃጢአታቸው ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ሁሉ ቁርባንና መሥዋዕት ይባል ነበር ። ቁርባን የእህሉ መሥዋዕት፣ የእንስሳው ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን ቁርባን ወይም መሥዋዕት የሚባለው እግዚአብሔር ለሰዎች ያቀረበው ነው፤ ከዚህም ጋር ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡበት እግዚአብሔርም ወደ ሰዎች የሚቀርብበት መንገድ መሆኑን ቃሉ ያመለክታል።

ቅዱስ ቁርባን የሚባለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ነው። ቅዱስ ቁርባን፥ መሥዋዕት ተብሎ ይጠራል።

በምሥጢረ ቁርባን የሚገኝ የማይታይ ፀጋ፦ በሚታየው በኀብስቱና በወይኑ የማይታየውን የክርስቶስን ሥጋና ደም እንቀበላለን፤ ስርየተ ኃጢአትን እናገኛለን። ከክርስቶስ ጋር ኀብረትን እናገኛለን። ከምእመናን ሁሉ ጋርም አንድነት ይኖረናል። በሥጋውና በደሙ የዘለዓለም ሕይወትን እንወርሳለን።

የኀብስቱና የወይኑ መለወጥ፦ ካህኑ ነቅዕ የሌለበትን ንጹሕ ኀብስት በጸሕል እንደዚሁም የጠራውን ወይን በጽዋዕ አድርጎ ጸሎተ ቅዳሴውን ያደርሳል፤ ከፍሬ ቅዳሴው መካከል "… የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ያደርገው ዘንድ ቅዱስ መንፈስን ኃይልንም በዚህ ኀብስትና በዚህ ጽዋዕ እንድትልክ አቤቱ እንለምንሀለን፤ እንማልድሀለን” የሚለውን ጸሎት በሚጸልይበት ጊዜ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ኀብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምላክ ወይኑም ተለውጦ ደመ አምላክ ይሆናል ፤ (ቅዳሴ ሐዋርያት) ኀብስቱና ወይኑ በሚለወጡበት ጊዜ መልካቸውና ጣዕማቸው እንዳለ ነው፤ መለወጡን የምንመለከተው በእምነት ዓይን ነው።

እንደ ቤተክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ቅዱስ ቁርባን ፍጹም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው እንጂ ምሳሌ አይደለም። (ማቴ 26፥27-28 1ኛ ቆሮ 10 ፥16፥ 11፥ 23-27) እነዚህ ጥቅሶች ሁሉ የሚያመለክቱት የምንቀበለው ኀብስትና ወይን ፍፁም የክርስቶስ ሥጋና ደም መሆኑን ነው። ይህም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መሰረት በማድረግ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ኀብስቱና ወይኑ በካህኑ መሣሪያነት በመንፈስ ቅዱስ ሥራ በቃለ እግዚአብሔር ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋና ደም እንደሚሆን በሰፊው ተናግረዋል፤ ጽፈዋልም።

ምሥጢረ ቁርባንን መቀበል የሚገባቸው፦ በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት መሠረት አምነው የተጠመቁ ሥጋውንና ደሙን መቀበል ይችላሉ፤ ከዚያም በኋላ በየጊዜው ራሳቸውን በንስሐ እየመረመሩ ኀጢአታቸውን በመናዘዝ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን ትፈቅዳለች። በንስሐ ሳይዘጋጁ በድፍረት የሚቀበሉ ቢኖሩ ግን ዕዳ እንደሚሆንባቸው ታውጃለች።

(ይቀጥላል) 👇👆
1
(ቀጣይ ክፍል) 👇👆

4. ምሥጢረ ክህነት

ክህነት ማለት አገልግሎት ማለት ነው። በዚህም መሠረት ካህን ማለት አገልጋይ ማለት ነው። ምሥጢረ ክህነት ፦ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ምሥጢራትን ለመፈጸምና ምእመናንን ለመምራት በጳጳሳት አንብሮተ እድና ጸሎት ለሚገባቸው የሚሰጥ ምሥጢር ነው። ሰባቱን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ለመፈጸም የሚያስችል ይህ ምሥጢረ ክህነት ነው። (የሐዋ 20፥28)

