እምነትና መታመን ከአማኝና ከጽኑ ጓደኛ እንደሚወረስ ሁሉ መጠራጠርም ከተጠራጠረ ባልንጀራ ይወረሳል፡፡ ስለሆነም ከእነዚህ ሰዎች ጋር ባልንጀራ ከመሆን መራቅ ይገባል! ይህን ልናደርግ ባንችል እንኳ ንግግራቸውን በንቃት በማዳመጥ የሚሉትን በሙሉ አለማምን ያስፈልጋል፡፡
የመጠራጠር ምንጮች ከሆኑትና ጥርጥሬን ከሚያነሳሱት ነገሮች መካከል አንዱ ንባብ ነው፡፡ መጠራጠር ያለባቸውን መጻሕፍት ሙሉ ለሙሉ ከእኛ አስወግደን ሊገነቡን የሚችሉ መጻሕፍትን መርጠን ማንበብ እንጂ እምነትንንና ሞራልን የሚያጠፉ መጻሕፍትን ማንበብ አያስፈልግም፡፡ አንዳንድ ጸሐፊዎች የጸኑ ጻድቃንን በመቃወም በአንባብያን ውስጥ ጥርጥሬን ያነሣሣሉ፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሌሎች የማያውቁትን እነርሱ እንደሚያደርጉት አድርገው ያቀርባል፡፡ ሌላው የጥርጥሬ መንሥኤ በአብዛኛው ሐሰት ሆኖ የሚገኘው ሐሜት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዙሪያ የሚነጋገሩ ወሬዎችን ማመን የለብንም፡፡ እኛም እነዚህን ሐሜቶች እንደ ገደል ማሚቶ ደጋግመን አናስተጋባ! ይህን የምናደርግ ከሆነ በጥርጥሬ የተሞላን ሰዎች እንሆናለን፡፡
ከዚህ አንጻር የአባታችን የአብርሃምን ታሪክ ስንመለከት እርሱ ለረዥም ዓመታት ምንም ልጅ ሳይወልድ ቆይቷል፡፡ አንድ መከራ ወይም ችግር ገጥሞአቸው ለረዥም ጊዜ ያለ ምንም መፍትሔ የሚቆዩ ሰዎችም በዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡
በመከራ የሚመጣ መጠራጠር
ጌዴዎን በጥርጥሬ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔርን መልአክ የጠየቀው ጥያቄ ለዚህ ምሳሌ ይሆነናል፡፡ ‹‹… እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ እግዚአብሔር ከግብጽ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ?›› (መሳ.፮፥፲፫)
ከፊት የተጋረጠ ታላቅ አደጋ ወይም መከራ ሰውን ጥርጥሬ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡ የእስራኤል ሠራዊት በጎልያድ ፊት የነበራቸው የጥርጥሬ ስሜት ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ግን ከሠራዊቱ በእምነት ምንም ዓይነት ጥርጥሬ ሳያድርበት በሙሉ ልብ ሆኖ ጎልያድን ‹‹እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል…›› ብሎታል፡፡(፩ኛ ሳሙ. ፲፯፥፵፮)
መከራ ለረዥም ጊዜ ሲረዝምና አንድ ሰው በጥርጥሬ ማዕበል ውስጥ ሲወድቅ የእግዚአብሔርን ምሕረት ይጠራጠራል፤ ወይም ሰውየው በእርሱ ላይ ጥንቆላ እንደተደረገበት አድርጎ ስለሚቆጥር የሚመጣበትን ችግር ለማስቆም ወደ ጠንቋዮች ቤት ይሄዳል፡፡ መከራና ረዥም ጊዜ በሀሳብና በጥርጥር ያልተሞላ ብርቱ ልብ ይፈልጋል፡፡
ጥርጣሬ የሰውን ልጅ እምነት ከሚሸረሽሩ ዋነኛ መሰናከያዎች ውስጥ በመሆኑ ውስጣችን እንዲኖር መፍቀድ የለብንም፤ ከእግዚአብሔር የሚያርቀን እና ለጥፋት የሚዳርገን እንዲሁም ከአምላካችን ደኅነትን እንዳናገኝም የሚያግተን በመሆኑ ልንጠራጠር አይገባም፡፡ በዚህ ጊዜም ከመጣው ቸነፈር እና መከራም ፈጣሪያችን ሊጠብቀን በፍጹም ልብ ማመን እንጂ መጠራጠር አይገባም፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን በፍጹም እምነት እንድናምን ይርዳን፤ አሜን፡፡
[ምንጭ፤ የዲያብሎስ ውጊያዎች (፪ኛ መጽሐፍ)፤ በግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፤ ትርጉም አያሌው ዘኢየሱስ]

👍3
ከምግብና ከመጠጥ ያልተቆጠበ ሰው ለክርስቶስ ሕይወቱን መስጠት እንደሚከብደው ግልጽ ነው፤ ድፍረት ያላት ነፍስ ቀጣይነት ባለው መንፈሳዊ ልምምድ ራስን መግዛት ለሥጋ ፈቃድ የሚያስፈልገውን ምግብና መጠጥ በመተው የሥጋ ፈቃድን ድል መንሳትንና የሥጋ ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላታል፤ ይህች ነፍስ የሚመጣባትን ከባድ ነገር ሁሉ እስራትም ቢሆን ግርፋትም ቢሆን መቋቋም ይቻላታል።
በእግዚአብሔርና በተጋድሎ የፀኑ ሰዎች ሥጋቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትነትን መቀበል ይቻላቸዋል፤ በአካላዊ ስሜት ብቻ ሳይሆን ከመጾም በሚገኘው መንፈሳዊ ጥቅም ሰማዕታት ጾምን የስልጠና ትምህርት ቤት አድርገውታል።
የጾም ቀናት የሚጠቅሙን ለመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በኃጢአታችን እንድንፀፀት እና ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ብቻ ሳይሆን ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ያለንን ፍቅር ለመግለጽም ይጠቅሙናል፤ ሰማዕታት የጾምን፣ የፀሎትን እና የብሕትውናን ሕይወት የኖሩ ናቸው፤ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው፤
"የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዚህችም ዓለም የሚጠቅሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነው"[1ኛ ቆሮ 7፥34]
❖ እውነተኛ ጾም አንድን ሰው ራሱን እንዴት መቆጣጠር እንዳለበት ያሰለጥነዋል፤ ቀሪ ሕይወቱን እንዴት መኖር እንዳለበት እንዲያውቅ ያደርገዋል፤ ራስን መቆጣጠር ለቅድስና ሕይወት መሠረት ነው፤ ጾም ቅጣት ሳይሆን ደስታ ነው።
[አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የሕይወት መዓዛ መጽሐፍ]

© ጉባኤ፦ ጸሎት ©
💡የቅዱስ አንብሮስ የንስሐ ጸሎት💡
"ቁስሌን የሚፈውስልኝ ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተን ብቻ እከተላለሁ ፡፡ በአንተ ካለው የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ይለየኛል? መከራ ፣ ጭንቀት ወይስ ረሃብ? በምስማር እንደ ተያዘ እኔ በፍቅር ሰንሰለቶችህ ታስሬአለሁ። ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ኃጢአቶቼ በበረታው ጎራዴህ ከእኔ ቁረጥ ፡፡ በፍቅርህ እስራት ጠብቀኝ በእኔ ውስጥ ያለውን የተበላሸውን ነገሬ አስወግድ፡፡ በፍጥነት ወደ እኔ ና የበዛውን ፣ የተሰወረውንና የደበቀውን መከራዬን ፍጻሜ አበጅለት ፡፡ አንተ የቆሸሸውን በውስጤ ያለውን አፅዳ፡፡
በኃጢአቶቻችሁ ውስጥ ሰካራም ሀሳቦችን የምታወጡ ፤ እናንተ ምድራዊ ሰዎች ሆይ ስሙኝ ፈዋሼን አጊንቻለሁ ፡፡ እርሱ በሰማያት ተቀምጧል በፈውሱ ምድርን ሞልቷል። እርሱ ብቻ ህመሜን ሊፈውስ የሚችለው። እሱ ብቻ ነው። እርሱ ብቻ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰወረውን የሚያውቅ ፣ የልቤን ሀዘን ፣ የነፍሴን ፍርሃት ሊያስወግድ የሚችል። ክርስቶስ ጸጋ ነው ፣ ክርስቶስ ሕይወት ነው ፣ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው! አሜን"።
ይህን ባሰብኩ ጊዜ.....

❤5👍2🥰1
የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል።
ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ።
"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር!! እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ!! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል።
[አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ]
¶¶@nshachannel

✝ ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል። ስለዚህም በመጽሐፍ _"አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው "ተብሎአል። [መዝ 136*8_9] የባቢሎን ልጅ [የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። [1ቆሮ 10*4] ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።
[አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ]
¶¶@nshachannel
¶¶@nshachannel
[አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ]
¶¶@nshachannel
¶¶@nshachannel
👍2🥰1
Forwarded from ፍኖተ ሕይወት
በተመሳሳይ ኃጢአት እየወደቅሁ ተቸገርኩኝ፤
ምን ላድርግ?
ክፍል፦1
#አንድ ሰው “ምን ላድርግ?” ብሎ ሲጠይቅ መንፈሳዊ ሕይወትን መፈለጉ ማሳያ ነው፡፡
አንድ ክርስቲያን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” የሚል ጥያቄ ካነሣ ለማደግ መፈለጉን፣ መንፈሳዊ መፍትሔ መሻቱን፣ እግዚአብሔር እንደሚረዳው በማያጠያይቅ መንገድ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ፣ ቀራጮች እንዲኹም ጭፍሮች እየመጡ፡- “ምን እናድርግ?” ይሉት ነበር /ሉቃ 3፡10-14/፡፡ ስለጠየቁም “ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ” ብሏቸዋል /ማቴ 3፡8/፡፡
ሐዋርያት ሲያስተምሩ፡- “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” ያሉት የገባቸው ናቸው /ሐዋ.2፡37/፡፡ ስለዚኽ ምንም ደካሞች ብንኾንም ድካማችንን ከእኛ የሚያርቀው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር “በርሱ ቃል እታነፃለኁ፤ እመከራለሁ” ብሎ “ምን ላድርግ?” ብሎ መጠየቅ ታላቅነት፣ አንድም ትሕትና፣ አንድም የመንፈሳዊ ሕይወት ፍላጎትን የሚያሳይ ነውና ኹል ጊዜ ጠያቂዎች ለካህናት፣ ለቤተ ክርስቲያን መምህራን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” ብለው ሲጠይቁ ሊበረታቱ ይገባቸዋል፡፡
ጥያቄው የብዙ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ፡- “ሰው ኾኖ የማይበድል እንጨት ኾኖ የማይጤስ” እንዲሉ እንደየኑሮአችን ደረጃ፣ እንደየሥራችን ዓይነት ይለያይ እንደኾነ እንጂ ክርስትና ሕይወታችን ስንመላለስ አንድ ከሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ ኃጢአት የሚስማማን መኾኑ ነው፡፡ በርግጥም “ምን እናድርግ?”
#የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ማወቅ- አንድ
ሰው የሚወድቅበት ሀጥያት ሌላኛው ሰው የማይወድቅበትና ትኩረት የማይሰጠው ሊኾን ይችላል፡፡
ከዚኽ አንጻር “በተመሳሳይ ኃጢአት ደጋግሜ እወድቃለኁ” ያልነው ኃጢአት ምንድነው? እየተደጋገመ ያስቸገረን ምንድነው? ከምንም በፊት የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን አጢኑት፡፡ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ከለዩ በኋላ ለዚያ ከሚዳርጉን ቦታዎች፣ ወይም ጓደኞች፣ ወይም ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ወደምንወድቅበት ኃጢአት የሚገፋፉ ኹኔታዎችን፣ ቦታዎችን ወይም ጓደኛን በአጠቃላይ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መራቅ ያስፈልጋል፡፡ “ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ኾነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ኾነህ ትገኛለህ” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት /መዝ.18፡26/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም “አትሳቱ፤ ክፉ ባለንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” ይላል /1ኛ ቆሮ15፡33/፡፡ በዚኽ መሠረት ጠያቂያችን ብቻ ሳይኾኑ ኹላችንም ኃጢአትን ደጋግመን የምንሠራው በኹኔታዎች ተጽዕኖ ነው? ወይስ በጓደኞች ግፊት? ወይስ በምንሰማው፣ በምናየው፣ በምንዳስሰው ተጽዕኖ? ይኽን በአግባቡ ከለየን በኋላ ከምንጩ ለማድረቅ ለዚያ ከሚዳርጉ ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ ይኽን ስናደርግም ከምንም በፊት ኅሊናን ማሳመን ይጠይቃል፡፡ በመቀጠልም አካላዊ ውሳኔ መስጠትን ነው፡፡ ለኃጢአት በሚዳርግ ቦታ ተቀምጠን “በፍጹም አይነካኝም፤ አይደርስብኝም” ማለት መመጻደቅ ነው፡፡ ሰይጣንም እኛን ለመጣል አያርፍምና የምንወድቅበትንም መንገድ ያዘጋጃልናል በኅሊናም በአካልም ከዚያ መሸሽ ያስፈልጋል፡፡
የጴጢፋራ ሚስት ዮሴፍን ለክፉ ሥራ ስትከጅለው ቆሞ አልተሟገተም፤ ጥሏት ሸሸ እንጂ /ዘፍ.39/፡፡ ስለዚኽ ለተደጋጋሚ ኃጢአት ከሚዳርጉንና ከሚገፋፉን ነገሮች “እችለዋለኁ፤ እቋቋሟዋለኁ” ብሎ መመጻደቅ ሳይኾን መሸሽ ካለብን መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ እንደየኹኔታው በይበልጥም ከክፉ ቦታዎች፣ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ ኃጢአቱ በሥጋም በነፍስም ጎጂ እንደኾነ ማስተዋል፡፡ ይኽ በተመሳሳይ እየወደቅንበት ያለው ኃጢአት በሥጋም ጭምር የሚጎዳን ይኾናል፡፡
ከክርስትና ሕይወት ባሻገር ስብእናን የሚያጎድፍ፣ ጤናን የሚያውክ ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ አንጻር የዚኽ ጉዳት በጥልቀት ማስተዋል ያስፈልጋል፤ ጉዳቱን ማሰብ ለመጠንቀቅ ይረዳልና፡፡

ምን ላድርግ ?
ክፍል፦ ሁለት
#ከንስሐ አባታችን፣ ከመምህራን እንዲኹም ከመጻሕፍት ትምህርት ማግኘት የእድገት በደረጃ ነው፡፡ በአንድ ጀምበርም ለውጥ ላይመጣ ይችላል፡፡ በመኾኑም በሒደት ያንን የመተው መስመር ውስጥ እንድንጠነክር ከዚኽ ኹኔታም ፈጽመን ለመራቅ በራሳችን ጉልበት ብቻ አንችልም፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናልና /ዮሐ15፡5/፡፡ በዚኽም መሠረት ከመምህራን የምንሰማው የእግዚአብሔር ቃል፣ ከመጻሕፍት የምናገኘው፣ ከመምህረ ንስሐም በጸሎትና በምክር የምናገኘው ሐሳብ ያ እያጠቃንና እየጣለን ያለውን እንዲኹም የምንደጋግመውን ኃጢአት ለማስወገድ ኃይል ይኾነናል፡፡
#መንፈሳዊ ተግባራትን ማዘውተር፡፡ እንግዲኽ እንደየ ክስተቱ ለየትኛውም የኃጢአት ተግባር መንፈሳዊ ሕይወት፣ መንፈሳዊ ተግባር ድል መንሻው ነው። ይኽም “እንዲኽ ያለውን ክፉ መንፈስ ያለ ጾም ያለ ጸሎት ከእናንተ አይወጣም” እንዳለ /ማር.9፡29/ ጾምን፣ ጸሎትን፣ ንስሐን የሕይወታችን መሠረት ማድረግ ነው፡፡ መተውን መለማመድ፡፡ ይኽም ማለት ጠቢቡ ሰለሞን “ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” እንዳለ /ምሳ 23፡17/ “እስኪ ዛሬ ተቆጥቤ ልዋል” ብሎ መወሰን ማለት ነው፡፡
ከዚያ ከምንጠላው ግን ደግሞ እየወደቅንበት ካለው ስሕተት ተቆጥበን ከዋልን ማታ ላይ ተመስገን ብሎ ጸልዮ ማደር ነው፡፡ ነገም ሲነጋ “ዛሬም እንዲኹ እንደ ትናንትናው መንፈሳዊ መንገድና ሒደት ልዋል፡፡ ዛሬም እንዲኽ ካለው ተግባር ፍጹም ተቆጥቤ መዋል አለብኝ፡፡ ደግሞም እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያስችለኛል፡፡ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ኹሉን እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያበራታኛል” ስንልና ዕለት ዕለት ኹኔታውን እየኰነንነው፣ እያወገዝነው፣ “በዚያ መንፈስ ዛሬ አልውልም፡፡ ይልቁንም በመንፈሳዊ
መንገድና በጥንካሬ እውላለኁ” ብለን ስንወስን ያን ውሳኔአችንን እያደነቅን ስለተደረገልን ጥንካሬም ተመስገን እያልን ልምምድ ማድረግ ይቻላል፡፡ ደጋግመን የምንሠራው ኃጢአት እጅግ ብዙ ዘመናት ከእኛ ጋር የቆየ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ኃይል በላይ የኾነ ኃጢአት የለም፡፡ ዋናው የእኛ ውሳኔ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የምንታለለው እዚኽ ጋር ነው፡፡ ለመተው እንፈልጋለን፤ ለመተው ግን በተግባር አንወስንም፡፡
ንስሐ መግባት የማይፈልግ ሰው የለም፤ በተግባር ወስኖ የሚገባ ግን ጥቂት ነው፡፡ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ መኖር የማይፈልግ ክርስቲያን አይኖርም፡፡ ብዙዎች መቁረብ ይፈልጋሉ፤ ወስነው የሚቆርቡት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ከዝሙት ኃጢአት መራቅ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ዝሙትን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ምስሎችን እንዲኹም የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ዘፈኖችን እንዲኹም ጽሑፎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ንግግሮችን ሲከታተሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚኽን ሰዎች ስናያቸው በውስጣቸው ከዚያ ኃጢአት የመራቅ ፍላጎት አለ፤ ተግባሩ ላይ ግን ከዚያ የሚያሸሻቸው አይደለም፡፡
ለዚኽም ነው ጌታ “ብዙዎች ይፈልጋሉ፤ አይችሉምም” ያለው /ሉቃ13፡24/፡፡
ስለዚኽ ከኃጢአት መራቅ የሚፈልግ ሰው የመተው ልምምድን አኹንኑ መጀመር አለበት፡፡ “ዛሬ ዘፈን አላዳምጥም፡፡ ዛሬን በዚኽ ምትክ መዝሙር አዳምጣለኁ” ብሎ መለማመድ አለበት፡፡ በዚኽ ውሳኔው ጸንቶም ዛሬን ይውላል፤ ያድራልም። ሌሎች ነገሮችም እንደዚኽ ናቸው፡፡ የመጠጥ ልምድ ያለው ሰው “ዛሬ አልጠጣም፤ ዛሬ በምጠጣበት ሰዓት እዚኽ ቦታ እሔዳለኁ፡፡ እዚያ ሒጄ እውላለሁ ። "በበጎ ነገር አሳልፈዋለኁ” ሲል ዛሬን ይውላል፡፡ ማታ ላይ ሲመሽ “ለካ ይቻላል፡፡ ለካስ እኔ ከበረታኁ እግዚአብሔር ያስችለኛል” የሚለውን በኅሊናው ያሳምናል፡፡ ነገሮችን የመተው ልምምድ በተግባር ማሳየት ማለት ይኸው ነው፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያ ያስቸግረን የነበረው ተደጋጋሚ ኃጢአት ታሪክ ይኾናል፤ ለሌላ ሰው መካሪ ኾነን ራሳችንን በለውጥ ቦታ ላይ እናገኘዋለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦መቅረዝ ዘተዋሕዶ

"ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ። ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን።"
(#አባ_እንጦንስ - 'በበረሃው ጉያ ውስጥ' መጽሐፍ የተወሰደ)
¶¶@nshachannel
¶¶@nshachannel
(#አባ_እንጦንስ - 'በበረሃው ጉያ ውስጥ' መጽሐፍ የተወሰደ)
¶¶@nshachannel
¶¶@nshachannel
👍3🥰2
አንባቢ ሆይ በማስተዋል ያንብቡ!!
ያዕቆብ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
¹⁵ ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥
¹⁶ ከእናንተ አንዱም፦ በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
¹⁷ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
¹⁸ ነገር ግን አንድ ሰው፦ አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
¹⁹ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
²⁰ አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?
²¹ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
²² እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
²³ መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
²⁴ ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
²⁵ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
²⁶ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

👍2❤1
መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ የምናገኘው ጥቅም ብዙ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በመውደድ የሚገኘው ርዳታ በእውነት ያለ ሐሰት እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህን በማስመልከተም ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፡- “ወኵሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ - የተጻፈው ኹሉ ለእኛ ምክር ለእኛ እዝናት ሊኾን ተጽፏል” (ሮሜ.15፡4)፤ “ዝንቱ ኵሉ ዘረከቦሙ ለእልክቱ ምሳሌ ተጽሕፈ ለአእምሮ ወለተግሣጽ ዚአነ እለ በድኅረ መዋእል - እነዚያን ያገኛቸው መከራ ኹሉ በኋላ ዘመን ለምንነሣ ለእኛ ምክር እዝናት ሊኾን ተጽፏል” (1ኛ ቆሮ.10፡11)፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የኹሉም ዓይነት መድኃኒቶች ሳጥን ነው፡፡ የትዕቢት ቁስሉ ይሽርለት ዘንድ የሚሻ ሰው በዚህ ሳጥን ውስጥ ጽኑ መድኃኒትን ያገኛል፡፡ ልል ዘሊልነትን ለመጣል፣ ፍቅረ ንዋይን ከእግሩ ሥር ለመርገጥ፣ መከራን ለመናቅ፣ ጥብዓትን ገንዘብ ለማድረግ፣ ትዕግሥትንም ለማግኘት የሚፈልግ ሰው መድኃኒቱን ከዚህ ሳጥን ውስጥ ያገኛል፡፡
በከፍተኛ ሥጋዊ ድኽነት ውስጥ የኖሩትን፣ በጽኑ ሥጋዊ ሕመምም የተሠቃዩትን አይቶና ገድላቸውን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አንብቦ መጽናናትን የማያገኝ ማን ሰው አለ? የመጻጉዕን ታሪክ አንብቦ ጥበብ መንፈሳዊን ገንዘብ የማያደርግ ማን ሰው አለ? ምክንያቱም መጻጉዕ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ሙሉ ሽባ ነበር፡፡ በእያንዳንዷ ዓመት መዳንን ይናፍቅ ነበር፡፡ ይህን ኹሉ ዓመታት በበሽታ ተይዞ እያለ ግን ተስፋ አልቆረጠም ነበር፡፡ ስላለፈው ዓመታት ብቻ ሳይኾን ለወደፊቱም ተስፋ አልቆረጠም ነበር፡፡
እንዲያውም የመከራውን ታላቅነት ተመልከቱ! ተመልከቱና አድንቁ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡- “ልትድን ትወዳለህን?” ባለው ጊዜ፡- “አዎ ጌታ ሆይ! ነገር ግን በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም” ይላልና፡፡
ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር አለ? እኮ ከዚህ በላይ ምን አስጨናቂ ኹኔታ አለ? ለብዙ ዘመናት ሥቃይ ከመታገሡ የተነሣ የተወቀረ ልቡን ተመለከታችሁን? ለብዙ ዓመታት መከራ ከመቀበሉ የተነሣ የልቡ ሁከት እንደ ምን ጸጥ እንዳለለት አያችሁን? ምክንያቱም ከአንደበቱ አንዲት የማጉረምረም ቃል አልወጣችም፡፡ በብዙዎች ዘንድ እንደምንሰማው የተወለደባትን ቀን አልረገመም፡፡ “ይህን ያህል ዓመት ታምሜ እያየኝ፥ እንዴት ልትድን ትወዳለህን ብሎ ይጠይቀኛል?” ብሎ አልተበሳጨም፡፡ “ወደ እኛ የመጣኸው በሕመማችን ላይ ጥዝጣዜ ለመጨመር ነውን? ልትድን ትወዳለህ ወይ ብለህ የምትጠይቀኝስ በእኔ ላይ ለማፌዝ ነውን?” አላለም፡፡ ታዲያ ምን አለ? ተረጋግቶና ከፍ ባለ ትሕትና ኾኖ “አዎን ጌታ ሆይ!”
ተመልከቱ! እያናገረው ያለው እንኳን ማን መኾኑን አያውቅም፡፡ እያናገረው ያለው ሊያድነው ይችል እንደ ኾነና እንዳልኾነ አያውቅም፡፡ ቢኾንም ግን ተረጋግቶ ያለበትን ኹኔታ ነገረው፡፡ ከዚህ በላይ ምንም አልጠየቀውም፡፡ እንዲሁ የሕመሙን ታሪክ ለባለመድኃኒት እንደሚናገር ሰው ኾኖ ነገረው፡፡ ምናልባት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል ብሎ ቢያስብ ነው፡፡ ኢየሱስስ ምን አለው? “ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ኺድ!”
… ስለዚህ ዕለት ዕለት መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ እንደ በሽታችን ዓይነት እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ጽኑ መድኒቶችን እናገኛለንና እናንብብ፡፡
[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]

እግዚአብሔር ተስፋ አድርግ
ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሠራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሠራም ብለው በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሠራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የሥራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይናቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል። "እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።" [መዝ 26*14 ]
እግዚአብሔርን ጠብቅ
እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ፤ በእምነት፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል። "እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።" [ሮሜ 8፥28] "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም።" [ኢሳ 40፥31] ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው። "ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል" የሚል ቃል ተጽፏል [መዝ 102፥5] ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል።
ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? [ሐዋ 1፥7] አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው። ችግርህን እግዚአብሔር በጊዜው እንደሚያቃልለው መጠባበቅ የአንተ ሥራ አይደለም።
[#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ]

ክርስቲያን ሆይ ይህን ልብ በል!!
ወገኔ ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእግዚአብሔር ወዳጆች ለተባሉት ወንድም/እኅት/፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ጋር ከበዛው ጸጋቸው ተካፋይ፣ ከእርሱም ምስክሮች ጋር አንድ ማዕድ የምትካፈል፣ የቅዱሳን ርስት ወራሽና ቅን በሆነው ፍርዱ ደስ ይልህ ዘንድ ከነቢያት የፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጥክ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋር በምስጋና የምትሳተፍ፣ ከሱራፌልም ጋር የምትነጋገር፣ ከኪሩቤል ጋር በሰማያዊ ዙፋን ላይ የተቀመጥክ ፣ ከክርስቶስ የጸጋ ስጦታ ተካፋይ የሆንክ፣ የብቸኛ ልጁ ሰርግ ታዳሚ ትሆን ዘንድ የተጠራህ የሰማያውያን ሠራዊተ መላእክት ወዳጅ፣ የሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ዜግነት ያለህ ነህ፡፡
አእምሮህ ውስጥ እነዚህ በክርስቶስ ለአንተ የተሰጡት የእግዚአብሔር ቸርነቶች ከተቀመጡ የጨለማው ዓለም ገዢ አገልጋዮች የሆኑ አንተን ሊያሰነካክሉህ አይችሉም፡፡ በንስሐ ጽና፡፡ ሕሊናን ከሚያቆሽሹ ከንቱ አስተሳሰቦች ራስህን ንጹሕ አድርግ፡፡ ከእነዚህ ፈጽመህ ራቅ ከንቱ በሆኑ አስተሳሰቦችም አትሸበር፡፡”
[አብርሃም ሶርያዊ]

❤3👍1
ለቅዱሳን ቤተሰቦቹ የጸሎት መልስ የሆነው፣ ለዚህች ዓለም የሚነድና የሚያበራ መብራት የነበረው፣ የሥጋን ጣዕም ያልቀመሰው ፍጹም ተሐራሚ፣ ተፈጥሮው የሰው ኑሮው የመልአክ የነበረው፣ ዕረፍትን የማያውቅ የበረሃው ሰው የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደቱ ዛሬ (ሰኔ 30) ይታሰባል።
ቅዱሱ ሰማዕት እንደ ኖኅ ጻድቅ የነበረ፣ እንደ አብርሃም በእግዚአብሔር የተወደደ፣ እንደ ዮሴፍ የታሰረ፣ እንደ አቤል በአመጻ የተገደለ፣ እንደ ሄኖክ አካሄዱን ከአምላኩ ጋር ያደረገ ነው።
በመንፈስ ቅዱስ አሳዳጊነት በመላእክት አገልግሎት በበረሃ ያደገው ዮሐንስ ክብሩ እንዴት ያለ ነው? እርሱ እንደ ሕፃናት ባለቀሰ ጊዜ የሚያባብለው ሰው አልነበረም። "አይዞህ ልጄ" እያለች የምታጽናናው እናቱም ገና በልጅነቱ ተለይታዋለች። ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻውን በበረሃ አልተወውም። አጥንት በሚያለመልም የመላእክት ምስጋና አረጋጋው። በልዩ ጥበቡም አሳድጎ በመንፈስ እንዲጠነክር አደረገው። የእግዚአብሔር አብን ልጅ ዮሴፍ በናዝሬት (የሰው ልጅ) እንዳሳደገ፣ የዘካርያስን (ለሰውን) ልጅ ዮሐንስን እግዚአብሔር በበረሃ አሳደገ።
ዮሐንስ ነቢይ ነው። ግን ከነቢያትም ይበልጣል። እርሱ እንደ ሌሎቹ ነቢያት የመሲሑን መምጣት በመንፈስ ዓይቶ "ይመጣል" ብቻ አላለም። "እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ብሎ ወደ እርሱ በመጠቆም ሲጠበቅ የኖረው ለመምጣቱም አብሣሪ ሆኗል። እርሱ ነቢያቱ ሊያዩ የወደዱትን ግን ያላዩትን፣ሊሰሙ የፈለጉትን ግን ያልሰሙትን አይቷል፤ ሰምቷልም። ወልድን የዳሰሰ፣ አብን የሰማ፣ መንፈስ ቅዱስን ያየ እንደ ዮሐንስ ያለ ነቢይ ማን አለ?
ዛሬ የተወለደው ቅዱስ ዮሐንስ አምላኩን ማገልገል የጀመረው ገና በእናቱ ማኅጸን ሳለ ነው። ነቢዩ ለፈጣሪው በደስታ የሰገደው ገና ከተፈጠረ በ180ኛው ቀኑ ነው። ታዲያ እኛ እግዚአብሔርን ለማገልገል ለምን ቀጠሮ እናረዝማለን? ገና ነን እንደርስበታለን እንዴት እንላለን? ከዛሬው ባለ ልደት አንጻር ለአገልግሎትና ለምስጋና በጣም የዘገየን አይመስላችሁም? የታደለው ቅዱስ ዮሐንስ በስድስት ወሩ ሰገደ። የእኛስ ይህ አፈርና ትቢያ የሚሆን ሰውነታችን ሳይወድቅ በፊት ፈጣሪውን የሚያገለግለው መቼ ነው?
"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል"
ሉቃ 1፥14
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

❤6
“ብዙ ሰዎች ኢዮብ ያስደንቃቸዋል” ብላችኋል፡፡ ትክክልም ተገቢም ነው፤ የተጋደለው ተጋድሎ ታላቅ ነውና፥ በትዕግሥቱና በቅድስናው ስለ እግዚአብሔር ምስክርነቱና ከዲያብሎስ ጋር ባደረገው ጥቡዕ ተጋድሎ ተጋድሎውንም በፈጸመበት ድል ነሺነት ቅዱስ ጳውሎስን ሊተካከል የሚችል ነውና፡፡ ኾኖም ግን የቅዱስ ጳውሎስ ተጋድሎ ለወራት ሳይኾን ለብዙ ዓመታት የዘለቀ ነው፤ ዘወትር ወደ አንበሶች መንጋጋ ይገባ ነበር፤ ስፍር ቊጥር ከሌላቸው ፈተናዎች ጋር ይጋፈጥ ነበር፡፡ በዚህም ከዐለት ይልቅ ጽኑዕ መኾኑን አስመስክሯል፡፡ [እንደ ኢዮብ] በሦስት ወይም በአራት ጓደኞቹ ሳይኾን በመምለክያነ ጣዖታትና በቢጽ ሐሳውያን ኹሉ ተሰድቧል፡፡ ስሙን እያነሡ አስነውረዉታል፤ ተፍተውበታል፤ ሰድበዉታልም፡፡
ኢዮብ እንግዶችን በመቀበልና ድኾችን በመንከባከብ ታላቅ ነበር፡፡ ይህንን አንክድም፡፡ ነገር ግን ኢዮብን በዚህ ረገድ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ስናነጻጽረው ሥጋ ከነፍስ የምታንሰውን ያህል ያንስብናል፡፡ ለምን ቢሉ ኢዮብ ሕሙማን ቢንከባከብ በሥጋ የታመሙትን ነው፤ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ ግን የተንከባከበው በነፍስ የታመሙትን ነው፡፡ ተወዳጅ ጳውሎስ በመንፈስ ሽባና አንካሳ የኾኑትን ይመራቸው ነበር፤ የተራቆቱትንና የኃጢአት ብርድ የሚያሰቃያቸውን ደግሞ መንፈሳዊ የመራቀቅ ልብስን ያለብሳቸው ነበር፡፡
የተወዳጅ ኢዮብ ቤት ለእንግዶች የተከፈተ ነበር፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ነፍስ ግን ለዓለም ኹሉ የተከፈተች ነበረች፤ በእንግዳ ተቀባይነቷም ፍጹም ኵላዊት ነበረች፡፡ እርሱም ራሱ ይህን በማስመልከት፡- “በእኛ አልጠበባችሁም፥ በሆዳችሁ ግን ጠቦባችኋል” ብሏል (2ኛ ቆሮ.6፡12)፡፡ ኢዮብ ለተቸገሩት ሰዎች ከነበሩት ብዙ በጎችና ከብቶች በልግስና ይሰጣቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ከገዛ ሰውነቱ በቀር ምንም አልነበረውም፡፡ ነገር ግን ሰውነቱን ሌሎች ሰዎችን ለማገልገል ተጠቅሞበታል፤ እርሱ ራሱ እንዲህ እንዳለ፡- “እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ” (ሐዋ.20፡34)፤ በሰውነቱ ሥራ የተራቡትን ይመግባቸው ነበር፡፡
“ትሎች፣ ቁስሎችም ኢዮብን እጅግና ሊታገሡት ከሚችል በላይ አሠቃይተዉታል” ብላችኋል፡፡ እውነት ነው፤ እስማማለሁ፡፡ ኾኖም ግን ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ ለዓመታት የተቀበላቸውን ግርፋቶች፣ ብዙ ጦም፣ ዕራቁት መኾን፣ ሰንሰለቶች፣ እስራቶች፣ መከራዎች፣ በገዛ ወንድሞቹ በኩል የነበረው ፍርሐት፣ በአሕዛብ በኩል የነበረውን ፍርሐት፣ በአጠቃላይ በዓለም ኹሉ በኩል የነበረውን ፍርሐት፣ ከዚህ እጅግ የሚበረታውም በወደቁት በኩል የነበረውን ጭንቀት፣ ለአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ የነበረውን አሳብ፣ በተሰናከሉት በኩል የነበረውን ድንጋጤ ብታስቡ ነፍሱ እነዚህን ኹሉ ከመሸከም አንጻር ምን ያህል ከብረት ይልቅ ጽንዕት እንደ ነበረች ታያላችሁ፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስ ታግሦ የቻለው የተወደደ ኢዮብ በሥጋው የቻለውን ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለወደቁት ሰዎች በነፍሱ ያገኘው ኀዘን ትሎች በኢዮብ ሰውነት ላይ ካደረሱበት ጥዝጣዜ በላይ የሚጠዘጥዝ ነው፡፡ ከዓይኖቹ የእንባ ወንዞች ቀን ከሌሊት ፈስሰዋል፡፡ በአንዲት ነፍስ መጥፋት ምክንያትም አንዲት ሴት ከሚያገኛት ምጥ በላይ እጅግ ጣር ይይዘው ነበር፡፡ “ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል” እንዲል ያደረገውም ይኸው ነው (ገላ.4፡19)፡፡
#ውዳሴ_ጳውሎስ_በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

▬▱▬▱▬▱🌷▱▬▱▬▱▬
ግእዝን በርቀት በ ፲፪ኛ ዙር ለመማር ለተመዘገባችኹና ለምትመዘገቡ በሙሉ።
▪ የምዝገባ ጊዜው የሚጠናቀቀው ሐምሌ ፲፪ , ፳፻፲፭ ዓ.ም ማታ ፲፪ ሰዓት ድረስ ብቻ ይኾናል።
▪ ትምህርቱ የሚጀመረው እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሰኞ ሐምሌ ፲፯, ፳፻፲፭ ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰዓት አቈጣጠር ጧት ፲፪ ይኾናል።
▪ ትምህርቱ የሚሰጠው በዚኹ የቴሌግራም ቻናል ሲኾን ትምህርቱን በተመለከተ አንዳንድ መልእክቶች ከሐምሌ ፰ ጀምሮ ስለሚተላለፉ እንድትከታተሉ በትሕትና አሳስባለኹ።
እስካኹን ወደቻናሉ ያልገቡ መማር
የሚፈልጉ ካሉ ወደ ቻናሉ የሚገቡበትን
ሊንክ እንድትልኩላቸው እና የምዝገባውን የመጨረሻ ቀን እንድታሳውቋቸው አደራ
እላለኹ።
@geezdistance12
● ማሳሰቢያ፦ መመዝገብ ማለት ቻናሉን " Join" ማለት ብቻ ነው። በዚኽ ቻናል ውስጥ ያላችኹ ተመዝግባችዃል ማለት ነው።
▬▱▬▱▬▱🌷▱▬▱▬▱▬
መምህሩ ቻነሉን በ 12 ስለሚዘጉት ተሎ join ብትሉ እና ሼር ብታደርጉ ጥሩ ነው። እሳቸው ትርፋቸው የኛ መማር ብቻ ነው። እባክዎ join ብለው ይማሩ።

👍5🔥1
"ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ በሕፃንነቱ ዮሴፍ በጣም ይወደው ስለነበር እንደ መጠኑ ወንበር ሠርቶ ከፊቱ ያስቀምጠው ነበር። መዓዛውን አሽትተው ደስ እያላቸው የዮሴፍ ልጆች እኔ ልያዝ እኔ ልያዝ ይነጣጠቁት ነበር። ኢየሱስን አይቶ የልቡን ኀዘን ያልዘነጋ የለም። እርሱን ማየት ኀዘንን ያርቃል። እርሱን ማየት ችግርን ያባርራል። ቃሉን መስማት የልብ ኀዘንን ነቅሎ ይጥላል። አንድ ጊዜ ፊቱን አይተው ሁልጊዜ እርሱን ለማየት ያልሳሳ ያልናፈቀ የለም። ሕፃናትም እርሱን አይተው በፍቅሩ ይቃጠሉ ነበር። ጎልማሶች ባዩት ጊዜ ደስታ ያድርባቸው ነበር። እርሱን ማየት ስንቅ ደስታ ይሆናቸው ነበር። እርሱን አይቶ ቃሉን ሰምቶ የሰለቸ የለም። ዘመድ የሞተባቸው ሰዎች ጌታን ሲያዩ ኀዘናቸው ይጠፋላቸው ነበር። እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብፅ ይዛው በተሰደደች ጊዜ የግብፅ ልጆች ንዑ ንርአዮ ለወልደ መንክራት እያሉ እየሄዱ ያዩት ነበር"።
ምንጭ:-አረጋዊ መንፈሳዊ ትርጓሜ ድርሳን 24
ምንጭ:-አረጋዊ መንፈሳዊ ትርጓሜ ድርሳን 24
👍5❤2
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡
ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡
ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

መልካም የመውጫ ፈተና (exit exam) ይሁንላችሁ። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን። የእስከዛሬው ልፋታችሁን፤ ድካማችሁን የቤተሰባችሁን ድካም እግዚአብሔር በቸርነት ይመልከትላችሁ። አልፋችሁ ለመመረቅ ለወግ ለማዕረግ ያብቃችሁ። መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ የፍኖተ ሕይወት መልካም ምኞት ነው!!!
የአምላክ እናቱ እመብርሃን ጓዳችንን ትሙላ።
የአምላክ እናቱ እመብርሃን ጓዳችንን ትሙላ።
❤5🙏4
በሕማም፣ በመከራና መሥዋዕት በመሆን ፍቅራችን ይፈተናል
ፍቅርን የሚያውቅ ሰው ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ሰው በመጀመሪያ መሥዋዕት ለማድረግ መልመድ ያለበት ከእርሱ ውጪ በሆኑ ነገሮች ማለትም ገንዘቡን፣ ጊዜውን እና ሀብቱን በመለገስ ነው፤ መስጠት ከማግኘት አንድ ነውና፡፡ ለሰዎች ደስታ እንደራሱ የሚጨነቅ እርሱ ፍቅርን ያውቃል፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ይኖራል፡፡ መሥዋዕትነት መክፈል ካልቻልን ግን ፍቅር አልገባንም ማለት ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔርን ማፍቀር ካልቻልን ደግሞ ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ማግኘት አንችልም፡፡
ፍቅር የሚፈተነው በሕማም በመከራና መሥዋዕት በመሆን ነው፤ መሥዋዕት መሆን የማይችል ሰው የማይወድ ወይም የማያፈቅር ሰው ነው፡፡ የሚወድ ሰው ከሆነ ግን ለመውደድ ማንኛውም ነገር መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡
የአባቶች ሁሉ አባት የተባለው አብርሃም ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር የተነሣ ወገኖቹንና የአባቱን ቤት ትቶ በመውጣት በአንድነት በድንኳን ውስጥ ኖሯል፤ ይሁን እንጂ አብርሃም ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር ያሳየው አንድ ልጁን በመሠዊያው ላይ ባስተኛው ጊዜ ነበር፡፡ እርሱ በልጁ ዙሪያ እንጨቶች ሰብስቦ ካቀጣጠለ በኋላ መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው ቢላዋ የያዘ እጁን ቃጥቶ ነበር፡፡
ነቢዩ ዳንኤል እግዚአብሔርን በወደደ ጊዜ ወደ ተራቡ አናብስት ይወረወር ዘንድ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል፡፡ ሦስቱ ወጣቶች እንዲሁ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ያረጋገጡት በእቶኔ እሳት ውስጥ በመወርወር የከፈሉት መሥዋዕትነት ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ፍቅር የገለጠው እንዲህ በማለት ነው፤ ‹‹አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ፤….›› (ፊል. ፫፥፰-፱)
አባታችን ያዕቆብ ከራሔል ጋር በፍቅር በወደቀ ጊዜ ስለ እርሷ ብዙ መሥዋዕትነት ከፍሏል፡፡ እርሱ ራሔልን ለማግኘት ለሃያ ዓመታት ያህል በቀን ሀሩንና በሌሊት ቁር መድከም ነበረበት፡፡ ይሁን እንጂ ለእርሷ ከፍተኛ ፍቅር ስለ ነበረው እነዚህ ዓመታት ለእርሱ እንደ ጥቂት ቀናት ነበር ያለፈለት፡፡ እኛም ለሰው ዘር በሙሉ ሲል በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ ለቀረበው ለኢየሱስ ክርስቶስ የምናቀርበው መሥዋዕት በዚህ ምድር የሚገጥመን ችግር በወጣት፤ የሚደርስብንን መከራ እና ሥቃይ በትዕግስት በማለፍ ነው፡፡
‹‹ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና›› እንደተባለውም ጌታችን ኢየሱስ መሥዋዕት ሆኖ ካዳነን በኋላ እኛም የምናቀርበው ለእርሱ መባ እና ምጽዋዕት ኃጢአታችንን ያስተሰርይልናል፡፡ ይህም በቤተክርስቲያን ለመዘከርም ሆነ ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓል ለማክበር ስንሄድ እግዚአብሔር የምናቀርበው ስጦታ ነው፤ ሆኖም ግን በእምነት እና በበጎ ምግባር ያልተደገፈ ማንኛውም ስጦታ በእርሱ ዘንድ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ሁሉን የሚያይ አምላካችን ልባችንን እና ኵላሊታችንን ይመረምራልና የውስጣችንን ክፋት ስለሚያውቅ የምናቀርበውን መሥዋዕት አይቀበለውም፤ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በድፍረት በመርገጣችንም በኋላኛው ዓለም ይቀጣናል፡፡ (ዕብ. ፲፥፫-፬)
አባቶቻችን ሰማዕታትን ካህናት ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር የተነሣ ደማቸውን፣ ሕይወታቸውን እና መደላደላቸውን መሥዋዕት አድርገው አቅርበዋል፡፡ እነርሱ ለእግዚአብሔር የተለየ ፍቅር ስለነበራቸውና ሥቃይን ስለተለማመዱት ፈጽሞ ፈርተው አያውቅም ነበር፡፡
እኛም እንደ አባቶቻችን ለእምነታችንም ሆነ ለሃይማኖታችን ሰማዕት መሆን ባንችል እንኳን በዚህ በምድራዊ ሕይወታችን ማንኛውም ዓይነት ችግር እና መከራ ሲገጥመን ባለመማረር ሥቃዩንም ተቋቁመን ፈተናችንን ማለፍ ይጠበቅብናል፤ ከራሳችን አልፎ ለሌሎች መዳን ምክንያትም ልንሆን እንችላለን፡፡ ያን ጊዜም በሰላም፣ በፍቀር እና በአንድነት እንኖራለን፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር በሰላም እና በፍቅር አንድንኖር ፍቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