Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
998 - Telegram Web
Telegram Web
©....ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ.....©

ዲያቆኑ በቅዳሴ መካከል ከሚላቸው አንዱ ነው።ምሥራቅ የማኅደረ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው።አንድም የጌታችንን ነገረ ምጽአቱን አስቡ ሲል ነው።በቅዳሴ ጊዜ ሌላ ዓለማዊ ሀሳብ ልናስብ አይገባም።ከመላእክቱ ጋር እግዚአብሔርን እያመሰገንን መሆኑን መዘንጋት የለብንም።በሥጋ ከቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን በሀሳብ ግን ሌላ ቦታ ልንሆን አይገባም።ነገራተ እግዚአብሔርን በቅዳሴው ሰዓት የሚነበቡ የወንጌል እና የሐዲሳት እንዲሁም የመልእክተ ጳውሎስ ክፍላትን እንዲሁም አጠቃላይ ካህኑ ዲያቆኑ የሚለውን እኛም የምንመልሰውን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። ለተመስጦ እንዲረዳን ግእዝ ቋንቋውን እንወቀው። እያንዳንዱ የሚደረገው ድርጊት ምሳሌ እና ምሥጢር ስላለው ያንን ጠይቀን ተምረን እንወቀው።
                         
ከቅዳሴ በፊት መሥዋእቱ የሚዘጋጅባት ቤት ቤተልሔም ትባላለች።ቤተልሔም ከዋናው ሕንጻ ቤተክርስቲያን በስተምሥራቅ የምትገኝ ስትሆን ምሳሌነቷ ክርስቶስ ለተወለደባት ቤተልሔም ነው።ከዚያ ከቤተልሔም ወደ መቅደስ ይሄዳል።መቅደስ የቀራንዮ ምሳሌ ነው።የቤተክርስቲያን ውስጠኛዋ ክፍል መቅደስ ትባላለች።በቀራንዮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም እንደፈሰሰ ሁሉ።በዚች መቅደስም የክርስቶስ ሥጋ እና ደም የሚፈተትባት ናትና።ከዚያ ቀጥላ ያለችዋ መካከለኛዋ ክፍል እና ሥጋ ወደሙ የምንቀበልባት ደግሞ ቅድስት ትባላለች።ሊቃውንት ማኅሌት የሚቆሙባት እና መጀመሪያ እንደገባን የምናገኛት ክፍል ደግሞ ቅኔ ማኅሌት ትባላለች።
                             
ከቅዳሴ በፊት ልዑካኑ እንዲሰበሰቡ የሚደወለው የተጋብኦ ደወል ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል እያሉ ያስተማሩ የቅዱሳን ነቢያት ምሳሌ ነው።ኖኅ በቀን ሦስት ጊዜ ደወል ይደውል ነበር።ይኽውም ጠዋት ለጸሎት ተነሱ ለማለት፣ ከሰዓት ደግሞ የምሳ ሰዓት ደረሰ ለማለትና በሠርክ ደግሞ መሥዋእት ለማሳረግ ነበር። #የግብር ደወል ማለትም ገና ቅዳሴ ሲጀመር የሚደወለው ሲሆን የብሥራተ ገብርኤል ምሳሌ ነው። #የወንጌል ደወል የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት ምሳሌ ነው። #የእግዚኦታ ደወል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ምሳሌ ነው። #የድርገት ደወል የሐዋርያት የ፸፪ቱ አርድእት ስብከት ምሳሌ ነው።ምሳሌነቱ እያሰብን ልናስቀድስ ይገባናል።
                          
ጻኡ ንኡሰ ክርስቲያን የሚለው በምጽአት ጊዜ ጌታችን ኃጥዓንን ሑሩ እምኔየ የሚላቸው የመዓቱ ምሳሌ ነው።ወንጌል ከተነበበ በኋላ መጋረጃው (መንጦላእቱ) ይዘጋል። ይኽውም ከምጽአት ፍርድ በኋላ ምንም ዓይነት ምሕረት እንደሌለ የሚያሳይ ምሳሌ ነው።ጌታችን በቸርነቱ በቀኙ ከሚቆሙት ጋር ያቆመን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
5🙏2👍1👏1
© ......ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን...... ©

ንኡሰ ክርስቲያን የሚላቸው የሃይማኖት እና የምግባር ተብለው ይከፈላሉ።የሃይማኖት የተባሉት ሳይጠመቁ እድሜያቸው ትልቅ የሆኑ ሰዎች ወደ ትክክለኛዋ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሲመጡ አዕማደ ቤተክርስቲያንን እየተማሩ እስከ 3 ዓመት ይቆያሉ። በዚህ በሦስት ዓመት ውስጥ ቅዳሴ እስከ ፍሬ ቅዳሴ ድረስ ይቆዩና ፍሬ ቅዳሴ ሲጀመር ንኡሰ ክርስቲያን የሆናችሁ ውጡ ይባሉና ይወጣሉ። ይኽውም በዚሁ በሦስቱ ዓመት ውስጥ ነው እንጂ ከተጠመቁ በኋላ አይደለም።ከፍሬ ቅዳሴ በፊትስ ለምን ይቆያሉ ቢሉ ከዚያ በፊት ያለው የቅዳሴ ክፍል በስፋት ትምህርት ያለበት ነው።እንዲማሩ ነው።ከፍሬ ቅዳሴ በኋላ ግን የተጠመቁት ብቻ የሚቀበሉት ቁርባን የሚፈተትበት ስለሆነ ሙሉ በሙሉ አምነው ተጠምቀው እስኪመጡ ድረስ አይቆዩም።
                         
ሁለተኛው ንኡሰ ክርስቲያን የሚባሉ የምግባር ናቸው።የተጠመቁት ምእመናን ኃጢኣታቸውን ለመምህረ ንሥሓቸው ነግረው ንሥሓ አባታቸው በቀኖና እስከዚህ ቀን ድረስ በበረሀ ሁናችሁ እስከዚህ ቀን ድረስ በአጸደ ቤተክርስቲያን ሆናችሁ እያስቀደሳችሁ ስትጨርሱ ከቤተክርስቲያን ገብታችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚባሉት ናቸው። በበደሉት በደል ምክንያት ለተወሰኑ እለታት በቀኖና ቤተክርስቲያን  እንዳይገቡ የሚከለከሉ ንኡሰ ክርስቲያን ይባላሉ።
                             
