Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1129 - Telegram Web
Telegram Web
ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው::
ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9)

እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ?

መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም::

የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
👍3
+ የሚካኤል ክንፉ +

ቅዱሳን መላዕክት፣ ጻድቃን ሰማዕታት ብዙ ጊዜ ሲዖልን በምልጃቸው በርብረው ሰይጣንን ጉድ ቢሰሩትም የቅዱስ ሚካኤል ግን ይለያል። በእርግጥ ሲዖልን በርብሮ ነፍሳትን በማውጣት እመቤታችንን የሚተካከላት የለም፤ ምክንያቱም በወለደችው በአንድ ልጇ ሲዖልን ባዶ አስቀርታበት ሰይጣንን ጉድ ሰርታው ነበር። ለዚህም ነው ከፍጥረት ሁሉ አስበልጦ ሰይጣን እመቤታችንን የሚጠላት። ከእመቤታችን ቀጥሎ ግን ነፍሳትን ከሲዖል በምልጃው በርብሮ በማውጣት ቅዱስ ሚካኤልን የሚተካከል ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ወፍጮ ቤት ገብቶ የወፍጮ ብናኝ ሳይነካው መውጣት እንደማይችል ሁሉ ቅዱስ ሚካኤልም ለየሆነ ጉዳይ ሲዖል ደረስ ብሎ ሲወጣ በክንፉ ነፍሳትን ሳይዝ መውጣት አይችልበትም።

ገና ሲነበብ አጋንንትን በሚያርደው በድርሳነ ሚካኤል ጥቅምት ንባብ ላይ እንዲህ ያለ ውብ ተዓምር ተጽፎልናል። "ከደቂቀ አዳም ወገን ሰውነቱ በኃጢአት የረከሰ አንድ ሰው ነበረ፤ ያ ሰውም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ከተንኮልና ከክፋት በስተቀር አንዳችም በጎ ሥራ ሰርቶ አያውቅም። ነገር ግን አንድ ዓላማ ብቻ ነበረው፤ ይኸውም በየወሩ ቅዱስ ሚካኤልን በዓል ማክበር፣ ዝክሩን እየዘከረ ለነዳያን ማብላት ማጠጣት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ያ ሰው ሞተና አጋንንት ይህች ነፍስ የኛ ናት በማለት ሲደነፉ ሚካኤል ግን የኔ ናት እያለ ይከራከር ነበር።

እንዲህም የኔ ናት፣ የኔ ናት በመባባል ከጌታ ዙፋን ፊት ስለቀረቡ ጌታ አራት አማራጭ ነገሮች አቀረበላቸው። ይህም፦ ሚካኤል ወስዶ ይደብቀው፣ እናንተ ግን ፈልጋችሁ ብታገኙት ውሰዱት፤ ወይም እናንተ ወስዳችሁ ሸሽጉትና ሚካኤል ፈልጎ ካገኘው ይውሰደው፤ ከእነዚህ አንዳቸውን ምረጡ አላቸው። እነርሱ ግን ሚካኤል ወስዶ ከመንበረ መለኮት ቢሸሽገው ምን ለማድረግ እንችላለን እያሉ በሃሳብ ጭንቅ ተዋጡ። ከብዙ የሃሳብ መለዋወጥ በኋላም እኛ እንሸሽገዋለን ብለው ያን ሰው ዕመቀ ዕመቃት አውርደው የገሃነመ እሳት አዝዋሪት ባለበት ጥልቅ ባሕር ውስጥ ደበቁትና እንግዲህ ሚካኤል ፈልጎ ያግኘው ተባባሉ።

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል እነዚያን አጋንንት ከዚህ ቦታ አካባቢ ዘወር በሉ አላቸውና ወደ ሲዖል ገብቶ መፈለግና መበርበር ጀመረ፤ ነገር ግን የሚፈልገውን አላገኘም ነበረ። ነገር ግን ፈልጎ ሲወጣ በአንድ ክንፉ ፯ ዕልፍ ነፍሳት አወጣ፤ በሁለተኛውም ክንፉ እንዲሁ አወጣ፣ በሦስተኛውም አወጣ፣ በመደጋገምም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነፍሳትን አወጣ፤ ሆኖም ሊያገኘው አልቻለም። በዚህ ሰው ምክንያት ያወጣቸው ነፍሳት ቁጥራቸው 7540 ደረሰ፤ ከነዚህም ውስጥ ያልተጠመቁ አረመኔዎች ይገኙባቸው ነበር። ያን ጊዜ የሰማይ መላዕክት ሁሉ ይህስ እጅግ በጣም አስደናቂ ነገር ነው አሉ።"

ከዚህ ውብ ታሪክ የምንማረው ነገር ቢኖር ቅዱስ ሚካኤልን ይሁን ማንኛውንም ቅዱስ መዘከር በፍርድ ቀን ጠበቃ ማቆም ማለት ነው፤ ስለ እኛ ነፍስ ከአጋንንት ጋር ይከራከሩልናልና። የሚገርመው ደግሞ በዚያ ኃጥእ ሰው ቅዱስ ሚካኤልን መዘከር ምክንያት ብዙ ሺህ ነፍሳት ምሕረትን አገኙ። እኛም የፈለገ ኃጢአተኛ ብንሆን ቅዱሳንን መዘከራችን ከእኛ አልፎ የብዙ ነፍሳት መዳኛቸው ሊሆን ይችላልና ቅዱሳንን ከመዘከር መባዘን አይገባንም።
በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!

እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው።

በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው።

በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችኋል።

እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል።

በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
👍1
እስኪ ንገረኝ! ምንስ ታስባለህ? በነፍሱ መከራ የሚቀበለው የትኛው ነው፡- የተሳደበ ሰው ወይስ የተሰደበ ሰው? የተሳደበ ሰው እንደ ኾነ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም አስቀድሜ እንደ ነገርኩህ አንድን ሰው ኃጠአተኛ የሚያሰኙት ከውስጥ ከሰውዬው የሚመነጩ ክፋቶች እንጂ ከአፍአ የሚመጡ አይደሉምና ከድርጊቱ ራሱ የታወቀ ነው - “ስሜት” መባሉም ለዚህ ነውና፡፡ ዳግመኛም በተሳዳቢው ላይ በሚፈጥሩት ነገር የታወቀ ነው፡፡ ተሳዳቢው ሲቈጣ ዓይነ ልቡናው ይታወራልና፤ አእምሮው ይታወካልና፤ [የጤና መታወክ ሳይቀር] ሌሎች ስፍር ቊጥር ጉዳትም ይደርስበታልና፡፡ ስለዚህ መከራ እየተቀበለ ያለው ተሰዳቢው ሳይኾን ተሳዳቢው መኾኑን መረዳት ይቻለናል፡፡

ምናልባት “እርሱ ልጄን ሞኝ ብሎ ተሳድቦአል” ልትለኝ ትችላለህ፡፡ እኔም እልሃለሁ፡- መሳደብ ራስን መጉዳት እንደ ኾነ ነግሬሃለሁ፤ ስለዚህ ሰውዬው ደካማ ኾኖ ስለ ተሳደበ አንተም እርሱን መስለህ ደካማ ኾነህ የስድብ አጸፌታ አትስጥ፡፡ እስኪ ልጠይቅህ! አንተም መልስልኝ! ይህ ሰው ልጅህን በመሳደቡ መልካም ነገር አደረገን? መቼስ “አዎ መልካም አድርጓል” አትለኝም፡፡ እንግዲያውስ አንተም እርሱ የፈጸመው መልካም ያልኾነን ግብር አታድርግ፡፡ ልጅህ በተሰደበ ጊዜ ወይም በእንደዚህ ዓይነት ሌሎች ኹኔታዎች ውስጥ በልብህ ሊፈጠር የሚችለውን ስሜት እረዳለሁ፡፡ ኾኖም እርሱን [ተሳዳቢውን] ባለመምሰል በራስህ ላይ መከራን ከማምጣት ተከልከል እልሃለሁ፡፡

ምናልባት “እንደዚህ በማድረጌ እንዳሸነፈኝ ቈጥሮ ቢንቀኝስ? ይህ ሳይበቃውና ከልጄም አልፎ እኔንም ጭምር ቢሰድበኝስ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ እኔም፡- “እንዲህ ያደረገውን ሰው በተሳሳተ መንገድ እየኼደ እንደ ኾነ በትሕትና ገሥጸው፣ ራሱን ከመጉዳት በቀር እርሱ አንተን በፍጹም ሊጎዳህ እንደማይችል ምከረው” ብዬ እመክርሃለሁ፡፡ በየውሃት፥ በልብ ውስጥ ያለውን የቊጣ ስሜት መፈረካከስ ይቻላልና፡፡ ስለዚህ በየውሃት ወደ ተሳዳቢው ኺድና ገሥጸው፡፡

ሰዎች እኛን ሲጎዱን ወደ እነርሱ የምንኼደው ግን እኛ እንደ ተጎዳን ለመናገር እንዳልኾነ በደንብ አስተውል፡፡ የምንኼደው ተጎጂዎቹ እነርሱ ራሳቸው ስለ ኾኑና ስለ እነርሱ መዳን ስንል ነው፡፡ ስለዚህ አንተም ወደ ተሳደበው ሰው ስትኼድ ልጅህ በመሰደቡ ምክንያት ወይም አንተ ራስህ እንደ ተሰደብክ በመቁጠር አይኹን፡፡ ተሳዳቢው ሰው አንተን ንቆህ አጥቅቶህ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ልጄ ተሰደበ ወይም እኔ ተናቅሁ ተጠቃሁ ብለህ አትኺድ፡፡ መኼድ ያለብህ ተሳዳቢው ሰው ራሱን እየጎዳ እንደ ኾነ አስበህና ስለ እርሱ መዳን ብለህ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ሰይፍ የሰላውን የቊጣ ሰይፍህን መልሰው፤ ወደ ሰገባውም ክተተው፡፡

(ነገረ መከራ - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ )
ኮቲባነት

ኮቲባ የትእማን ገረድ የነበረች ሴት ናት። ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ወደ ግብፅ ስትሰደድ ውሃ ለመጠጣት ከእነ ትእማን ቤት ጠየቀች። ትእማን ግን ነገረኛ ስለነበረች ድንግል ማርያምን አንቺን የመሰለች መልከኛ ጸባይሽ ክፉ ሆኖ ነው እንጂ ትሰደጂ ነበርን እያለች በነገር መጎንተል ጀመረች። በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ውሃ ካለሽ ልትሰጪን ይገባ ነበር። ከሌለሽ ደግሞ ካለበት ያድርሳችሁ ብለሽ መመረቅ እንጂ ሌላ ክፉ ነገር ለምን ትናገሪያለሽ አላት። ይህን ጊዜ ኮቲባ ገረድ የሆነችላትን ትእማንን ያስደሰትኩ መስሏት ሕጻኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ከድንጋይ ላይ ጣለችው። ጌታም ትእማንን ከነ ቤተሰቦቿ ዝንጀሮ አደረጋቸው።

ኮቲባነት ሌሎችን ለማስደሰት ሲባል ከእውነት ጋር መጣላት ነው። የኮቲባነት ዋና መርሕ ሌላውን ለማስደሰት የእግዚአብሔርን ቃል መጣል (አለመፈጸም) ነው። እባካችሁ እንደኮቲባ አንሁን። ሰውን ለማስደሰት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል አንጣል። መርሓችን እውነት ይሁን። መርሓችን ቃለ እግዚአብሔር ይሁን። በነጻነት ልናስብ በነጻነት ተፈጥረናል። የትእማን ገረድ ሆነን ጌታን እንዳንጥል እንጠንቀቅ። ትእማን ኃላፊ ናትና። ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙም የሚኖረው ጌታ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ራሳችንን በትእማን ግላዊ አስተሳሰብ ሳይሆን በእግዚአብሔራዊው ቃል እንለካው። ኮቲባነት ይቁም። ኮቲባነት መንጋነት ነው። ኮቲባ ትእማንን ያስደሰትኩ መስሏት ጌታን ጣለችው። ሰውም የሰው መንጋ ሲሆን መንጋ የሆነለትን አካል ያስደሰትኩ እየመሰለው ከፈጣሪው ቃል ሲያፈነግጥ ይውላል። የምንመራበትና ማንኛውንም ጉዳይ የምንለካበት ሰው ሳይሆን ቃለ እግዚአብሔር ይሁን።
ኮቲባነት ይቅር። መቼም መች የማይሳሳተውን እግዚአብሔርን እንከተል።

መምህር በትረ ማርያም አበባው
ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይኾናል!!

የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይኽ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲኽ ይላል፦ "ጠላትኽ ቢወድቅ ደስ አይበልኽ፥ በመሰናከሉም ልብኽ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17

ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ኹኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚኽ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ጽናትን ወደማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።

ለእግዚአብሔር የሚኾን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ደግሞ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።

ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
🙏1
+• ከበግ መካከል ተኩላ •+

"እውነተኛ በጎች እስከሆንን ድረስ በተኩላዎች ብንከበብም ስንኳ ድል እናደርጋለን" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በአንድ ወቅት አንድ 'ባህታዊ ነኝ' ባይ በወሎ ተነስቶ ነበር:: በሕዝቡ መካከል ስለ እርሱ ያልተባለ አልነበረም:: ጻድቅ ነው፥ ቅዱስ ነው፥ ከብቃት ደርሷል ተባለ:: ከሁሉ በላይ ጎልቶ የተሰማው ግን "ክንፍ አውጥቷል" የሚለው ነገር ነበር:: የተከታዮቹ ቁጥር እየበዛ ሲሄድ ጉዳዩ በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ገብርኤል ጋር ይደርሳል:: እርሳቸውም ባሕታዊ ነኝ ባዩን ከቢሯቸው አስጠርተውት ይመጣል:: እርሱ ከገባ ወዲያም አንድ ፈርጠም ያለ ሰው ከበሩ አቁመው ጥያቄያቸውን ጀመሩ::

ብጹዕ አቡነ ገብርኤል "የሚባለው ሁሉ እውነት ነው ወይ?" እያሉ ሲጠይቁት የሚሰጠው መልስ ሁሉ የማይጨበጥ ሆነባቸው:: ሰውየው እቅጩን መናገር አልፈለገም:: በዚህ ጊዜ ጫን አድርገው "በል አወጣህ የተባለውን ክንፍ ሳታሳየኝ ከዚህ አትሄድም" ይሉታል:: ከበሩ ወጠምሻ ሰው እንደቆመ ያስተዋለው ሰውየው መሸሻ እደሌለው በገባው ጊዜ ደበሎውን ገለጥ አደረገው:: የአሞራ ላባ ደበሎው ላይ ተሰፍቷል:: "ኧረ አባታችን ሰዉኮ ይህቺን አይቶ ነው'ንጂ የሚያወራብኝ እኔ ክንፍ አላወጣሁም" ብሎ መለሰላቸው:: በሕዝቡ ሞኝነት እጅግ ያዘኑት ብጹዕ አቡነ ገብርኤልም "የእኛ ሕዝብ የሚበላውን ይወዳልና ሒድና ደህና አድርገህ ብላው" ብለው አስናበቱት::

ጌታችን "የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።"(ማቴ 7:15) በማለት ሐሰተኛ ነቢያትን እና መምህራንን በተኩላ መስሏቸው ነበር:: "ጌታችን ለምን እነዚህን ሐሰተኛ ሰዎች በተኩላ መሰላቸው?" ካልን ጉዳዩ ከተኩላ ጸባይ ጋር የሚገናኝ ነው:: ተኩላ በተፈጥሮ እጅግ ተንኮለኛ ፍጡር ናት:: በመንጋ ያሉ በጎች መካከል ገብታ ሁሉን ካልያዝኩ ብላ አታባርርም:: ከዚህ ይልቅ ተነጥላ የቀረችውን ታጠቃለች፤ ቶሎ ለመግደልም የበጉን ስስ ጉረሮ ትይዛለች:: ቀበሮ ፊት ለፊት ከማጥቃት ይልቅ አድብቶ ማጥቃትን የምትመርጥ እንስሳ ናት::

ጌታችን ተኩላዎቹ "የበግ ለምድ የለበሱ" መሆናቸውን ተናግሯል:: ተኩላ እንኳን የበግ ለምድ ለብሳ ተመሳስላ ይቅርና እንዲሁም በማድፈጥ የተካነች እንስሳ ናት:: መጠኗም ከበግ ጋር የተስተካከለ ስለሆነ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላን ከበጎች መካከል ለይቶ ማውጣት ለእረኛ እጅግ ከባድ ነው:: ሐሰተኛ መምህራንና ነቢያትም እንዲሁ ናቸው:: ተኩላ የተባሉት ሐሰተኞች እንደ እውነተኞቹ ነጠላውም፥ ካባውም፥ ጥምጣሙም፥ መስቀሉም፥ ቆቡም ሆነ አስኬማው ላይቀርባቸው ይችላል:: በሁሉም ከተመሳሰሉ ታዲያ በምን እንለያቸው?

ጌታችን እንድንጠነቀቅ ብቻ አልነገረንም፤ የምንለይበትንም ብልሃት “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ" (ማቴ 7:15) ብሎ ነገረን እንጂ:: የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ በግ መምሰል እንጂ በግ መሆን አይችልም:: በግ እንደሚጮኸው መጮህ፥ በግ ተቃቅፎ እንደሚተኛው መተኛት፥ በግ ሳር እንደሚግጠው መጋጥ አይችልም:: በመሆኑም ከተግባሩ ይታወቃል:: በተመሳሳይ ሐሰተኛ መምህራን እና ነቢያትም መምሰል እንጂ መሆን አይችሉም:: የመንፈስ ፍሬዎች የተባሉትን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣ የውሃነት እና ራስን መግዛት (ገላ 5:22-23) ሲያደርጉም ሆነ ለማድረግ ሲሞክሩ አይታዩም:: ከዚህ ይልቅ ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ ግማሽ አምኖ ግማሽ መካድ፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት እና ይህንን የመሰሉትን (ገላ 5:19-21) ለማድረግ ይጣደፋሉ::

ልብ በሉ... ተኩላ በግ መምሰል እንጂ በግ መሆን አይችልም:: አስመሳይም ከደበሎው ላይ ላባ ማሰፋት እንጂ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ክንፍ ማውጣት አይችልም::

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

(ከአቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ)
አባ ሩፎስ እንዲ አለ፡፡ እንድ አባት እንዲሀ ነገረኝ በሰማይ አራት ደረጃዎች አየሁ፡፡ በመጀመሪያ እርከን ፈጣሪውን ሳያማርር የሚያመሰግን በሽተኛ አየሁ ፣ሁለተኛው እንግዶችን በፍቅር የሚቀበል ሰውን ተመለከትኩ ፣ በሦስተኛው ማንንም ሳያይ በረሃ የሚያቋርጥ ሰው አየሁ፡፡ በአራተኛው ደግሞ ለአባቱ ስለ ጌታ ብሎ የተባለውን ሁሉ የሚፈጽምን ሰው አየሁ፡፡ በመታዘዝ የሚኖረው የወርቅ ሐብል አሥሮ የወርቅ ጋሻ ታጥቆ ከሁሉም የበለጠ ክብር ተጎናጽፎ አየሁት፡፡ ይመራኝ የነበረውን ይህ አራተኛው ከሁሉ የበለጠ ክብር ለምን ተሰጠው ብዬ ጠየኩት፡፡እርሱም እንግዳ የሚቀበል ሰው በራሱ ፈቃድ የሚሰራ ነው ፤ ተአዛዚው ግን የራሱን ፍላጎት ሁሉ ትቶ፣ በእግዚአብሔር እና በመንፈሳዊ አባቱ ታምኖ ይኖራል አለኝ፡፡ ይህን የመሰለ የላቀ ክብር ያገኘውም በዚህ የተነሳ ነው ሲል መለሰልኝ፡፡ ልጄ ሆይ ተመልከት ለክርስቶስ ሲባል የሚፈጸም ከሆነ መታዘዝ እንዴት ታላቅ ነገር መሰልህ እናንተ የዚህን በጎ ምግባር ገጽታዎች በመጠኑ ተገንዝባችኋል፡፡ መታዘዝ ሆይ የታማኞች መዳኛ፣ መታዘዝ ሆይ የበጎ ምግባሮች ሁሉ እናት፣ መታዘዝ ሆይ የመንግስተ ሰማያት መግለጫ ፣መታዘዝ ሆይ የመንግስተ ሰማያት መክፈቻና የሰው ልጅ ከምድር ወደዚያ እንዲያርግ የምታስችይው ፤ መታዘዝ ሆይ የቅዱሳን ሁሉ ምግብ ፤ ለሚጠቡሽ ወተታቸው ፣ ቅዱሳን ባንቺ ፍጹማን ሆኑ ፤ መታዘዝ ሆይ የመላእክት ወዳጅ፡፡

(ከበረሃው ጉያ ውስጥ)
4
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ

‘’ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች ታሪክ መጽሐፍ ነው፡፡ አታላዩ ያዕቆብ እስራኤል ተብሎ አባት ሆነ ፣ ነፍስ የገደለው ሙሴ ትሑትና ነጻ አውጪ ሆነ ፣ ስምኦን ጴጥሮስ ሆነ ፣ ሳውልም ጳውሎስ ሆነ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች የታሪክ መጽሐፍ ነው’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‘የኖኅ መርከብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ሆኖም ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ እጅግ ትለያለች፡፡ ወደ መርከቡ የገባ ዶሮ ሲወጣም ዶሮ ነው፡፡ ተኩላውም ከመርከቡ ሲወጣ ተኩላ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ግን ዶሮ ገብቶ ርግብ ሆኖ ይወጣል፡፡ ተኩላውም በግ ሆኖ ይወጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኃጢአተኞችን ተቀብላ ጻድቃን አድርጋ የምታወጣ መርከብ ናት’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‘’አልጋ መግዛት ለምትፈልጉ ኑ አልጋ ላሳያችሁ! ይህ አልጋ የተራ ሰው ወይም የወታደር አልጋ አይደለም፡፡ የንጉሥ አልጋ ነው፡፡ ንጉሥም ቢባል ተራ ንጉሥ ሳይሆን በዓለም ሁሉ የሚዘመርለት ታላቅ ንጉሥ አልጋ ነው፡፡ የንጉሥ ዳዊትን አልጋ ላሳያችሁ፡፡ ይህ አልጋ ከወርቅ ወይም ከአልማዝ ወይም ከከበሩ ድንጋዮች የተሠራ አይደለም፡፡ ይህ አልጋ ከዕንባ የተሠራ አልጋ ነው፡፡ እርሱ ‘ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ ፤ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ’ ብሏልና’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‘’ኃጢአት ከጣለችው ይልቅ ውዳሴ ከንቱ የጣለችው ሰው ይበዛል" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‘‘ደሃው ወደአንተ ሊለምን ሲመጣ ‘ራቁቱን ሆኖ የሚለምነው ሲያስመስል ነው‘ ትላለህ፡፡ እርሱን አታላይ ያደረገው ግን የአንተ ጭካኔ ነው፡፡ ርኅሩኅ ብትሆንለት ኖሮ አንተን ለማራራት ሲል እንዲህ ባልደከመ ነበር፡፡ እሱ እኮ በየቀኑ እየመጣ ይለምነኛል ብለህ አትበሳጭ በየቀኑ የሚለምንህ እርሱም እንደ አንተ በየቀኑ ስለሚበላ ነው’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‘’ንግግርህ ምንም ያህል እውነተኛ ቢሆን በቁጣ ከተናገርክ ሁሉንም ነገር ታጠፋዋለህ" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ነገ ለአንተ የተሸለ ነው"

ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡

ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።

ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)
🙏5👍21
#ያልተሰጠህን_አትሻ

የተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፡፡ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል። አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፣ በተሰጠህ ጸጋ ለእግዚአብሔር ተገዛ፡፡ ማር አብዝቶ መመገብ እንዳይመች እንደዚህም ሁሉ ያልተሰጠውን መሻት አይገባም አያስመስግንም፡፡

ነፍስ ያልተሰጣትን ጸጋ በመሻት እንዳትደክም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፡፡ የምታየው ማየት ቢኖር እውነተኛውን ምትሐት ሆኖ ታየዋለህ ፤ ሕሊና ያልሰጡትን ጸጋ በመሻት በማውጣት፣ በማውረድ የተሰጠውን ያጣል፡፡

ሰሎሞን መልካም ነገር ተናገረ "በሰጡት ጸጋ የማይኖር ሰው ቅጽር የሌላትን አገር ይመስላል" ብሎ ያን ማንም እየገባ እንዲዘረፈው እሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል ፤ አንተ ብሩህ አእምሮ ሰውነትህን ያልተሰጣትን ጸጋ እንዳትሻ ከልክላት፡፡

ከቁመተ ሥጋ የወጣ አብዝቶ መገበርን ከአንተ አርቅ ያልተሰጠህን መሻት ከአንተ አርቅ፡፡ ባልተሰጠህና በተሰጠህ ጸጋ መካከል ትሕትናህን፣ ንጽሕናህን መጋረጃ አርጋቸው:: አንድም በተሰጠህ ጸጋ ላይ ያልተሰጠህን ጋርደው፡፡ በንጽሕና፣ በትሕትና፣ በልቡናህ የምታስበውን መንፈሳዊ ክብር ታገኛለህ::

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
👍6
#የትሩፋት_ሥራ_ጀምር

ጨክነህ ቆርጠህ የትሩፋትን ሥራ ጀምር፡፡ በትሩፋት አጠገብ እየተጠራጠርህ አትኑር፡፡ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ከማመን ተስፋ ወጥተህ በልብህ እንኳ አትጠራጠር፡፡ ትሩፋትህ ረብህ ጥቅም የሌለው እንዳይሆን የትሩፋት ሥራ ክቡድ አይምሰልህ፡፡ መሐሪ እግዚአብሔር ለለመኑት ሰዎች ጸጋውን ፈጽሞ እንዲሰጣቸው እመን እንጂ ስጦታው እንደየሥራችን አይደለም፡፡ በትጋታችን፣ በማመናችንና በመሻታችን መጠን ነው እንጂ እንደ ሃይማኖትህ ይደረግልህ ብሏልና፡፡

የትሩፋት ሥራም ይህች ናት፣ አንዱ መተምተሚያ አዘጋጅቶ መሐል ራሱን ይተመትመዋል፡፡ በየጊዜው በሚጸልየው ጸሎት እንዳያፍር ትቀርበኛለች ብሎ ያዝናል፡፡ አንዱ አብዝቶ ይሰግዳል፣ ልጸልይ ያለውን ይጸልያል፣ ስለ ጸሎቱ ፈንታ ብዙ ያለቅሳል፣ በልቅሶው ረብህ ጥቅም ያገኝበታል፡፡ አንዱ የልቡና ሥራ የምትሆን ትሩፋትን በመዘከር ይጋደላል፣ ወደ ተወሰነለት ጸጋ ይደርሳል፣ አንዱ ምግብ ነስቶ ሰውነቱን በረኃብ ያስጨንቃታል ጸሎቱን መፈጸም የማይቻለው እስኪሆን ድረስ፣ አንዱ ተናዶ እየመላለሰ ዳዊት ይጸልያል። በመድገም ዘወትር ጸሎትን ገንዘብ ያደርጋታል፣ አንዱ መጽሐፍ ለመመልከት፣ ለመድገም ጽሙድ ሆኖ ይኖራል፣ አንዱ ከአምላክ በተገኙ መጻሕፍት ያለውን ትርጓሜ ምሥጢር ያስበዋል፣ ያስተውለዋል፣ ይመረምረዋል። ወደ ሥራው ይሳባል፤ አንዱ የዐቢይ ምዕራፉን መለያ አይቶ ምሥጢሩን ያደንቃል፣ ዝምታ ይሰለጥንበታል፡፡ በልማድ መጽሐፍ ከመመልከት በልማድ ከመድገም ይከለከላል፡፡

አንዱ ደግሞ ሁሉንም አንድ አድርጎ ይሠራቸዋል፡፡ በዚህም ይሰለቻል፡፡ ዓለማዊ ሥራ ይሠራል፣ ለሐኬት ጽሙድ ሆኖ ይኖራል። አንዱ መጽሐፍ ከመመልከት ጥቂት ምሥጢር ያገኛል፡፡ በዚህም ትዕቢት ያድርበታል፡፡ በሰው መዘበት ያድርበታል፤ ይበድላል፡፡ አንዱ የልማድ ምክንያት ይሰለጥንበታል፣ አንዱም ይህን ሁሉ ድል ይነሣል፤ ከዚህ ሁሉ ይጠበቃል፡፡ ዕንቁ ክርስቶስን ገንዘብ እስኪያደርገው ወደኋላ አይመለስም፡፡ ደስ ብሎህ እግዚአብሔር ያዘዘውን የትሩፋት ሥራ ጀምር፡፡

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
#ቁጣ_ድል_አይንሣህ #ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ

ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት። ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው፤ በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው፡፡ ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው፣ ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር፡፡ ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት፡፡

በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ፡፡ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና፣ አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል፤ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡

ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል፡፡ ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ፡፡ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል።

ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት፤ ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት። አንዱንስ እንኳን አትቈጣ፣ ተቈጥተህ አታሳዝነው፣ ቍጣ ድል አይንሳህ፡፡ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን፣ ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት፡፡ በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና፡፡ ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት፤ እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው፤ በቍጣ አትናደድበት፤ ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና።

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
#ክፉ_አሳብ

ልጆቼ! ከመጀመሪያውኑ ክፉ አሳብ ባታስቡ መልካም ነው፡፡ ካሰባችሁ ግን ቢያንስ አትናገሩት፡፡ በዚያው በሕሊናችሁ ውስጥ እያለ ዝም አሰኙት፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም ወዳለመኖር ይኼዳል፡፡

እኛ ሰዎች ነን፡፡ በመኾኑም ብዙውን ጊዜ ክፉ፣ ያልተገቡና ጸያፍ ነገሮችን እናስባለን፡፡ ነገር ግን ቢያንስ እነዚህን አሳቦች አንናገራቸው፤ ቢያንስ ወደ ቃል አንለውጣቸው፡፡ ወደ ውጭ እንዳይወጡ አምቀን እንያዛቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እየከሰሙና እየደከሙ እየጠፉም ይኼዳሉ፡፡ አንድን እንስሳ ወደ ጉድጓድ ብትጥሉትና ጉድጓዱንም በመክደኛ ብትከድኑት ያ ወደ ጕድጓድ የጣላችሁት እንስሳ የሚተነፍሰውን አየር አጥቶ ይሞታል፡፡ ምናልባት ጥቂት ቀዳዳ ካገኘ ግን በዚያች ቀዳዳ በምትገባው አየር በሕይወት መቆየት ይችላል፡፡ ሲጨንቀውም እናንተን ክፉኛ ለመጉዳት ይዝታል፤ ከወጣም በኋላ ይጎዳችኋል፡፡ ልክ እንደዚሁ እናንተም በልቡናችሁ የተመላለሰውን ኩላሊታችሁ ያጤሰውን ክፉ አሳብ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖረው አድርጋችሁ ብትከድኑት (ብታፍኑት) ይሞታል፤ ከመኖር ወዳለመኖር ይለወጣል፡፡ በአንደበታችሁ በመናገር ጥቂት ቀዳዳ ከከፈታችሁለትና እንደ እንስሳው እንዲተነፍስ ከፈቀዳችሁለት ግን ክፉው አሳብ ክፉ ግብርን ይወልዳል፡፡ ያቆጠቁጣል፡፡ በአሳብ ሳለ ከጎዳችሁ በላይም በገቢር ተወልዶና ተለውጦ ክፉኛ ይጎዳችኋል፡፡

(#የክርስቲያኖች_መከራ #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ገጽ 7➛በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
5👍1
#መጽሐፍ_ቅዱስ

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡

አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመሰለስ ብለው”
ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡

ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡
👍91
2025/07/12 09:28:24
Back to Top
HTML Embed Code: