tgoop.com/perkytipsbyvenu/972
Last Update:
ሴቷ አካሏን የውበትና የደስታ ምንጫ አድርጋ ስትጠቀምበት፣ ወንዱ ግን ከስራ ያሳረፈውን አካሉን ምን ያድርገው? ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በከፍተኛ የድብርት ስሜት የሚሰቃዩት ለዚህ ነው። ከዚህ ድብርት ለመውጣት እሱም እንደ ሴቶች አካሉን የውበትና የደስታ ምንጭ አድርጎ እንዳይጠቀምበት ተፈጥሮ ፀጋዋን ነፍጋዋለች:: እናም በማሽኖች ግፊት፣ አካል ከስራ ጡረታ መውጣቱ የወንዱን የሃይል ምንጭ እያደረቀው ሄዷል። ወንዱ ይሄ ደካማነቱ እንዳይገለጥበት ሴቷን የድሮውን የአለባበስ ሥነ ምግባር እያነሳ እሷም አቅመ ቢስ እንድትሆን ይጥራል። በዚህ ረገድ ወንዱ ሴቷን ማስገደድ ስለማይችል ያለው አማራጭ የሃይል ምንጩን ‹‹ከጉልበት›› ወደ ‹‹ዕውቀት» ማሸጋገር ነው:: እሱ የሃይል ምንጩን እያሸጋገረ፣ እሷን ግን አሁንም የሃይል ርሃብተኛ እንድትሆን ይፈልጋል፡፡
ችግሩ ግን፣ 21ኛው ክ/ዘ ላይ «የግለሰብ ነፃነትና እኩልነት›› የሚባሉ አዳዲስ እሴቶች መምጣታቸው ነው፡፡ እናም በዚህ ዘመን ላይ «ዕውቀት›› ለሁለቱም - ለወንዱም ለሴቷም - እኩል የሃይል ምንጭ እንዲሆን ለሁለቱም እኩል ዕድል ተሰጥቷቸዋል። ይሄን ዕድል ተጠቅመው ወንዱና ሴቷ የዕውቀት ባለቤት ቢሆኑ እንኳ፣ ሴቷ ግን ሌላ ተጨማሪ የሃይል ምንጭ አላት - አካሏ/ውበቷ። በመሆኑም በ21ኛው ክ/ዘ ላይ የወንዱ የሃይል ምንጭ ‹‹ዕውቀቱን ብቻ ሲሆን፣ የሴቷ የሃይል ምንጭ ግን ሁለት ናቸው «ዕውቀትና ውበት»፡፡ በመሆኑም ወንዱ በሃይል ሚዛን እየተበለጠ ሄዷል። ይሄንን ደካማነቱን ለማካካስና የሃይል ሚዛኑን ከሴቷ ጋር ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ምንጭ ፦ ፍልስፍና ፫
ፀሀፊ ፦ ብሩህ አለምነህ
#ፍልስፍና_ከፈላስፎች
BY Perky tips🩰✨
Share with your friend now:
tgoop.com/perkytipsbyvenu/972