tgoop.com/phillosophy/1300
Last Update:
የፈላስፋው ጥመት...
፨፨፨
የጠርጣሪነት ፍልስፍና (scepticism) ጀማሪ እንደሆነ የሚታመንለት የጥንቱ ፈላስፋ ፊሮ አንድ ቀን ጥበብን ያካፍላቸው ዘንድ ወደጋበዙት ሰዎች በማለዳ አመራ። በቦታው ሲደርስ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ተሰብስቦ ሲጠብቀው ተመለከተና ወደተዘጋጀለት የከፍታ ቦታ በዕርጋታ ወጥቶ ቆመ። ፊሮ ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት ጥያቄ ወረወረ፦
<<ዛሬ እዚህ የተሰበሰባችሁት ከእኔ ልትማሩ ነው?>> ተማሪዎቹ በአንድ ድምፅ አዎንታቸውን ገለፁ።
<<እንግዲያውስ ስለምን እንደማስተምር ታውቃላችሁ ማለት ነዋ?>> አለ ፊሮ።
<<ኧረ ምንም አናውቅም>> አሉ ተማሪዎቹ አሁንም በአንድ ድምፅ።
<<ስለምን እንደማስተምር ካላወቃችሁማ ዝም ብዬ ማውራት አልፈልግም>> አለና ከመድረኩ ወርዶ ወደ ቤቱ አመራ።
በነጋታው አሁንም በዚያው ቦታ ህዝቡ ተሰብስቦ ይጠብቀው ጀመር። ፊሮም መጣና በእርጋታ ወደ መድረኩ ወጣ።
<<ዛሬስ ስለምን እንደማስተምር አውቃችኋልና?>> በማለት ጠየቀ።
የተሰበሰበው ህዝብ በአንድ ቃል አዎንታቸውን ገለፁ።
ፊሮም <<ካወቃችሁትማ ወደ ቤቴ ልሂድ....>> በማለት ከከፍታው ላይ ወረደ።
በሚቀጥለው ቀን ወደ ቦታው ሲያመራ አሁንም ህዝቡ ተሰብስቦ እየጠበቀው ነው። የዚያን ቀን ግን ህዝቡ መልሳቸውን አዘጋጅተው ነበር የጠበቁት።
ፊሮም ወደ ከፍታው ከወጣ በኋላ፦<<ዛሬስ ስለምን እንደማስተምር ታውቃላችሁ..?>> አለ።
ህዝቡም፦<<ግማሾቻችን እናውቃለን፤ግማሾቻችን ደግሞ አናውቅም...>> አሉት።
ፊሮም፦<<እንግዲያውስ ግማሾቻችሁ የምታውቁት፤ ለግማሾቹ የማያውቁት ንገሯቸው!..>>
ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ
፨፨፨
፨ አሁን በእናንተ አረዳድ በፈላስፋው ላይ ነው ወይስ በተከታዮቹ ላይ ነው የሚፈረደው...?
ለሀሳብ አሥተያየትዎ
👇👇👇
@SSR60 ወይም
@abdu23 ላይ ይጠቀሙ !!!!
@phillosophy @phillosophy
BY ፍልሥፍናና የህይወት እውነታ
Share with your friend now:
tgoop.com/phillosophy/1300