PHILLOSOPHY Telegram 1470
1. "ማሰብ አቁም ፥ የችግርህ ሁሉ ማቆሚያ እዚያ ላይ ነው !! (2)

አሁን ላነሳው የምፈልገው ሃሳብ ደግሞ ሌላው ሰው ለእኛ የሚያስበውን "ሃሳብ" በማወቅ ፍላጎት ይገለጻል ። በምድራዊ ህይዎታችን ዙሪያ የምናገኛቸውን ሰዎች ስለእኛ ምን እንደሚያስቡ ከግምት ባለፈ እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ያስቸግራል ። እናም የዘወትር ሃሳባችን ከመልካሙ ነገር ይልቅ በከፋው ገጠመኛችን የተጠመደ ሆኖ እንደ አስጨናቂ ህልም በየቅጽበቱ የሚያባንን መከራ ይሆንብናል ። ሂዎት ከተቸረችው የአበባ ገጸ በረከት ይልቅ ለአእምሯችን ቅርብ የሚሆንብን እሾሁ ነው ። ስለ አበባው ማንስ ግድ ይለዋል ?? ፡፡ ከወዳጅህ ይልቅ ጠላትህን ማሰብ ትልቁ ስራህ ነው ። የአእምሮህን የእስከዛሬ ድርጊት ለአፍታ መለስ ብለህ በትግስት ብታስበው የምትወዳቸውን ሳይሆን የምጠላቸውን በማሰብ የቱን ያክል ተጠምዶ እንደኖረ መረዳት ትችል ነበር ። የሰው ልጅ አእምሮ መርሳትን ጸጋው አድርጎ ቢቀበለውም ይህ ጸጋ ግን ለወዳጆቹ እንጅ ለጠላቶቹ እንደማይሆንም መረሳት የማያሻው ለዚህ ነው ። አእምሮውን ለመልካም ያዘጋጀ በአንጻሩ ውበትን ለመመልከት ፥ ከአበባው በረከትም ለመቋደስ የሚቸግረው አይሆንም ። አእምሮ በተቀደደለት የሃሳብ ቦይ ሲፈስ እንዲሁ የሂዎት ልምዱን ከተዋበው ገጠመኙ እየሰበሰበ መጓዝ ከቻለ ዙሪያውን በውበት ይከበባል !! ። ለዚህ ደሞ ብቸኛው መፍትሄ የአእምሮን የሃሳብ አቅጣጫ ለመቀየር መወሰን ይሆናል ። እዚህ ላይ ቀጣይዋን ወግ ለሃሳባችን ማጠያከሪያ አድርገን እናምጣት >
በአንድ የአይሁድ ምኩራብ የተከሰተ ታሪክ ነው ። ምኩራቡን አይሁድ እንደገዳም የሚጠቀሙበት ሲሆን የዚህ ምኩራብ ሊቀ ካህን ደግሞ በባህሪው እጅግ ቁጡና ኮምጫጫ ነበር ። በዚያ ገዳም ውስጥ ኑሯቸውን የመሰረቱ ሁለት ጓደኛሞች ዘወትር ሳይለያዩ የሚፈጽሙት አልድ ልማድ ቢኖር ከአትክልቱ ስፍራ እግራቸውን መጓዝ ነው ። በማለዳ ለአንድ ሰኣት ፥ ምሽት ላይ እንዲሁ ለአንድ ሰአት ይህንን የእግር ጉዞ ሳያቋርጡና ሳይለያዩ ለረጅም ጊዜ የሚፈጽሙት እነዚህ ሁለት ወጣቶች የቀረውን ጊዜያቸውን ደግሞ የእምነት መጽሃፍትን በማጥናትና በመማር እንዲሁም ሌሎች የገዳሙን ስራዎች ሲከውኑ ያሳልፉ ነበር ፡፡ ይሁንና እነዚህ ሁለት ወጣቶች ዘወትር በአእምሯቸው እየተመላለሰ የኒያስስባቸው አንድ ጉዳይ ነበር ፡፡ ይሄውም " በአትክልት ስፍራው እግራቸውን ሲያፍታቱ ሲጋራ ማጨስ እንዲፈቀድልን ሊቀ ካህኑን እንዴት እንጠይቀው ? " የሚለው ነው ። ሁለቱን ጓደኛሞች በሲጋራ ሱስ የተጠመዱ ቢሆንም በዛ ገባም ውስጥ በተቀደሰው የአይሁድ ምኩራብ ይህን ድርጊት መፈጸም ቀርቶ ማሰብም ትልቅ ወንጀል እንደነበር ያውቁታል።
ምንም እንኳን እጅን በአንበሳ አፍ የመክተት ያህል አስፈሪ ቢሆንም ወጣቶቹ የሱስ ስቃዩን መቋቋም ባለመቻላቸው ሊቀ ካህኑን ለየብቻ እየሄዱ ለማስፈቀድ ወሰኑ ። " እንደምታውቀው ሊቀ ካህኑ አደገኛ ሰው ነው ፥ ምን እንደሚለን እንግዲህ ፈጣሪ ያውቃል " ተባባሉ ።
በቀጣዩ ቀን አንድኛው እንባው ባይኑ ቀርሮ ተቆጥቶና አዝኖ ከምኩራብ ሲወጣ ጓደኛው በአትክልት ስፍራው እግሩን እያፍታታ በአበቦች መአዛም እየተዝናና ሲጋራውን ሲያጨስ ተመለከተው ። " አምላኬ ሆይ ! ሊቀ ካህኑን ሳትጠይቅ ሲጃራ ማጨስ ጀመርክ ? " በማለት አፈጠጠበት ።
ጓደኛው ግን ፈገግ ብሎ " የለም !! ተይቂያለሁ " አለው ።
በዚህ ጊዜ አንደኛው ጥልቅ ሃዘን ተሰማው ፥ ምን አይነት ሰው ነው ? እኔ አሁን ገብቸ ስጠይቀው እኮ በጩኸትና በስድብ ነው ያባረረኝ ። ምን እንዳለኝ ታውካለህ ? " ይህ ቦታ እኮ ገሃነም አይደለም ! ሲጃራ ማጨስ የምትፈልግ ከሆነ ገሃነም ሄደህ አጭስ " በማለት አባረረኝ ፥ ለመሆኑ ለአንተ እንዴት ለፈቅድልህ ቻለ ? " በማለት ተየቀው ።
ጓደኛውም ፈገግ ብሎ " መጀመሪያ ምን ብለህ እንደጠየከው ልትነግረኝ ትችላለህ ? " በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መለሰ ።
እሱም " የእኔ ጥያቄ ከዚህ ጋር ምን ያገናኘዋል ? " አለው
ጓደኛውም " እሱን ቦሃላ እነግርካለሁ በቅድሚያ ግን ምን ብለህ እንደጠየከው ማወቅ እፈልጋለሁ" አለው
" በቀላሉ ላስረዳው ፈልጌ በቀን ሁለት ሰአት ያክል የጸሎት ጊዜ እንዳለን ታውቃለህ . . . . . በእነዚህ ሰአታት ከአትክልቱ ስፍራ እንድንሄት የተፈቀደ ነው ፥ ስለዚህ እየጸለይኩ ሲጋራየን ማጨስ እችላለሁ " በማለት ነበር የጠየኩት አለው ።
በዚህ ጊዜ ጓደኛው "አየህ ! ሃዳብህ በሊቀ ካህኑ ፍርሃት ተይዟል እና አጠያየቅህንም እንዲሁ በተሳሳተ መልክ አቀረብከው ። እኔ ግን በሃሳቤ ስለ ሊቀ ካህኑ አስቀድሜ የወሰንኩት ነገር ቢኖር ሲጃራ ማጨሴን እንደማይቃወም ስለነበረ ጥያቄየን በዚህ ሃሳብ መሰረት አቀረብኩለት " ጌታዮ!! ሲጃራ በማጨስበት ጊዜ መጸለይ እችላለሁን ??" አልኩት ። እሱም ተደስቶ " በሚገባ እንጅ . . . .በማንኛውም ጊዜ ፈጣሪህን ማሰብ የተገባ ነው " በማለት ፈቀደልኝ ብሎ እየሳቀ ወደ ሲጋራ ማጨሱ ተመለሰ ።

ጥበብ ቅጽ ( 2 )
ገጽ 29 - 31
ሃይለጊዮርጊስ ማሞ

ማንኛውም ሰው የሃሳቡን ፍሬ እንደሚበላ ምንም ጥርጥር የለውምና አእምሯችን የሚወልዳቸውን ሃሳቦች በሚገባ ማጤን እና የተሻለውን መርጦ መጓዝ የተሻለ ነገን እንድንኖር ያደርገናል ባይ ነኝ

tgoop.com/phillosophy/1470
Create:
Last Update:

BY ፍልሥፍናና የህይወት እውነታ

Share with your friend now:
tgoop.com/phillosophy/1470

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Informative Activate up to 20 bots Choose quality over quantity. Remember that one high-quality post is better than five short publications of questionable value. Write your hashtags in the language of your target audience. To delete a channel with over 1,000 subscribers, you need to contact user support
from us

Telegram ፍልሥፍናና የህይወት እውነታ
FROM American