Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1021 - Telegram Web
Telegram Web
® ተግሣጸ ዮሐንስ አፈወርቅ ©

#ንሥሓ
ተግሣጽ 4፡ እሾህ ባይወጋን ባንቆስል መልካም ነበረ። ያቆሰለን ካለ ግን በቁስላችን ላይ መድኃኒት ልናደርግበት ይገባል። ኃጢአት ባንሰራ መልካም ነበረ። ከሰራንም ግን ፈጣሪ ይቅር ይለን ዘንድ እንጸጸት ንሥሓ እንግባ። ሰናይኬ ከመ ኢንቆስል። ወእመሰቦ ዘአቁሰለነ ንደይ ፈውሰ ውስተ ቁስላቲነ።

#ትእግስት
ተግሣጽ 4፡ ሰዎች በሚዘልፉን በሚሰድቡን ጊዜ እንታገሥ። እንዳንበድልም (መልሰን እንዳንዘልፍ እንዳንሳደብ) ራሳችንን እንጠብቅ። ተግሣጽ 30፡ ለተዓጋሥያን የተዘጋጀውን አክሊል ወይም ክብር እንቀዳጅ ዘንድ የሚመጣብንን ፈተና ሁሉ እንታገሥ። ተግሣጽ 4፡ ንትዐገሥ እንከ ሶበ ይዘልፉነ። ወንትዐቀብ ከመ ኢነዐብስ።ተግሣጽ 30፡ ወንትዐገሥ ኩሎ ዘይመጽእ ላእሌነ።

#ትጋት #ጸሎት
ተግሣጽ 5፡ የማያልፍ ክብር የማታልፍ መንግሥተ ሰማያትን እናገኝ ዘንድ እንትጋ። ጸሎትን እናብዛ። ጸሎት ኃጢአትን ሁሉ የሚደመስስ መድኃኒት ነውና። ኢንኅሥሥ እረፍተ ከመ ንርከብ አክሊለ ዘኢየኀልፍ።ናብዝኅ እንከ ጸልዮ። ጸሎትሰ መድኃኒት ውእቱ ወአሰሳሌ ኩሉ ኃጣውዕ።

#ፍቅረ #ንዋይ
ተግሣጽ 11፡ የገንዘብ ፍቅር አያንድድህ። ገንዘብም አያሸንፍህ። ተግሣጽ 20፡ ጥሪት እና ገንዘብ በዚህ ምድር የሚቀሩ ናቸው። ነፍስ ግን ከእነርሱ የከበረች በመሆኗ ትታቸው ወደ ሰማይ ትሄዳለች። ኢያንድደከ ፍቅረ ንዋይ። ወኢይማዕከ ስስእት።ተግሣጽ 20፡ ንዋይሰ ወጥሪት ይተርፉ በዝየ። ነፍስሰ ተኀድጎሙ ወተሐውር ከሐ።

#ሐልዮ #ነቢብ
ተግሣጽ 14፡ ከሐልዮ ኃጢኣት መዳን የሚቻለው እንዴት ነው ካሉ። ነገራተ እግዚአብሔርን በማሰብ እና መልካም ነገሮችን በማሰብ ነው። ይትከሀል በተዘክሮ ሰናያት ወተዛውዖ በነገረ እግዚአብሔር ልዑል እንዲል። ፈጣሪን አዘውትረን ስናስብ ክፉ ሀሳቦች ከሕሊናችን ይጠፋሉ። እግዚአብሔር በገቢር በተሰራ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን በነቢብ በተሰራ ኃጢኣትም ስለሚፈርድ አፋችን ክፉ ነገርን እንዳይናገር እንከልክለው። አኮኖሚያዊ እግዚአብሔር ዘይኴንን በገቢር ባሕቲቱ አላ በእንተ ቃልሂ እንዲል።

#ጽናት
ተግሣጽ 24፡ መርከበኛ መርከቡን ባሕሩን ሁሉ አዙሮ ከወደቡ ሊደርስ ጥቂት ሲቀረው መቅዘፉን ቢያቆም መርከቡ ይሰጥምና ገንዘቡን ሁሉ ያጣል። የቀደመ ትጋቱ ከንቱ ይሆናል። ከማሁኬ ሥርዓተ ምግባር ዘጽድቅ። የጽድቅ ሥራም ይህን ይመስላል። እስከ እለተ ሞታችን ተግተን ካልሠራን ጥቂት ዘመን ሲቀረን ቸልተኛ ከሆንን የሠራናውን መልካም ምግባር ሁሉ እናጣለን።

#ራስን #መጠበቅ
ተግሣጽ 1፡ ወዳጆቼ ሆይ የነፍስ ንጽሕናችንን እንጠብቅ ዘንድ ይገባናል። ነፍሳችንን ከሚያጠፉ ክፉ ነገሮች ፈጽመን መራቅ ይገባናል። ይደልወነ ኦ ፍቁራንየ ንዕቀብ ንጽሕናነ። ወኢንቅረብ ግሙራ ኀበ ምንትኒ እምርኩስ።


ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
በመ/ር በትረማርያም አበባው
👍21
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሃይ. አበ 67፣ 13 "ኃይላት አዕረግዎ ለኤልያስ ኀበ ተአዘዙ ወቃለ እግዚአብሔር ዋህድ ለሊሁ ዐርገ በሥልጣኑ እስመ እግዚአ ኃይላት ውእቱ" ይላል።

ትርጓሜው ኤልያስን የታዘዙ መላእክት ወደታዘዙበት ቦታ አሳረጉት። አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የመላእክት ጌታ ነውና በሥልጣኑ ዐረገ ይላል። ክርስቶስ ያረገው ዕርገት የባሕርይ ዕርገት ነው። ኤልያስ ያረገው ዕርገት ደግሞ የጸጋ ነው ያውም ደግሞ በሠረገላ ነው። ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው። በክርስቶስ ዘንድ ምንታዌ (ሁለትነት) የለም። ቅዱሳት መጻሕፍትም ጠንቅቀው ወልድ ዋሕድ ይሉታል። ክርስቶስ ዐረገ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ሲባል ሥጋ በተዋሕዶ አምላክ መሆኑን ያሳውቀናል። ይህም የሆነው ገና በማኅፀን በጊዜ ተዋሕዶ ነው። በ፵ ቀን ዐረገ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ሲል የማዳን ሥራውን ፈጸመ ማለት ነው እንጂ ቀድሞውንም ከጊዜ ተዋሕዶ በኋላ ንቡር ነው።
                              
ቅዱስ ቄርሎስ በሃይ. አበ. 124፣34 "እስመ ክርስቶስ ኢተቀብዐ በእንተ መፍቅድ ዘቦቱ አላ ለሊሁ ቀባኢ ውእቱ። እጠቀም ብሎ የከበረ አይደለም። እርሱ ሌላውን ያከብራል እንጂ። ወዐርገ ኀበ ሥልጣነ መለኮቱ እንዘ ሰብእ ውእቱ ሰው ሲሆን በአምላክነቱ ሥልጣን ከበረ። ተብህለ በእንቲኣሁ ከመ ውእቱ ተለዐለ ፈድፋደ በእንተ ትሕትና ወሕፀፅ እንተ ዘትስብእት ወንዴት ትሑት ሥጋን ስለተዋሐደ ከበረ ተባለ" ይላል።

ክርስቶስ ማለት ቅቡዕ (የተቀባ) ማለት ነው። ይህም ሥለ ሥጋው የተነገረ መሆኑን ይህ ቃል በግልጽ ይነግረናል። በቃልነቱ ከጊዜ ተዋሕዶ በፊትም ክቡር ነውና። ቅድመ ተዋሕዶ አምላክ ያልነበረ ሥጋ በጊዜ ተዋሕዶ አምላክ መሆኑን ይነግረናል። ተቀብዐ ማለት ከበረ አምላክ ሆነ ተብሎ ይተረጎማል። ሥጋ አምላክ የሆነው ደግሞ ከቃል ጋር ሲዋሐድ ነው። ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ የሚባለው ለዚህ ነው። መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ (ክብር) ሆነው የሚል ትምህርት የለም። ይህን የሚሉ ቅብዐቶች ናቸው። ሥላሴ በክብር አንድ ናቸውና። በሥላሴ ዘንድ አብ ቀባዒ፣ ወልድ ተቀባዒ፣ መንፈስቅዱስ ቅብዕ የሚባል አካላዊ ግብር የለም። አካላዊ ግብር ወላዲነት፣ አሥራጺነት፣ ተወላዲነት፣ ሠራጺነት ነው። ኵነታትም ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ ናቸው። አካላዊ ግብር ሦስቱ አካላት የሚለዩበት ነው። በአካላዊ ግብር ተገናዝቦ የለም። ይህም ማለት በአብ ወላዲነት ወልድ ይወልዳል አይባልም። በኵነታት ግን ተገናዝቦ አለ። ይህም ለምሳሌ በአብ ልብነት ወልድ ያስባል፣ በወልድ ቃልነት አብ ይናገራል እንላለን። አብ ለባዊ ለርእሱ ሆኖ በእርሱ ወልድ እና መንፈስቅዱስ ለባውያን ሆነው ይኖራሉ። አለባውያን ለፍጡራን ነው። ወልድ ነባቢ ለርእሱ ሆኖ በእርሱ አብና መንፈስቅዱስ ነባብያን ሆነው ይኖራሉ። አንባብያን ለፍጡራን ነው። መንፈስቅዱስ ሕያው ለርእሱ ሆኖ በእርሱ አብና ወልድ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ። ማኅየውያን ለፍጡራን ነው። አብ ወልድ መንፈስቅዱስ በሥልጣናዊ ግብር አንድ ናቸው። በክብር፣ በሥልጣን፣ በመዓርግ አንድ ናቸው። በአንዷ ክብር ሦስቱም አካላት ይጠሩባታል። ይኽውም አብ ክቡር፣ ወልድ ክቡር፣ መንፈስቅዱስ ክቡር ቢል አንድ ክብር ነው። አብ ቀባዒ (አክባሪ)፣ ወልድ ቀባዒ (አክባሪ)፣ መንፈስቅዱስ ቀባዒ (አክባሪ) ቢል ይሆናል። ለዚያ ነው ሃይ. አበ. 124፣34 ወልድን ለሊሁ ቀባዒ ውእቱ ያለው። በሥልጣናዊ ግብር አንዱ አካል የተጠራበት ለሌኛው አካልም መጠሪያ ይሆናል። ወልድን አብ አስነሳው ሲል ብታየው ማስነሣት የአብ ግብር ብቻ አይምሰልህ። በሌላ ቦታ ወልድ ወተንሣእኩ በሥልጣን ባሕቲትየ ሲል ይገኛልና። በሥልጣናዊ ግብር (ባሕርያዊ ግብር) አብ ወልድ መንፈስቅዱስ አንድ ናቸው። ሥላሴ በክብር አንድ ናቸው። ስለሆኑም አንዱ አክባሪ አንዱ ከባሪ አይደሉም። ሠለስቱ አካላት በክብር አንድ የሆኑ አክባርያን (ቀባዕያን) ናቸው እንጂ። ሃይ. አበ 113፣2 ዕሩያነ መዓርግ ወክብር እንዲል።
                            
ከበረ ሲል ብታገኘው እንኳ ስለተዋሐደው ሥጋ እየተናገረ መሆኑን ልብ በል። ምክንያቱም ቅዱስ ቄርሎስ በሃይ. አበ 74፣37 እንደገለጸው "ወመጻሕፍትሰ ቦ ዘይቤላ በእንተ መለኮቱ ወቦ ዘይቤላ በእንተ ትስብእቱ እንዘ ውእቱ ከመ አምላክ ወሰብእ ወቦ ዘይቤላ በእንተ መለኮቱ ወትስብእቱ ኅቡረ"።

መጻሕፍት ስለአንዱ ክርስቶስ ሲናገሩ አምላክም ሆኖ ሳለ ስለሰውነቱ የሚናገሩበት ጊዜ አለ። በዚህ ጊዜ አምላክነቱን ዘንግተው አይደለም። ራሱ ክርስቶስ ሲያስተምር ብዙ ቦታ ላይ ራሱን የሰው ልጅ እያለ ይናገር ነበር። በዚህ ጊዜ አምላክነቱን ዘንግቶ አይደለም። ሰው ሆኖም ሳለ ስለአምላክነቱ የሚናገሩበት ጊዜ አለ። በዚህ ጊዜ ሰውነቱን ዘንግቶ አይደለም። በአንድ ጊዜ ስለሰውነቱም ስለአምላክነቱም የሚናገሩበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና ሲል ሁለቱን በአንድ ላይ እንደተናገረ ለቡ። ስለዚህ ጌታ ራሱን የሰው ልጅ ባለበት መንገድ ቅቡዕ ተብሏል። የከበረው ሰውነቱ ነውና። በቃልነቱማ ድሮም ክቡር ነው። ወዐርገ ኀበ ሥልጣነ መለኮቱ ሲልም ሰው ሲሆን በአምላክነቱ ሥልጣን ከበረ ማለት ነው።
                            
ቅዱስ ባስልዮስም በሃይ. አበ 96፣53 "ወሶበ ተንሥአ ዐርገ ውስተ ሰማያት ወዘኒ ወረደ ዘእንበለ ሥጋ ውእቱ ዘዐርገ ሥግወ ወአሐዱ ውእቱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ወኢወሰከ ኍልቆ ራብዐየ ወኢካልዐ ገጸ ወነበረ በየማነ አብ" ይላል። ትርጉሙ ከተነሣም በኋላ ወደሰማይ ዐረገ። ሥጋ ሳይይዝ የመጣ እርሱ ሰው ሆኖ ዐረገ። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እርሱ ነው። ለሥላሴ አራተኛ ለቃል ሁለተኛ አልሆነም። በአብ ዕሪና ኖረ ይላል። ከተዋሕዶ በኋላ ይህ የሥጋ ይህ የቃል አንልም። አንድ ክርስቶስ እንላለን እንጂ። የተራበውም፣ የተራቡትን ያጠገበውም ያው አንዱ ክርስቶስ ነው። ሰው የተባለውም፣ አምላክ የተባለውም ያው አንዱ ክርስቶስ ነው።
                              
እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ
በትረማርያም አበባው
https://www.tgoop.com/betremariyamabebaw ነው
                         
https://www.youtube.com/@edenawizechristos
                          
Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721
ታስታውሰኛለህ

እዘምር ነበረ
እፈራክ ነበረ
አስቀድስ ነበረ
እዎድክ ነበረ ነበረ ነበረ ነበረ
ነበረ ያልኩኝ ነውር ላይ ከርሜ፣
ያንገበግበኛልህ አንተን ያህል አባት መስቀሌ ደግሜ ።
የመመለስ መንገድ ባይሆንም ለጌታ፣
መጣል ግን አይከፋም የነበርን ቦታ።
የሰንበት ቀንና ሰንበት ትምህርት ቤት
ትዝታ የሌለው ባይኖርም አንዳች ቤት።
በልጅነት ድሮ፣
አሾረው ነበረ የደብሩን ከበሮ።
እላለው እላለው
በጊዜ በእድሜ እየደበዘዙ
ዘምሬ ነበር ማለት የሚያበዙ
ከነበር ፉከራ ጀርባ ተቀምጠን
አታውቁም ከመባል ፍረሀት ሮጠን
ሰንበት ትምህርት ቤት መልዕክት ዮሐንስ
መልከዕ እየሱስ ዘልቄ ነበረ የሚለው ሰው ቁጥር ያውም በተውሶ
ሰንበት መማር እና ሰንበት ማክበር ቀረ ነበርን ከልሶ
ነበርን በንባብ ነበርን በውርድ ነበረን በዜማ
ስናጠና ከርመን አየው ተላለፈን
ለእግዜሩም ለሰው ነበርን የተረፈን
ሙዳዬ ምፅዋት የመያዝን ትህትና
አሀን ተቀየርን በሚይዙ ሰዎች ውስጣችን ሳይቀና፣
አሁን ተቀየርን በሚይዙ ሰዎች ውስጣችን ሳይቀና።
ልክ እንደ ጅልነት ልክ እንደ ልጅነት ሰፈረነው ሲያበቃ
እኛም እንዲ ነበርን ማለት ሆነ በቃ
ትህትና ሰበርን ትህትና ቀበርን
ስናጠናው አለን መልከዓ ነበርን
ታስታውሰኛለህ
አትይብኝ ድንጉጥ ነበሴን፣
አትይብኝ ፍሬ ከርሴን።
ቁመናዬን አትታዘብ
እኔ ከንቱ መዘባዘብ
አትበርብረኝ ኩላሊቴን፣
ታውቀው ዬለህ ባዶ ቤቴን
ባዶ ሰው ነኝ አንተን ባምንም
አትመዝነኝ አልመዝንም
ስንት እመዝን እንደው
ቆዳዬን ብቀደው
ስንት ይሆን ምለካው
ጨርቁን እስክነካው
እንጃልኝ ተማፅኖዬ አንዲት
ነውሬን ተውልኝ
ሽማዬን ክላልኝ
ጨፍነህ ላሞኝህ
የውሸቴን ልሸኝህ
በልዘልቅ እንኳን ቤትህ ልርገጠው ደጅህን
በዚያው ባንተ አይንህ ጋርድልኝ አይንህን
እኔማ እኔማ ገዛው አልባስጥሮስ
ገና ነው የኔ ጦስ
እኔማ ገዛው መባ ጧፍ
ገና ነው የኔ አፍ
እኔማ ገዛው መጋረጃ
የኔን ነገር እንጃ
ታውቀኝ ዬለህ (2) ያንን መልኬን
ምን ቀየረው ያን ታሪኬን
መቼ ዎጣው ከእቅፍህ
ምን ጊዜ ነው የሸሸሁት
ምን እለት ነው ከእኛ ስር ያመለጥኩት
ምን ሰዓት ነው ምን ቅፅበት ነው ምን ደቂቃ
ትተወኛለህ ዎይ ለሞት እስክበቃ

ታስታውሰኛለህ
እዘምር ነበረ
አስቀድስ ነበረ
እፈራህ ነበረ
እዎድህ ነበረ ነበረ ነበረ ነበረ
ነበረ እያልኩኝ ነውር ላይ ከርሜ
ያንገበግበኛል አንተን ያህል አባት መስቀሌ ደግሜ

ታስታውሰኛለህ አሁንም ልጅህ ነኝ
እኔ ፈራሀለው ፍቅር እያመመኝ
ተለውጫ ቢፈርስ ፀጋና መንገዴ
መልኬን የማይረሳ እየሱስ ዘመዴ ክርስቶስ ዘመዴ አግዚአብሔር ወዳጄ
ታስታውሰኛለህ አሁንም በክብር
ቆዳዬን በለጠው ነውሬን ስደምር
ነበርኩኝ በቤትህ የምለማመንህ
ነበረኩኝ በቤትህ ያሞቀኝ እጣንህ
አይኖችህ ናፈቁኝ እጆችህ ናፈቁኝ
እቅፍህ ናፈቀኝ
ሰላም ያልኩት አለም ጭራሽ አስጨነቀኝ
ቅዳሴው እንዳለው ችለው ለታደሉ
አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ያስጨክኑማሉ
አስጨክነኝ በአለም አስጨክነኝ በሀጥያት አስጨክነኝ በቃ
ትተወኛለህ ዎይ ለሞት እስክበቃ
አስጨክነኝና ልመለስ ከቤትህ
ተብዬ ልጠራህ እግዚአብሔር አባትህ
አስጨክነኝ
አስጨክኝኝ ማርያም
አትህጂ ትነሺኝ አኑሪኝ በግርግም
ግድ ሆኖብኝ እንጂ ከልጅሽ ቤት መራቅ እኔ አልፈልግም
ግድ ሆኖብኝ አይደል (2)የምመላለሰው
እንጂ ከአባትህ ቤት ምን ይሻለዋል ሰው
ያነጫንጨኛልህ (2)
የእናቱ መዳፍ ከእጁ እንደቀሙት
ልረፍና ጥሪኝ ከልጅሽ ስር ልሙት
ፍቅርሽ የለው ጠረፍ
መንገዴ ይቅናና ጥሪኝና ልረፍ
ደከመኝ ጌታዬ ደከመኝ ጌታዬ ደከመኝ የኔ አምላክ
ደከመኝ ማርያም ደከመኝ እመአምላክ
ወይ እንደሰው አልሆንኩ ወይ እንደመላአክ
መጀገን ከበደኝ በገዛ ስጋዬ
ልተኛበት ያልኩት አላስተኛ አለኝ የገዛ አልጋዬ
እሺ በለኝና
አስጨክነኝ እና
ልመለስ ከቤትህ በፍቅር በስምህ
ስጋዬን በስጋ ደሜንም በደምህ
አስጨክነኝ በአለም እንዳልሆን ግያስ
አስጨክነኝ እና ከቤትህ ልመለስ
ሙዳዬ ምፅዋት ልያዝ

ታስታውሰኛለህ
እዘምር ነበረ
አስቀድስ ነበረ
እፈራህ ነበረ
እዎድህ ነበረ ነበረ ነበረ ነበረ
ነበረ እያልኩኝ ነውር ላይ ከርሜ
ያንገበግበኛል አንተን ያህል አባት መስቀሌ ደግሜ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከ ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን
8👍1
ነገረ ተዋሕዶ ክፍል 3

እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ያለ ከሆነ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ ማለት ምን ማለት ነው? በሁሉ ቦታ ያለ ከሆነ ወረደ ወጣ የሚለው ቃል እንዴት ነው የሚል ጥያቄ ይነሳል። በነገራችን ላይ ዕርገት 2 ነው። መጋቢት 29 በጊዜ ተዋሕዶ ሥጋ በቃል ዐረገ ይባላል። ይህ ዕርገት የርኅቀት ያይደለ የርቀት ዕርገት ይባላል። ይህን ሊቃውንቱ በየሐተታቸው ስጋ የቃልን ረቂቅነት በተዋሕዶ ገንዘብ በማድረጉ የሚናገሩት ነው። ይህ ፍሬ ነገሩ ሥጋ ቃልን ሲዋሐድ በድንግል ማኅጸን ሳለ በቃል በኪሩቤል ጀርባ ተቀመጠ የሚለውን ምሥጢር የያዘ ነው። ሁለተኛው ከትንሳኤ በኋላ በአርባኛው ቀን ቃል በሥጋ ዐረገ ይባላል። ይኽውም የርቀት ያይደለ የርኅቀት ዕርገት ይባላል። ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምእት ላይ የሥጋ ዕርገት በማኅጸን የቃል ዕርገት በ40 ቀን የሚለው ይህን ምስጢር የያዘ ነው።

ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ውስተ ኩሉ በሐውርት መለኮቱ ይላል። መለኮት በሁሉ ቦታ ያለ ነው ስለዝህ መውረድ መውጣት የለበትም። ወረደ ወጣ መጣ ሄደ የሚሉ ቃላት በሥጋዌ ተዋሕዶን ሲገልጹ በብሉያት ትርጓሜ ብዙ ጊዜ ረድኤትን ያመለክታሉ። ለምሳሌ እግዚአብሔርሰ ገሐደ ይመጽእ ሲል በረድኤት ይመጣል ረድኤት ይሰጣል ማለት ነው። በትንቢትነቱ ካየነው ደግሞ ሥጋን ይዋሐዳል ማለት ነው። ይህ ለምጽአትም ይሆናል። ለዚህም ነው ሊቁ በሃይማኖተ አበው። አኮ ዘፈለሰ እመካን ውስተ መካን ከመ መላእክት። እሙንቱሰ ይትኀጥዑ እመካኖሙ ሶበ ይትፌነው ለመልእክት ውእቱሰ ነስአ ሥጋነ እንዘ ምሉዕ ውእቱ በኩለሄ ያሉት። እንደ መላእክት ከቦታ ቦታ የሄደ አይደለም። መላእክትስ ከሰማይ ወደ ምድር ሲላኩ ከሰማይ ይታጣሉ ከምድር ይገኛሉ። በሰማይ ሲኖሩ በምድር ይታጣሉ። ጌታ ግን ምልዓቱን ሳይለቅ ሥጋችንን ነሳ ይላል። በደንብ መርምረው። ነስአ ወረደ ኮነ መጽአ ተወልደ ኀደረ በምስጢረ ሥጋዌ በምስጢራዊ የትርጓሜ አብነት ተዋሐደ ተብለው ይተረጎማሉ።

ጥር 11 በጥምቀት ጊዜ ኀዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ ቆመ ማእከለ ባሕር እንላለን ትርጉሙ 99ኙን ነገደ መላእክት ትቶ በባሕር መካከል ቆመ ማለት ነው። ትቶ የምትለዋ ቃል ባሕርየ መላእክትን አለመዋሐዱን ሲያሳይ ነው። ይህም ሐዋርያው ኢነስኦ ለዘነስኦ እመላእክት የነሳውን ሥጋ ከመላእክት የነሳው አይደለም አላ እምዘርዐ አብርሀም የሰውን ሥጋ ነሳ እንጂ ከሚለው ጋር የተያያዘ ቃል ነው።

ሥጋ የከበረ ከቃል ጋር ስለተዋሐደ ነው። ሃይ.አበ. 31÷5 ወከመዝ ይተረጎም ነገሩ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘይቤ ቃል ሥጋ ኮነ። በነሲኦቱ ሥጋ እም እግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም። ሥጋ ረከበ ዕበየ በተሳትፎቱ ወበተዋሕዶቱ ምስለ ቃል። ዮሐንስ ወንጌላዊ ቃል ሥጋ ኮነ ያለው ከድንግል ማርያም ሥጋን ስለነሳ ነው ካለ በኋላ ሥጋ ከቃል ጋር በመዋሐዱ ታላቅነትን አገኘ ይላል።ያዝልኝ።ሥጋ ታላቅነትን ያገኘ ከቃል ጋር ስለተዋሐደ ነው ነው ያለን እንጂ መንፈስቅዱስ ክብር ሆኖት አላለም። ለዚያም ነው ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ የምንለው።

ሃይ.አበ.121-123 ባለው እዩት እንዲህ ይላል እመቦ ዘይብል ከብረ በመንፈስ ቅዱስ ውጉዘ ለይኩን።በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል ቢኖር የተወገዘ ይሁን አለ። ከዚያ ወዘይገብርዎሂ አብ ወመንፈስ ቅዱስ ይገብር ወልድሂ አለ። ይህች ግብር ሥልጣናዊት ናት።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየ!!!
መምህር በትረማርያም አበባው
(የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር)
የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
2👍1
ትንሳኤ ልብ
የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማየት ከፈለግን መጀመሪያ የእኛ የእያንዳንዳችን ልብ ትንሳኤ ያስፈልገዋል።

1ኛ ጸሎት፦ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መነጋገር ነው። ስለዚህ ከፈጣሪ ጋር ከመነጋገር የበለጠ ምንም ነገር ስለሌለ ከማንኛውም ነገር በፊት ቢያንስ በ7ቱ ጊዜያት (3, 6, 9, 12, 3, 6, 12) ሰዓት መጸለይ አለብን።ጸሎት ምስጋና ያለበት ልመና ነው።ፈጣሪ በቸርነቱ ስላደረገልን ነገር ሁሉ በፍቅር ማመስገን አለብን። መላእክት ይህን ሁሉ ጸጋ የሰጣቸውን ፈጣሪ በፍቅር ያመሰግኑታል። ተፈጥሮን እንድንኖርባት የሰጠን አካላችንን ካለመኖር አምጥቶ የሰጠን ለእኛ የሚያስፈልጉን አየርን ውሃን እና ሌሎች ነገሮችን የሰጠንን ፈጣሪ ማመስገን ይገባል።

2ኛ ይቅርታ፦ከፈጣሪ ውጭ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ ፍጹም አይደሉም ሊሳሳቱ ይችላሉ።በዚህን ጊዜ እኛም ብዙ ስህተቶችን እንደሰራን በማስታወስ ፈጣሪ ግን በቸርነቱ በይቅርታ ይቅር እንዳለን በማሰብ እኛም በሌሎች ላይ ስህተት የመሰለ ነገር ስናይ ከቂም ከበቀል ይልቅ በይቅርታ ልብ አይተን ፈጣሪ እኛን ይቅር እንዳለን እነርሱንም ይቅር እንዲላቸው በርኅራኄ ማየት ነው።

3ኛ ፍቅር፦ ይህ እግዚአብሔርን መውደድ እና ሰውን መውደድ ተብሎ ይከፈላል። እግዚአብሔርን መውደድ ማለት ለትእዛዞቹ መገዛት ሲሆን ሰውን መውደድ ማለት ደግሞ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌሎች እንዲደረግ አለመፈለግ እና አለማድረግ ሲሆን በአንጻሩ ለእኛ ሊደረግልን የምንፈልገውን የምንመኘውን ነገር ለሌሎችም መመኘትና ማሰብ ነው።

4ኛ እውነት፦ እውነት ማለት ውሸትና ግምት ያልተቀላቀለበት ግነት የሌለበት ነገሩን እንደነገርነቱ ብቻ በጥራት ማቅረብ መናገር ማለት ነው።ከሰዎች ክብርን እና አድናቆትን ሽተን ወይም ሰዎችን ለማበሳጨት ወይም ለማስደሰት ብለን ያልተደረገን ነገር በልብ ወለድ ወይም በእውነቷ ላይ ጨመርመር እያደረጉ ማውራት ውሸት ስለሆነ ልንተወው ይገባል።

5ኛ ጾም፦ ጌታችን ዝንቱ ዘመድ ኢይወጽእ ዘእንበለ በጾም ወበጸሎት ብሎ እንደተናገረው ክፉ ሀሳቦቻችንን ከአዕምሮ ለማስወጣት ጾም ወሳኝነት አለው።ጾም ማለት በተወሰነ ጊዜ ከምግብ በተወሰኑ ዕለታት ከጥሉላት መከለከል ለዘላለም ደግሞ ክፉ ከማየት ክፉ ከመስማት አጠቃላይ ሕዋሳቶቻችንን ከክፉ ነገር መጠበቅ ነው።አእምሯችንን ከሚበክሉ ነገሮች መራቅ ነው።

6ኛ ቁርባን፦ የሰው ልጅ የሚቀደሰው ንሥሓ ገብቶ የጌታችንን ክቡር ሥጋውን ክቡር ደሙን በልቶ ጠጥቶ ነው።በዚህም አምላክ የጸጋ ውኅደት ይዋሕደናል። መልካሙን መንገድም ይመራናል።

7ኛ ተግባረ ዕድ፦ ይህም ማለት በዚህች ምድር እስካለን ድረስ የምንበላውን የምንለብሰውን እና ሌሎች ለሥጋችን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት መስራት ነው።ጌታም ጥረህ ግረህ ብላ ብሎናል።ስለዚህ ከፈጣሪ ሕግ የማያወጡ ሥራዎችን ማረስ መቆፈር ማስተማር መጻፍ ማከም ሕንጻ መስራት ወዘተ የመሳሰሉ ስራዎችን መስራት ነው።

8ኛ ንሥሓ፦ ይህ ደግሞ ቅጣት እንደሚያስቀጣ እያወቅን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት የሰራነውን በደል በንሥሓ አባቶቻችን በኩል ተናግረን ቀኖና ተቀብለን እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቀን ወደ መልካም ስራዎች የምንገባበት በር ነው።ንሥሓ መጸጸት ማለት ነው።ምን ነክቶኝ ነው ይህን ክፉ ስራ የሰራሁት ብለን ጌታዬ ሆይ በቸርነትህ ማረኝ የምንልበትና ጥፋታችንን ለማረም እና መልካም ስራ ለመስራት ከፈጣሪ የሚሰጥ ሁለተኛ ዕድል ነው።ወድቄ ልሰበርና እጠገናለሁ እንደማንል ሁሉ።ኃጢአት ልስራና ንሥሓ ልግባ ግን አይባልም። ኃጢአት ለመስራት አቅዶ ንሥሓ ለመግባት ማሰብ አይገባም።እስከዛሬም አድርገነው ከሆነ ለዚህም ንሥሓ ገብተን ሕይወታችንን ማስተካከል ይገባናል።

9ኛ ትሕትና፦ ይህ ደግሞ እኛ በብዙ መንገድ ደካሞች አላዋቂዎች መሆናችንን አውቀን በሌሎች አለመፍረድን ያካትታል።አለማወቅ ስለሚገድበን ፈጣሪ በተለያዩ አምሳላት ስለሚገለጽ ለማንኛውም ሰው ራስን ከልብ ዝቅ ማድረግ ነው።ሁሉም ሰው ከአንተ የከበረ እንደሆነ አስበህ መኖር ማለት ነው።ትሕትና ደካማነታችንን አውቀን ረድኤተ እግዚአብሔርን መሻት ነው።

10ኛ ትዕግሥት፦ ይህ ደግሞ ነገር አላፊ ቻይ መሆን ማለት ነው።ክፋትን በክፋት ላለመመለስ መታገል ነው። ሰው ሲሰድበን መልሰን ላለመስደብ ፈጠን ፈጠን የሚል ሕዋሳታችንን መግታት ነው። ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ብሎናል ጌታችንም።

በነገራችን ላይ ልባችን ከተመለሰ እንደ ፈያታይ ዘየማን በአጭር ጊዜ ገነት የሚያስገባንን ስራ መሰራት እንችልለን።ቂርቆስ ታላቅ ሰማእት ለመሆን በዚች ምድር የኖራት 3 ዓመት በቂ ነበረች።እኛም ቀሪ ዘመናችንን 1 ቀንም ትሁን 1 ሰዓት መልካም ሰርተንባት እንለፍ።

እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን።
አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይገባል።
👍52
አርጋኖን ዘሠሉስ

ምዕራፍ ፬
፲፰. ሰይጣን ከቶ እንደ ጸሎት ማስታጎል የሚወደው የለም፡፡ ጸሎት ፍላጻ ነውና ዓይኑን ይወጋዋል፡፡ ከሚጸልዩ ሰው አንደበት እሳት ወጥቶ ሰይጣንን ያቃጥለዋልና፡፡ ሰይጣንም ስለዚህ ከበጎ ሥራ ሁሉ ጸሎትና ትጋትን ይጠላል፡፡
፲፱. ይልቁንም ያንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፋጫል የምስጋናሽ ወሬ በርሱ ዘንድ መራጃ ነውና ራሱን ይቆርጠዋል፡፡
፳. ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡
፳፩. ባንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ ባንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡
፳፪. በግብር አምላካዊ አምላክን ለመውለድ በመፅነስሽ ጊዜ እርሱ በአይሁድ ልቡና ዕንቅፋትን አገባ፡፡ እንዲህ ሲል በዘር በሩካቤ እንደተወለደ ከዩሴፍ እንደሆነ፡፡
፳፫. በአይሁድ ልቡና ቅናትን አሳደረ በልጅሽም ላይ እንዲተባበሩ የግድ አላቸው እንዲሰቅሉትም እሺ በጎ አሰኛቸው፡፡
፳፬. ሰቅለውም ርኩሳን አይሁድ ምራቃቸውን በፊቱ እንዲተፉበት እስኪሞትም ድረስ ስርግርግ ለማለቱ መፃፃውን ከሐሞት ጋራ እንዲያጠጡት አደረጋቸው፡፡
፳፭. ሙቶም ከተቀበረ በኋላ በመቃብሩ ጠባቂዎች እንዲሾሙ አይሁድን ዘበዘባቸው ጠባቂዎች እንደተነሣ በነገራቸው ጊዜ ዳግመኛ ዘበዘባቸው፡፡
፳፮. ለጠባቂዎቹ ወርቅ እንዲሰጧቸው የትንሣኤውን ምስክርነት ያሳብላቸው ዘንድ ሌሊት እኛ ተኝተን ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሠርቀው ወሰዱት እንዲሉ አስተማራቸው፡፡ (ማቴዎስ ፳፰፣ ፲፪- ፲፫ ) ፳፯. በዕረፍትሽም ጊዜ የአይሁድን አርበኞች በልጅሽ ደቀ መዛሙርት ላይ በጠላትነት አስነሣ በድንሽን ጥለው እስከ ሸሹ ድረስ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ሰይጣን አንቺን ይጠላልና፡፡

ምዕራፍ ፲፪
፲፮. አንቺን ለማመስገን ቃሌን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ለውዳሴሽም በኃይል እጮኻለሁ ለዘፈንሽም በእጆቼ አጨበጭባለሁ ለልልታሽም በእግሮቼ አሸበሽባለሁ፡፡
፲፯. ለክብርሽም መገዛትን እሰጣለሁ፡፡ ስግደትም ለገናንነትሽ፡፡ ከሆድሽም ፍሬ ባፌ እጨምራለሁ የፍሬሽም ደም ለዦሮየ የጣፈጠ ነው፡፡
፲፰. የሽቱሽም መዓዛ ላፍንጫዬ ያማረ የተወደደ ነው፡፡ የድንግልናሽ ምስጋናም ደረቅ ጠጅ እንደጠጣ ልቡናዬን ደስ ያሰኛል ስላንቺ ደስታዬ ምን ያህል ነው ሐሤቴ ስለ ክብርሽ ምንኛ ነው፡፡
፲፱. አነጋገርሽ ያማረ ነው፡፡ ነገርሽም የጣፈጠ ከንፈሮችሽም የኃሤት መፍሰሻ አንደበትሽም የምስጋና ጎርፍ ያለበት ነው፡፡ እጅግ አማርሽ እጅግም ተወደድሽ መልክሽ ምንኛ ውብ ነው፡፡ ውድሽም እንደ ምን ነው፡፡ ፍቅሬ ሆይ በደስታሽ ይህ ቁመትሽ የሰሌን ዛፍ ይመስላል፡፡ (መሐ ፯፣ ፯-፰)
፳. የልብስሽም ሽታ እንደ ሽቱ ሽታ ነው፡፡ ያፍንጫሽም መዓዛ እንደ ወይን ጨርቋ ነው፡፡ ያፍሽም አከፋፈት እንደ ቀናንሞስ አበባ ምዑዝ ነው፡፡ ከሊባኖስ ዕንጨት ሁሉ ጋራ፡፡ (መሐ፣ ፬-፲፬)
፳፩. ሁለንተናሽ ያማረ የተወደደ በመንፈሳዊ ጌጽ የተጌጠ ነው፡፡ የምስጋና መብራት ይከብሻል፡፡ ከመለኮታዊ ብርሃን ጋራ የብርሃን እናት ሆይ የመሢሕ እናት የአምላክ እናት የዓለም መድኃኒት እናት የናዝሬቱ ኢየሱስ እናት ሆይ ከልጅሽ ዘንድ ለምኝልኝ፡፡
፳፪. ለሥጋዬ መበረታታትን ለነፍሴ ዕረፍትን ለልቤ ኃሤትን፡፡ ከዛሬም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ሕይወትን ከልጅሽ ከወዳጅሽ አሰጭኝ፡፡
፳፫. እመቤቴ ሆይ ከሞት ለዘለዓለሙ ታድኚኝ ዘንድ አድኚኝ አልልም፡፡ እንዲህማ እል ዘንድ ለዘለዓለም የሚኖርስ ሞትን የማያያት ማነው፡፡ (መዝሙር ፹፱-፵፰)
፳፬. እኔስ የምለው እንዲህ ነው፡፡ ንስሐ እስክገባ ድረስ እንዲቆይልኝ፡፡ የንስሐ ፍሬንም እስካቀርብለት ቸርነቱንም ደስ እስካሰኝ እንዲጠብቀኝ፡፡
፳፭. እመቤቴ ሆይ አንቺ ጠበቂኝ፡፡ ለዘወትርም ከኔ እንዳትርቂ ነፍስና ሥጋዬን ወዳንቺ አደራ እሰጣለሁ በዕድሜየም ሁሉ ለዘወትር አትተይኝ በዚህ ዓለም ከሚመጣብኝ መከራ ሁሉ ጠብቂኝ፡፡
3👍2
#መልአኩ #ቅዱስ #ዑራኤል

የጌታን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን የረጫትና የቀደሳት ይህ ግሩም መልአክ ነው።ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ እንዲል። ዑራኤል አንድም ዑርኤል ይለዋል። ዛሬም እግዚአብሔር ባወቀ ቤተክርስቲያን የሚታነጽ በት  ቦታ የጌታ ደም የነጠበበት ልዩ ቦታ ነው። በመብረቅ በነጎድጓድ የተሾመ መልአክ ነው። ዋልያ ከጸነሰች በኋላ ስትወልድ የወለደችው ግልገል ግማሽ አካሉ ከማኅፀኗ ወጥቶ ግማሽ አካሉ በሆዷ ቀርቶ ብዙ ቀናት ይቆያል። በዚህ ጊዜ ግማሽ አካሉ ከሆድ ግማሽ አካሉ ከውጭ ወጥቶ ሳር እየበላ ለጥቂት ጊዜ ይቆያል። ቅዱስ ዑርኤል ነጎድጓድና መባርቅትን ባሰማ ጊዜ ያ የዋልያ ግልገል ደንግጦ አፈትልኮ ከእናቱ ማኅፀን ይወጣል። መላእክት ብዙ ናቸው። እፅዋትን፣ እንስሳትን፣ ግዑዛን ፍጥረታትን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ በፈጣሪ የተሾሙ ናቸው። ዑራኤል ነቢዩ ሄኖክን የረዳ መልአክ ነው። መብረቅ በበረቀ ጊዜ አበቦች ይፈካሉ። ፍጥረታትን ሁሉ የሚመግብ እግዚአብሔር ይመስገን።

የመልአኩ ረድኤት አይለየን!!!
9
ወፎች ከምድር ከፍ ብለው ሲበሩ በቀላሉ [በወጥመድ] አይያዙም፤ አንተም እንደዚሁ ከላይ ያሉ [ሰማያዊ] ነገሮችን የምትመለከት ከኾነ በወጥመድም ኾነ በማንኛውም ዓይነት መሣሪያ በቀላሉ አትያዝም፡፡ ዲያብሎስ ወፍ አዳ’ኝ ነው፡፡ ስለዚህ ከቀስቶቹ ከፍታ መጥቀህ ብረር፡፡ ወደ ላይ ወደ አርያም የወጣ ሰው ከዚያ ወዲያ የዚህን ዓለም ማናቸውም ነገሮች አያስደንቁትም፡፡

ወደ ተራሮች ጫፍ በወጣን ጊዜ ከተማይቱና ግንቦቿ በጣም ትንሽ መስለው እንደሚታዩን፣ ሰዎችም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ጉንዳኖች እንደሚመስሉን እንዲሁ አንተም ወደ መንፈሳዊ ጥበብ ከፍታ ስትወጣ በምድር ላይ ካለው ነገር አንዱስ እንኳን አይማርክህም፡፡ ከዚህ ይልቅም ሰማያዊ ነገሮችን ስታስብ ገንዘብም ቢኾን፣ ክብርም ቢኾን፣ ሹመትም ቢኾን፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገርም ቢኾን በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው የዚህ ዓለም ክብሮች ኢምንትና ከሞቱ ነገሮች በላይ ምንም ረብ ጥቅም የሌላቸው ናቸው፡፡ እንዲህም በመኾኑ እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ፡- “ዓለሙ በእኔ ዘንድ ስቁል [ምዉት] ነው” (ገላ.6፡14)፡፡ ጨምሮም እንዲህ ሲል ተግሣጹን ተናገረ፡- “በላይ ያለውን አስቡ” (ቈላስ.3፡2)፡፡ በላይ ያለውን? አንተ ጳውሎስ! እየተናገርክ ያለኸው ስለ ምን ዓይነት ጸሎት ነው? ፀሐዩ ያለበትን፣ ጨረቃ ያለችበትን ነውን? “አይደለም” [ይላል ቅዱስ ጳውሎስ]፡፡ እንኪያስ የት ነው? መላእክት ያሉበትን ነውን? ሊቃነ መላእክት ያሉበትን? ኪሩቤል ያሉበትን? ሱራፌል ያሉበትን? “አይደለም” [ይላል ቅዱስ ጳውሎስ]፡፡ ታዲያ የት ነው? “ሀበ ኀሎ ክርስቶስ በየማነ እግዚአብሔር ይነብር - ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ [በአብ ዕሪና] ባለበት [በላይ ያለውን አስቡ]፡፡”

ስለዚህ ተወዳጅ ጳውሎስን እንታዘዘው፤ ይህንንም ዘወትር እናስብ፤ በወጥመድ ለተያዘች ወፍ ክንፏ ምንም ጥቅም እንደሌለው፣ ክንፎቿን ማማታቷም ለከንቱና ለማይጠቅም እንደ ኾነ እንዲሁ አንተም አንዴ በጽኑ በክፉ ዝሙት ከተያዝህ በኋላ አሳቦችህ ጥቅም የላቸውም፤ የምትችለውን ያህል ብትታገልም እንኳን ተይዘሃል!

ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው በወጥመድ እንዳይያዙ ነው፡፡ ሰዎችም የማሰብ ኃይልን የተሰጣቸው ኃጢአትን እንዲያስወግዱ ነው፡፡ እንግዲህ እንዲህ የማሰብ ኃይል ተሰጥቶን ሳለ ይባስ ብለን ከምድር አራዊት በታች የማናስተውል ከኾንን ሊደረግልን የሚችል ምሕረት ወይም ይቅርታ እንደ ምን ያለ ምሕረት እንደምንስ ያለ ይቅርታ ነው?

በወጥመድ ተይዛ የነበረች ወፍ ድንገት ከወጥመዱ ብታመልጥ፣ ወደ ወጥመድ ገብቶ የነበረው አጋዘንም ወጥመዱን በጣጥሶ ቢኼድ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በተመሳሳይ ወጥመድ እነዚህን መያዝ ከባድ ነው፤ የሕይወት ተሞክሮ ለኹለቱም ጥንቃቄን አስተምሯቸዋልና፡፡ እኛ ግን ምንም እንኳን በተመሳሳይ ወጥመድ ብንያዝም ተመልሰን ወደዚያው ወጥመድ እንወድቃለን፤ ምንም እንኳን በለባዊነት የከበርን ብንኾንም አእምሮ እንደሌላቸው እንስሳት እንኳን ቀድመን አናስብም፤ አንጠነቀቅምም! ሴትን በማየት እልፍ ጉዳቶችን ተቀብለን ወደ ቤታችን የተመለስነው፣ በዝሙት ተመኝተንም ስናበቃ ለአያሌ ቀናት ያዘንነው ስንቴ ነው? ነገር ግን ከዚያ በኋላም ቢኾን በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠንቃቆች አልኾንም፤ አንዱን ቁስል ሳናገግም ዳግመኛ ወደዚያ ክፉ ጠባይ እንወድቃለን፤ በተመሳሳይ መንገድ እንያዛለን፤ እጅግ ጥቂት ለኾነች የደስታ ሽርፍራፊ ብለንም ረጅምና ተደጋጋሚ ሥቃይን እንቀበላለን፡፡ ዘወትር “በወጥመዶች መካከል እንደምትኼድ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ” የሚለውን ኃይለ ቃል ደጋግመን ለራሳችን ብንናገረው ግን ከእነዚህ ጉዳቶች ኹሉ እንጠበቃለን (ሲራ.9:13)፡፡
👍31
መካነ ቅዱሳን ጺማ አቡነ ዘርዓቡሩክ ገዳም የት ነው ያለ ትለኛለች?? ለምን ፈልገው ይሆን ብየ ዞር ዞር ብየ ሳነብ አንድ ዲያቆን "ቦታውን የረገጠ ድንግልና ያስመልሳል" የሚል ጽሑፍ ጽፎ ያንን አንብባ ነው ለካ። ሳታስበው ድንግልና እንደሌላት በመንገሯ ለዲያቆናት ውለታ ውላለች። ሕዝቤ ድንግልናውን ለማስመለስ ሲሯሯጥ ታየኝኮ። ጎበዝ እረ እየተደማመጥን። ሥጋዊ ድንግልና ከሄደ ሄደ ነው። መመለሻ መላም የለው። ክህነትህም ከሚስትህ ውጭ ካለች ሴት ደርሰህ ከሆነ የፈረሰ አይመለስም።ከሄደ ሄደ ነው። ለዝያኮ ነው ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ቀርበህ ተማር። በልብ ወለድ ትምህርት (በጒስዓተ ልብ) አትሸወድ የምልህ።

የነፍሥ ድንግልና ግን ንሥሐ ተገብቶ ይመለሳል። ንሥሓሰ ትሬስዮ ለዘአበሰ ከመ ዘኢአበሰ ወለዘማዊ ድንግለ ይላልና። ለተክሊል አስፈላጊ ነው የተባሉ የነፍስም የሥጋም ድንግልና ናቸው ። ሌላው ቅዱሳት ገድላት ድርሳናትን  ስናነብ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምረው የወጡትን እናንብብ። አንዳንዱ ደግሞ ግንኙነት አድርጌያለሁ ግን አልደማሁም። ስለዚህ ድንግል ነኝ ይልሀል። ምን ዓይነት ጣጣ ነው። ድንግልናኮ የመድማት ያለመድማት ጉዳይ አይደለም።ግንኙነት የማድረግ ያለማድረግ ጉዳይ ነው። ግንኙነት ካደረገ ወንዱም ሤቱም ድንግልና የላቸውም።አለቀ። ድንግልና ቃሉ ተደንገለ ተጠበቀ ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ከግንኙነት (ሩካቤ) መጠበቅ ማለት ነው። ድንግልናን መጠበቅ ትልቅ ክብር ነው። ብዙዎች ስሜታቸውን ገትተው ድንግልናቸውን ጠብቀው ይቆያሉ። ይህ ነው ክርስትና። ክርስትና ለስሜት መገዛት ሳይሆን ስሜትን መግዛት ነው።

ለማንኛውም ጺማ አቡነ ዘርዓቡሩክ ያለው ጎጃም ውስጥ ሲሆን አፄ በካፋ ተወልደው ያደጉበት ቦታ ነው። ገዳሙም የታላቁ ቅዱስ አባት የአቡነ ዘርዓቡሩክ ነው። በቅዱሳት መካናቶቻችን የሚያፌዝ ሲመጣ ዝም አንልም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየ!!!
መምህር በትረማርያም አበባው
(የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር)
👍6
© ምክር ለወጣት ሴቶች ©

ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡ የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡

አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ

ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!

ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"

ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡

የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር #በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡

በመጀመሪያ መንግስታችሁን (#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)

ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡

#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት

ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ እበረታቷቸው።

ምንጭ፦ ተግባራዊ ክርስትና
👍81
ፍኖተ ሕይወት፡
መልካምነት


❖ አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፤ አንድ ቀን አባቱ "ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፤ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፤ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡

❖ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፤ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፤ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ።

❖ ፍርድ ቤት የተባለው የሰው ልጅ_ይችን ዓለም ተሰናብቶ የሚኖርባት የዘላለም ቤቱ ሲሆን

፩- የመጀመሪያው አልችልም ያለው ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ።

፪- ሁለተኛው ፍርድ ቤቱ አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፤ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም።

፫-  ሶሰተኛው እሰከ መጨረሻው አንተ ጋር ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፤ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡

❖ ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና።
1
ምክረ አበው

"ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጦም ነው፡፡የምንጦምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጦም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡"
[ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ]

"ጸሎት ለማድረግ ወደ እግዚአብሔር ስትቀርቡ ራሳችሁን እንደ ኣንድ ኣነስተኛ ጉንዳን እንደ አንድ በምድር ላይ እንደሚሳብ ኣነስተኛ ፍጥረት እንደ አንድ ደቃቃ አልቅትና እንደ አንድ ተብታባ ሕፃን ቁጠሩ።"
[ኣባ ይስሓቅ]

"የማያቋርጥ ጸሎት ማለት ሁለንተናችሁን ለእርሱ በመስጠት ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ማድረግ ማለት ነው፥፥ በዚህ ጊዜ ሕይወታችሁን ሁሉ የማያቋርጥ ጸሎት ይሆናል።"
[ቅዱስ ባስልዮስ]
👍32
[ ነገረ መንፈስቅዱስ ]

መንፈስ ቅዱስ በሁሉ ቦታ ያለ ነው፡፡ታድያ ለሐዋርያት ወረደ ማለት ምን ማለት ነው? ወረደ የሚለው በአካል በሁሉ ቦታ ላለ አይነገርምና፡፡ ወረደ ማለት ጸጋውን ሰጠ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ይህ ጸጋም ከአብ እና ከወልድ ተለይቶ የመንፈስ ቅዱስ ብቻ የሆነ የተለየ አካላዊ ግብር አይደለም፡፡ የሦስቱም ባሕርያዊ ግብር (ሥልጣናዊ) ግብር ነው እንጂ፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ ጸጋ ዘአብ ያለውን ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በቅዳሴ ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ብለውታል፡፡ ባሕርያዊ ግብር ስለሆነ ሦስቱም ይጠሩበታልና፡፡

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወረደ ማለት ጸጋ ለሰው ተሰጠ ማለት ነው፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን መንፈስ ቅዱስ ይለዋልና፡፡ ይህን ጸጋ ደግሞ ቤተክርስቲያን ተቀብላ እስከ ዕለተ ምጽአት ለሚነሱ ሰዎች ስታድል ትኖራለች በዚህም ምክንያት የጸጋው ግምጃ ቤት ትባላለች፡፡ በነገራችን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ከምጽአት በኋላም እየተሰጠ ለዘለዓለም ይኖራል እንጂ አያልቅም፡፡ ይህንንም የመጻሕፍተ መነኮሳት መተርጉማን ተወስኮ ዘነሳእያን ይሉታል፡፡ መንግሥተ ሰማያትን ገንዘብ ላደረጉ ሰዎች እየተጨመረ የሚኖር ጸጋ ማለት ነው፡፡

ቤተክርስቲያን በዕለተ ጰራቅሊጦስ ተወለደች መባሉ ሙሉ ጸጋን አግኝታ ጸጋን የምትሰጥ ሆነች ለማለት ነው፡፡ ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ካገኙ በኋላ ፈሪ የነበሩት የማይፈሩ ሆኑ፡፡ እስከሞት ድረስ እውነትን እየመሰከሩ የሐሰትን ሐሰትነቱን እየገለጡ ኖሩ፡፡ ሃይማኖት የራስን እውነት መናገር ብቻ አይደለም፡፡ የሌላውንም ስህተት ሳይፈሩ ስሕተትነቱን መናገር ነው፡፡ ቅዱሳን ሊቃውንት እነ ዮሐንስ አፈወርቅ የሚታወቁትም በዚህ ነው፡፡ እዉነትን በአደባባይ ይሰብካሉ፡፡ ውሸትን ደግሞ በአደባባይ ያጋልጣሉ፡፡

ሃይማኖተኝነት ይህ ነው፡፡ የአንተን እውነት ብቻ እየተናገርክ በሁሉ ዘንድ መወደድ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ውሸት በመናገር በብዙዎች ዘንድ መጠላትም አለበት፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅ ግዞት የተፈረደበት የንግሥቲቱን ክፉ ስራ በማጋለጡ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ሲወርድ ጥቡዓን ሆኑ ማለት ይህ፡፡ ማንንም ሳይፈሩና ሳያፍሩ የውሸትን ውሸትነት የእውነትን እውነትነት በአደባባይ ገለጡ ማለት ነው፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው ብዙው ሰው ይጠላቸው ይሰድባቸው ነበር፡፡ ያ ብቻ አይደለም ይገድሏቸውም ነበር፡፡

ጰራቅሊጦስ፡
ጰራቅሊጦስ ማለት ናዛዚ የሚያረጋጋ ማለት ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መጽንዒ የሚያጸና ማለት ነው። ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ ማለት ነው።
ጰራቅሊጦስ ማለት ከሣቲ ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።

እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘተሰውጠ ላእለ ሐዋርያት። በመንፈስ ቅዱስ በነገረ ኩሉ በሐውርት።

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ!
በሐዋርያት ላይ ያደረ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ይደርብን!!!
👍32
[ እኔ ግን እኔ አይደለሁም ]

አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው። በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ። ይህንን የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኁዋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው።
ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ።
ይህች ሴትም እየሳቀች :-
አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች

እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላት።

ክርስትና የወደቀ የሚነሣበት የረከሰው የሚነጻበት ሕይወት ነው። በዚህ መስመር ያለፉ ሁሉ ትናንትን እየተዉ ሌላ ማንነትን ይለብሳሉ። ትልቁ ፈተና ሰዎች ተነሥተህ እያዩህም እንኩዋን መውደቅህን አለመርሳታቸው ነው። ፈጣሪ "ከእንግዲህ አትበድል" ብሎ ይቅር ቢልህም ሰዎች ግን ይቅር አይሉህም። "ድመት መንኩሳ ዓመልዋን አትረሳ" እያሉ እየተረቱ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ ይገፉሃል እንጂ እንድትለወጥ አይፈቅዱልህም።

ሳውል አሳዳጅ ነበረ ዛሬ ግን ሐዋርያ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ግን እርሱን ለማመን ተቸግረው ነበር። ከመመረጡ ጀምሮ "ኸረ እርሱ አይሆንም" ብለው ለፈጣሪ ምክር የሠጡም ነበሩ። ከተመረጠ በኁዋላም ለመቀበል ተቸግረው ከሐዋርያት አሳንሰው ያዩት አልጠፉም። እርሱም በትሕትና  "ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ቢልም፡ "ጭንጋፍ" ብሎ ራሱን ያለ ጊዜው ከሚወለድ ጽንስ ጋር አነጻጽሮ ዘግይቶ የተጠራ መሆኑን ቢናገርም ከሐዋርያት በምንም የማያንስ ሐዋርያ ነበረ። እነርሱ በትናንት ማንነቱ ሊያዩት ቢሹም እርሱ ግን "እርሱ አልነበረም"  እርሱ መኖር አቁሞ በእርሱ ይኖር የነበረው ክርስቶስ ነበረ።

አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም። በጣም መልካም ስትሆንላቸውም አያምኑህም። ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ። መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ ይችላሉ። መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። ፍቅር የትግል ስልት የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ።

ዮሴፍ የገጠመው ይህ ነበር። በሃያ ብር ሸጠው ግብፅ ያወረዱት ወንድሞቹን ይቅር ብሎ በፍቅር ተቀበላቸው። አባታቸውን ያዕቆብን አስመጥቶ በክብር በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው። ከዓመታት በኁዋላ አረጋዊው ያዕቆብ ሞተ።
ይሄን ጊዜ የዮሴፍ ወንድሞች ድንገት ስብሰባ አደረጉ፡ "አባታችን ከሞተ በኁዋላ ቢበቀለንስ?!" ብለው ስጋታቸውን ተመካከሩ።
ስለዚህ ዶልተው መጡና እንዲህ አሉት :-
አባታችን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናዝዞ ነበር። እባክህን የወንድሞችህን በደል ይቅር በል። (ዘፍ 50:15-21) ዮሴፍ ይኼን ሲሰማ አለቀሰ። ይቅርታን አድርጎም አለመታመኑ አመመው።

እርሱ ለእነርሱ ድሮም ክፉ አልነበረም። አሁን ደግሞ ላደረሱበት በደል እንኩዋን ፈጣሪውን የሚያመሰግን ሆኖአል። "እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው" ነበር ያለው። ምንም በደል ቢደርስበት እነርሱ አልተለወጡ ይሆናል እንጂ እርሱ ግን ትናንት የሚያውቁት ዮሴፍ አይደለም። "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላቸው።

[ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ]
👍32
"እግዚአብሔር ሊምረው የወደደውን ሰው የቅድስት ድንግል ማርያምን ፍቅር ያሳድርበታል!!"

[አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ]
6👍3👏1
​​ፆመ ሐዋርያት

አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ

1.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል
ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23

2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን
ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን።

3. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14

4. በረከተ ምርትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14

5. የነፋስ በረከትን እናገኛለን
ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን !

ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜንንንን !!!
👍3
"ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ  በሕፃንነቱ ዮሴፍ በጣም ይወደው ስለነበር እንደ መጠኑ ወንበር ሠርቶ ከፊቱ ያስቀምጠው ነበር። መዓዛውን አሽትተው ደስ እያላቸው የዮሴፍ ልጆች እኔ ልያዝ እኔ ልያዝ ይነጣጠቁት ነበር። ኢየሱስን አይቶ የልቡን ኀዘን ያልዘነጋ የለም። እርሱን ማየት ኀዘንን ያርቃል። እርሱን ማየት ችግርን ያባርራል። ቃሉን መስማት የልብ ኀዘንን ነቅሎ ይጥላል። አንድ ጊዜ ፊቱን አይተው ሁልጊዜ እርሱን ለማየት ያልሳሳ ያልናፈቀ የለም። ሕፃናትም እርሱን አይተው በፍቅሩ ይቃጠሉ ነበር። ጎልማሶች ባዩት ጊዜ ደስታ ያድርባቸው ነበር።  እርሱን ማየት ስንቅ ደስታ ይሆናቸው ነበር። እርሱን አይቶ ቃሉን ሰምቶ የሰለቸ የለም። ዘመድ የሞተባቸው ሰዎች ጌታን ሲያዩ ኀዘናቸው ይጠፋላቸው ነበር። እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብፅ ይዛው በተሰደደች ጊዜ የግብፅ ልጆች ንዑ ንርአዮ ለወልደ መንክራት እያሉ እየሄዱ ያዩት ነበር"።
      ምንጭ:-አረጋዊ መንፈሳዊ ትርጓሜ ድርሳን 24
                            
በተለያየ ኀዘን እና መከራ ያላችሁ የተከበራችሁ ክርስቲያኖች ከኀዘን ከመከራ ትወጡ ዘንድ ኑ ክርስቶስን በዓይነ ኅሊና ተመልከቱ፣ ቃሉን ስሙ። ቂም በቀል የያዛችሁብኝ ሰዎች የእኔን ደካማነት ተረድታችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ። የይቅርታ አባት የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች ናችሁና። ይቅር ተባብለን አንድነታችንን እናጽና። ያለፈውን ጥፋታችንን እግዚአብሔር ይቅር ይበለን። ወደፊትም እንዳናጠፋ ይጠብቀን። ክፋትን ምቀኝነትን ጥላቻን ከልቡናችን እናስወግድና በምትኩ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ጽድቅን ገንዘብ እናድርግ።
                           
ክርስቶስን በዓይነ ሕሊናቸው እያዩ፣ በዕዝነ ኅሊናቸው እየሰሙ ሁልጊዜም ያለኀዘን የሚኖሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው። እኛም እኛን ለማዳን በመስቀል ተሰቅሎ ያዳነንን የፍቅር አባት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ኑ እናመስግነው።
                          
©በትረማርያም አበባው
                         
ንሕነ ዘክርስቶስ
https://www.youtube.com/@edenawizechristos
                          
Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721
👍3
"ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው"

ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጦም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጦም ጦምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴ.6፡21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ  ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡

ጦምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወቅት እንለምነው፡፡ ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም  ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

[ቅዱስ ኤፍሬም]
👍5🥰2🙏1
“እንደማይሰጥ ይዘገያል”
(ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት)

ጸሎት የምንጸልይባቸው የየራሳችን ምክንያቶች አሉን፤

ጥሩ የትምህርት ውጤት፣   ጤና፣   የተሳካ ሥራ፣    መልካም ትዳር፣   ከሕይወት ፈተና መራቅ፣   መልካም ቤተሰብ፣    ልጅ፣   ለንስሓ እና ቅዱስ ቍርባን መብቃት ወዘተ…

የሰው ልጅ በዘመናት ለአምላኩ ከጸለያቸው ጸሎቶች መካከል ይገኙበታል።

አዳም ከጸጋ ከተራቆተ በኋላ ከገጠመው የሕሊና ሕመም (የቀደመውን ደስታ እና ሰላም ማጣት) የተነሣ፣   መንግሥተ ሰማያትን ይለምን ነበር።

ሰው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር አገብሮት መጸለዩ እንዳለ ሆኖ፣  ትልቁ የጸሎት መነሻ ግን ማጣት ነው።

የቀደመ ሰላም፣   ፍቅር፣   ትዳር፣   ልጅ፣   ጤና፣   የተስተካከለ ሕይወት በማጣት እግዚአብሔር ደጅ ለጸሎት የቆምነው እልፍ ነን።

አዳም መንግሥተ ሰማያትን፣ የቀደመ ክብሩን፣ የቀደመ ሰላሙን፣ የቀደመ ጤንነቱን አጥቶ ፤ ለንስሓ እና ለጸሎት እንደቆመ ማለት ነው፤ ጸሎቱ ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ተሰማለት።

ለመልሱ ተግባራዊነት ደግሞ 5500 ዘመንን ቆየ። እንደቆይታው ግን የማይፈጸም ይመስል ነበር።

እግዚአብሔር መልሱን ለመስጠት 5500  ዘመን መቆየቱ የራሱ ምክንያት አለው!
ልክ የእኛን ጸሎት መልስ ለመስጠት እንደሚዘገየው ማለት ነው።

ብዙዎቻችን ከመዘግየቱ የተነሣ ተስፋ ከማጣት ጀምሮ እግዚአብሔርን እስከ መካድ እንደርሳለን[ተስፋ እንቆርጣለን]።

ለአዳም 5500 ዘመን እንደቆየበት ምክንያት፣  ለኛም ጥያቄ መዘግየት ምክንያቶች ምንድናቸው የሚለውን ለማሰብ ለአዕምሯችን ዕድል አንሰጠውም።

ይልቁን  የመልሱን መዘግየት እንደ መቅረት አድርገን እንገነዘባለን።

ለረጅም ጊዜ ደጁ ተመላልሰን የጸለይነው ጸሎት መልስ አልባ መስሎ ይሰማናልና።

እግዚአብሔር እኛ በፈልገነው ወቅት መልሱን ስላልሰጠን ተስፋ እንቆርጣለን፤ እግዚአብሔር ጨርሶ የተወን ያክል ይሰማናል።

የሠለስቱ ምእት ቅዳሴ ይኽን ነገር ሲገልጥ  "እንደማይሰጥ ይዘገያል" ይለዋል እግዚአብሔርን፤

እውነት ነው እግዚአብሔር መስጠቱ ለማይቀር ይዘገያል፤ የሚዘገይበትም የራሱ ምክንያቶች አሉት።

እኛም ለመረዳት መሞከር ያለብን፣ እነዚያን ምክንያቶች እንጂ መዘግየቱን እንደመቅረት መረዳት የለብንም።
👍121
2025/07/14 09:59:48
Back to Top
HTML Embed Code: