ORT_TIKSOCH Telegram 134
#መጋቢት_1
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም
#የተባረከ_የመጋቢት_ወር_ቀኑ_ዐሥራ_ሁለት ሲሆን ከሌሊቱ ሰዓት ጋር ትክክል ነው። ከዚህም በኋላ ይጨምራል።

መጋቢት አንድ በዚህች ቀን የኢየሩሳሌም አገር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_በርኪሶስ አረፈ፣ የሰማዕቱ #የቅዱስ_እለእስክንድሮስ መታሰቢያው ነው፣ የሄኖክ ልጅ #ቅዱስ_ማቱሳላህ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከቅዱስ_መርቆሬዎስ ከመታሰቢያ በዓሉ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርኪሶስ

መጋቢት አንድ በዚህች ቀን የኢየሩሳሌም አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ በርኪሶስ አረፈ። ይህም አባት ክርስቲያኖችን በሚወዳቸው በቄሣር እለእስክንድሮስ ዘመነ መንግሥት ተሹሞ ሳለ ሐዋርያት ሲጠብቋቸው እንደነበረ በበጎ አጠባበቅ ሕዝቡን ጠበቃቸው።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ እለእስክንድሮስ ሞተ ከእርሱም በኋላ ቄሣር መክስሚያኖስ ነገሠ፡፡ ክርስቲያኖችንም በጽኑዕ መከራ አሠቃያቸው ከእርሳቸውም ብዙዎችን ገደላቸው። ሀገሮቻቸውን ትተው የተሰደዱም አሉ። ይህም አባት ሽሽቶ ወደ ገዳም ገባ ሕዝቡም ፈልገው አጡት።

ከዚህም በኋላ ስሙ ዲዮስ የተባለ ሌላ ኤጲስቆጶስ በላያቸው ሾሙ። እርሱም በጥቂት ቀን አረፈ። ከዚህ በኋላ ስሙ አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ።

የስደቱም ወራት በአለፈ ጊዜ ይህ አባት በርኪሶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ተመለሰ። አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሹመው አገኛቸው።

ወደርሳቸውም በደረሰ ጊዜ ሕዝቡ በመምጣቱ ደስ አላቸው አግርንዲኖስም ተመልሶ በመንበረ ጵጵስናው ላይ እንዲቀመጥ ለመነው በታላቅ ድካምም በወንበሩ ላይ አስቀመጡት። ከአግርንዲኖስም ጋራ አንዲት ዓመት ኖረ አግርንዲኖስም አረፈ።

አባ በርኪሶስም እጅግ እስኪያረጅና እስኪደክም ድረስ ኖረ ወገኖቹንም ሌላ ኤጲስቆጶስ በላያቸው እንዲሾሙ ለመናቸው እነርሱም አይሆንም አሉ።

በዚያም ወራት የቀጰዶቅያ ኤጲስቆጶስ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር። እርሱም በውስጥዋ ሊጸልይና ወዳገሩ ሊመለስ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። ሥራውንም በጨረሰ ጊዜ የበዓሉም ቀኖች በተፈጸሙ ጊዜ ወዳገሩ ሊመለስ ወደደ።

በ #መድኃኒታችን ትንሣኤ በዓል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መግቢያ ወደ ዕገሌ ደጃፍ ውጡ ወደ ደጃፉ መጀመሪያ የሚገባውን ያዙት በጵጵስና ሥራም ይረዳው ዘንድ ከበርኪሶስ ጋራ አድርጉት የሚል ቃል እነሆ ተሰማ።

ወጥተውም ወደ ደጃፉ በደረሱ ጊዜ እለእስክንድሮስን አገኙት ይረዳውም ዘንድ ያለ ፈቃዱ ከአባት በርኪሶስ ጋራ አደረጉት። እስከሚአርፍበትም ጊዜ አብሮት ኖረ።

መላ የሕይወቱ ዘመን አንድ መቶ አሥራ ሰባት ዓመት ሆነ ኤጲስቆጶስነት ሳይሾም ሰማንያ አንድ ዓመት ኖረ በሹመቱም ላይ ሠላሳ ስድስት ዓመታትን ኖረ። #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ በርኪሶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_እለእስክንድሮስ

በዚህችም ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ እለእስክንድሮስ መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ ሰማዕት የሮም ሀገር ሰው ነው ለእርሱ ባለመታዘዙና ለረከሱ ጣዖቶቹ ባለመሠዋቱ ከሀዲው መክስሚያኖስ ጽኑዕ ስቃይን አሠቃየው።

እጅግ ከባድና ታላቅ የሆነ ደንጊያ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ አሥሮ ሰቀለው። ብዙ ግርፋትንም ገረፈው ጐኖቹንም ቀደደ በፊቱም ላይ የእሳት መብራት ጨመሩ።

ሥቃዩንም ባልፈራ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጀ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ እለእስክንድሮስ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ማቱሳላ

ዳግመኛም በዚህች ዕለት የሄኖክ ልጅ የማቱሳላህ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ እርሱም 969 ዓመት የኖረ ሲሆን የአዳም 7ኛ ትውልድ የሆነው የሄኖክ ልጅ ነው፡፡ አዳም ሴትን ወለደ፣ ሴት ሄኖስን፣ ሄኖስ ቃይናን፣ ቃይናን መላልኤልን፣ መላልኤል ያሬድን፣ ያሬድ ሄኖክን ሄኖክ ማቱሳላህን ወለደ፡፡ ማቱሳላህም ላሜሕን ወለደ፣ ላሜህም ኖኅን ወለደ፡፡ ማቱሳላህም 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ዐረፈ፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን ልዩ የሆነች በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#መጋቢት_1 ቀን የሚከበሩ #ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማቱሣላ (በ969 ዓመቱ ያረፈበት)
2.ቅዱስ በርኪሶስ ዘኢየሩሳሌም
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ
4.ቅዱስ መርቆሬዎስ
5.አባ ሚካኤል ዘሃገረ አትሪብና አባ ዮሐንስ ዘሃገረ ቡርልስ
(ሃይማኖተ አበውን: ግፃዌንና ስንክሳርን ያዘጋጁ ናቸው)

#ወርኀዊ_በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

=>+"+ ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ:: ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና:: ሌሊቱ አልፏል: ቀኑም ቀርቧል:: እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ:: +"+ (ሮሜ. 13:11)

በግዕዝ➞ #ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ #ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ #ኢየሱስ_ክርስቶስ።

በአማርኛ➞ #ጌታ_ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የ #ጌታ እናቱ በ #ማርያም ጸሎት #ኢየሱስ_ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)...... ይበሉ!!!

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

#ስንክሳር_ዘወርኃ_መጋቢት_1

tgoop.com/ort_tiksoch/134
Create:
Last Update:

BY Orthodox pictures

Share with your friend now:
tgoop.com/ort_tiksoch/134

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

SUCK Channel Telegram Select: Settings – Manage Channel – Administrators – Add administrator. From your list of subscribers, select the correct user. A new window will appear on the screen. Check the rights you’re willing to give to your administrator. While the character limit is 255, try to fit into 200 characters. This way, users will be able to take in your text fast and efficiently. Reveal the essence of your channel and provide contact information. For example, you can add a bot name, link to your pricing plans, etc. "Doxxing content is forbidden on Telegram and our moderators routinely remove such content from around the world," said a spokesman for the messaging app, Remi Vaughn. There have been several contributions to the group with members posting voice notes of screaming, yelling, groaning, and wailing in different rhythms and pitches. Calling out the “degenerate” community or the crypto obsessives that engage in high-risk trading, Co-founder of NFT renting protocol Rentable World emiliano.eth shared this group on his Twitter. He wrote: “hey degen, are you stressed? Just let it out all out. Voice only tg channel for screaming”.
from us

Telegram Orthodox pictures
FROM American