5. ምሥጢረ ንስሓ

ንስሓ መጸጸት ከኃጢአት መመለስ ራስን ማደስና መለወጥ ማለት ነው። ንስሓ ተነሳሒው በአናዛዡ ካህን በኩል ከራሱ ከእግዚአብሔር በእውነተኛ ኀዘን ሥርየተ ኃጢአትን የሚቀበልበት ምሥጢር ነው።

ከአዳም የተወለደ ሁሉ ከአዳም በተወረሰው የኀጢአት ዘርዕ ምክንያት የኃጢአት ዝንባሌ አለበት፤ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲያስረዳ እንዲህ ይላል ። “…እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የሥጋ ነኝ፤…የማልወደውን የማደርግ ከሆንኩ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም በእኔ የሚኖር ኀጢአት ነው እንጂ” ። (ሮሜ 7፥ 15-18) ስለዚህ ሰው ከጥምቀት በፊት የሠራው ኀጢአት ሁሉ በጥምቀት ይሰረይለታል፤ ከጥምቀት በኋላ የሰራው ኃጢአት ግን በንስሓ ይሰረይለት ዘንድ እግዚአብሔር ምሥጢረ ንስሓን ለሰው ልጆች ሰጥቶአል።

አመሰራረቱ፦ ምሥጢረ ንስሓን የመሠረተ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ከትንሣኤው በኋላ ሥልጣነ ክህነትን ለሐዋርያት በሰጣቸው ጊዜ ምሥጢረ ንስሓን መሥርቷል። (ዮሐ 20፥21-23) ከዚያም አስቀድሞ ኃጢአተኛውን ከኃጢአቱ መፍታትና ማሠር እንደሚችሉ በነገራቸው ጊዜ የምሥጢረ ንስሓን ተስፋ ሰጥቶአቸው ነበር ( ማቴ16፥19፣ ማቴ18፥18) በመሰረቱ ኀጢአትን የማስተሰረይ ኃይል ለጌታችን ብቻ ነው (ሉቃ 5፥20) ነገር ግን ይህን ኃይል ራሱ ጌታችን ለሐዋርያት ሰጣቸው፤ በሐዋርያትም በኩል ለጳጳሳትና ለቀሳውስት ተሰጣቸው። (ዮሐ 20፥21-23)

ተነሳሒው ማለት ኀጢአተኛው ስለሰራው ኀጢአት ከፍተኛ ጸጸት ልባዊ ኑዛዜ መናዘዝ ወደ ሠራው ኀጢአት እንደገና ላይመለስ መወሰን በክርስቶስ ጽኑዕ እምነት በምሕረቱም ፍጹም ተስፋ ማድረግ አለበት።

ኀጢአትን ለካህን አምኖ መናዘዝ ያስፈልጋል ፤ ካህኑም ኑዛዜውን በምሥጢር መጠበቅ አለበት። ኑዛዜ ራስን በካህኑ  ፊት መክሰስና መውቀስ ማለት ነው። ኑዛዜ ኀጢአተኛውን በሰራው ኀጢአት እንዲገሰጽ እንዳይመለስበትና እንዲያፍርበት ያደርገዋል። ንስሓ መግባት የሚገባው ኀጢአትን በተገነዘቡ ጊዜና ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል በፊት ነው።

በምሥጢረ ንስሐ የሚገኝ ጸጋ፦ ተነሳሒው በመምህረ ንስሓው ፊት ቀርቦ ኀጢአቱን በሚገባ ከተናዘዘ በኀጢአቱ ካለቀሰ ስርየተ ኀጢአትን ያገኛል። ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቃል ፤ የነፍስ ሰላምንና ዕረፍትን ያገኛል፤ በድሎ የነበረው እንዳልበደለ ይሆናል፤ ፍጹም ተሐድሶና ለውጥን ያገኛል።

ካህኑ ለተነሳሒው የሚሰጠው ቅጣት (ቀኖና)፦ ተነሳሒው የኃጢአቱን ክብደት እንዲያስታውስ ካህኑ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት ፆም ፣ጸሎት፣ ስግደት፣ ምጽዋት እንዲሰጥ ያዝዘዋል።

6 ምስጢረ ተክሊል

ተክሊል የሚባለው ቃል ለሙሽሮች በጋብቻቸው ጊዜ የሚፈጸመውን ሥርዓት ቃል ኪዳንና የሚቀዳጁበትን አክሊል የሚለብሱትንም ልብስ መርዓ የሚያመለክት ነው። ምሥጢረ ተክሊል ሙሽራውንና ሙሽሪትን አንድ የሚያደርግ መለኮታዊ ጸጋን የሚያሰጥ የጋብቻ አንድነት የሚያጸና ምሥጢር ነው። ጋብቻ ወይም ምሥጢረ ተክሊል ከሌሎች ምሥጢራት ተለይቶ ምሥጢራዊና ተፈጥሯታዊ ነው። ምስጢራዊ መባሉ ፀጋ እግዚአብሔር ስለሚሰጥበት ነው። ተፈጥሮታዊ መባሉም ማንም በተፈጥሮ ባሕርዩ ስለሚፈጽመው ነው።

ምሥጢረ ተክሊል በድንግልና ኖረው ለሚጋቡ እንጂ ለፈቶች አይደረግም። ከአንዲት ሴት በላይ ወይም ከአንድ ወንድ በላይ ለሚያገቡ ምሥጢረ ተክሊል አይፈፀምም።

በምሥጢረ ተክሊል የሚገኝ ፀጋ፦ ምሥጢረ ተክሊል የሙሽራውንና የሙሽራይቱን ባሕርያዊ አንድነት ወደ ንፁሕ መንፈሳዊ አንድነት ይለውጣል። እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ጋብቻ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያኑ አንድነት ምሳሌ ነው ። በመሆኑም የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ለዘለዓለም እንደሆነ ባልና ሚስት ሳይለያዩ እንዲኖሩ የሚያስችል መንፈሳዊ ሃይልንና አንድነትን በምሥጢረ ተክሊል ያገኛሉ። ጋብቻ ከሁለቱ አንዱ ካልሞተ ወይም አመንዝራ ካልሆነ በቀር አይፈርስም፤ እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው ሊለይ አይገባውም።

7 ምሥጢረ ቀንዲል

ምሥጢረ ቀንዲል የታመሙ ምእመናን በቅብዓ ቅዱስና በቀሳውስት ጸሎት ለነፍስና ለሥጋ ፈውስ የእግዚአብሐርን ፀጋ የሚቀበሉበት ምሥጢር ነው።

በምሥጢረ ቀንዲል የሚገኝ ፀጋ፥ በሽተኛው ቀንዲል ሲቀባ በሥጋዊ ደዌ ደክሞ የነበረው መንፈሳዊ ሃይሉ ይበረታል፤ ከዚህም ጋር በምሥጢረ ቀንዲል በሽተኛው ስርየተ ኀጢአትን ያገኛል፤ ይህም ኑዛዜ ሲጨመርበት ነው።

ይቆየን
👍6
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ሰው ሆይ አስተውል

የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል፦

በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ
ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ 6፥12-14)

ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)

ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)  ስንቶቻችን ነን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደሶች እንደሆንን የምናውቀው?

ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእረፍትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)

የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ…የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ 39፥28)

ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)

:…የወይን ጠጅ ከሚጠጣ ጋር አትቀመጥ (ምሳ 23፥20)

ዘፈን የሰነፎች ዜማ ነው (መክ 7፥5)

በዛም አጋንንት ይዘፍናሉ (ኢሳ 13፥21)

ስንቶቻችን ነን እነዚህን የእግዚአብሔርን ቃላት እየጠበቅን ያለነው?

ሠምተን ለመለወጥ ያብቃን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዘለዓለሙ አሜን!!!
👍51
® ምክረ አጋንንት ©

በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ

ልጹም ትላለህ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ። ልመጽውት ትላለህ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። ንስሐ ልግባ ትላለህ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ። ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ ላስቀድስ ትላለህ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ። ጸበል ልግባ ትላለህ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ። አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። በአንድ ልወሰን ትላለህ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ።

በመጨረሻም የተወሰነልህ ግዜ ያልቃል
ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል።
# ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
# ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
# ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
# ልጣላው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
# ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ፣ ቀልቶ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ተመቸህ እኮ!› ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ።
# ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ፣ ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል። እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት፣ ወደ ሆቴል ቤት፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት፣ ወደ ሱፐር ማርኬት፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል። በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል። መስገድ ያቅትሃል። መጾም ይከብድሃል። ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል። ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል። ደም ብዛት አስይዞ ሴት ያዝልሃል/ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል። የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል። ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል። ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል። ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር ያደርጋታል።

# በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ፤ እንደ አብርሃም፣ እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር።

# ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል። እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች።

# የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች። ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን። ሁላችንም ወደ እግዚያብሄር ተመልሰን ንስሐ እንግባ።
5👍1
መዝሙር 36
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤
² እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።
³ በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።
⁴ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
⁵ መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።
⁶ ጽድቅህን እንደ ብርሃን ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣል።
⁷ ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው። መንገድም በቀናችለትና ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና።
⁸ ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፤ እንዳትበድል አትቅና።
👍6
#ትልቁ ጥበብ እግዚአብሄርን መፍራት ነው።
#ትልቁ እውቀት በራስህ መፍረድ ነው።
#ትልቁ ፍቅር የወንድምህ በደል መሸከም ነው።
#ትልቁ ፍርሃት ያለንስሃ ሞት ነው።
#ትልቁ ሃብት ንፁህ ልብ ነው።
#ትልቁ ስኬት በመንገድህ ሁሉ እግዚአብሄርን ማስቀደም ነው።
#ትልቁ መንፈሳዊነት ወድቀህ መነሳት  ነው።
#ትልቁ ክብር የዓለም ክብር መጥላት ነው።
#ትልቁ ስልጣኔ ራስህን መምሰል/መሆን ነው።
#ትልቁ ስጦታ ለበደለህ ይቅርታ መጠየቅ ነው።                                                          
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!                              
6👍4🥰1
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን! †


እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።

በአንድ ሀገር አስተራኒቆስ የሚባል መኮንንና ሚስቱ አፎምያ ይኖሩ ነበር፡፡ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ቅዱስ ሚካኤልን የሚወዱ ነበሩ፡፡ ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ በቅዱስ ሚካኤልም ስም ድሆችን እየረዱ ሲኖሩ አስተራኒቆስ ይታመማል፡፡ ያን ጊዜም ሚስቱ አፎምያ እኔን ይጠብቀኝ ዘንድ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አሠርተህ ስጠኝ አለችው፡፡ እርሱም እንደለመነችው በልዩ ልዩ ጌጣጌጥ በወርቅ ቅብ አሠርቶ ሰጣት፤ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ባሏ ሞተ፡፡

ቅድስት አፎምያ ባሏ ከሞተ በኋላ ዘወትር በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት እየቆመች የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እዘንልኝ ምሕረትን ከአምላክህ ለምንልኝ ጠብቀኝ እያለች ትፀልይ ነበር፡፡ ሰይጣንም በጾም በጸሎቷ በምጽዋቷ ቀናባት ሊያሳስታትም ፈልጎ ብዙ ልጆች የየዘች ሴት መስሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ ቅድስት አፎምያንም ‹‹ጾም አታብዢ በኋላ ትከሻለሽ ፤ ለድሆች አትመጽውቺ በኋላ ድሀ ትሆኛለሽ፤ ጸሎት ማብዛት ምንም አይጠቅምሽም፡፡ ደግሞ ባል አግብተሽ ልትኖሪ ይገባል፤ እኔም የመጣሁት ከንጉሡ ተልኬ ነው፤ ንጉሡ አንቺን ሊያገባ ይፈልጋል፤ አንቺም ይህን እድል ተጠቀሚበት›› አላት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን በሰይጣን ንግግር አልተታለለችም፤ ይልቅ ጾም ጸሎት እንደሚያስፈልግ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እየጠቀሰች ነገረችው፡፡ ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል እንዲሳለም ብታመጣ ሰይጣን ፈርቶ ሮጠ፡፡ ቅድስት አፎምያንም ‹‹በያዝሽው ሥዕል አትመኪ በሰኔ 12 ቀን ሚካኤል በአምላኩ ፊት ሊሰግድና የሰዎችን ልመና ሊያቀርብ በእግዚአበሔር ፊት ሲቆም ያን ጊዜ መጥቼ አስትሻለሁ›› አላት፡፡ እርሷም በትእምርተ መስቀል ብታማትብ ከአጠገቧ ጠፋ፡፡ እርሷ ግን ዘወትር በጾም በጸሎት ትተጋ ነበር፡፡

በሰኔ 12 ቀን ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ተገለጠ፡፡ ለቅድስት አፎምያም "ሰይጣን ያለውን ሰምቻለሁ እጠብቅሽም ዘንድ ከሰማይ ወረድኩ ስለዚህ ለእኔ ስገጂልኝ" አላት፡፡ ቅድስት አፎምያም "እውነት አንተ ሚካኤል ከሆንክ በቤቴ ውስጥ እንዳለው ሥዕል የመስቀል ምልክት የታለ የያዝከው? አለችው፡፡ ሰይጣንም "ለእኛ ለመላእክት እኮ ምንም ምልክት የለንም አላት፡፡ እርሷም መልሳ ንጉሥ ማኅተም የሌለውን ደብዳቤ ቢልክ የሚያመነው የለም እንዲሁ መስቀል ያልያዘን መልአክ ሁሉም ይንቀዋል አይቀበሉትም" አለችው፡፡ ያን ጊዜም ሰይጣን መልኩን ለውጦ ጨለማ መስሎ ዘሎ አነቃት፤ እርሷም ‹‹የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ከጠላቴ አድነኝ›› አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ሊያጽናናት ታላቅ ብርሃን ለብሶ መጣ ቤቱንም በብርሃን ሞላው፡፡ ሰይጣንንም በበትረ መስቀሉ መታውና መሬት ላይ ጣለው ሰይጣንም "እባክህን አታጥፋኝ" ከእንግዲህ ሥዕልህ ወዳለበት ስምህ ወደተጠራበት አልደርስም አለው፡፡ ያኔም ሰይጣንን አዋርዶ አሳፍሮ ተወው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም "አፎምያ ሆይ! ዛሬ ነፍስሽ ከሥጋሽ ትለያለች መላእክትም ነፍስሽን ወደ ገነት ያሳርጓታል ስለዚህም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒጂና ጸሎት አድርጊ" አላት፡፡ እርሷም ንጹሕ ልብስ ለብሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደችና የጌታችንን ሥጋና ደሙን ተቀበለች፡፡ ከዚያም ንብረቷን በሙሉ ሸጣ ለድሆች እንዲሰጥ ለጳጳሱ አደራ ሰጠችው፡፡ በቤቷ የነበረውም ሥዕል በርሮ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ገባ ካለ ገመድ ተንጠለጠለ፤ ቅጠል አወጣ ፍሬም አፈራ፡፡ ብዙ አጋንንት ያደረባቸው የታመሙም ሰዎች ቅጠሉን ቆርጠው ወስደው ይታጠቡበትና ይድኑ ነበር፡፡

"ኦ ሚካኤል! ኦ ሚካኤል! ኦ መተንብል!
ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፥
ዘእምርኡሳን ርኡስ ወዘእምልዑላን ልዑል
ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል!"

ቅዱሳን መላእክት እንደ ታላቅ ወንድም የሚያስቡልን የሚንከባከቡን ከሰይጣን ወጥመድ የሚያድኑን ናቸው። የቅዱሱ መልአክ ተራዳኢነት አይለየን!!!
👍5
[ ምክረ አበው ]

|must read|
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡"

(ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
5🙏1
ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ባለው ነዳይ ወንድምህ ውስጥ ካላገኘኸው በቅዱስ ቍርባንም ውስጥ አታገኘውም። ስለዚህ መመጽወትን ገንዘብ አድርግ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
3
ለመንፈሳዊ ልምምድ ምክሮች

በእግዚአብሔር ህግ ብርሃንነት ራስህን እየመረመርክ ድክመቶችህን ፈልግ፡፡ ትንንሽ ድክመቶች እንኳ ቢሆኑ አትናቃቸው፤ምክንያቱም
ያድጋሉና፡፡ ‹‹ወይናችን አብቧል ኑ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ፡፡››(መኃ 2፣15)

ራስህን ከማፅደቅ ተቆጠብ
ለስህተቶችህም ማስተባበያ አትፈልግ ራሱን የሚያፀድቅ ሰው ዘወትር ባለበት መሔድ እንጂ የሚያሻሽለው አንድም ነገር የለምና፡፡ ምክንያቱም ባይኑ ፊት ከእርሱ በላይ ሰው የለም ለራሱ እንከን የለሽ ነው፡፡ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ይህን ያደረኩት በዚህ ምክንያት ነው እያለ ሲያስተባብል ወድቆ ይቀራል፡፡ለራሱ ትክክለኛ ግምት ያለው የማይመፃደቅ ሰው ግን ድክመቱን መናዘዝ ብሎም ማስወገጃውን መንገድ መለማመድ ይችላል፡፡ ችግሮችህ ስር ሰደው ሰውች ሊገልጡብህ የሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ የሚሰማህ መሸማቀቅ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ቀደም ብለህ እራስህ ገልጠሐቸው ለመፍትሔው ልምምድ ብታደርግ ይህ ሁሉ ነገር ባንተ ላይ አይከሰትም፡፡

ሁሌም ራስህን ሁነህ ተገኝ
በሕይወትህ ቅንነት የሚነበብብህ ሰው ሁን፡፡ መጽሃፍትን ስታነብም ሆነ ስብከት ስታዳምጥ ጉድለቶችህን እየፈለክ ይሁን፡፡ ሰምተህ ለማድረግም ተነሳሳ፡፡

የኃጢያት ስሩ አንድ ነው
ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም እርስ በራሳቸው የተያያዙ መሆናቸውንም እርግጠኛ ሁን፡፡ አንድ የተወሰነ የሀጢያት አይነትን ለመቅረፍ ስትነሳ ሳታውቀው.ሌሎችንም እየበጣጠስክ መሆኑን እወቅ፡፡እንዲሁም አንድ በጎ ሥነ ምግባርን ለማዳበር ስትለማመድም ቢሆን ሌሎች ብዙ ሥነ ምግባራትን እያተረፍክ መሆኑን ልብ በል፡፡ ሥነ ምግባራቱም በአንድ ሠንሰለት የተያያዙ ናቸውና።
3👍2
ስለምን ይጨነቃሉ?

፩•ስለ ኃጢአትዎ?-አይጨነቁ "ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።" ይላል (ኢሳ ፩÷፲፰)- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።"(ማቴ 11÷28)

፪• ስለ ሞት?-ምንም አያስቡ " ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።* (ዮሐ 11÷26) -" ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።" (ምሳ 13÷14)

፫• ስለ ፍርድ ቀን? ፣በጭራሽ " ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።" ይላል ( ማቴ24÷44) - "ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።" ተብሏል(ዮሐ 6÷40)

፬• ስለ መከራ? ፣ አያስቡ ቅዱስ ጳውሎስ "እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ክፉም ደጉም ለበጎ መሆኑን ያስታውሱ።" ፣ብሎዎታል (ሮሜ 8÷28)

፭• ስለ ጤንነትዎ ? "ምን በወጣዎት " ልብሱን ብቻ የዳሰሰው እንደሆነ እድናለሁ ያለችውን ሴት ያስታውሱ ••• ልብ ይበሉ ።" የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች። ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ ብላለችና። ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ። ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ።" ( ማር 8÷27-30)

፮•ስለ ሀብት?: የሚያሳስብዎ አይሁን! " ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።፤ ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።የተድላ ምድር ትሆናላችሁና አሕዛብ ሁሉ ብፁዓን ብለው ይጠሩአችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።"( ት•ሚል፫÷፯-፲፪)

፯• ስለ ሥልጣን? አይቸገሩ " በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፣ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤ እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" ፣የሚለውን ልብ ያስታውሱ ( ማር 10÷43-44)

፰• ስለትዳር ፣? ሐሳብ አይግባዎ ።" የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።"፣(ዘፍ 24÷7) ብሎ ባሪያዎቹን የላከ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ መልካም ሚስት እንዳገኘለት አይዘንጉ።ስለዚህ ለእርሰዎም እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አጋዥ ያገኛሉ እርሰዎ ግን በጸሎት ይትጉ! ጠቢቡ ሰሎሞን " ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።"ይላል ( ምሳ ፲፱÷፲፬)

፱•ስለ ቤተሰብዎ ? ችግር የለም ። -በጸሎት በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አቅርቡ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ይላል ( ፊልጵ ፬÷፮)

፲• ስለ ሰዎች? በፍጹም አይጨነቁ::ጳውሎስ ቅዱስ " በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል።የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።"ይላል ሮሜ ፲፬÷፩-፭)
      

በመ/ር ተመስገን ዘገዬ
👍61
“ወላዲተ አምላክ” የቃሉ ትርጉም

“ወላዲተ አምላክ” የሚለው ቃል ምንጩ ግሪክ ሲሆን በግሪኩ (በጽርዑ) ቴዎቶኮስ (Θεοτόκος - theotokos) የሚል ሲሆን ትርጉሙም “የእግዚአብሔር እናት”፣ “የአምላክ እናት” “አምላክን የወለደች” ማለት ነው። “ወላዲተ አምላክ” የሚለው የሁለት ቃላት ጥምረት የሚገልጸው ዋና ሃሳብ ሲሆን ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሰው የሆነውና በእኛ ባሕርይ ተወልዶ የተገለጠው ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው የሚለውን መሠረታዊ የሆነውን የክርስትና እምነትና ትምህርት ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት፣ አምላክን ወልዳለች ስንል እግዚአብሔር በባሕርየ መለኰቱ የተገኘው ከእርሷ ከተወለደ በኋላ ነው ለማለት አለመሆኑ ግልጽ ቢሆንም መታወስ ግን ይኖርበታል። እግዚአብሔር በባሕርዩ ጥንትና ኋላ የለበትም፣ አስገኚና መነሻም የለውም፤ እርሱ ከጊዜ ጽንሰ ሃሳብ ውጭ የሆነ ዘለዓለማዊ አምላክ ነውና። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ያለ ነው። ለዚህ ነው ሙሴ “የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁ ጊዜ ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ?” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ዘሀሎ ወይሄሉ - IAM THAT I AM - ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ላከኝ በላቸው” በማለት ራሱን የገለጠው በዘለዓለማዊ ህላዌው ነው። ዘጸ. 3፥13-14 ስለዚህ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፣ ተወለደ ስንል በሥጋዌ ምሥጢር ስለ ተፈጸመው ነገር ማለታችን መሆኑ መዘንጋት የለበትም።

እግዚአብሔር ስንል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን እንደ መሆኑ ሰው የሆነውና በእኛ ባሕርይ የተወለደው ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነው እግዚአብሔር ቃል በተለየ አካሉ ነው። ቅዱስ ወንጌል “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” በማለት ስለ ቃል ቀዳማዊነትና እግዚአብሔርነት ከተናገረ በኋላ ዘመን ከተፈጠረ በኋላ ስለሆነው ነገር ሲናገር ደግሞ “ቃልም ሥጋ ሆነ፣ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ” በማለት የቃልን ሰው መሆን ይነግረናል። ስለዚህ አካላዊ ቃል ሰው ሲሆን በማኅፀኗ የፀነሰችውና በድንግልና የወለደችው እመቤታችን ናት ስለዚህ እርሷን ወላዲተ አምላክ ያሰኛት ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ስለሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “... ወእምኔሆሙ ተወልደ ክርስቶስ በሥጋ ሰብእ ዘውአቱ አምላክ ቡሩክ - ከእነርሱም [ከእስራኤላውያን] ክርስቶስ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው” እንዳለ። ሮሜ. 9፥5

ይህ “ወላዲተ አምላክ” የሚለው ቃል ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “ቃል ሥጋ ሆነ” ሲል የገለጸውንና ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ “የጌታዬ እናት” በማለት የገለጸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በአንድ ላይ ጠቅልሎ የሚይዝ ቃል ነው። ዮሐ 1፥14፣ ሉቃ 1፥43 “ቃል ሥጋ ሆነ” ማለትም አካላዊ የእግዚአብሔር ቃልና የእግዚአብሔር ቃል ከእመቤታችን የራሱ ገንዘብ አድርጎ ፈጥሮ የተዋሐደው የእኛ ባሕርይ በማኅፀነ ድንግል ማርያም፣ በምሥጢረ ተዋሕዶ ያለ መጠፋፋትና ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለያየትና ያለ መከፋፈል አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነዋል ማለት ነው።

ተዋሕዶውም አካላዊ ብቻ ሳይሆን ባሕርያዊም ስለሆነ እመቤታችን የወለደችው ብቻ ሳይሆን የፀነሰችውም ሥግው ቃልን - በባሕርዩ አምላክ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። ስለዚህ ይህ “ወላዲተ አምላክ” የሚለው ቃል የእመቤታችንን የወላዲተ አምላክነት ክብር ከሚናገረው በላይ የክርስቶስን ማንነት በተመለከተ ሊኖረን የሚገባውን መጽሐፍ ቅዱሳዊና ኦርቶዶክሳዊ እምነት ጠቅልሎ የሚይዝ መሠረታዊ ቃል ነው።

ምንጭ፦
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
መድሎተ ጽድቅ - ገጽ 276-277
👍2
"ኃጢአትን ባትሰራ መልካም ነው ፤ ኃጢአት ከሠራህ ሳትቆይ ንስሐ ብትገባ መልካም ነው። ንስሐ ከገባህ ዳግመኛ ወደ ኃጢአት ባትመለስ መልካም ነው። ወደ ኃጢአት ካልተመለስክ ይህ በእግዚአብሔር ዕርዳታና ቸርነት መሆኑን ብታውቅ መልካም ነው። ይህንን ካወቅህ ስለአለህበት ሁኔታ እግዚአብሔርን ብታመሰግን መልካም ነው።"

[ቅዱሱ ሰብ ባስልዮስ ]
@nshachannel ~ĴÔĨÑ ŦĤ€ ĈĤÃŇÑÉĽ
4
2025/07/14 17:08:14
Back to Top
HTML Embed Code: