tgoop.com/nuiman_9/13
Last Update:
የወሎዬ ዉበት
(ኑዕማን ኢድሪስ)
ቡና ልጠጣ ከተቀመጥኩበት በረንዳ ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች በክርክር ተጠምደዋል። የክርክራቸዉ መነሻ ሁለት ሴቶች በመንገድ ሲያልፉ ተመልክተዋል። ጸጉራ ላይ ሻሽ ጣል ያደረገቸዉ ሴት ዉበቷ የሁሉንም ወንድ ልብ ፈትኗል። አብራት ያለችዉ ሴት ግን ጸጉሯን አንጨባራ፤ በሱሪ ተወጥራ፤ በመነጽር ለመጉላት ብትሞክርም አዲሱ የንግድ ባንክ ህንጻ ስር እንደሚገኝ ሳር ቤት ኩስስ ብላ ታየቻቸዉ።
ሁለቱም ወሎዬ ሆነዉ እንዴት በዉበት ይቺኛዋ በለጠች በማለት ሁሉም የየራሱን ሀሳብ ይሰነዝራል።
እንደኔ ራቅ ብለዉ ዉይይታቸዉን የሚያደምጡ አባት "በወሬያችሁ ገባሁ መሰል ብለዉ..." ንግግራቸዉን ቀጠሉ። ሁሉም ወደሳቸዉ ዙሪዉ ምን እንደሚሉ ለማዳመጥ ትኩረት ሰጧቸዉ። "... ወሎ የዉበት ምንጭ፤ የቆንጆ መፍለቂያ ሀገር ናት። አርጎባዉ፤ ኦሮሞዉ፤ ሶዶማዉ ተደማምሮ ወሎዬ ነዉ። ታዲያ ሴቶቻችን በሄዱበት ሀገር ሁሉ የወንድን ልብ ከፍተዉ እንዲገቡ ዉበትንና ገራገርነትን አብዝቶ አድሏቸዋል። ሴቶች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ ወሎዬዋ ከሁሉም ደምቃና አሸብርቃ ትታያለች። ምክንያቱም ወሎዬ ናታ..." አሉ። እኔን ጨምሮ በበዙሪያችን ያሉ ሰዎች በሽማግሌዉ ሰዉ ንግግር ተስበናል። ማሳረጊያቸዉ ምን ይሆን ብለን ጓጉተናል። "... እና ልጆቼ የወሎ ሴቶች ከሁሉም ይበልጥ ተዉበዉ የመታየታቸዉ ሚስጥር 'ሂጃባቸዉ' ነዉ።..." አሉ። ሁላችንም ተደነቅን። ያላስተዋልነዉ ነገር ነበር።
ዙሪያ ገባዉን ቃኝተዉ እየሰማናቸዉ እንደሆነ ሲያዉቁ ንግግራቸዉን ቀጠሉ "... ሂጃብ ዉበት ነዉ። ጸጉሯ ላይ ሻሿን ጣል ስታደርግ ፀሃዩ ላይ ጨለማን ጥሎበት አለምን በዉበት እንደምታስገርመዉ ጨረቃ ደምቃ ትታያለች። ሃያማኖቷ ደግሞ ክብሯን ይጨምርላታል፤ ቁጥብ ያደርጋታል። እና ልጆቼ የሴቶቻችን ዉበት ሚስጥር ሂጃባቸዉ ነዉ። ይሄን ደግሞ አሁን አብረዉ ካለፉት ሴቶች አረጋግጣችኃል።" ብለዉ ንግግራቸዉን ቋጩ።
Telegram.me/Nuiman_9
Photo - ከዚሁ መንደር
BY Nuiman (ኑዕማን)
Share with your friend now:
tgoop.com/nuiman_9/13