OHTUBE Telegram 93
"የፊት ጭንብልና ተያያዥ ወቅታዊ መረጃዎች" - ፕሮፌሰር የሺጌታ ብርሀኑ
.
የኮሮና ቫይረስ ወደ ሰዉነታችን የሚገባው በሶስቱ የአካል ክፍሎች ማለትም በአፍ፣ በአፍንጫና በዐይን በኩል ነው:: የኮሮና ቫይረስ አካላዊ መጠን ከጉንፋን ቫይረስ አካላዊ መጠን ስለሚበልጥ የፊት ጭንብል በማድረግ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ መከላከል የሚቻልበትን ዕድል ፈጥሯል::
.
በመሆኑም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ከሚረዱ አብይ እርምጃዎች አንዱ የፊት ጭንብል (Face Mask) ማድረግ ነው:: ሆኖም ግን ስለፊት ጭንብል የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ትምህርታዊ መረጃ ቢሰጥም ከኮሮና ቫይረስ ባህሪ በደንብ አለመታወቅና ከጭንብል ተፈላጊነትና ኢኮኖሚያዊ ጫናው ጋር ተያይዞ ጭንብል ማን ያድርግ፣ ምን አይነት ጭንብል ይደረግ፣ ጭንብል መቼ ይደረግ፣ ወዘተ የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪና አከራካሪ እንደሆነ ቀጥሏል::
.
ደረጃውን የጠበቀና በአግባቡ የተደረገ የፊት ጭንብል (Surgical Mask, N95 Mask/Respirator) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን የሚከላከለው በሶስት መንገዶች ነው::
.
1. ቫይረሱ ያለበት ታማሚ ወደ ጤነኛ ሰው እዳያስተላለፍ ማገዝ (ሌሎችን መጠበቅ)
-------------------
ቫይረሱ ያለበት ታማሚ ጭንብል ካደረገ በሚያስነጥስበት፣ በሚያስልበትና በሚናገርበት ጊዜ (እንዲሁም በሚተነፍስበት ጊዜ በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት) ከአፍና ከአፍንጫ የሚወጣውን ቫይረስ የተሸከመ ጠብታ/ጥቃቅን ፍንጣቂዎች በጭንብሉ የዉስጠኛው ክፍል #95 በመቶ ይዞ በማስቀረት ቫይረሱ አየር ላይ እንዳይሰራጭ፣ በቅርብ ርቀት በሚገኙ እቃዎች/ቁሳቁሶች ላይ እንዳያርፍና በንክኪና በትንፋሽ ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ ይከላከላል::
.
2. ጤነኛ ሰው በቫይረሱ ከተበከለ አየር ወይም ከባቢ እራሱን እንዲጠብቅ ማገዝ (እራስን መጠበቅ)
-------------------
ቫይረሱ የሌለበት ተጋላጭ ሰው ጭንብል ካደረገ ወደ ዉስጥ በሚተነፍስበት ጊዜ የሚስበው አየር የተበከለ ከሆነ (ማለትም ኮሮና ቫይረስ የተሸከመ ጠብታ/ፍንጣቂ የያዘ ከሆነ) ተጋላጩ ቫይረሱን ባደረገው ጭንብል ጠብታውን/ፍንጣቂውን በማስቀረት ቫይረሱ ወደ አፍና አፍንጫ እንዳይገባ ያግዛል:: በንፅፅር ሲታይ N95 የሚባለው ጭንብል 95 በመቶ የመከላከል ብቃት አለው:: ቫይረሱ በአየር ላይ ረዘም ላለ ሰዓት መቆየት እንደሚችል ስለታወቀ ሕዝባዊ በሆኑ ቦታዎችና በጤና ተቋማት ጭንብል ማድረግ ተገቢ ነው::
.
3. ቫይረሱ በእጅ አማካኝነት ወደ አፍና አፍንጫ እንዳይገባ መከላከል (ንክኪን መቀነስ እራስን መጠበቅ)
-------------------
ቫይረሱ የሌለበት ተጋላጭ ጭንብል ካደረገ በንክኪ አማካኝነት ቫይረሱ በእጁ ላይ ካለ ከጥንቃቄ ጉድለት በእጁ አፍና አፍንጫውን ሲነካ ቫይረሱን በጭንብሉ የውጨኛው ክፍል በማስቀረት በእጅ ንክኪ የሚመጣዉን መተላለፍ እንዲቀንስ ያግዛል:: ጭንብሉ በእጅና በአፍ፣ በእጅና በአፍንጫ መካከል ጊዜአዊ ንክኪን ተከላካይ አጥር/ከለላ/ በመሆን ያገለግላል::
.
ብዙ ሰዎች ፊታችሁን ንፁህ ባልሆነ እጅ አትንኩ የሚለውን የበሽታ መከላከያ መንገድ መተግበር ስለሚቸገሩ ጭንብል ማድረጉ ይህ የመከላከያ ዘዴ እንዲከበር ከማድረግ አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል:: ሆኖም ግን እጅን በሳሙና በአግባቡ ቶሎ ቶሎ በመታጠብ የእጅ ንፅህናን መጠበቁ አንዱና ዋናው የመከላከያ ዘዴ በመሆኑ ጭንብል አድርጌአለሁ በሚል እሳቤ/አጓጉል የደህንነት ዋስትና ስሜት/ ከመታጠብ መዘናጋት ፈፅሞ አይገባም:: የጅን ንፅህና ካልተጠበቀ ጭንብሉን ለማስተካከል ሲባል በሚደረግ ተደጋጋሚ ንክኪ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል::
.
✍️ ጭንብል ማድረግ ያለበት ማነው? መደረግ ያለበትስ መቼ ነው?
.
የኮሮና ህመም ምልክት ያለባቸው ሰዎች ዋናዎቹ የቫይረሱ አስተላላፊዎች መሆናቸው እሙን ቢሆንም በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት:-
1.ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች 30 ከመቶ ገደማ የሚሆኑት ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያሳዩ የሚቀሩ (asymptomatic patients) ቢሆንም የተሸከሙትን ቫይረስ ወደ ጤነኛ ሰው ሊያስተላልፉ ይችላሉ::
2. በቫይረሱ ተይዘው ገና ምልክት ያላሳዩ ሰዎችም (presymptomatic patients) ምልክት ከማሳየታቸው በፊት ባሉት ቀናት ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ይችላሉ::
.
ከዚህ በመነሳትም አንዳንድ ሀገራት ሁሉም ሰዎች ከቤታቸው ሲወጡ ቫይረሱ እንዳለባቸው እውቅና ወይም ጥርጣሬ ሳይኖራቸው ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ የፊት ጭንብል እንዲያደርጉ ይመክራሉ::
.
ሁሉም ሰው ከቤቱ ውጪ በሕዝባዊና አጋላጭ ቦታዎች አፍና አፍንጫውን በጭንብል ቢሸፍን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንደሚረዳ የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል በ25/07/2012 ዓ.ም ምክረ ሃሳቡን ሰጧል:: የዓለም የጤና ድርጅትም ሃሳቡን ደግፎታል::
.
አተገባበሩ እንደ ሀገራት ነባራዊ ሁኔታ የሚለያይ ሲሆን በሕዝባዊና አጋላጭ ቦታዎች ጭንብል ማድረግ አስገዳጅ ወይም የዉዴታ ግዴታ ሊሆን ይችላል:: የምክረ ሃሳቡን ትግበራ ፈታኝ ያደረገው ዓለም የገጠማት ከፍተኛ የሕክምና ጭንብል (Surgical Mask and N95 Mask) እጥረትና የዋጋ ንረት ነው:: በተወሰነ ደረጃ የሀብታም ሀገራትም ችግር ቢሆንም ድሃና ተረጅ ሀገራት ግን ለጤና ባለሙያዎች የሚሆን እንኳን በቂ የሕክምና ጭንብል (Surgical Mask and N95 Mask) ማቅረብ አለመቻላቸው ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል::
.
ስለሆነም እጥረቱ ሳይባባስ የበሽታ መከላከሉንም ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ
1. የጤና ሞያተኞችና ሌሎች በስራቸው ባህሪ ተጋላጭ ያልሆኑ፣
2. የበሽታው ምልክት የሌለባቸውና
3. ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ሰዎች የሕክምና ጭንብል ደረጃ የሌላላቸው ከድርብርብ የጥጥ ጨርቅ/ልብስ/ የተሰሩና በድጋሜ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ የፊት መሸፈኛዎችን (Reusable Simple Cloth Face Coverings) አጥቦና ተኩሶ መጠቀም ይህን ማግኘት ካልተቻለም በድርብ የአንገት ፎጣ/'ስካርፍ'/፣ ድርብ ነጠላ፣ ድርብ ሂጃብ፣ ወዘተ አፍና አፍንጫን መሸፈን ከቻሉ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳያዉቁ ወደ ሌሎች የሚያስተላልፉበትን አጋጣሚ በመቀነስ የቫይረሱን አጠቃላይ ስርጭት ለመግታት ድርሻ እንደሚኖረው የድርጅቱ ጠበብቶችና የተላላፊ በሽታ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል::
.
ሆኖም ግን ይህ ምክረ ሀሳብ የበለጠ ዉጤታማ የሚሆነው ሰዎች አካላዊ ርቀትንና የእጅ ንፅህናን ጠብቀው ከተንቀሳቀሱ ነው:: የፊት ጭንብል ማድረግ ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን እንደማይተካ መገንዘብ የግድ ይላል::
.
በሀገራችን የሚታየው የሕክምና ጭንብል (Surgical Mask and N95 Mask) አጠቃቀምና ተገቢነት ጥያቄ የሚያስነሳና እጥረት የሚያባብስ በመሆኑ በሀገሪቱ ያለውን የበሽታ ስርጭትና የጭንብል እጥረት ባገናዘበ መልኩ ሀገራዊ የጭንብል አጠቃቀም መመሪያ በማውጣት ወይም አቅጣጫ በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ እንዲሰርፅ ማድረግ ያስፈልጋል። በተጨማሪም እንደ 'N95' አይነት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ የጤና ባለሞያዎች አገልግሎት መዋል ይችሉ ዘንድ ጭንብሉ ያላቸው ሰዎች ለጤና ተቋማት በመስጠት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል።

ትኩረት❗️
----
እጃችን በሳሙና እንታጠብ
አካላዊ እርቀትን እንጠብቅ
ከተቻለ ከቤት አንዉጣ
ጤና ተቋማትን እንደግፍ

www.tgoop.com/ohtube

tgoop.com/ohtube/93
Create:
Last Update:

BY OH TUBE

Share with your friend now:
tgoop.com/ohtube/93

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Earlier, crypto enthusiasts had created a self-described “meme app” dubbed “gm” app wherein users would greet each other with “gm” or “good morning” messages. However, in September 2021, the gm app was down after a hacker reportedly gained access to the user data. Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp. Add up to 50 administrators Image: Telegram. Telegram has announced a number of measures aiming to tackle the spread of disinformation through its platform in Brazil. These features are part of an agreement between the platform and the country's authorities ahead of the elections in October.
from us

Telegram OH TUBE
FROM American