Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1109 - Telegram Web
Telegram Web
    +++ "እየጠላን የምናደርገው" +++

ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?! በነገራችን ላይ ይህ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ራሱ ሐሜት ነው።

የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው፡፡  በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ  የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ  እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት  ሔዋን ነበረች፡፡(ዘፍ 3፥1-5)

   የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር እያደረገ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል? ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡

በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።

ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።

ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ "መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው" ማድረግ ይቻለን ነበር።

"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።

ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።


"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15

[ዲያቆን አቤል ካሳሁን]
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል:
‹‹መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ፤ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማን ነው?›› (ሮሜ.፰፥፴፭)

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በፍጹም እምነት አምላኩን የሚወድ ቢኖር መራብም፣ መጠማትም፣ መታረዝም፣ መደብደብም፣ መታሰርም ሆነ መገደል ቢሆን ይህንን ፍቅረ እግዚአብሔር የሚለይ ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል በዚህ አንቀጽ አስረድቷል፡፡ ሐምሌ ፭ የሚዘከረውም በዓል ቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ሃይማኖታቸው ምክንያት በሮማው ንጉሥ ኔሮን ሰማዕትነት የተቀበሉበትን በማሰብ ነው፡፡ በየዓመቱ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍትም በዚህ ዕለት ይከበራል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ ከነገደ ሮቤል በእናቱ ደግሞ ከነገደ ስምዖን ወገን ነው፤ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ እናትና አባቱ ‹ስምዖን› ብለው ጠርተውታል፡፡ በግሪክ "ስምዖን"፣ በዕብራይስጥ "ኬፋ" ይባላል፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ‹ጴጥሮስ› ብሎ ጠርቶታል፤ ትርጕሙም ዓለት (መሠረት) ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ልዩ ስሟ ጌንሴሬጥ በምትባል መንደር ዓሣ ያሠግሩ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚተዳደረው በዓሣ አጥማጅነት የነበረ ሲሆን፣ ሰዎችን በወንጌል መረብ እያጠመደ ወደ ክርስትና ሕይወት ይመልስ ዘንድ ጌታችን ለሐዋርያነት ጠርቶታል፡፡ (ሉቃ.፭፥፲፣ማር.፩፥፲፮)

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ነው። ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነበር፤ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ።

ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው።

ቅዱስ ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ ሆኖ ተሹሟል፡፡ ለአገልግሎት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በእስያ፣ በሮም፣ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በገላትያና በሌሎችም አገሮች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በስብከቱ ምክንያትም ልዩ ልዩ መከራን ተቀብሏል፡፡ በክርስቶስ ኀይል በመታመኑ በክርስቶስ ስም ጣቢታን ከሞት አስነሥቷል፤ ይህም አንዱ ድንቅ ተአምራቱ ነው (ሐዋ.፱፡፴፮)፡፡ ከተሰጠው ጸጋ ብዛት የተነሣ በጥላው ሕሙማን ይፈወሱ ነበር (ሐዋ. ፭፥፲፭)፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ሁለት መልእክታትን ጽፏል፡፡ (፩ኛእና ፪ኛ ጴጥሮስ)

የቅዱስ ጴጥሮስ በሰማዕትነት

በቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመን የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፣ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዓወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሀገሪቱ መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሣለ በተገለጸለት ጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› በማለት ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹ዳግም ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው››  በማለት መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር፡፡ ስትሸመግል እጅህን ታነሣለህ፤ ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደ ማትወደውም ይወስድሃል›› በማለት አሟሟቱን የሚያመለክት መሆኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡ (ዮሐ.፳፩፥፲፰) 

ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ ስላልነበረ በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡ እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ  እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይሆን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ስፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ

ቅዱስ ጳውሎስ የጥንቱ ስሙ ‹ሳውል› ይባል ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ በ ፲፭ ዓመት ዕድሜው በገማልያ ትምህርት ቤት በመግባት የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ተምሯል፡፡ በ፴ ዓመቱም የአይሁድ ሸንጎ አባል ሆኗል፡፡ (፩ኛቆሮ.፩.፲፯፣ሐዋ.፳፪.፫) ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር፡፡ በ፴፪ ዓመት ዕድሜውም ከኢየሩሳሌም ሁለት መቶ ሃያ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ ከባለሥልጣናቱ አገኘ፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመሆኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ሁሉ ያሳድድ ነበር፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተደብድቦ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር፡፡ (ሐዋ.፯፥፶፰፣ ፳፪፥፳) ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ከመንገድ ላይ ለሐዋርያነት ተጠርቷል፡፡ (ሐዋ.፱፥፩-፴፩፣፳፪፥፩-፳፩) ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በመላው ዓለም እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኗል፡፡ ሲሰብክም ጣዖት አምላኪ፣ ሕመምተኛ፣ ችግረኛ፣ አረማዊና አይሁዳዊ እየመሰለ ብዙዎችን አስተምሮ ለእግዚአብሔር መንግሥት አዘጋጅቷል:: (፩ኛቆሮ.፱፥፲፱-፳፫) ዐረብ፣ አንጾኪያ፣ እልዋሪቆን፣ ሊቃኦንያ፣ ሦርያ፣ ግሪክና ልስጥራን ካስተማረባቸው አገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ወንጌልን በመስበኩ ምክንያትም ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራና ሥቃይ ደርሶበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ በልብሱ ቅዳጅም ሕሙማን ይፈወሱ ነበር፡፡ (ሐዋ.፲፱፥፲፩) ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ሌላ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ፲፬ መልእክታት አሉት፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነት አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መሆኑን ተረድቶ፣ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡፡ ንጉሡም በቍጣ እንዲሞት ፈረደበት፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ሮማውያን የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የሚቀጣው ሰው የሌላ አገር ዜጋ ከሆነ ከፍርዱ ውጪ ተጨማሪ ቅጣት ይቀጡትና ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የሮም ዜግነት ስለ ነበረው ሳይገርፉ በአንድ ቅጣት ብቻ በሰይፍ እንዲገደል ወስነውበታል፡፡ ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፤ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡
👍2
በገዳዮቹና በተከታዮቹ ፊትም የክርስትና ሽልማቱ የእግዚአብሔር መንግሥት መሆኑን የሚያስገነዝብ ቃል እያስተማረ እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጽድቅ አክሊል ለመቀበል ይቻኮል ነበር፡፡ (፪ኛቆሮ. ፬፥፮-፲፰) ወታደሮች ሊገድሉት ሲወስዱትም ከንጉሥ ኔሮን ወገን የሆነችውን የአንዲት ብላቴና መጐናጸፊያ ‹‹ዛሬ እመልስልሻለሁ›› ብሎ ከተቀበላት በኋላ ‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፡፡ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል›› በማለት ራሱ በመልእክቱ እንደ ተናገረው ፊቱን በብላቴናዋ መጐናጸፊያ ተሸፍኖ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ አገልግሎቱን በሰማዕትነት ፈጽሟል፡፡ (፪ኛጢሞ.፬፥፯-፰)