መጋረጃ ወይም መንጦላእት የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው። የቤተክርስቲያን ሦስቱ በሮች የሦስቱ ሥላሴ ምሳሌ ናቸው። ደጀ ሰላም የምትባለው በምዕራብ አቅጣጫ ከመግቢያ በር ላይ የምትገኝ ቤት ናት።ምሳሌነቷ የገነት ነው። ቀሳውስት ደጀሰላም ትንሽ ቆይተው ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡ ቅዱሳንም እስከ እለተ ምጽአት ድረስ በገነት ቆይተው በኋላ በክብር ወደምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት የመግባታቸው ምሳሌ ነው።ሌላው በቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ የሚደረገው የሰጎን እንቁላል የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው።ምሳሌነቱም እንዲህ ነው።ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈሉ ድረስ አትለያቸውም። ምግቧን ለመፈለግ ስትሄድ እንኳ ባሏን ተክታ ነው። ለአንድ አፍታ ከእይታ ውጭ ካደረገቻቸው ግን እንቁላሉ ይበላሻል።ሰጎን የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው። እንቁላሎቹ የምእመናን ምሳሌ ናቸው። መንፈስ ቅዱስ እኛን ሁልጊዜም እንደሚጠብቀን ያስረዳናል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
👍3
#ደብተራ_ማለት
(በመምህር ገብረ መድኅን)

1ኛ፦ ደብተራ 'ብርሃን' ማለት ነው፦ እግዚአብሔር በብርሃን ድንኳን ሊቀ ነቢያት ሙሴን በአምሳለ ንጉሥ ተገልጾ በብርሃን ድንኳን በሰባት የእሳት መጋረጃ 22ቱን ሥነ ፍጥረት በልቡናው ሥሎ ቃል በቃል 570 ጊዜ አነጋግሮታል፤ የደብተራ ልጅ ማለት የብርሃን ልጅ ማለት ነው። ወይም ሰማያዊ ወልደ ሰማያዊ ማለት ነው።

2ኛ፦ ደብተራ 'ኦሪት' ናት ባስልኤል ኤልያብን ያህል ጠበብት ሙሴን ያህል ነቢይ አሮንን ያህል ካህን አሥነስቶ ያሳነጻት ናት። ታቦተ ሕጉ ያለባት አምልኮቱ የሚመሠከርባት ሕጉ የሚነገርባት ድንኳን ደብተራ ኦሪት ትባላለች፤ የደብተራ ልጅ ማለት የሕግ ልጅ የመቅደስ አገልጋይ ማለት ነው። ሕገ ኦሪትን ያወቀ እንደሙሴ እንደ አሮን ያለ ማለት ነው።

3ኛ፦ ደብተራ 'ድንግል ማርያም' ናት በአምሳላዊት ድንኳን በረድኤት ይገለጽ የነበረው እግዚአብሔር በንጽሕና በቅድስና በታነጸች በአማናዊት ደብተራ በእመቤታችን ማህጸን በኩነት ተገልጿልና ደብተራ ትባላለች። የደብተራ ልጅ ማለትም የድንግል ማርያም የቃል ኪዳን ልጅ ማለት ነው። እንደ ጴጥሮስ እንደ ጳውሎስ መሆን ነዋ!

4ኛ፦ ደብተራ መስቀል መድኅነ ዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል መሠዊያ ነውና ደብተራ ተብሏል ሕያው ደመ መለኮት የነጠበበት ቅዱስ መስቀል የከበረ ደብተራ ነው፦ የደብተራ ልጅ ማለትም የመስቀል ልጅ ማለት ነው።ወይም መስቀለኛ መስቀላዊ ማለት ነው።

5ኛ፦ደብተራ ርዕሱ ድንኳን ይባላል በዘር በሩካቤ ያይደለ እንበለ ዘር እንበለ ሩካቤ የተወለደ የመድኅን አካሉ ደብተራ ተብሏል ሠዋዒ ተሠዋዒ ተወካፌ መሥዋዕት ነውና እንደ ብሉይ ሊቀ ካህናት ከአፍአ ወደውስጥ ደመ በግዕን ይዞ ለሥርኤት ወደ ደብተራ ኦሪት አልገባም ራሱን በደብተራ ርዕሱ አቀረበ እንጂ፦የደብተራ ልጅ ማለትም የክርስቶስ ልጅ ማለት ነው።በክርስቶስ የሚያምን የክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።

6ኛ፦ደብተራ ቤተ ክርስቲያን፦ ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡባት መቅደሰ ወንጌል ደብተራ ተብላለች አገልጋዮቿም ካህናተ ደብተራ ይባላሉ፤ የደብተራ ልጅ ማለትም የመቅደስ አገልጋይ ቅዳሴውን የሚቀድስ፣ ቅኔውን የሚቀኝ፣ ድጓውን የሚያዜም፣ ዝማሜውን የሚዘም ብራናውን የራመመ ቀለሙን የቀመመ ማለት ነው። የረቀቀ የተራቀቀ ምጡቅ መርጌታ ማለትኮ ነው!ከደብተራ ሙያ አንዱን ሳያውቁ መንቀፍ ወፍ ነዳሽ ጉም አፋሽ መሆን ነው።

ለደብተራነት መዐርግ መድረስ ጭንቅ ነው እንጂ ልጅ መሆንስ ቢሹትም አይገኝ።

ደብተራ እያሉ መተንኮስ በይፋ ክርስትናን እና ክርስቲያኖችን በመጥላት የሚደረግ ሥሁት ድንቁርና ነው። ጠንቋይን ለተከበረው ደብተራ መስጠት አይቻልም ጨለማ ከብርሃን ጋር ኅብረት የለውምና። የሀገር በቀል የዕውቀት ሀሳቦችን የደብተራ ዕውቀት ነው አንቀበልም አንሰማም ማለት ግን ኦርጂናል የጣሊያን አእምሮ ነው። ደብተራ ዶክተሮች ሳይኖሩ ዶክተር ነበር። በተውሶ ጭፍን ግልበጣ የተሠራ አእምሮ እውነትን ካልተጠላት የተማረ አይመስለውም ማለት ነው። ከውሸተኛ ተንኮለኛ ቁም ነገር አገኛለሁ ከማለት ዑቅያኖስ ሜዳ ሁኖ እህል ይዘራበታል ማለት ይቀላል። ወይም ሰሜን ተራራ ደልዳላ ሜዳ ይሆናል ማለት ይሻላል።

(በመምህር ገብረ መድኅን እንየው)
👍1
© ......  ክብረ ቅደሴ  ........ ©

ሀሌ ሉያ ማለት ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ማለት ነው። አንድም ሀሌ ሉያ ማለት ስብሐት ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል ማለት ነው። በቅዳሴ በማኅሌት ብዙ ጊዜ የምንሰማው ቃል ስለሆነ ብናውቀው መልካም ነው ብየ አስባለሁ። አንድ ባሕታዊ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከምስጋናሽ ሁሉ ማንን ትወጃለሽ ብሎ ጠየቃት። እርሷም ልጄ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረ ዳዊትንና አቡነ ዘበሰማያትን የሚደግምን  ሰው በጣም እንደሚወደው ሁሉ እኔም ውዳሴ ማርያምን እና ቅዳሴ ማርያምን የሚጸልይ ሰውን እወደዋለሁ ከልጄ ከወዳጄ ከኢየሱስ ክርስቶስ አማልጄም ጸጋ በረከት ረድኤት አሰጠዋለሁ ብለዋለች።
                        
ቅዳሴ የሚቀድስ ሰው እግዚአብሔርን የሚቀድስ አይምሰለው ራሱ ይቀደሳል እንጂ እንዲል። እግዚአብሔርን ብናመሰግን ለእግዚአብሔር የሚጨመርለት ምንም ነገር የለም። እኛ ግን በማመስገናችን የምናገኘው ታላቅ ጥቅም አለን። ምስጋናን ወይም ቅዳሴን ሊቃውንቱ የመላእክት ምግብ ይሉታል። ወኅብስተ መላእክቲሁ በልኡ እጓለ እመሕያው የሚለውንም። የመላእክትን እንጀራ ምስጋና ሰዎች ስቡሕ ውዱስ እያሉ አመሰገኑ ማለት ነው። ሁልጊዜም ቢሆን ንሥሓ እየገባን እያስቀደስን ልንቆርብ ይገባናል። በቅዳሴ ጊዜ ማውራት ውርውር ማለት እና እንደጠቅላላው ቤተክርስቲያን ውስጥ አለማዊ ነገር ልንነጋገር አይገባንም። በቅዳሴ መካከል ይጫወቱ የነበሩ ሕጻናትን እንኳ መልአክ እንደቀሰፋቸው መንፈሳውያት መዛግብት ያስረዳሉ። ስለዚህ ሕጻናትንም ሥርዓት እንዲማሩ እንዲያውቁ ልናስተምራቸው ይገባል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
👍32
ዝም ያልነውኮ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የማይገደን ሆነን አይደለም።.ዝም ያልነው የሚሰማ በሌለበት መናገር ከነፋስ ጋር የመነጋገር ያኽል ቢሆንብን ነው እንጅ።.የማንጮኸው ሕመሙ ባይበረታብን አይደለም፤ ለሐኪም እንጅ ለከፈን ሻጭ ሕመምን መንገር ቢሆንብን ነው እንጅ።.የሹመት ናፍቆት ለጸናባቸው ምንደኞችም.በሐዋርያት.እግር.ተክተን.እንደማንቀበላቸው ያልተናገርነው ብፁዓን አባቶቻችን እንዲህ ላለ ሌባ ወንበዴ አሳልፈው ይሰጡናል ብለን ስለማንጠረጥራቸው ነው። የዝምታችን ምክንያት ይህ ስለሆነ ነው እንጅ የሁላችንም ሀሳብ እንደ መምህር ኃይለ ማርያም ነው። ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያት ጉባኤ ናት እነሱን የመሰለ ሁሉ ይሾም!!!

©ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

ምንጭ፦ ድምፀ ተዋሕዶ (https://www.tgoop.com/onesinod)
👍3
"እግዚአብሔርን ከግርማው ታላቅነት የተነሣ ብቻ አትፍራው ከፍቅሩ ታላቅነት የተነሣ ፍራው
«ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ»

ኖላዊ ኄር
5👍2🥰2
#መጽሐፍ_ቅዱስ_ሥዕላትን_ይፈቅዳልን?
(#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ)

ክፍል - ፩

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የሚመለከት ሰው እጅግ የተዋቡ የጌታችን፣ የድንግል ማርያም፣ የመላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕላት ቤተ መቅደሱን ሞልተውት ያገኛል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን በሥዕላቱ ፊት ዕጣን ሲያጥኑ፣ መብራት ሲያበሩ፣ ሲሳለሙና ሲሰግዱ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ደግሞ 'ይኼ እኮ ጣዖት አምልኮ ነው!' "በላይ በሰማይ ካለው ፤ በታች በምድርም ካለው ከምድርም በታች በውኃ ካለው የማናቸውንም ነገር ምሳሌ ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም" ተብሎ በዐሠርቱ ትእዛዛት ላይ ተጽፎ የለምን? ብለው ይከራከራሉ፡፡ (ዘጸ. 20፥4)

በእርግጥም እግዚአብሔር በሰማይም ፣ በምድርም ፣ ከምድርም በታች ባሉ በማናቸውም ነገር የተቀረጸ ምስል አታድርግ ብሎ በግልጥ ማዘዙ ማስተባበያ የሌለው እውነት ነው፡፡ ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ትእዛዝ በግልጥ ተጽፎ ካለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ካሉ የመላእክትን ፣ በምድር ካሉ የቅዱሳን ሰዎችን ሥዕላት ለመቅረጽም ሆነ ለመሳል እንዴት ደፈረች? እውነት ይኼንን በግልጥ የተቀመጠ ሕግ እያየች ሥዕላትን ለማዘጋጀት ምን አነሣሣት? የሚለው ጥያቄ የግድ መመለስ ያለበት ነው፡፡

በቀጥታ ወደ ምላሹ ከመግባታችን በፊት ከዚያው ከኦሪት ዘጸአት ሳንወጣ ጥቂት ምዕራፎችን እንሻገርና እናንብብ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው ፡- "ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ … አንደኛውን ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላ ወገን አድርገህ ሥራ … ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘርጉ፤ የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ ፤ ፊታቸውም እርስ በእርሱ ይተያያል … እኔም በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ አነጋግርሃለሁ" (ዘጸ. 25፥18-22)

ልብ አድርጉ፤ ከአምስት ምዕራፎች በፊት 'ከሰማይ ፣ ከምድርና ከባሕር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ' ብሎ ለሙሴ ያዘዘው እግዚአብሔር አሁን ደግሞ በሰማይ ካሉ መላእክት መካከል የሆኑትን የኪሩቤልን ሁለት ምስል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ፣ ክንፎቻቸውን እንዲዘረጉና እንደሚናተፍ ዶሮ እንዲተያዩ አድርጋቸው ፣ እኔም በእነርሱ መካከል አነጋግርሃለሁ አለው፡፡

ከዘጸአት ሳንወጣ እግዚአብሔር አሁንም ለሙሴ እንዲህ አለው፡- "መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ አድርግ ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ" በማለት ከወርቅ ከተቀረጹት ሁለት ኪሩቤል በተጨማሪ በመጋረጃ ላይ በጥልፍ መልክ ኪሩቤል እንዲሣሉ አዘዘው፡፡ (ዘጸ. 26፡30-31)  እግዚአብሔር በሰማይ ካሉት የማንንም ምሳሌ አታድርግ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ራሱ የሚጥስ አምላክ ነው ሊባል ይችላልን? ኪሩቤል ‹በሰማይ ካለው ማናቸውም ነገር› ውስጥ አይደሉምን? የተቀጠቀጠ ወርቅስ የተቀረጸ ምስል አይደለምን? ይህን ጥያቄ እንደ ዋዛ መተው እንዴት ይቻላል?

ይቀጥላል......
2
መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላትን ይፈቅዳልን?
#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

ክፍል -፪

መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘጸአት ብቻ ቢሆን ሁለት ማስረጃ ጠቅሰን እንተወው ነበር፡፡ ሆኖም መጽሐፉ በዚህ አላበቃም ፤ እግዚአብሔር ‹‹እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሠጠው›› ተብሎ የተነገረለት ጠቢቡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ሲፈጽም ይህንን አደረገ፡- "በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ፤ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሌላኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ … ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው" ይላል፡፡ (1ኛ ነገ. 6፥23-28)

ጠቢቡ በዚህ አልበቃውም ፤ የቤተ መቅደሱን ግንብ ዙሪያውን ባዶ እንዲሆን አልተወውም "በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ" ይላል፡፡ (1ነገሥ. 6፡29) በአጭሩ ጠቢቡ ሰሎሞን እንደ ሙሴ በመጠን ያነሡ ሳይሆኑ ዐሥር ክንድ የሚረዝሙ ኪሩቤልን ከወይራ ሠርቶ በወርቅ ሲለብጥ ከምድርም አበባና ዘንባባን በቤተ መቅደሱ ምስል አድርጎ ቀረጸ፡፡

'የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ' የሚለው ቃል የመላእክትን ሥዕልና ቅርጽ የሚከለክል ከሆነ ይህ ሕግ ክብር ይግባውና ሕጉን ባወጣው በእግዚአብሔርና በባሪያዎቹ በሙሴና በሰሎሞን ተጣሰ ማለት ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕግ ስለእነዚህ ዓይነቶቹ የቅዱሳን ሥዕላት የወጣ ሕግ አልነበረም፡፡ ሕጉ የሚጠናቀቅበት 'አትስገድላቸው አታምልካቸውም' የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የከለከላቸው የተቀረጹ ምስሎች አምላኬ ነህ ተብለው ለፈጣሪ የሚገባ የአምልኮ ስግደት የሚሰገድላቸው ጣዖታትን እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ለማንኛውም በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከሰማይ ከምድር ከባሕር ያሉ ፍጥረታትን በምስል ቀርጾ አምላኬ አንተ ነህ ብሎ እንዳይሰግድ የተከለከለው ክልከላ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መላእክት መቅረጽ አይገባም ለማለት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የተሳሳተ መሆኑን ራሱ ባለቤቱ ሕጉን ከሠራ በኋላ በዚያው ዘመን የመላእክቱን ሥዕልና ቅርጽ በማሠራት አሳይቶናል፡፡

እዚህ ላይ አንድ ነገር እናስተውል፤ ከላይ ባየናቸው የቤተ መቅደሱ ውስጥ ሥዕላት በተደጋጋሚ የተሣሉት መላእክት ብቻ ከመላእክትም ኪሩቤል ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እንደምናየው ከሙሴ በፊት የነበሩ እንደ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ሥዕላቸው በቤተ መቅደሱ ለምን አልተሣለም? ምናልባት ለቅዱሳን ሰዎች ሥዕል አይገባ ይሆን? ያሰኛል፡፡ አይደለም፤ እንደሚታወቀው ቤተ መቅደሱ የሰማያት ምሳሌ ሲሆን በሰማያት በልዕልና የሚኖር አምላክ ከሕዝቡ መካከል በረድኤት የሚገለጥበት ሥፍራ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ያሉት ነገሮች ሁሉም በሰማያት በእግዚአብሔር መንግሥትና ከእግዚአብሔር ጋር ያሉትን ነገሮች የሚወክሉ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ሆኖ ወደ ሲኦል በወረዱበት በዚያ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከእግዚአብሔር ረድኤት ርቀው በሞት ጥላ መካከል ናቸውና የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ በሆነው መቅደስ ውስጥ አልተሣሉም፡፡ በዚያ ቤተ መቅደስ የተሣሉት መላእክት ከመላእክትም ለታቦቱ ዙፋንነት ምሥጢር የሚቀርቡት በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋኑን የሚሸከሙት ኪሩቤል ናቸው፡፡

ይቀጥላል......
2
መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላትን ይፈቅዳልን?
#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
ክፍል - ፫

#ሥዕላት_ለምን_ይጠቅማሉ?
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ሥዕላትንየሰማይ መስኮቶች ይላቸዋል፡፡ በቤተ መቅደስ ቆሞ የመላእክቱን ሥዕል ፣ የሥላሴን ዙፋን ፣ የቅዱሳኑን ኅብረት የሚመለከት ሰው ለአፍታ በሕሊናው ወደ ሰማያት መመሰጥና የላይኛውን ነገር ማሰብ ይችላልና ሥዕላት የሰማይ መስኮቶች ናቸው፡፡ የሚያስደንቀው ሥዕላት ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚበልጡ የእግዚአብሔር ቃል መማሪያዎች ናቸው፡፡ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሊገነዘብ የሚችለው ወይ ሊያነበው በሚችለው ቋንቋው ተተርጉሞ ሲቀርብለት ነው፤ አለዚያም ደግሞ ማንበብ የሚችል ፊደል የተማረ ሰው ከሆነ ብቻ ነው፡፡

ሥዕላት ግን ከዚህ መድልዎ የጸዱ አስተማሪዎች ናቸው፡፡ የየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ ያለ አስተርጓሚ ሥዕላትን አይቶ ሃሳባቸውን ለመረዳት ይችላል፡፡ ምንም ፊደል ያልቆጠረ ሰው ቢሆንም ሥዕላትን አይቶ መማርና መጠቀም ይችላል፡፡ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ከጌታችን የዕለተ ዓርብ መከራ ሥዕላት ፊት ብናቆማቸው ሁለቱም የጌታችንን ሥቃይ ፣ መውደቁን መነሣቱን ፣ መገረፉንና መሰቀሉን አይተው ያለቅሳሉ፡፡ ያለ ቋንቋ እንቅፋትነት አብረው ሊማሩ የሚችሉት ስብከት የሚገኘው ሥዕላት ላይ ብቻ ነው፡፡ ያልተማረ ሰውም ከሌሎች የማነስ የበታችነት ሳይሰማው እኩል መረዳት የሚችልበት አስተማሪው ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው፡፡

የቤተ ክርስቲያን ሐኪሞች (Doctors of the Church) ከሚባሉት አባቶች አንዱ የሆነው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የጌታችንን ስቅለት የሚያሳይ ሥዕልን ባየ ጊዜ የተሰማውን ሲገልጥ "ይህንን ሥዕል በተመለከትሁ ጊዜ ያለ ዕንባ ልመለከተው አልችልም፤ ምክንያቱም ሰዓሊው በጥበባዊ መንገድ ታሪኩን ፊቴ ላይ ስላመጣብኝ ነው" ብሏል፡፡ ይህንን የጎርጎርዮስን ምስክርነት ያየው ዮሐንስ ዘደማስቆ ደግሞ በእንተ ሥዕላት አምላካዊያት (On the Divine Images) በተባለው ጥንታዊ መጽሐፉ "ሥዕላት እንዲህ ዓይነቱን የቤተ ክርስቲያን ሐኪም እንዲያለቅስ ከረዱት ለአላዋቂ የዋሐንማ ምን ያህል ይረዳቸው ይሆን?" ብሎ አድንቋል፡፡

ውድ አንባቢ፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔርን የሚያገለግለው በጸጋው እንደሆነ መቼም ታምናለህ፡፡ የመዘመር ጸጋ ያለው ሰው የክርስቶስን መከራውን የሚገልጽ ዝማሬን ሲዘምር ሰዎች ዝማሬውን ተጠቅመው ከፈጣሪ ጋር በተመስጦ ይገናኛሉ፡፡ ጥሩ የመስበክ ጸጋ የተሠጠው ሰው ደግሞ የጌታን መከራ በርቱዕ አንደበቱ በመግለጽ ሰዎች በሕሊናቸው ወደ ቀራንዮ እንዲገሰግሱ ያደርጋል ፤ ጸሐፊው ደግሞ በብዕሩ መሣሪያነት ሰዎች የጌታን መከራ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ ሠዓሊስ?

ይቀጥላል......
👍1
መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላትን ይፈቅዳልን?
#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

ክፍል - ፬

ጥሩ የመሣል ጸጋ ያለው ሰው እንደ ዘማሪው መዘመር ፣ እንደ ጸሐፊው መጻፍ ፣ እንደ ሰባኪው መስበክ ባይችል በተሠጠው ጸጋ የጌታችንን በደም የተለወሰ ፊት ፣ በመስቀል እንደ ቆዳ የተወጠረ ሰውነት በቀለምና በብሩሹ ተጠቅሞ በመሣልና በማሳየት ምስል መከሰትና ሰዎች የተዋለላቸውን ውለታ እንዲረዱ ማድረግ ይችላል፡፡ እንግዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሥዕል አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች በተዘዋዋሪ እያሉ ያሉት "ሠዓሊያን በተሠጣቸው ጸጋ አያገልግሉ" ነው፡፡ (ይኼን ጉዳይ የሠዓሊያን ማኅበር ቢያስብበት ሳይሻል አይቀርም)

የሰባኪ ዓላማው ክርስቶስን በሰዎች ልቦና እንዲሣል ማድረግ ነው፡ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ  ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል" ብሎ ነበር፡፡ አክሎም "የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር ፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን አዚም አደረገባችሁ" ብሎም ገሥፆአቸው ነበር፡፡ (ገላ. 4:19 ፣ 3፡1) ይህ ሁሉ ጥረቱ ሰዎች ክርስቶስንና የመሰቀሉን ነገር በልባቸው እንዲሥሉ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ የሐዋርያው ንግግር ሁለት ነገሮችን መረዳት እንችላለን፡፡ አንደኛው ምጥ እስኪይዘው በሰዎች ልብ በስብከቱ ለመሣል የሞከረውን የክርስቶስ መከራ ሠዓሊ ቢሆን ኖሮ ሥሎ ከማሳየት እንደማይመለስ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በጳውሎስ ትምህርት ሰዎች ጌታን እንደተሰቀለ ሆኖ በልባቸው መሣል (imagination) ከተፈቀደላቸው በልባቸው የሣሉትን የመስቀሉን መከራ የሥዕል ችሎታ ኖሯቸው በወረቀት ላይ ሲያሠፍሩት ኃጢአት ሊሆን አይችልም የሚለውን ነው፡፡   

ሥዕልን መከልከል የሠዓሊነትን ጸጋ ለጣዖት አምልኮ እንጂ ለክርስትና የማይሆን ጸጋ ነው እንደማለት ነው፡፡ 'ሥዕላት ከማስተማሪያነት ያለፈ  እግዚአብሔርን ለማምለክ ይውላሉ ወይ?' ከተባለ መልሱ ስብከትና መዝሙር ለአምልኮ አይውልም ወይ ነው፡፡ ሥዕላት ማለት የተሣሉ ስብከቶች፣ የተሣሉ መዝሙራት ናቸው፡፡ ሠዓሊያንም በቡሩሽ የሚሰብኩና የሚዘምሩ ድምፅ አልባ ሰባኪያንና ዘማርያን ናቸው፡፡ 

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በሥዕላት አማካይነት ፈጣሪዋን ታመልካለች፣ ቅዱሳንን ደግሞ ታከብራለች እንጂ ሥዕላቱን አታመልክም፡፡  በመዝሙር ፈጣሪን ማምለክ ማለት መዝሙርን ማምለክ እንዳልሆነ ሁሉ በሥዕል ፈጣሪን ማምለክም ሥዕሉን ማምለክ አይደለም፡፡ በሥዕላቱ ፊት የምናደርገው ስግደትና አክብሮትም ለሥዕሉ ሳይሆን ለሥዕሉ ባለቤት ነው፡፡ በድርሳነ ሚካኤል 'አኮ ዘንሰግድ ለረቅ ወለቀለም ወለ ግብረ ዕድ' 'የምንሰግደው ለወረቀቱ ለቀለሙ ወይም ለሰው የእጅ ሥራ አይደለም' ተብሎ እንደተጻፈው በሥዕሉ ፊት የምናደርገው ነገር ሁሉ የሚመለከተው በሥዕሉ የተወከለውን አካል እንጂ ሥዕሉን አይደለም፡፡ 

ይቀጥላል.....
መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላትን ይፈቅዳልን?

#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

ክፍል - ፭ (የመጨረሻ ክፍል)

በዓለም ታሪክ እንደሚታወቀው በስምንተኛው ክፍለ ዘመን በክርስትናው ዓለም የሥዕላት ውዝግብ (Icon controvercy) ተነሥቶ ብዙ ደም አፋስሶ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ሥዕላትን የሚያመልኩ (iconolatrilism) እና ሥዕላትን የሚጠሉ (iconoclasm) ሆነው በሁለት ጎራ ተከፍለው ነበር፡፡ በወቅቱ ሥዕል ጠሎቹ ከቄሣሩ ጋር ተመሣጥረው መተኪያ የማይገኝላቸውን ጥንታውያን ሥዕሎች ሲያቃጥሉና በመዶሻ ሲያፈርሱ ነበር፡፡ ቄሣሩም የክርስቶስን ሥዕል በመሬት ላይ አስነጥፎ እየረገጠ "እኔ ክርስቲያን ነኝ ይኼን ሥዕል ግን ጌታ ስላልሆነ እረግጠዋለሁ" እስከማለት ደርሶ ነበር፡፡

የኒቆማድያው እስጢፋኖስ የተባለ አባት በቄሣሩ ፊት ታስሮ በቀረበ ጊዜ በወቅቱ የቄሣር ምስል ይታተምበት የነበረውን መገበያያ ገንዘብ ከመሬት ላይ ጥሎ ረገጠው፡፡ ወታደሮቹ ነገሩን ሳያስተውሉ 'እንዴት የቄሣርን ምስል ትረግጣለህ' ብለው ሊመቱት ሲቃጡ "ይህ ቄሣርን የሚወክል ምስል እንጂ ቄሣር አይደለም ስረግጠው ግን ተቆጣችሁኝ ፤ የሰማይና ምድር ንጉሥ የክርስቶስ ምስልን ግን ቄሣራችሁ ሲረግጠው እያያችሁ ክርስቶስ አልተነካም ብላችሁ ዝም ትላላችሁ" ብሎ ገሥፆአቸዋል፡፡

በዚህ በምዕራቡ ክርስትና የሁለት ጎራ ውዝግብ ያልተሳተፈችው ምሥራቃዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን በዚያ ብትኖርም ኖሮ ሁለቱንም ጎራ አትደግፍም ነበር፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያናችን ሥዕላትን አትጠላምም፤ አታመልክምም፡፡ በሥዕላት የሚከበረው የሥዕሉ ባለቤት ነውና የሚሠጠውም ቦታ እንደተወከለው ባለቤት ማንነት ይወሰናል፡፡ ይህ ውዝግብ ያበቃው በታሪክ ሰባተኛው የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ (The seventh ecumenical council) ተብሎ በሚታወቀው ጉባኤ ላይ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆን የመሳሰሉ አባቶች ባቀረቡት ሚዛናዊው ኦርቶዶክሳዊ አቋም ነው፡፡

ስለ ሥዕል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትና አስፈላጊነት ይህችን ታህል ካየን በሥዕላት ተአምር ይፈጸማል ወይ? የሚለውን አጭር ጥያቄ ተመልክተን እንቋጭ፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልሱ "ጳጳሱ ቅስና አላቸው ወይ" ብሎ ለጠየቀው "ተርፏቸው ይናኙታል" የተባለው መልስ ትዝ አለኝ፡፡ ሥዕላት ተአምር እንደሚሠሩ ከማስረዳት መልሱ ኪሩቤል የተሣሉባት ታቦተ ጽዮን ተአምር ሠርታለች ወይ ብሎ መጠየቅ ይቀልላል፡፡

የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ያረፈባቸውን ሕሙማንን ይፈውስ ነበር፡፡ (ሐዋ. 5፥15) የጴጥሮስ ጥላው ያለ ብሩሽ በብርሃን ረዳትነት የተሣለ ሥዕሉ አይደለምን? የጳውሎስስ ልብስ አልፈወሰምን? (ሐዋ.19፥11) ልብሱስ የጳውሎስ በረከት ያደረበት ጨርቅ አይደለምን? በፈጣሪና በቅዱሳኑ ስም የተሣሉ ሥዕላትም በራሳቸው ኃይል የላቸውም፡፡ በሥዕላት የተወከሉት ቅዱሳን ግን ከፈጣሪ በተሠጣቸው ሥልጣን በሥዕሉ ላይ ተአምር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ከጥቅስ ይልቅ ወዝ የሚፈስሳቸውን የእመቤታችንን ሥዕላት፣ በሀገራችን ዓመት ጠብቆ በማሕሌት መካከል በከበሮው ምት ትክክል በሥዕሉ ላይ ያለው ፈረስ የሚዘልለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕልን እንድትጎበኙ እንጋብዛለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
👍31
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

      †    እንኳን አደረሳችሁ    †   
ግንቦት ፲፪ [12] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ     
             የቅዱሳን  በዓል

ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?  

ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ፫፻፵፯ [347] ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ [ፍልስፍና] ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ፲፭ [15] ዓመቱ ነበር:: በ፪ [2] ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

ቅዱሱ ገና በ፲፮ [16] ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር::

ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል " አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ ፲ [10] ዓመት አቁሞታል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ ፪ [2] ጊዜ አጋዘችው::

በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ፬፻፯ [407] ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ፷ [60] ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::

አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ [ግብዣ አዘጋጀ]:: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ ፲፪ [12] ቱ ሊቃነ መላእክት [እነ ቅዱስ ሚካኤል] በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::

ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::

በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::

"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ [ማቴ.፩፥፳፭] (1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::

"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::

አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::

ሊቁ ባረፈ በ፴፭ [35] ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን
ባርኳል::

ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው :-

- ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
- አፈ በረከት
- አፈ መዐር [ማር]
- አፈ ሶከር [ስኳር]
- አፈ አፈው [ሽቱ]
- ልሳነ ወርቅ
- የዓለም ሁሉ መምሕር
- ርዕሰ ሊቃውንት
- ዓምደ ብርሃን [የብርሃን ምሰሶ]
- ሐዲስ ዳንኤል
- ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ [እውነተኛው]
- መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
- ጥዑመ ቃል - - -

እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን::

ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ፶፮ [56] ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል::

እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::

ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር ያድለን::

ምንጭ፦ ተዋሕዶ
👍41
መለኪያችን ዶግማውና ቀኖናው ይሁን። ብፁዓን አባቶቻችን ዶግማና ቀኖናውን ካስጠበቁልን እንደልጅነታችን በፍቅር እንታዘዛለን። ካላስጠበቁ ደግሞ በፍቅር እንቃወማለን።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
በመ/ር በትረማርያም አበባው
6
ደህና አድርገህ ትወቅጠውና በጣም ሲቆጣ_
____
ፕራንክ ነው ትለዋለህ!? እንዴት ያለው ዘመን ደረስን
👍5🤔2
© ከዝምታና ከመናገር የቱ ይሻላል? ©

አቀድም አእኲቶቶ ለእግዚአብሔር።
ዝምታ በግእዝ አርምሞ ይባላል። የቅድስና በር ነው። ከ10ሩ መዓርጋተ ቅድስና የመጀመሪያው አርምሞ ነው። በሌላ በኩል ተናገሩ ድንቅ ሥራውን በእውነት መስክሩ ይላል። ታዲያ መቼ በምን ጉዳይ የት ለምን እንናገር ዝምስ እንበል የሚለው ብዙ ጊዜ ያከራክራል። ጠቢቡ ሰሎሞን ቦ ጊዜ ለኩሉ ብሏል። ለመናገርም ጊዜ አለው ዝም ለማለትም ጊዜ አለው።
                        
ዝምታን በሚመለከት እምተናግሮ ይኄይስ አርምሞ ከመናገር ዝም ማለት ይሻላል ሲባል።መናገርን በሚመለከት ደግሞ ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ይላሉ።የሆነ ሆኖ መቼ ዝም እንበል መቼስ እንናገር የሚለውን እንመልከት።
                        
አርምሞ=ዝምታ
ዝምታ ነገርን በልብ የመያዝ ታላቅ ጥበብ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወንጌል ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ብሏል። የዝምታ አስፈላጊነት በነቢብ ወይም በንግግር ከሚሰሩ ኃጢአቶች ራስን ለማራቅ ነው። የነቀፋ የስድብ የሐሜት የውሸት የትምክህት የዘፈን የተርእዮ ሀሳብን የሚያንጸባርቁ ነገሮች ሲያጋጥሙን ከመናገር ይልቅ ዝም ማለት ይሻላል። ንግግርህ ለሰሚውም ለአንተም ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ወይም ሥጋዊ ጥቅምን የማይሰጥ ጉዳይ ከሆነ ባትናገረውና ዝም ብትል ይሻላል።
                         
ተናግሮ=መናገር
የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለመመስከር ለሌላውም ለማስተማር እና ለማሳወቅ የምንናገረው ነገር የጽድቅ መንገድ ነው።ወተዝያነው እምዕለት ዕለት አድኅኖቶ።በቀን በቀን የእግዚአብሔርን ማዳን ይነጋገሩ ነበር ተብሏል።አሁን ዘመናችን ከፍቶ እንጂ ቀድሞ አባቶቻችን እናቶቻችን ሲገናኙ ነገራተ እግዚአብሔርን ነበር የሚነጋገሩት። የቅዱሳንን ህይወት እያነሱ ይማማሩበት ነበር።ስለዚህ ሰሚው አካል ሰምቶ በመንፈሳዊ ወይም በዓለማዊ ረገድ ጥቅም የሚያገኝበት ከሆነ ተናገር።
                        
ተናግረኽው በአንተ ላይ ከንቱ ውዳሴን ተርእዮን ትእቢትን የሚያመጣብህ ከሆነ መጀመሪያውንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ። ሰሚውን የሚያሳዝን የሚያናድድ የሚያበሳጭ ንግግር ከሆነ አለመናገር ነው።በሃይማኖት ጉዳይ ግን ከሃዲውን ይከፋዋል ተብሎ ሃይማኖትን ከመመስከር ወደኋላ ማለት አይገባም።
                            
ሌላው ግን አጥርተን በማናውቀው ጉዳይ ባንዘባርቅ መልካም ነው። ብንጠየቅ መልስ መስጠት የምንችለውን ጉዳይ ነው መናገር ያለብን። በሆይ ሆይ ከሌላ ሰው በሰማነው ጉዳይ ግን ዝም ብንል የምናተርፍ ይሆናል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
በመ/ር በትረማርያም አበባው
👍3
ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተክርስቲያን ቅድስት ወማኅበርነ በውስቴታ ።

ክብርት ስለምትሆን ስለዚች ቤተክርስቲያን ፥ ውስጧም ስላለ አንድነታችንም ጸልዩ ።

እግዚአብሔር ማንን እንደሚሰማ አታውቁምና ስለእራሳችሁ   እንደምትጸልዩት ሁሉ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ ቸላ ሳትሉ ስለቤተክርስቲያን ጸልዩ!።

[ እግዚአብሔር ያስበን ]
👍53
" የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል " -  ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

- የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ #በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል።

- ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ ውይይት ተካሂዷል።

- በመጨረሻ ሁሉም አባቶች ተወያይተው ቤተክርስቲያንን የሚጠቅመው ምንድነው ? የሚለው ላይ በመምከር ዛሬ ውሳኔ ተላልፏል።

- የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ ተወስኗል። የመጀመሪያው ችግር ያለባቸው ሀገረ ስብከት የሚል ሲሆን አሁን 7 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል እነሱ በሚያቀርቡት ጥናት ሹመት ይካሄዳል። የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል። ዋናው ነገር ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመው የትኛው ነው ? የሚለውን የጉባኤው አባላት በሙሉ ተስማምቶ ፣ በአንድ ልብ፣ በአንድ ሃሳብ፣ በመነጋገር ውሳኔ ተላልፏል።

- ረቡዕ የማጠቃላይ መግለጫ በቅዱስ ፓትርያኩ ይሰጣል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ፦

" ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን፤ ምዕመናን በሙሉ ተጨንቃችኃል፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ነው ሌላ ጊዜ ወሬም ብዙ ይበዛል በዚህ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በጣም ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን ፤ በእውነት እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ግሩም የሆነ የትምህርት ጊዜ፣ ግሩም የሆነ የውይይት ጊዜ ፣ ቤተክርስቲያን ለይተን የምትፈልገው ምንድነው የሚለውን የተወያየንበት ጊዜ ነው እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ።
👏1🙏1
#ድርሳነ #ቄርሎስ #ወጰላድዮስ

...........መስቀል መሳለም............
ይህን መጽሐፍ የጻፈው ቅዱስ ቄርሎስ ነው።ጰላድዮስ የቄርሎስ ደቀመዝሙር (ተማሪ) ነው።ተረፈ ቄርሎስ 19 ላይ "ኃጢኣት ስንሰራ እየተከታተለ ክፉ ክፉውን የሚመዘግብ እና በሞትን ጊዜ ያንን የጻፈውን በፈጣሪ ፊት ሪፖርት የሚያደርግ እኩይ ፍልስጣ የሚባል ጋኔን አለ" ይላል።ከካህናት መስቀል በምንሳለምበት ጊዜ እኩይ ፍልስጣ ከጻፋቸው ንኡሳን ንኡሳን ኃጢአቶቻችን የሚደመሰስ አለ። በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል ብሎ ጌታችን እንደተናገረው።ይሁንና ምን ዓይነት ኃጢኣቶች እንደሚደመሰሱልን ስለማናውቅ ኃጢኣት መሆኑን ያወቅነውን ሁሉ ንሥሓ ልንገባበት ይገባል።ተረፈ ቄርሎስ 1 ባለመድኃኒት የታመመን ሰው መድኃኒት ሰጥቶ እንደሚያድነው ሁሉ ካህናትም በነፍስ ደዌ ማለትም በኃጢአት የተያዙ ሰዎችን በንሥሓ በትምህርት ያድናሉ።ድርሳነ ቄርሎስ 3፣4 በሃይማኖት ጸንተው ጥሩ ስነምግባር ያላቸው ሰዎች ጠላቶቻቸውን ያሸንፋሉ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
2👍2
#ፍቅረ #ቢጽ// #ባልንጀራን #መውደድ

ተግሣጽ 1፡ ምስጋና ይግባውና ፈጣሪ አንደበትን እንድንሳደብበት ሐሰት እንድንናገርበት እና እርስ በእርስ እንድንከራከርበት አልሰጠንም። እርሱን እግዚአብሔርን አመስግነን እንድንጠቀምበት ነው እንጂ። ለሚሰሙን ሰዎችም በንግግር ደስ እናሰኛቸው ዘንድ ነው፡ወደመልካምም እንስባቸው ዘንድ ነው። እስኪ አንተ ሰው ንግረኝ እገሌ ክፉ ነው ብትል የምታገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ተግሣጽ 3 በንግግርህ መልካም ሁን። ተግሣጽ 25፡ አንተ ሰው ከከፍታህ ወርደህ ወደ ስድብ ጉድጓድ አትውደቅ። ተግሣጽ 1፡ ባልጀራውን የሚያከብር እግዚአብሔርን ያከብራል። ተግሣጽ 3፡ እግዚአብ ሔራዊት የሆነች ፍቅር ሁሉን እንደ ወንድም አድርጎ መውደድ ነው።ተግሣጽ 19፡ ፍቅር በባልንጀራ ላይ ክፉ አታሳስብም ክፉም አታሰራም። ለራሳችን ክፉ እንደማናስብ ሁሉ ለሌላውም ክፉን ማሰብ የለብንም። ሁሉን እንደራስህ ውደድ ተብለን ተነግረናልና። ክፉ በሰራ ጊዜ በራሱ የሚቀየም በራሱ የሚቆጣ አለን?!። ራሱን ይቅር ይል የለምን። እንዲህ ከሆነ አንተም በሌላው አትቆጣ አትቀየም። ይቅር በል እንጂ።ምጽዋት የፍቅረ ቢጽ መገለጫ ነው።ምጽዋት የተሠራ ለሀብታሞች ብቻ አይደለም። ጸሪቀ መበለት ካላት በመመጽወቷ በፈጣሪ ዘንድ ተመስግናለችና።

"እስመ ፈጣሪ ሎቱ ስብሀት ኢወሀበነ ልሣነ ከመ ንጽርፍ ቦቱ።ወንንብብ ሐሰተ ወንትገዐዝ በበይናቲነ።አላ ከመ ንሰብሖ ቦቱ። ለእግዚአብሔር ልዑል ወናስተፍሥሖሙ በንባብ ለእለ ይሰምዑነ ከመ ይኩኖሙ በቁኤተ ወንስሐቦሙ ኀበ ሠናይ። ንግረኒ እስኩ ኦ ብእሲ ምንት ብከ በቁኤት ለእመ ትቤ እገሌ እኩይ ውእቱ። ተግሣጽ 3፡ ኩን ሠናየ በቃልከ። ተግሣጽ 25፡ ኢትደቅ እምልእልናከ ውስተ ግበ ጽርፈት። ተግሣጽ 1፡ ዘያከብር ቢጾ ያከብሮ ለእግዚአብሔር። ተግሣጽ 3፡ ወፍቅርሰ ዘበእንተ እግዚአብሔር ዛቲ ይእቲ አፍቅር ኩሎ ከመ አኃዊከ። ተግሣጽ 19፡ ፍቅርሰ ኢታገብር እኩየ ወኢታሔሊ እኩየ ወኢታሔሊ ኅሡመ በላእለ ቢጽ። መኑ እምሰብእ ዘይትቄየማ ለነፍሱ ወይትመዓዕ ላእሌሃ አኮኑ ይሣሀላ።

የንጉሥን አዋጅ ማፍረስ ንጉሡን ማዋረድ እንደሆነ፤ አንድም ሕንጻውን መንቀፍ ሐናጺውን መንቀፍ እንደሆነ፤ ፍጡርን መንቀፍ ፈጣሪውን መንቀፍ ነው። ስለዚህ ሰውን አትጥላ።


ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
በመ/ር በትረማርያም አበባው
4🙏2👍1
መዝሙር 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

"¹ አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
² እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ሁልጊዜ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይጓደዳል?
³ አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፤ ጠላቴ፦ አሸነፍሁት እንዳይል፥
⁴ የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።"
7
2025/07/14 17:03:33
Back to Top
HTML Embed Code: