tgoop.com/ortodoxtewadochannal/4197
Last Update:
"እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች"
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
በማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን የሰጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የሀገራችን የሰላም ሁኔታ ላይ ለተሳታፊዎቹ መልእክት አስተላልፈዋል።
"ቤተ ክርስቲያን አንድ ሁኑ ብላ ታስተምራለች፤ ጥላቻን መገዳደልን ታወግዛለች፤በንግግር በውይይት ፍቱ ትላለች" ያሉት ብፁዕነታቸው "ይህንን አቋሟን በበጎ የማይመለከቱ ግን ይኖራሉ" ብለዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመልእክታቸውም "እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች" በማለት "ወላዋይና አድርባዮች ስለሆንን፣ ምን አገባኝ ብለን መስለን ስላለን ሀገሪቱን ዋጋ እያስከፈልን ነው፤ የወገን ደምም ሲፈስ ማየት ተለምዷል ሲሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም " ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
BY ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

Share with your friend now:
tgoop.com/ortodoxtewadochannal/4197