ደቀ መዛሙርቱም ራሱን ከአንገቱ ጋር ቢያደርጉት እንደ ቀድሞው ደኅና ሆኖላቸው በክብር ገንዘው ቀብረውታል፡፡ ሰያፊው ቅዱስ ጳውሎስን እንደ ገደለው ለመናገር ወደ ንጉሡ ሲመለስም ያቺ መጐናጸፊያዋን የሰጠችው ብላቴና ‹‹ጳውሎስ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ራሱን ተቈርጦ በመጐናጸፊያሽ ተሸፍኖ ወድቋል›› ሲላት ‹‹ዋሽተሃል፤ እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ በኩል አልፈው ሔዱ፤ እነርሱም የመንግሥት ልብስ ለብሰዋል፤ በራሳቸውም በዕንቍ ያጌጡ አክሊላትን አድርገዋል፤ መጐናጸፊያዬንም ሰጡኝ፤ ይህችውም እነኋት፤ ተመልከታት›› ብላ ሰጠቸው፤ ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው፤ አይተውም አደነቁ፤ ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡ ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ጨለማውን ዓለም በማድመቃቸው ‹ብርሃናተ ዓለም› ተብለው ይጠራሉ፤ የቅዱሳኑ አገልግሎት፣ ገድላቸው እና ተአምራቸው በመጽሐፈ ስንክሳር፣ በዜና ሐዋርያት እና በገድለ ሐዋርያት

በሰፊው ተጽፎ ይገኛል፡፡

እኛም በዓለ ዕረፍታቸውን ለማስታወስ ያህል ታሪካቸውን በአጭሩ አቀረብን፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ያቆዩልንን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጠብቀን፣ በክርስቲያናዊ ምግባር ጸንተን እንድንኖር፣ በመጨረሻም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንድንበቃ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

ምንጭ፡-
•  ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፤
•  መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሐምሌ ፭ ቀን፤

ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
🙏2👍1
13. ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ
13. ethiopia hoy tenesh
✞ ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ

ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ ክብርንም ልበሽ
በአዲስ ምስጋና ይሞላ ልብሽ
የተወደደ ነው በእግዚአብሔር ህዝብሽ/2/

ንብረቱ ጠፊ ነው ከንቱ የማይረባ
በግፍና ቅሚያ በአመፅ ሲገነባ
ሲሳይሽ ብዙ ነው ከአምላክ የተስልሽ በረከት ለማግኘት መስራት ነው ጠንክረሽ
/አዝ =====

የአሕዛብ ብልፅግና አያስቀናሽ ፍፁም
ኃላፊ ጠፊ ነው ምኞቱም ዓለሙም
ደመና ነውና ይበናል በቅፅበት
በግፍ የተገኘ የተከማቸ ሀብት
/አዝ =====

ይልቅ በቅንነት በሰላም ለሰራ
ሲሳዩም ብዙ ነው ክብሩም እያባራ
ጉቦና ፍትሕን ማጣመም እንዳንለምድ
ከወንጌሉ ጋር አለብን መዛመድ
/አዝ =====

እግዚአብሔር ያለው ሰው ለእርሱ የታመነ ከግፍ ስራ ሕመም አካላቱ ዳነ
ክርስቲያን ነኝ ብሎ ጉቦ የሚበላ
የሚያቃጥል እሳት ያገኘዋል ኋላ

[ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ]
4
❖ ድንግል ማርያምን ከመጠን በላይ እወዳታለሁ ብለህ አትፍራ የቱንም ያህል ብትወዳት  ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚወዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና ❖ !!!

  [ቅዱስ ማክስሚላን]
👍42
ሥርዓተ ጸሎት

ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” /የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን/ ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡- ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

➜በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

1,በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል
በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/

2, በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል፦ በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል፡፡ ልባችንን የቂም በቀልና የክፋት ምሽግ አድርገን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ “ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመዘርዕ ዘወድቀ ማእከለ አሥዋክ” /የቂመኛ ሰው ጸሎት በእሾህ መካል እንደ ወደቀ ዘርዕ ነው/ /መጽሐፈ መነኮሳት/፡፡

3, ሀሳባችንን ሰብስበን አንድ ልብ በመሆን መጸለይ ይገባል፦ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የጰራቅሊጦስ ዕለት አንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ /የሐ. ሥራ 2፡1-4/

4, በመፍራት ማለት ንስሐ በመግባት ከልብ በመጸጸት መጸለይ ይገባል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/፦ ነቢዩ ሕዝቅያስ በመፍራትና ከልብ በመጸጸት ሆኖ ስለጸለየ በዕድሜው ላይ አሥራ አምስት ዓመት ተጨምሮለታል፡፡ /2ኛ ነገሥት 20፡1-6/ /ኢሳ. 38፡1-5/

5, በጸሎት ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ተሠርቷል
“በጽባሕ እቀውም ቅድሜከ ወአስተርኢ ለከ”/በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እታይሀለሁም/ /መዝ. 5፡3/

6, ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ይገለጽ ዘንድ የተነገረለት ነውና ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

7, በጸሎት ጊዜ መስገድ ይገባል
ይኸውም ጸሎቱን ስንጀምርና ስንጨርስ እንዲሁም በጸሎት ጊዜ ስግደትን ከሚያነሳ አንቀጽ ስንደርስ መስገድ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

8, ጸሎት ስንጀምር በትእምርተ መስቀል /በመስቀል ምልክት/ ማማተብ ይገባል
ስናማትብም ከላይ ወደታች ከግራ ወደ ቀኝ ነው፡፡ ይህም ምሳሌ አለው፡፡ ከላይ ወደታች የምናማትብበት ምክንያት የሰላም አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት የመውረዱ ምሳሌ ነው፡፡ ከግራ ወደቀኝ የምናማትብበት ምክንያት ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ስለእኛ ሞቶ ከሞት ወደ ሕይወት ከኀሣር ወደ ክብር፣ ከሲኦል ወደገነት የመመለሱ ምሳሌ ነው፡፡ በቀኝ ገነት፣ በግራ ሲኦል ይመሰላልና፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

በመስቀል አምሳል የምናማትብባቸው ጊዜያቶችም ጸሎት ሲጀመርና መስቀሉን ከሚያነሳ አንቀጽ ሲደረስ ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

9, ዐይኖችን ወደላይ አቅንቶ መጸለይ ይገባል
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ባስነሳው ጊዜ ዐይኖቹን ወደላይ አቅንቶ እንደጸለየ ሁሉ የሚጸልይ ሰው ዓይኖቹን ወደ ላይ ማንሳት እንዲገባ ነው፡፡ /ዮሐ. 11፡41/

10, ለሌሎችም መጸለይ ይገባል
ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን፤ ለሌሎችም መጸለይ ይገባል፡፡ ኤርምያስ ለሀገር ሰላም መጸለይ እንደሚገባ ‹‹በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ ስለእርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ›› /ት.ኤር. 29፡7/፡፡ ታመው በየሆስፒታሉ፣ በየቤቱ ለሚገኙ ወገኖቻችን፣ በየማረሚያ ቤቱ ላሉ በአጠቃላይ በተለያየ ችግር ለሚንገላቱ ሁሉ መጸለይ ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአገር መጸለይ ይገባል፡፡ “ትድኑም ዘንድ እያንዳንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ” /ያዕ. 5፡16/

ከዚህ ቀጥሎ የጸሎት ጊዜያትን እናያለን

“ስብዐ ለዕለትየ እሴብሐከ” /በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ/ /መዝ. 118፡164/ ሲል ነቢዩ ዳዊት በተናገረው መሠረት በቀን ሰባት ጊዜ መጸለይ እንደሚገባ ታዟል፡፡

ይህም እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

ሰው ከእንቅልፍ ነቅቶ ከመኝታው ተነስቶ ገና ሥራ ሳይጀምር የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ /በነግህ/በ3 ሰዓትበ6 ሰዓትበ9 ሰዓትበ11 ሰዓት /በሠርክ/በመኝታ ጊዜበመንፈቀ ሌሊት /ከሌሊቱ በ6 ሰዓት/

7ቱ የጸሎት ጊዜያት ከላይ የተገለጹት ሲሆኑ በተለይ የጧትና የሠርክ ጸሎት በቤተክርስቲያን መሆን እንዲገባው ታዟል፡፡

የሦስት ሰዓትና የሌሎች ጊዜያት ጸሎት ግን በቤትም ቢሆን በሌላ ቦታ ቢጸለይ አይከለከልም፡፡ ከነዚህ ጊዜያቶች የአንዱ የመጸለያ ጊዜ ቢደርስና የሚጸልየው ሰው ለመጸለይ ከማይችልበት ቦታ ቢሆን በልቡ የሕሊና ጸሎት ማድረስ እንዲገባው ታዟል፡፡

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ሀሳበ ልቡናችንን እንዲፈጽምልንና እንዲሁም ከልዩ ልዩ ፈተናና መከራ እንዲያድነን ሁልጊዜ መጸለይ ይገባል፡፡ ሰው ፈተና፣ መከራ ሲገጥመው ይጨነቃል እንቅልፍ ያጣል እንቅልፉ ጭንቀት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጭንቀት ምንም የሚገኝ ነገር የለም፡፡ ይህንንም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው” /ማቴ. 6፡27/ ሲል ተናግሯል፡፡

ፈተና፣ መከራ ሲገጥመን ተግተን መጸለይ እንጂ መጨነቅ አይገባም፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ “በምንም አትጨነቁ ነገር ግን ጸልዩ እያመሰገናችሁ ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ” /ፊልጵ. 4፡6/ ሲል ተናግሯል፡፡

ይህ ዓለም የፈተና፣ የመከራ ዓለም ነው፡፡ እንደውም በዚህ ዓለም ስንኖር ከደስታው ይልቅ የሚያመዝነው ፈተናው፣ መከራው ነው፡፡ ይህንን ደግሞ የምንቋቋመው በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር በመነጋገር ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተግተን በመጸለይ ከፈተና እንደምንድን ሲገልጽ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ “ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት” /ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ/ /ማቴ. 26፡41/፡፡

በዚህ መሠረት አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከፈተና፣ ከመከራ እንዲያድነን ተግተን እንጸልይ፡፡

ንስሓ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲሁም በቅዱሳን አማላጅነት ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ልዑል እግዚአብሔር ወሰን በሌለው ቸርነቱ ይርዳን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
           
ከላዕከ ወንጌል በእደ ማርያም ይትባረክ /ቀሲስ/።
6👍1
እንኳን ለፈጣሪያችን ለቅድስት ስላሴ አመታዊ በአል በሠላም አደረሠን ።
ሀምሌ ፯☞በዚችም ቀን ልዩየሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የይስሐቅንም ልደት አበሠሩት ባረኩት አከበሩትም። መጽሐፈ ስንክሳር ዘሐምሌ ሰባት ሥላሴ ማለት በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንዳለ ለአበው ለነቢያትና ለሐዋርያት መገለጡን አምነን የምንማረው ትምህርት ነው፡፡ሥላሴ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስት፤ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ የአንድ አምላክ በሦስትነት መገለጥን ለመረዳት በኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 ላይ በተገለጠው መሠረት “እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌችን እንፍጠር” ይላል፤ ይህ አገላለጽ “እግዚአብሔርም አለ” ሲል አንድነትን (አንድነታቸውን) “እንፍጠር” ሲል ከአንድ በላይ (ሦስትነትን) መሆንን ያስረዳል፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት 3፡22 ላይ “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” የሚለው አገላለጽ ከአንድ በላይ መሆንን የሚያስረዳ ነው፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት 11፡5-7 የተጠቀሰው “ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቅ”በማለት ሥላሴ የተናገሩት ከአንድ በላይ (ሦስትነት) መሆንን የሚያመለክት ነው፡፡በኦሪት ዘፍጥረት18 ላይ ሥላሴ ለአብርሃም እንደተገጹለት የሚያስረዳ ሀሳብ የያዘ አገላለጽ ሲሆን ሥላሴ ለአብርሃም በመገለጻቸው አብርሃም ሥላሴን በእንግድነት አሰተናግዷል፡፡የሥላሴ ባለሟል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በእርግናው ጊዜ ልጅ እንደሚያገን ተበስሮለታል፡፡ ዘሩ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ እንደሚበዛ በሥላሴ ቃል ተገብቶለታል፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጠመቅበት ጊዜም የሥላሴ ምስጢር ተገልጧል፡፡ “እግዚአብሔር አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው” ሲል እግዚአብሔር ወልድ ሲመጠቅ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ማቴ.3፡13 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን ሂዱና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀመዛሙርቴ አድርጉ” ማቴ. 14፡28 ሲል ሦስትነት የሚገልጽ መልእክት አስተላልፏል።እንግዲህ ሥላሴ ስንል በስም፣ በአካል፣ በግብር የተለዩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ይኸውም፡-የአካል ሦስትነት፡- አብ የራሱ መልክ፣ ገጽ፣ አካል አለው፡፡ወልድ የራሱ መልክ፣ ገጽ፣ አካል አለው፡፡መንፈስ ቅዱስ፡- የራሱ መልክ፣ ገጽ አካል አለው፡፡የስም ሦስትነት ስንል፡- የአንዱ ስም ለአንዱ የማይሆን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በመባል ይጠራሉ፡፡ የግብር ሦስትነት ስንል፡- አብ ወላዲ፣ አስራጺ ሲሆን ወልድ ተወላዲ ነው የተወለደውም ከአብ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ነው፡፡ የሰረጸውም ከአብ ነው፡፡ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡ በዓለ ሥላሴ በዓላት የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተደረገለትን የቸርነት ሥራ በማሰብ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎና ተአምራት በመስማትና በማሰማት የተደረገውን ድንቅ ነገር በመዘከር በደስታ የሚከበሩ ዕለታት ናቸው፡፡

☞የዛሬው ሐምሌ 7 ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ አብርሃምን የባረኩትና ልጅ እንደሚወልድ፣ መጻዒው ሕይወቱን የነገሩት ዕለት ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ቸርነታቸው፣ ፍቅራቸው፣ ትድግናቸው እንዳይለየን እንማጸናለን፡፡ የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
2👏1
#በቅዱስ_ኤፍሬም

ተወዳጆች ሆይ ኑ አባቶቼና ወንድሞቼ እግዚአብሔር ለርስቱ ለመንግሥቱ የለያችሁ ምእመናን ሆይ ኑ፡፡ የልጅነትን ማኅተም ያለባችሁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆይ ኑ፡፡ ልጆቼ ይኽን ለነፍሳችን ድኅነት እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ትምህርት ትማሩ ዘንድ ኑ፤ ጊዜ ሳለልን እንመካከር ዘንድ ኑ፡፡ ኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ነፍሳችንን እንገዛት ዘንድ እንቻኮል፡፡

ዓይነ ልቡናችን ብሩህ ይኾን ዘንድ ኑ በዕንባ እንታጠብ (እናልቅስ)፡፡ ባለጸጋዉም ድኻዉም፣ ልዑላንም ሕዝቦችም፣ ወጣቶችም ጐረምሶችም፣ ሽማግሎችም ሕፃናትም፣ በአጣቃላይ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ከምረረ ገሃነም መዳን የምትሹ ሁላችሁም ኑ፡፡

ከክቡር ዳዊት ጋር ሆነን ምሕረቱ የበዛ ባለጸጋውን እግዚአብሔርን “ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ" አቤቱ ፈጣሪዬ ልመናዬን ሰምተኽ በዓይነ ምሕረትህ እየኝ፤ ተመልከተኝ፡፡ "አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢኑማ ለመዊት" የሞት እንቅልፍ እንዳያንቀላፉ ዓይኖቼን አብራቸው” ብለን እንለምነው /መዝ.13፥3-4/፡፡ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን እንደነበረው እንደ ዓይነ ስዉሩ ሰውም፡- “ተሣሃለኒ ኢየሱስ ወልደ ዳዊት" የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ” ብለን እንጩኽ/ማር.10፥48/፡፡ ዝም እንል ዘንድ የሚቈጡን ቢኖሩም እንደ በርጠሜዎስ ልጅ እንደ ጠሜዎስ ዓይነ ልቡናችንን እስኪያበራልን ድረስ አብዝተን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንጩኽ፡፡ ስለዚኽ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፤ ብሩህ ልቡናንም ገንዘብ እናድርግ፡፡ ገጻችንም ከቶ አያፍርም፡፡ ኑ! ሃይማኖትንና ምግባርን አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማያትን ለመያዝ እንሩጥ። ይኽን ያደረግን እንደኾነም የዚህ ዓለም ነገር ከንቱ ሆኖ ይታየናል፡፡

ስለዚህ ራሳችንን ንቁ እናድርግ፤ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ብንመጣም አይዘጋብንምና ኑ እንፍጠን፡፡ ምሽቱ ቀርቧል፤ ለኹሉም እንደየሥራው የሚከፍለው ልዑለ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊመጣ ነው ፡፡
👍82
ክርስቲያናዊ ሕይወት

ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ሕይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል” [1ዮሐ 2፡16] በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ [ተረግሞ] የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ [እንደ ተፈታ]፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡

የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” [ማቴ 16፡18] በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በሕያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡

ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት [ኢሳ 8፡16] ፤ ወንድሞች [ማቴ 8፡10] የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ [የሐዋ 11፡26]

በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በሕይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የሕይወት ምንጭ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚአብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከከንቱ ዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ [እግዚአብሔር የለም] ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡

እግዚአብሔርን ማወቅ፡-
●ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል


በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሔርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ሕይወት ነበር፤ አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” [ሉቃ 19 ፤9] በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡

●ታሪክን ይቀይራል

ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡

2.  በዕምነት ማደግ
ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው”

3. በእግዚአብሔር ፍቃድ መኖር
እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡[የሐ2፡17] የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”[ሉቃ22፡42] ምክንያቱም ሐዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል [ፊሊ1፡13]

4. እግዚአብሔርን መምሰል
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት በአገልግሎት ሲቆይ በርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ  እናንተም እንዲሁ አድርጉ[ዮሐ13፡14] [ምንም እንኳን መልካምነት የባህርይው ቢሆንም] በማለት ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው መጽሐፍ ያስተምረናል ፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ”[1ኛቆሮ 11፡1] በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬ በማድረግ የሥጋን ሥራ በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡[ገላ 5፡18] ይህንን በማድረግ ቅዱሳን ቅድስናን ገንዘብ አድርገዋል፡፡ “እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል”[2ጢሞ 4፡8]።

5. ፍቅር ሊኖረን ይገባል
በክርስትና መጀመሩያውም መጨረሻውም ፍቅር ነው፡፡ ምክንያቱም “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” [1ዮሐ 4፡8] በመሆኑም ያለ ፍቅር ክርስትና የለም፡፡ቢኖር እንኳን ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ከንቱ ነው “ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ”[1ቆሮ 13፡1]።

6. ከመስቀሉ መካፈል
የጠፋውን በግ ፍልጋ ራሱን ባዶ ያደረገው ክርስቶስ [ፊሊ 2፡8] ድሉ በመስቀል ስለ ተጠናቀቀ ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ከመስቀሉ ተካፋይ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ከመስቀሉ ስር የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን መውሰድ፤ የተቆረሰውን ቅዱስ ሥጋ መብላት፤ የፈሰሰውን ክቡር ደም መጠጣት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ [ዮሐ 19፡27፤ ዮሐ 6፤56] ይህ ሁሉ ሲሆን ለዘለዓለም በሕይወት እንኖራለን ማለት ነው፡፡

ስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን!!!
👍52
“ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።”
— ምሳሌ 16፥32
👍53
#ጸሎታችን_የማይሰማው_ለምንድን_ነው?”
ክቡር ዳዊት ሲናገር፡- “እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል” ብሏል (መዝ.4፡3)፡፡ በዚህ መነሻነትም፡- “ታዲያ ብዙ ሰዎች ጸሎታቸው የማይሰማው ለምንድን ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነዚህ ሰዎች የማይጠቅማቸውን ጸሎት ስለሚጸልዩ ነው፡፡ አዎ! በዚህ ጊዜ ጸሎታቸው ባይሰ’ማ ለእነርሱ በጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር የማይረባንን ነገር በለመንነው ጊዜ፥ ልመናችንን የሚሰማ ቢኾን ኖሮ ጸሎታችን በመሰማቱ ብቻ ደስ ባልተሰኘን ነበርና፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን ተጣርተን ባልሰማን ጊዜ እናመስግነው፡፡ የማይረባንን ነገር ለምነነው ጸሎታችን ከሚሰማን ባይሰማን ይሻለናልና፡፡

አንዳንድ ጊዜም ጸሎታችን በግድየለሽነት የሚቀርብ ከኾነ፥ እግዚአብሔር መልሱን ያዘገይብናል፡፡ ለምን? ከልብ የመነጨ ጸሎት እስክናደርስ ድረስ! ይህ በራሱ ለእኛ የሚሰጠው በቁዔት ቀላል አይደለምና፡፡ መጽሐፍ እንዳለ “እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥” ከእናንተ በላይ የስጦታን ምንነት፣ መቼ መስጠት እንደሚገባ፣ ምን መስጠትም እንዳለበት የሚያውቅ እግዚአብሔርም መስጠት ያውቅበታል (ማቴ.7፡11)፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕ ጳውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ እግዚአብሔር ጸሎቱን ያልሰማው! ለዚህም ነው የተወደደ ሙሴ “ፊትህን አሳየኝ” ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው! ስለዚህ እኛም ጸሎታችን ባይሰ’ማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ፡፡ ልል ዘሊል ኾነን ጸልየን ከኾነም ልል ዘሊልነታችንን አስወግደን እንጸልይ እንጂ ድኩማን አንኹን፡፡ እንደዚህ አድርገን ጸልየን ሳለ ጸሎታችን ባይሰ’ማ ግን አምላክ የሚያደርገው ኹሉ ለጥቅማችን ነውና በፍጹም አንዘን፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
👍2
ውግዘት

አውጋዡም ተወጋዡም ተያይዘው ገደል የገቡ ናቸው። ምንም አዱስ ነገር አትጠብቁ። ሁለቱም ቀኖና ጥሰዋል።

ኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰቦች ስም ከገባችበት ጣጣ አትድንም። አዲስ ኢትዮጵያን መስራት ብቻ ነው። ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚመጥን ከሐዋርያት ቀኖና ፈቀቅ ያላለ ሲኖዶስ መፍጠር ግዴታ ነው።

የኦሮሚያውም፣ የመቀሌውም፣ የነገውም የወደቁ ናቸው። ሐዋርያትን ያልመሰለ ሲኖዶስ አልቀበልም። መለካዊነት ከበላው በሽ መልስ አብዲሳ ትእዛዝ የሚንቀሳቀስ በዐቢይ አማላጅነት የምታረቅ የወደቀ ነው። እናም ለአዲሱ የሲኖዶስ ምስራታ ራስህን አዘጋጅ።

[መ/ር ንዋይ ካሳሁን]

እስኪ በመድኃኔዓለም ስለ ቤተክርስቲያን በጸሎት ትጉ።
🙏6👍2
ክርስቲያናዊ ፍፁምነትን የምትፈልግ ከሆነ ሕሊናህንና ነፍስህን ከማይጠቅም ወሬ መጠበቅ አለብህ። የእግዚአብሔር ቃላት የነፍስን ሙቀት ያድሳሉ። እንድታድግ ከፈለግህ የእግዚአብሔርን ቃላት እንደ ህጻን ልጅ መጥባት አለብህ።

ዕለተ ሰንበት የዕረፍት ቀን ናት ሲባል  በደዌ እንደተያዘ ሰው ከአልጋ ተጣብቀህ ተኝተህ አትዋል። መልካም ሥራ ስራባት እንጂ።

[ቅዱስ አትናቴዎስ]
👍94
_ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፲፭__
አንቀጽ ፲፱ ስለ ዕለተ እሑድና ስለ ቅዳሜ እንዲሁም ስለበዓላተ እግዚእ ይናገራል።
፩) ክርስቲያኖች እንደ አይሁድ በዕለተ ቀዳሚት ሥራ ፈትተው መዋል አይገባቸውም። በዕለተ ቀዳሚት እንደ ክርስቲያን ሥራ ይሥሩ እንጂ። (ሐተታ) የታመመ መጠየቅ፣ የሞተ መቅበር ይገባልና።
                _
፪) በዕለተ እሑድ፣ በዕለተ ቅዳሜ፣ በክቡራን በዓላት ስግደት አይገባም። የተድላ የደስታ ዕለታት ናቸውና። ይህ አንቀጽ ውግዘት የሌለበት ነው። ባሕታዊ ፆር ተነስቶበት ቢሰግድ ዕዳ የለበትምና።
                _
፫) በዕለተ እሑድ ፍርድ ቤት አይሂዱ። እሑድ ቀን አያሟግቱ አያፋርዱ። በእሑድ ቀን ማንም ማን ገንዘቤን አምጣ ብሎ አይያዝ። ሁሉም ወደ ቤተክርስቲያን ይሂዱ እንጂ። ምእመናንም ዳኛ ግብሬን፣ አበዳሪ ብድሬን፣ ኤጲስ ቆጶስ አሥራት በኩራት፣ ነጋድራስ ቀረጥ አምጡ ይለናል ብለው ሳይፈሩ በንጽሕና በትህትና ሁነው ወደ ቤተክርስቲያን ይምጡ።
                _
፬) በዕለተ እሑድ ከነጋድራሶች አንዱስንኳ ወደቤተክርስቲያን ከሚሄዱ ሰዎች ቀረጥ ይቀበል ዘንድ የድፍረት ሥራ የሠራ ቢሆን እጥፍ አድርጎ ይክፈል።
                _
፭) ሁልጊዜ በቤተክርስቲያን ተሰብሰቡ። ይልቁንም በዕለተ እሑድና በዕለተ ሰንበት እንዲሁም በጌታ በዓላት ወደ ቤተክርስቲያን ተሰብሰቡ።
                _
፮) ጥቅም የሌለው ነገር አትናገሩ። የማይገባ ሥራም አትሥሩ።
                _
፯) ባሮች (የቤት ሠራተኛዎች) አምስቱን ቀን ሠርተው ቅዳሜና እሑድ ግን የእግዚአብሔርን አንድነቱን ሦስትነቱን ይማሩ ዘንድ ከቤተክርስቲያን ሆነው ይዋሉ።
                _
፰) ቅዳሜ መከበሯ ጌታ ፍጥረትን ከመፍጠር አርፎባታልና ነው። እሑድ መከበሯ ደግሞ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶባታልና ነው።
                _
፱) የጌታ ዐበይት በዓላት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው (ዐቢይነታቸው በአከባበራቸው ነው):-
         √ በዓለ ጽንሰት (ትስብእት) መጋቢት ፳፱
         √ በዓለ ልደት (ታኅሣሥ ፳፱)
         √ በዓለ ጥምቀት (ጥር ፲፩)
         √ በዓለ ሆሣዕና
         √ በዓለ ትንሣኤ
         √ በዓለ ዕርገት
         √ በዓለ ጰራቅሊጦስ
         √ በዓለ ደብረ ታቦር (ነሐሴ ፲፫)
         √ በዓለ ስቅለት
፲) የጌታ ንዑሳት በዓላት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው
        ® መስቀል (መስከረም ፲፯ & መጋቢት ፲)
        ® ስብከት
        ® ብርሃን
        ® ኖላዊ
        ® ጌና (ታኅሣሥ ፳፰)
        ® ግዝረት (ጥር ፮)
        ® ልደተ ስምዖን (የካቲት ፰)
        ® ደብረ ዘይት
        ® ቃና ዘገሊላ (ጥር ፲፪)
፲፩) የልደትና የጥምቀት ቁርባን በመንፈቀ ሌሊት ይሁን። ይኽውም ስለ ክብረ በዓሉ ነው።
                _
፲፪) የትንሣኤን በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ አታክብሩ። እኛን ለማዳን አንድ ጊዜ ስለሞተ በዓመት አንድ ጊዜ አክብሩ እንጂ። የትንሣኤን በዓል በዕለተ እሑድ እንጂ በሌላ ቀን አታክብሩ። በዶሮ ጩኽት ብሉ። ያም ባይሆን በነግህ ብሉ።
                _
፲፫) መዓርገ ቁርባን አምስት ናቸው። እነዚህም:-
  √ የትንሣኤ፣የልደት፣የጥምቀት ሌሊት በ፲ ሰዓት
  √ በዓለ ኃምሳ እና ቅዳሜ ጠዋት ፫ ሰዓት
  √ እሑድ ጠዋት ፩ ሰዓት
  √ በሰባቱ አጽዋማት በ፱ ሰዓት
  √ የጸሎተ ኃሙስ በሠርክ (፲፪ ሰዓት)
፲፬) በበዓላት ጊዜ በቤተክርስቲያን ተሰብስባችሁ መጻሕፍተ ነቢያትን ኦሪትን እያነበባችሁ፣ ዳዊት እየደገማችሁ አቡነ ዘበሰማያት እያላችሁ ጸልዩ። ለምእመናኑ ሊድኑበት የሚገባውን ንገሯቸው።
                _
፲፭) ከትንሣኤ በኋላ በስምንተኛው ቀንም በዓል አክብሩ (ዳግማይ ትንሣኤን ነው)።
                _
፲፮) ከሰሙነ ሕማማት እስከ ሰሙነ ትንሣኤ (እስከ ዳግማይ ትንሣኤ) አንድ በዓል ነውና ሥራ አትሥሩ።
                _
፲፯) ሐዋርያት ባረፉበት ቀን ሥራ አትሥሩ። ሐዋርያት ክርስቶስን ለማወቅ ያስተማሯችሁ መምህሮቻችሁ ናቸውና። ሀብተ መንፈስቅዱስንም ለመቀበል አብቅተዋችኋልና።
                _
፲፰) የተቻለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶድ በሰውነቱ መከራ የተቀበለባቸውን መካናት እጅ ይንሣ። የተነሣበትንም ቦታ ይይ። አምላክ በሠራቸው ግብራት ይከብር ዘንድ። (ሐተታ) መካነ ልደቱን አይቶ በረከተ ልደቱን፣ መካነ ጥምቀቱን አይቶ በረከተ ጥምቀቱን፣ መካነ ትንሣኤውን አይቶ በረከተ ትንሣኤውን ያገኛልና። ለመሄድ የማይቻለው ግን መብዓ ይስደድ። በዚያው የሚኖሩ ሰዎች ይረዱበት ዘንድ።
                                _
                         አንቀጽ ፳
አንቀጽ ፳ ስለ ሰማዕታት ይናገራል።
፩) ሰማዕታት በእናንተ ዘንድ የከበሩ ይሁኑ። በጌታ ስም ስላመነ በሃይማኖት ስለፀና ወደ መከራ ሥጋ የሚያገቡት ክርስቲያናዊን ከመርዳት ቸል አትበሉ። ምንም የሌላችሁ ብትሆኑ እንኳ ስለእነርሱ እናንተ ግማሽ እየበላችሁ የምግባችሁን ግማሽ ስጧቸው።
                _
፪) ሰማዕታት የክርስቶስ የመከራው ተሳታፊዎች፣ የመንፈስቅዱስ ማደሪያዎች ናቸው። የሰማዕታት ምስክራቸው ክርስቶስ ነው። ሰማዕታትን ከሚረዳቸው ሰዎች አንዱን መከራ ቢያገኘው ንዑድ ክቡር ይባላል። የሰማዕታት የመከራቸው ተባባሪ ሆኗልና። ክርስቶስን መስሎታልና።
                _
፫) ሃይማኖት አንለውጥም ስላሉ ከሀገር አስወጥተው የሚሰዷቸውን (የሚያሳድዷቸውን) ተቀብላችሁ ከረኀብ ከጥም አሳርፏቸው። በተቀበላችኋቸው ጊዜ ደስ ይበላችሁ።
                _
፬) ጌታ በዚህ ዓለም መከራ ኀዘን ያገኛችኋል ብሎናል። እስከመጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል። ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን የወደደ ሰው ይቅርታውን አያገኝም። የሰው ወዳጅ የእግዚአብሔር ጠላት ሊሆን ወዷልና።
                _
፭) ሥጋችሁን የሚገድሉትን ሰዎች አትፍሯቸው። ነፍሳችሁን ግን መግደል አይቻላቸውም። ይህንን ዓለም አትውደደው። በሰው መመካትን ተው። ከአለቆች ውዳሴ ከንቱን አንቀበል።
                _
፮) ለሌሎች ሰዎች የክህደት አብነት እንዳንሆን ወንድሞቻችንን በሃይማኖት በምግባር እናጽናቸው። በመከራ ብንጨነቅ በኃላፊው ዘመን የሚሆነውን መከራ ፈርተን ሃይማኖታችንን አንለውጥ።
                _
፯) ሰው አምኖ ሳይጠመቅ መከራ ቢደርስበት አይዘን። በክርስቶስ ስም አምኖ የተቀበለው መከራ የተወደደ ጥምቀት ይሆንለታልና። እስመ ተጠምቀ በደሙ (ለክርስቶስ) እንዲል።
                _
፰) ዓላውያንን ፈርቶ በግድ የካደ ሰው ቢኖር በኋላ ንስሓ ቢገባ ንስሓውን ይቀበሉት። ካህን ከሆነም ቅዳሴ ከመግባት አይከልከል። ይህን ወዶ አላደረገውምና። መከራ ሳያጸኑበት ገንዘቡን ሳይወስዱበት ፈርቶ አስቀድሞ የካደ ቢኖር ብዙ ዘመን በንስሓ ይኑር። ከዚያ በፍጹም ልቡናው ቢመለስ ሥጋውን ደሙን ሊቀበል ቢወድ ያቀብሉት።
👍53
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ስለ_ቤተክርስቲያን

"አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ ትበልጣለች ቢል አልተሳሳተም፡፡ የኖኅ መርከብ እንስሳትን ወደ ውስጥዋ ብታስገባም እንስሳት አድርጋ ጠበቀቻቸው እንጂ አልለወጠቻቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን እንስሳትን ትቀበላለች፤ ትለውጣቸውማለች፡፡ ለምሳሌ ወደ ኖኅ መርከብ ቁራ ገባ፤ የወጣውም ግን ቁራ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ገባ፤ የወጣውም ግን ያው ተኵላ ኾኖ ነው፡፡ እዚህ ቤተ ክርስቲያን ግን አንድ ሰው እንደ ቁራ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ ርግብ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ በግ ኾኖ ነው፡፡ እንደ እባብ ኾኖ ቢመጣ የሚወጣው እንደ ጠቦት በግ ኾኖ ነው፡፡ ተፈጥሮው ወደዚያ ስለሚለወጥ ግን አይደለም፤ ክፋቱ ስለሚርቅለት እንጂ፡፡ ስለ ንስሓ አብዝቼ የማስተምረውም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ንስሐ)

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

"ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ ኃጢአትህንም አርቃት፡፡ በአደባባይ የምትወድቀው ቊጥሩ ከምትነሣው ጋር እኩል ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ በደል ኃጢአት የምትሠራውን ያህልም ፍጹም ተስፋ ሳትቈርጥ ንስሐ ግባ፡፡ ኹለተኛ ብትበድል ኹለተኛ ንስሐ ግባ፡፡ በስንፍና ተይዘህ በፍጹም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለኝም አትበል፡፡ በእርግና ዘመን ብትኾንና ብትበድልም እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡ እዚህ ስትመጣ ካህናት [“እግዚአብሔር ይፍታሕ” ብለው] ከኃጢአት እስራት ፈትተው ይቅርታ ይሰጡሃል እንጂ “ለምን በደልህ?” ብለው አይፈርዱብህምና፡፡ ስለዚህ፡- “አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ ኃጢአትህም ይቀርልሃል (መዝ.50፡4)፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
2👍1
Track 10
Unknown artist
Ethiopian Orthodox Mezmur

🏷 አላዝን አልከፋ እኔ

🎙 ዘማሪት እንቁስላሴ||


አላዝን አልከፋ እኔ አላለቅስም እኔ
አላዝን አልከፋ እኔ አላለቅስም እኔ
መጽናኛዬ አለኝታዬ እያለ መድህኔ
መጽናኛዬ አለኝታዬ እያለ መድህኔ

ማቀርቀሬ መተከዜ
ተስፋ መቁረጥ መቅበዝበዜ
ለቅሶ ሀዘን ሁሉም አልፏል
በወደድከኝ ልቤ አርፏል

በማይጥለው በመዳፍህ
በሚሞቀው በእቅፍህ
አደላድለህ ይዘኸኛል
ሳታቆስል ማርከኸኛል

ያልፈረድከው በድካሜ
ፈውስ የሆንከኝ ለህመሜ
የማላጣህ እድሌ ነህ
ለዘላለም የማመልክህ

ሳትጸየፍ ተቀበልከኝ
ነጩን በፍታ አለበስከኝ
ልጄ አያልክ አቅፈኸኛል
ላትጠላኝ ወደኸኛል


@nshachannel
@nshachannel
4
ተወዳጆች ሆይ ኑ አባቶቼና ወንድሞቼ እግዚአብሔር ለርስቱ ለመንግሥቱ የለያችሁ ምእመናን ሆይ ኑ፡፡ የልጅነትን ማኅተም ያለባችሁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆይ ኑ፡፡ ልጆቼ ይኽን ለነፍሳችን ድኅነት እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ትምህርት ትማሩ ዘንድ ኑ፤ ጊዜ ሳለልን እንመካከር ዘንድ ኑ፡፡ ኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ነፍሳችንን እንገዛት ዘንድ እንቻኮል፡፡

ዓይነ ልቡናችን ብሩህ ይኾን ዘንድ ኑ በዕንባ እንታጠብ (እናልቅስ)፡፡ ባለጸጋዉም ድኻዉም፣ ልዑላንም ሕዝቦችም፣ ወጣቶችም ጐረምሶችም፣ ሽማግሎችም ሕፃናትም፣ በአጣቃላይ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ከምረረ ገሃነም መዳን የምትሹ ሁላችሁም ኑ፡፡

ከክቡር ዳዊት ጋር ሆነን ምሕረቱ የበዛ ባለጸጋውን እግዚአብሔርን “ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ" አቤቱ ፈጣሪዬ ልመናዬን ሰምተኽ በዓይነ ምሕረትህ እየኝ፤ ተመልከተኝ፡፡ "አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢኑማ ለመዊት" የሞት እንቅልፍ እንዳያንቀላፉ ዓይኖቼን አብራቸው” ብለን እንለምነው /መዝ.13፥3-4/፡፡ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን እንደነበረው እንደ ዓይነ ስዉሩ ሰውም፡- “ተሣሃለኒ ኢየሱስ ወልደ ዳዊት" የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ” ብለን እንጩኽ/ማር.10፥48/፡፡ ዝም እንል ዘንድ የሚቈጡን ቢኖሩም እንደ በርጠሜዎስ ልጅ እንደ ጠሜዎስ ዓይነ ልቡናችንን እስኪያበራልን ድረስ አብዝተን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንጩኽ፡፡ ስለዚኽ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፤ ብሩህ ልቡናንም ገንዘብ እናድርግ፡፡ ገጻችንም ከቶ አያፍርም፡፡ ኑ! ሃይማኖትንና ምግባርን አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማያትን ለመያዝ እንሩጥ። ይኽን ያደረግን እንደኾነም የዚህ ዓለም ነገር ከንቱ ሆኖ ይታየናል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ንቁ እናድርግ፤ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ብንመጣም አይዘጋብንምና ኑ እንፍጠን፡፡ ምሽቱ ቀርቧል፤ ለኹሉም እንደየሥራው የሚከፍለው ልዑለ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊመጣ ነው፡፡

/#ንስሐ - #በቅዱስ_ኤፍሬም /
ተአምረ ቅዱስ ሚካኤል

➡️ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን በዚህች ዕለት የመላእክት ሁሉ አለቃቸው: የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም በሆነ ተአምር ከከተማው #ኢየሩሳሌም ጋር ታድጐታል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ከመድኃኒታችን #ክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት በፊት #ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር::ደጋጉ #ዳዊትና #ሰሎሞን ካረፉ በሁዋላ የሕዝቅያስን ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም ነበር::

ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::

"እገብርልሃለሁ:: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ሃገሬን ግን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል:: ሕዝቤንም አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት::

➡️ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ : ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም #እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::

መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ #ቅዱስ_ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ #ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::"

➡️በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል::

በድንጋጤ ወደ #ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13,
2025/07/13 03:47:55
Back to Top
HTML Embed Code: