ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን? አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን? የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ የማይሰማው ይመስላችኋል? እንዴት አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
😢4❤1👍1
ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ!
ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 4፡4 ላይ ‘‘ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ’’ ካለ በኋላ መልሶ ‘ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ አንዴ ደስ ይበላችሁ ካለ ቢበቃም በዛው ዓረፍተ ነገር ድጋሚ ‘ደስ ይበላችሁ’ ማለት ለምን አስፈለገው? ለነገሩ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ላይ ደስ ይበላችሁ ያለው እዚህ ዓረፍተ ነገር ላይ ብቻ አልነበረም፡፡ በጣም አጭር በሆነው ባለ አራት ምዕራፉ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ 16 ጊዜ ደስ ይበላችሁ ፣ ደስ ብሎኛል ፣ ደስ ይበለን ፣ ደስታዬ ተፈጸመ ፣ ደስ አለኝ ፣ ደስታ ፣ ደስ ፣ ደስ ብሏል፡፡ በዚም ምክንያት የፊልጵስዩስ መልእክት የደስታ መልእክት ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህን የምታነቡ ሁሉ እኔም ከሐዋርያው ጋር ልላችሁ እወዳለሁ ፤ ደስ ይበላችሁ!
ምናልባት በዚህ ሰዓት በከባድ የመንፈስ ጭንቀትና ችግር ውስጥ ወይም በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያለ ሰው ይህንን የቅዱስ ጳውሎስ ‘ደስ ይበላችሁ’ ጥሪ ሲያነብ ‘አንተ ደልቶሃል ወዳጄ እኔ እንኳን ደስ ሊለኝ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶብኛል’ ማለቱ አይቀርም፡፡ የሚገርመው ግን ጳውሎስ ይንን ዐሥራ ስድስቴ ደስ ይበላችሁ የሚል ደብዳቤ የጻፈው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ እግሩ በሚቀዘቅዝ ጉድጓድ ውስጥ በሚከረክር ብረት ታስሮ ፣ እጆቹ ከመሬት ጋር በሰንሰለት ተጣብቀው እያለ ፣ ከታሠረ ሦስት ዓመት ሊሞላው ሲል በፈገግታ ተሞልቶ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፡፡
እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ደብዳቤ እንዲጽፍ ዕድል ቢሠጠው ምን ብሎ የሚጽፍ ይመስልሃል? ‘የእስር ቤቱ አበሳ’ ‘የወኅኒው ምሥጢሮች’ ‘ገራፊዎቼና ጭካኔያቸው’ ‘የግርፋቴ ጠባሳዎች’ የሚል ዓይነት የደረሰበትን ሥቃይ የሚገልጹ መጻሕፍት አይጽፍ ይሆን? ያም ባይሆን ለቤተሰቦቹ ሲጽፍ ‘ኸረ ቁንጫውን አልቻልሁትም! ምግቡ አልተስማማኝም ፣ እገሌ ምነው አልጠየቀችኝም ደህና አይደለችም? ፣ እነ እንቶኔ ግን የማይጠይቁኝ ለምን ይሆን? እኔ ለእነርሱ እንዲህ ነበርሁ? ነግ በኔ አይሉም ወይ? ‘ያስተዛዝበናል ይኼም ቀን ያልፍና’ የሚል ይዘት ያለው ሊሆን ይችላል፡፡
ይህም ባይሆን እንኳን ከእስር ቤት ውስጥ ሆኖ 16 ጊዜ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለቤተሰቡ የሚልክ ሰው አይኖርም፡፡ እንደዚያ ብሎ ቢጽፍ እንኳን ቤተሰቦቹ ‘አእምሮው እየተነካ ነው! እነዚህ ሰዎችማ የሆነ ነገር ሳይወጉት አይቀሩም! ራሱን ሊያጠፋ ይሆን?’ ብለው ይጨነቃሉ እንጂ የእስር ቤቱን እንኳን ደስ አላችሁ ከቁም ነገር ቆጥረው ‘እንኳን አብሮ ደስ አለን’ አይሉም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን ደብዳቤ ግን ቤተ ክርስቲያን ከማንበብ አልፋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አካተተችው፡፡ ጳውሎስ ደስ ያለው በእስር ቤቱ ፣ በሥቃዩ አልነበረም፡፡ ደስ ይበላችሁ ያለው በጌታ ነው! ከሚደርስበት መከራ በላይ የደረሰለት ፈጣሪ በልጦበት ውስጡ በደስታ ተሞልቶ ስለፈሰሰ ከታሰሩት አልፎ ውጪ ላሉት ደስታ እስከመመኘት ደረሰ፡፡ ጭንቅ ጥብብ ብሎህ ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ጳውሎስም እንዳንተ ጭንቅ ላይ ሆኖ ‘በጌታ ደስ ይበልህ’ እያለ ነው፡፡
እግዚአብሔርን ስታስብ መከራህ ሁሉ ትንሽ ይሆናል፡፡ ጳውሎስን በቀዝቃዛው ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ደስታ ያሰጠመው ፈጣሪውን አስቦ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበር ውጪ ላሉት ክርስቲያኖች ‘በደስታ እጸልያለሁ’ አለ ፣ እሱ በሌለበት በተለያየ ምክንያት ወንጌል የሚሰብኩ ሰባኪያን በመብዛታቸው ‘ክርስቶስ ይሰበካልና ደስ ብሎኛል’ አለ፡፡ እስር ቤት መጥተው ላልጠየቁት ሰዎችም ‘አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር’ እያለ በደብዳቤው አጽናንቶአቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ደስታ ምንጩ ግን ከመከራው በላይ እግዚአብሔርን ማየቱ ነበር፡፡
እምነት እንዲህ ነው ፤ ጳውሎስ እግር ከወርች ከመታሰሩ በላይ ያየው ጌታውን ነበር፡፡ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር ሲተኛ ያየው የአንበሶቹን ጥርስ ሳይሆን ፈጣሪውን ነበር፡፡ እስጢፋኖስ ድንጋይ ሲወርድበት ገለባ የመሰለው ጠላቶቹ በቀኝ እጃቸው ከያዙት ትልቅ ድንጋይ ይልቅ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ያለውን እየተመለከተ ስለነበር ነው፡፡ ወዳጄ ምናልባት በሕይወትህ የተጫነህ ድንጋይ ፣ ሊውጥህ የቀረበ አንበሳ አይጠፋም ፤ ጳውሎስና እርሱን መሳይ ቅዱሳን ግን ጥሪ ያቀርቡልሃል ፡፡ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበልህ!
ክርስትና የመጨነቅ የመጨፍገግ ሳይሆን የደስታ ሃይማኖት ነው፡፡ የተፈጠርነው ለደስታ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ማንም የማይነጥቀው ደስታ የሚሠጥ አምላክ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ‘በደስታ ተገዙ’ ተብለናል፡፡ /መዝ.100፡2/ ወንጌል የምሥራች ነው፡፡ ወንጌል የሚጀምረው ድንግሊቱን ደስ ይበልሽ ፣ እረኞችንም ደስ ይበላችሁ በማለት ነበር፡፡ ጥምቀቱንም ‘’በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ’ የሚል ምስክርነት አለበት፡፡ክርስቶስ መከራን ሲቀበልም ‘ነውርን ንቆ በፊቱ ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ’ ነበር፡፡ /ዕብ 12፡2/ በክርስቶስ የማመን የመጨረሻው ግብም ‘ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ የሚለውን የሕይወት ቃል መስማት ነው፡፡ /ማቴ 25፡21/
ጳውሎስ ‘’በጌታ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ ቅዱስ እንጦንስ የጳውሎስን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል ፦ በጌታ ደስ ይበላችሁ በዓለም አይደለም፡፡ በእውነት ደስ ይበላችሁ በዓመፅ አይደለም፡፡ በዘላለም ተስፋ ደስ ይበላችሁ በሚረግፉ አበቦች አይደለም፡፡ ደስታ ማለት ይህ ነው ፤ የቱንም ያህል በምድር ላይ ብትቆዩ እግዚአብሔር ቅርብ ነውና አትጨነቁ!’’
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ዓይነት ደስታ አለበት ፤ ወዳጄ አንተ አንዱን መርጠህ ደስ ይበልህ፡፡
ዳዊትን ተመልከተው ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ይልሃል፡፡ ልብ አድርግ ‘’ጎልያድን ግንባሩን ብዬ ስጥለው ደስ አለኝ’ አላለም፡፡ ንጉሥ ሆኜ የተቀባሁ ቀን ደስ አለኝ አላለም፡፡ እሱ ደስ ያለው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ያሉት ቀን ነበር፡፡ ‘እኔ እኮ ንጉሥ ነኝ ሥራ ይበዛብኛል ባይሆን እናንተ ሒዱ እኔ በገንዘብ ልርዳችሁ’ አላለም ፤ መሔጃ ያላጣው ባለጸጋ ንጉሥ ወደ ድንኳንዋ የእግዚአብሔር ቤት እንሒድ ሲሉት ደስ አለው፡፡ እዚያ ሔዶ ዙፋኑን አስዘርግቶ መንግሥትን በመወከል ‘መንግሥት ለእምነት ተቋማት ትኩረት ይሠጣል’ የሚል እግዚአብሔር ላይ የሚመጻደቅ ቅብርር ያለ ንግግር ሊያደርግ ፈልጎ አልነበረም፡፡ እርሱ የፈለገው እግዚአብሔር ሥር ለመውደቅ ነበር፡፡ ‘ከአእላፋት ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች ፤ በኃጢአተኞች በድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ’ አለ፡፡ /መዝ. 84፡10/
የዕንባቆምን ደስታ ተመልከተው ‘ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ’ ይልሃል፡፡ ኑሮው ምስቅልቅል ቢልም፣ ችግር ቢያስጨንቀውም በእግዚአብሔር ደስ ብሎት ነበር፡፡ /ዕን 3፡17፡18/
(ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

❤4👍1
➕( ቤተክርስቲያን ናት )
የምስጢር መፍለቂያ ስንዱ እመቤት
የእምነት አጽኖት የጸጋው ግምጃቤት
የፍቅር የሠላም የአስኳለ ክርስቶስ ተምሳሌት
ሊቃውንት የምታፈራ መዝገበ ምስክር
ጥበብ የምታስተምር ሃይማኖተ ባህር
የጠበል መገኛ የድኅነት መንገድ በር
እኩይ ሀሳብና እኩይ ተግባርን የምታወግዝልን
የሐዲስ ኪዳን ቤተሳይዳ ናት ቤተክርስቲያናችን
የግሩም ወይን ፀአዳ ጣፋጭ ናት ለሕይወት
ቢሸሿት የማትሸሽ የሁሉ አምባ መጠጊያ ናት
የድሆች መጠጊያ የመንፈስ ስብራት ወጌሻ
የእውቀት ማጣት የስንፍናን መደምሰሻ
በሥጋዊ ጾር ለተወጋች ነፍስ መፈወሻ
የጎደፈው ህሊና የሚኖር በአርነት
ማዲያት የወረረው የእኛን ማንነት
አየሁኝ አሻግራ አርቃ ክፋትን በስብከት
በባርነት የተገዛው ህልውና ሰጥታ ነፃነት
ቅዳሴው ወንጌሉን ለልጆቿ መግባ
በንስሐ በቁርባን የምታኖር ሕይወትን አጅባ
ይህ ሁሉ የምታደርግ ቤተክርስቲያን ናት
የሀገር መሠረት የሆነች መቀነት
አትኳት ኢየሱስ ነው በደሙ የመሰረታት
አባቶች አበው ሞተው ያቆዩልን
ሰማዕትነት ተቀብለው ለዚህ ያደረሱልን
ቤተክርስቲያን ናት የእኛ መንጦላይት
በአንድነት ሆነን ተግተን እንጠብቃት
የጌታችን ትእዛዝ እፈጽም በትጋት
ሁሉም ያልፋልና በእግዚአብሔር ቸርነት
ከእደጁ አንራቅ እንፁም እንፀልይ
ትጉና ፀልዩ ብሎናል ኤልሻዳይ
ሀጢያታችን በዛ የሞት ሞት ሞተናልና
ቤተክርስቲያናችን ተደፍራለችና
ማረን ማረን እንበል ይምረናልና
አትንኳት አትንኳት ናትና ነፍሳችን
የእኛ ማረፊያችን ወደብ መርከባችን
ቤተክርስቲያን ናት የእኛ ደሴታችን።
======////=====
ሰላም ለኪ ቤተክርስቲያን ቅድስት አምሣለ ኢየሩሳሌም ሠማያዊት ዘቀደሰኪ ክርስቶስ በደሙ ንጽሕት !

በጥቂቱ መታመን
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ!.." ማቴ 25፥21፡፡ ይህም ማለት በምድራዊ ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ማለት ነው፡፡ በዚኛው ዓለም ታማኝ ሆነ ከቆየህ በዘለዓለማዊነት ውስጥ እሾምሃለው ማለት ነው፡፡ ይህ መመሪያ በብዙ መስኮች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል... ዘመዶችህን በመውደድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ጠላቶችህንም በመውደድ ላይ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን የምትወድበት ጸጋ ያድልሃል ማለት ነው፡፡
በትርፍ ጊዜዎችህ እግዚአብሔርን የምታገለግል ከሆንህ በሕይወትህ ጊዜ ሙሉ በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ፍቅር ያድልሃል፡፡ የፈቃድ ኃጢአቶችን ከአንተ በማስወገድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ያለ ፈቃድ ከሚመጡ ኃጢአቶች ነጻ ያወጣሃል፡፡
ንቁ ኅሊናህን ከክፉ አሳቦች የምትጠብቅ ከሆንህ እግዚአብሔር ንቁ ያልሆነው ኅሊናህን ንጽሕና ያድልሃል፤ ከዚህ በተጨማሪ የህልሞችህን ንጽሕናም ያድልሃል፡፡ ልጅ እያለህ ታማኝ ከሆንህ እግዚአብሔር ውጊያዎች በሚበዙበት በወጣትነትህ ዘመን ውስጥም ታማኝነትን ያድልሃል ሌሎች ሰዎች ላይ በቃላት ብቻ የማትፈርድባቸው ሆነህ በመገኘትህ ታማኝ ከሆንህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነው በአሳብ እንዳትፈርድባቸው ያስችልሃል፡፡ ልክ እንደዚሁ ራስህን ከውጫዊ ንዴት በመጠበቅ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አውስጣዊ ቁጣ፣ንዴትና ቅናት ነጻ ያወጣሃል፡፡
በተለመዱ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፍሬዎች) ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታዎችን ያድልሃል፤ በመጀመሪያው ላይ ታማኝ ሆነህ ካልተገኘህ ሁለተኛውን ፈጽመህ ልታገኘው አትችልምና፡፡
እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚፈትሽህ በጥቂት ነገር ነው፡፡ በዚህች በጥቂቷ ነገር ላይ ታማኝ መሆንህ ካረጋገጥህ እርሱ በሚበልጠው ነገር ላይ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና አለመታመንህን በጥቂቷ ነገር ላይ ከገለጽህ ግን እግዚአብሔር በሚበልጠው ነገር ላይ አይሾምህም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ "ከእረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱህ ቢደክሙህ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ?" ኤር 12፥5 ብዙ ሰዎች ዝቅተኛውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችሉ ከፍተኛውን ኃላፊነት ለመቀበል ማሰባቸው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ሳይጠቀሙ ተጨማሪ ጸጋ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም "በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመዘንጋት ነው፡፡
("መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው" ከሚለው #አያሌው_ዘኢየሱስ ከተረጎመው #የብጹዕ_አቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደ!!!)

🤔1
ጥያቄ፦ ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልግ ዝግጅት ምንድን ነዉ???
[መልስ]፦
ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ (ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ)፣ ጊዜ ሱባዔ (በሱባዔ ጊዜ) እና ድኅረ ሱባዔ (ከሱባዔ በኋላ) ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
1ኛ ቅድመ ሱባዔ
(ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ)
በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት አለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይኾን ሱባዔ ቢገባ ከሱባዔው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ድካሙ ዋጋ ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባዔ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሐ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነውና፡፡ ከዚህም ባሻገር በአባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርጉልናል፡፡ ስለኾነም ቅድመ ሱባዔ ከንስሐ አባት ጋር መመካከር ተገቢ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው በሱባዔ ወቅት ልዩ ልዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንደዚሁም የንስሐ አባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር ከአንድ ምእመን ይጠበቃል፡፡ ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ ዓቅማችንና እንደ ችሎታችን መጠን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ነው፡፡
ለምሳሌ ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው አንድ ሰው በዋሻ እዘጋለሁ ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻሉ ሱባዔውን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዓቅምንና ችሎታን አገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡
ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የኾነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በአብዛኛው ሱባዔ የሚገባው አጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መኾን አለመኾኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በአጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሐራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በአጽዋማት ወቅት ብዙ አባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከአባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ከዚህ ላይ ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ አይያዝም ለማለት አይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ከአጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ ይችላል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የሚያጋልጡ መኾናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ሕሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ሕሊና ለመጸለይ አያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና አድባራት ቢኾኑ ተመራጭ ነው፡፡
2ኛ ጊዜ ሱባዔ
(በሱባዔ ጊዜ)
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ፣ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንደዚሁም ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ፣ ወደ ግራ፣ ወደ ቀኝ አለመዟዟር፤ በሰፊሐ እድ፣ በሰቂለ ሕሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል (መዝ. ፭፥፫)፤ መዝ. ፻፴፫፥፪፤ ዮሐ. ፲፩፥፵፩)፡፡ በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
3ኛ ድኅረ ሱባዔ
(ከሱባዔ በኋላ)
ለቀረበ ተማኅጽኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት፣ እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የሕሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህም ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መጽናትና መማጸን ይኖርብናል፡፡
[ፍኖተ ሕይወት]
[@nshachannel]

❤5🥰2🙏2👍1
ኑ ወደ ወይነ ቃና ሕይወት
ተወዳጆች ሆይ! ሕይወታችን ጣዕም አጥቶ፣ እንኳን ከክርስትና ከሰውነትም ወርዶ፣ በሌላ ነገር ተተብትቦብን ሊኾን ይችላል፡፡ ኑ! ኑ ከነትብታባችን፤ ኑ ከነጣዕም አልባነታችን! ኑ ወደ ክርስቶስ እንቅረብና ሕይወታችን ወይነ ቃና ይኹን፡፡
ርኅርኅተ ኅሊና፣ አቁራሪተ መዓት እመቤታችን ዛሬም ታሳስባለች፡፡ ልጇ ወዳጇን “ወይን እኮ የላቸውም፤ ጣዕም እኮ የላቸውም፤ የሕይወት መዓዛ እኮ የላቸውም፤ልጄ ወዳጄ እባክህን ወይነ ቃና አድርጋቸው” እያለች፡፡
እንኪያስ ኑ ከነባዶ ማንነታችን፡፡ ኑ ከነውሃው ማንነታችን፡፡ ኑ ከነ ጣዕም አልባው ማንነታችን፡፡ ኑ ወደ ፍቅር ክርስቶስ እንቅረብ፡፡ ኑ በጸሎት ወደርሱ እንቅረብ፡፡ ኑ በንስሐ ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡
ተወዳጆች ሆይ! ስለምን ከነ ሸክማችን እንቆያለን? ስለምን በኃጢአት እንደጐበጥን መሰንበትን እንመርጣለን? ስለምን በፆረ ገሃነም እንደተተበተብን እንኖራለን? ኑ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፡፡ ኑ ሸክማችንን እናራግፍ፡፡ ኑ ዕረፍተ ነፍስን እናግኝ፡፡ ኑ ወይነ ቃና እንኹን፤ ኑ ክርስቲያን (የክርስቶስ፣ ክርስቶሳውያን) እንኹን፡፡
ተወዳጆች ሆይ! የምንናገረው ስለ ቃላት ማማር አይደለም፡፡ ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንጂ፡፡ እስከመቼ በስደት? እስከ መቼ ከክርስቶስ ርቆ? እስከ መቼ በሞት ሕይወት? እስከ መቼ በዘፈን? እስከ መቼ በጫት? እስከ መቼ በዝሙት? እስከ መቼ በኃጢአት መንደር? እስከ መቼ? እኮ እስከ መቼ?
ኑ ወደ ወይነ ቃና ሕይወት!!! ቸርና ቅዱስ አባት ሆይ! በትብታብ የተያዘች ሰውነታችንን አበርታት፡፡ አንተን ወደ ማየት እንድትነቃቃ በመንፈስህ እርዳት፡፡ አማናዊው ወይን አንተን ጠጥታም ከክቡር ዳዊት ጋር “አጋንንት ሠሩልኝ፤ አንተ ግን ይንደዳቸው ይቆጫቸው ብለህ ሥጋኽን ሰጠኸኝ፡፡ ርእሰ ልቡናዬን በልጅነት ቀባኸኝ፡፡ ጽዋኽንም አትረፈረፍክልኝ” እያለች ታመሰግን ዘንድ በቸርነት እጅህ ደግፋት፡፡ አሜን!!!
መምህር ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

👍7
ከተቃራኒ ጾታ ጋር ረጅም ሰዓት በገለልተኛ ስፍራ አትቀመጥ አእምሮህ ንጹሕ ቢሆን እንኳን ለሌላው ፈተና እንዳትሆን፣ደግሞም ለሰዎች የሐሜት ምክንያት እንዳትሆን ፣ ግንኙነትህንበአደባባይ አድርገው ። የሚያዳልጡ ስፍራዎች ጎበዞችን ሳይቀር እንደሚጥሉም አትርሳ።
❤6
ሴት ሆይ ብዙ ወንዶች ይሯሯጡብሻል ወይስ ማንም ዞር ብሎ አያያይሽም ?ነገር ግን አንድ እውነት አለ ።ርካሽ ነገርን ሁሉም ሊገዛው ይሯሯጣል ፣ብዙ ደንበኞችም አሉት።አንቺም ብዙ ወንዶች ስለተሻሙብሽ እና ስላዋሩሽ ደስ አይበልሽ። ነገር ግን አንቺ እግዚአብሔርን ፍሪ አክብሪውም እንደዚህም በይው" አምላኬ ሆይ ለኔ የሚሆነኝም አዳም አንተ ራስህ ስጠኝ "ብለሽ ጠይቂው እርሱም ከጠየቅሽው በላይ ይሰጥሻል። ስለነገሮች አትጨነቂ ልቦናሽን በወንድ ፍቅር ሳይሆን በክርስቶስ ፍቅር አቃጥይው።ለሁሉ ወንድም አትሳቂ ዲያቢሎስ ሔዋንን ያሳታት አሳስቆ ነውና። ውድ ሴትን ማንም እየመጣ አያሳስቃትም። አባታችን አባ ሕርያቆስ ድንግል ማርያምን እንዲህ ሲል ገልጿታል
"ኦ ድንግል አኮ ወራዙት ስፉጣን ዘናዛዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወፁኪ በከመ ተብህለ ካህናት ወሊቃነ ካህናት ወደሱኪ።" "ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎረምሶች ያነጋገሩሽ አይደለሽም ።መላእክት ጎበኙሽ እንጂ እንደተባለውም ካህናት እና ሊቃነ ካህናት አመሰገኑሽ።"

❤6👍2
እግዚአብሔርን በሰው ተጎዳሁ ብትለው ከእኔ ምን ጎደለ? ይልሀል። ከዐሥር ወዳጅ እርሱ ይበልጣልና። እንኳን የተጠላ ሞት የተፈረደበትም እስረኛ ይኖራል። ሕይወት በእግዚአብሔር እጅ ናትና ማንንም አትፍራ። እየወደዱህም ትሞታለህ እየተጠላህም ትኖራለህ።
👍3