🌹
ጣ ዕ ም ፡ የ ሌ ለ ው ፡ ስ ብ ከ ት
ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር ፡፡
ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ የሰበከው ስብከት ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ‹ ንስሓ ግቡ › የሚል አዋጅ የለውም በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች !! ›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር ፡፡
የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም ፡፡
ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው ፡፡
የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል ? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል ? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ ትጠፋላችሁ › ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር ፡፡
ዮናስ ወደ ከተማይቱ ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሰጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም ፡፡
ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ › ብሎ አልሰበከም መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች › ብሎ ጮኸ ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን ( ማን ነው የሚገለብጣት ? › ለምን ትገለበጣለች ? › ‹ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ ? › ( ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል ? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም ? › አላሉም ፡፡
ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡ ‹‹ እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ››
አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል የነነዌ ሀገር ህዝቦች ሀገር የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር › አላሉም ፤ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ ፡፡
የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን › አላሉም ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም
ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹ የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ ›› የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ ‹‹ ነነዌ ትገለበጣለች ›› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር ፡፡ ‹‹ ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ ? ›› ብለው_አፉን አላፈኑትም ።
መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች።
ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ ! ብሎ አዋጅ አስነገረ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት ? ‹‹ መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን ? ( መክ . 10 ፡ 16 )
መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል ? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል ?
ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹ እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው › ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው ፡፡
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የቤተ መንግሥቱን ሁኔታ እንዲህ ይሥለዋል ፡፡
‹‹ የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች ፡፡ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ !! ››
ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም ‹‹ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ።
ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር ›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ ፡፡
ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር ፡፡
ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹ እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ › አላለም ፤ በተቃራኒው ‹ እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ › እስከማለት ደረሰ በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በማይሰጥ ስብከት ተሰብረው ራሳቸውን አዳኑ ፡፡
ብዙ ስብከት አልፈለጉም ፤ ክፋትን ለመተው እ.ና ይቅር በለን ለማለት የተሰበረ ልብ እንጂ በእውቀት መሞላት አያስፈልግም የኛ ኃጢአታችን ደግሞ ከነነዌ ሰዎች ከበለጠ ቆየ የጋራ ክፋታችንን በጋራ ንስሓ እንጠበው።
📖 የኤፍራጥስ ወንዝ መጽሐፍ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ጾመ ነነዌን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት "የዛሬዋ ነነዌ ኢትዮጵያ መሪዎች ልብ ገዝተው ወይም ራሳቸው ማቅ እስከለብሱና እስኪመለሱ ወይም ደንዳና ልባቸው ጎርፍ ሆኖ እንደ ፈርዖንና እንደ ሔሮድስ እንዲሁም ዲዮቅልጥያኖስ ይዟቸው እስኪሔድ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም።" ብለዋል።
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
Audio
✝ሰማንያ አራት ዓመት✝
ሉቃ 2÷37
Size:-29.4MB
Length:-2:08:31
አዲስ አበባ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የካቲት 8/2014ዓ.ም የተሰጠ
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ሉቃ 2÷37
Size:-29.4MB
Length:-2:08:31
አዲስ አበባ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የካቲት 8/2014ዓ.ም የተሰጠ
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ደግሞ አክሊል ሐዋርያዊ መልሶች - Apostolic Answers ላይ በክፋት ተነስተውበታል። ውሻ በሚቀደው እየገቡ፣ ያላለውን አለ እያሉ፣ አፉ ውስጥ ቃላት ለመክተት ጭምር፣ ገፍተው ለመጣል ይለፋሉ። ድንገት ከወደቀ ብለው "እኔም የአቅሜን ላዋጣ" በሚል፣ በሴራ የሚተጉም አሉ። ነገር ግን ማዕረግና መድረክ ተሰጥቷቸው፣ ማይክ ጨብጠው እንኳን መሥራት ያቃታቸውን ነው ለመሥራት፣ ክፍተት ለመሙላት እየጣረ ያለው።
በጣም ነው እንዴ ቅር ያላችሁ፥ ወጣቱ ስልኩን ይዞ ከሌላ ቦታ ሸሽቶ ስለእግዚአብሔር ስለቤተክርስቲያን ስለተማረ?
ነገሩ አድናቆትና ውዳሴ ያልቅ ይመስል "በጣም ደመቅህ፣ ትንሽ ደብዝዝልን፤ እንታይበት። ቁመትህ ረዘመ ትንሽ አጠር በልልን እንጂ" ነው። ውስጥ ውስጡን ቅናት ለበስ አድናቆት ነው። (Its a wicked way of appreciation) በርታልን፣ እንዴት እናግዝህ? ማለት ሲቻል፣ ጥፋልን ማለት በጣም ያሳፍራል።
ሁሌም ሥራ ላይ የሆነ ሰው በሰነፍ እይታ ይበዛበታልና፣ ሰነፎች በክፋት ዐይን ቢያዩት አይደንቅም። ግን መንፈሳቸው ያስፈራል። ያሳፍራል። አይበለውና እንዲህ ገፍተውት ቢወድቅላቸው "ብለን ነበር" ለማለት ነው። እንጂ ጥቂት መንፈሳዊ ዓላማ ይዘው ቢሆን ኖሮ፣ ከካማዊ ግብራቸው ይልቅ፣ እንደ ሴም እና ያፌት ወንድምን መሸፈኛ ሸማ ይዘው ይቀድሙ ነበር። ስህተት ያሉት ነገር ሲኖር እንደ ወንድም ቀርቦ ማውራት፣ መጸለይ እያለ ለማስጣት መሮጥ፣ እንደክርስቲያን ቀርቶ፣ በወል እንደ ሰውም ነውር ነው።
("የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም።" ~ ዘፍጥረት ፱: ፳፪ - ፳፫ )
ከሁሉም ያሳቀኝ ወንጌሉን እርግፍ አድርጎ ትቶት ግብረሰ*ምን normalize ለማድረግ ጧት ማታ በዚህ ገቡ፣ በዚህ ሄዱ እያለ፣ እየታገለ መስሎ በየሚዲያው፣ ያለእረፍት ግብረሰዶማዊነትን እያለማመደ ያለው ደረጀ ዘይትበሀል ሶያ በተንኮል ከተነሱት መሀል መሆኑ ነው። በሴራ ሽረባ የነደደ ሰው፣ መንፈሳዊነት እና እውቀት ቢደብሩት አይገርምም።
እንግዲህ ሰው ካነበበ፣ ካወቀ፣ ከተማረ ይጠይቃል፣ ፍሬ ከገለባ ይለያልና፣ ሰውዬው እንዳይረሳ ቢሰጋ አልፈርድበትም።
አኬ መቼም ትልቅ ሰው ነህ። በኩርንችቱም በቋጥኙም ደንቀፍቀፍ አትልም። በርታ። እንዳስጀመረህም ፍጻሜህንም ያሳምርልህ! በቀና ልብ የሚሰጡህ ትችቶች ድጋፍም ናቸውና እየወሰድክ፣ በጸሎትም እየበረታህ፣ ወደ ፊት በልለት ይለይለት። 👍🏾👍🏾
Stay blessed! የክርስቶስ ፍቅር እና ሞገስ አይለይህ።🙏🏿💙

🔴 እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል ? |...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
✝እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል?✝
Size:-82.9MB
Length:-1:38:35
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
Size:-82.9MB
Length:-1:38:35
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ቅድስት ቤተክርስቲያን ጠርታ ትሸልመው በቆብ እና በማዕረግ ስም ከመክበስበስ ውጭ ስራ ፈተው ያሉት ሰባክያን እና መነኮሳት አኬ ! የማንቂያ ደውል ነው።
በተረፈ የስምን ካባ የለበሳችሁ እና የእርሱ ከእናንተ መግነን አሳስቧችሁ አሁን ወዬ ወዬ የምትሉ የአውደ ምህረቱ መልክ ሰሪዎች እረፉ ! በነገራችን ላይ አንብቡ መማርም አይጎዳም ተማሩ !
ከሐሜት ትርቁ ዘንድ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
በተረፈ የስምን ካባ የለበሳችሁ እና የእርሱ ከእናንተ መግነን አሳስቧችሁ አሁን ወዬ ወዬ የምትሉ የአውደ ምህረቱ መልክ ሰሪዎች እረፉ ! በነገራችን ላይ አንብቡ መማርም አይጎዳም ተማሩ !
ከሐሜት ትርቁ ዘንድ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ድካሙን ተረድተን በፍቅር ቃል እናርመው!
...................................
አኬና ጓደኞቹ በቲክቶክ ያስነሱት የወንጌል አቢዮት ቀላል የሚባል አይደለም። ቤተክርስቲያን የሆነችውን ሳይሆን ባልሆነችው በሚዲያ የሚከሷት፣የሚወቅሷት ቀላል አልነበሩም። ዛሬ በቀላሉ ይኼን ማድረግ አይችሉም።
ምክንያቱም እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው የቤተክርስቲያንን እውነተኛ መልክ የሚገልጡ፤ እውነተኛ ትምህርቷንም የሚያስረዱ ቀላል የማይባሉ ልጆች በፕላትፎርሙ አሏትና።
አገልግሎት ደግሞ ይህ ነው። ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለሁሉ በሁሉ ቦታ መድረስ። ነፍሳትን ከእሳት ነጥቆ ወደ ክርስቶስ የፍቅሩ ጥላ ማድረስ። እነ አኬ በዚህ ረገድ የተሻለ ስራ እየሰሩ ነው። አቀራረባቸው የዘመኑን ወጣት የተረዳ ነው።
አሁን ላይ ትልቅ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ፈተና የሆነው በመንፈሳዊ እውቀት መታበይ ብዙም አይታይባቸውም። መንፈሳዊ እውቀት የምናውቀው ብቻ ሳይሆን የምንኖረው በሕይወት የሚገለጥ ነው። የምናስተምረው የምንኖረው ነው እንጂ የተማርነው እውቀት ብቻ አይደለም።
መንፈሳዊ እውቀት ሊቅ ለመባል ሳይሆን ቅዱስ ለመሆን ነው የምንማረው።
የምናስተምረው ይህንን እውነት ነው። ነገር ግን በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ድካም ይኖራል።
የደከመውን ማበርታት እንጂ ገፍቶ መጣል ግን ከእኛ አይጠበቅም። በወንድማችን አክሊል አገልግሎት እጅግ ከሚኮሩ ወንድሞች አንዱ ነኝ።
እጅግ ትልቅ ስራ የሰራ፤እየሰራም ያለ ብርቱ ወጣት ነው። የሚበረታታ የእቅበተ እምነት ሥራ እየሰራ የሚገኝ ወንድም ነው። የእቅበተ እምነት ሥራ ለአንድ አካል የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም። ሁሉም እንደ ጸጋው ሊወጣው የሚገባ ተግባር እንጂ። በዘመነ ተሐድሶ ከፍተኛ የእቅበተ እምነት ሥራ ሲሰሩ የነበሩ የሰ/ት ቤት ወጣቶች ናቸው። የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዝምታን በመረጡበት ጊዜ እንኳን ሳይቀር።ይህ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። አሁንም እነዚህ ልጆች ማበረታታት እንጂ ሌላ ስም በመስጠት ለማሸማቀቅ መሞከር አጅግ ትክክል ያልሆነ ተግባር ነው።
ይህ ማለት ግን ምንም ስሕተት የለም ማለት አይደለም። በብዙ ወንድሞች የተገለጹ እኔም የምቀበላቸው መታረም ያለባቸው ስሕተቶች አሉ።
ያውም የመሠረታዊ ትምህርት። ነገር ግን በፍቅር ቀርቦ ማረም፤ በጸሎት ማገዝ ፤ለውጪ ጎታች ለውስጥ ገፊ አሳልፎ አለመስጠት፤
ሰድቦ ለሰዳቢ ፣ነቅፎ ለነቃፊ አለማድረስ ይገባል።
አክሊልና የአክሊልን ሀሳብ ለይቶ መነጋገር ያስፈልጋል። በርኅራኄ ፣በፍቅርና በሚያንጽ ቃል ሊያርም የሚገባው ነገሮ እንዲታረም መሞከር እንጂ ከክርስቲያናዊ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ እጅግ ኦርቶዶክሳዊነት በሚያሳይ መልኩ ሳይሆን በስድብና " ልክ አስገባሃለው " አይነት ጽንፍ የረገጠ፤ግለሰቡ ላይ ያተኮረ፤ድካሙንና ልፋቱን የዘነጋ አካሄድ እንድናጣው ያደርገን ካልሆነ በቀር እንዲታረም አያደርገውም።
የእውቀት ትከሻ መለካካት የሚመስሉ ቤተክርስቲያንን የዘነጉ ድርጊቶች እኛንና ትምህርታችንን የሚከተሉ ምእመናን ዘንድ ትዝብት ውስጥ ከመጣሉም ባሻገር ፤የምናስተምረውን የማንኖር " ጠላትህ ውደድ " ብለን የምንሰብክ ወንድማችንን የምናሳድድ ሆነን መቅረባችን ነውና እራሳችን እንታዘብ።
ለአኬም እንዘንለት፣እንጸልይለት፤ ብርታቱን ሳንዘነጋ ከድካሙ እንዲበረታ እናግዘው።
ይህ ከሆነ ለእኛ የታዩን ስሕተቶቹ የማየት እድሉ ይኖረዋል። ወንድማችንን አዳነው ማለት ይህ ነውና።
አኬን እንደ ወንድም እንውደደው። ሀሳቦቹን ደግሞ እንዲያርም እናግዘው እንጂ አንግፋው።
❤የሚያንጽ የፍቅር ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችን ከቶ አይውጣ።
✍️ የኤፍሬም ዕይታዎች

Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
ሐዋርያት የሰበኩሽ
ሰማዕታት የሞቱልሽ
ጻድቃንም የከበሩብሽ
ተዋሕዶ ርትዕት ነሽ
ሰላም ተዋህዶ ሰላም ኦርቶዶክስ
የአትናትዮስ ሀውልቱ የዲዎስቆሮስ
የአዳም መመኪያ የሄዋን ሀገር
አንቺ አይደለሽም ሆይ የቅዱሳን ክብር
@ortodoxtewahedo
ሰማዕታት የሞቱልሽ
ጻድቃንም የከበሩብሽ
ተዋሕዶ ርትዕት ነሽ
ሰላም ተዋህዶ ሰላም ኦርቶዶክስ
የአትናትዮስ ሀውልቱ የዲዎስቆሮስ
የአዳም መመኪያ የሄዋን ሀገር
አንቺ አይደለሽም ሆይ የቅዱሳን ክብር
@ortodoxtewahedo
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚
#ጽናት
በጎ ሥራን አጽንቶ ከያዙት እግዚአብሔርን ያስገኛል፡፡ ሰይጣን የሚንቀው በጎ ሥራ የለምና የጀመራችሁትን በጎ ሥራ አጽንታችሁ ያዙ፡፡
#ኦርቶዶክሳዊያንን
👉 @ortodoxtewahedo ይጋብዙ፤
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
#ጽናት
በጎ ሥራን አጽንቶ ከያዙት እግዚአብሔርን ያስገኛል፡፡ ሰይጣን የሚንቀው በጎ ሥራ የለምና የጀመራችሁትን በጎ ሥራ አጽንታችሁ ያዙ፡፡
#ኦርቶዶክሳዊያንን
👉 @ortodoxtewahedo ይጋብዙ፤
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........
የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
👇👇👇
https://www.tgoop.com/+2ua4-eAbNTI1MTRk