PHILLOSOPHY Telegram 1563
ወንጀለኛው
(ካህሊል ጂብራን)

፨፨፨

አንድ በርሀብ የተጎዳ፣ ፈርጣማ ሰውነት ያለው ወጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ተቀምጦ እጆቹን በመዘርጋት ረሃብና ሃፍረት እየሸነቆጡት በሚያሳዝን ዜማ ይለምናል። ምሽት ላይ ከናፍሮቹ እና ጉሮሮው ደረቁበት። እጁ ግን እንደሆዱ ባዶ ነበር። ከተቀመጠበት ተነስቶ ከከተማ ወጣና በአንድ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ በምሬት ያነባ ጀመር። ከዚያም ረሃብ ውስጡን እየሞረሞረው ግራ የተጋቡ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላካቸውና እንዲህ አለ፤ <<ጌታዬ ሆይ፣ ወደ አንድ ሃብታም ሄጄ ስራ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት። እሱ ግን ቡትቶዬን አይቶ ፊቱን አዞረብኝ። የአንድ ትምህርት ቤት በር አንኳኳሁ፣ ግን ባዶ እጄን ነበርና ችላ ተባልኩ። ቁራሽ ዳቦ የሚያስገኝልን የትኛውንም አይነት ስረ ሞከርኩ፣ ይሄ ሁሉ ግን ከንቱ ነበር። ተስፋ በመቁረጥ እንዲመፀውቱኝ ለመንኩ፣ መፅዋቾቹ ግን ተመለከቱኝና <ጠንካራና ሰነፍ ነው፤ መለመን አልነበረበትም> አሉኝ... <<ጌታዬ ሆይ፣ እናቴ የወለደችኝ በአንተ ፍቃድ ነው። አሁን መጨረሻው ከመድረሱ በፊት ምድር ወደ አንተ እንድመለስ ፈቅዳልኛለች።>>

ይሄን ጊዜ ፊቱ ተለዋወጠ። ብድግ አለና አይኖቹን በቁርጠኝነት አጉረጠረጣቸው። ከአንዱ የዛፍ ቅርንጫፍ ወፍራም አርጩሜ ቆርጦ ወደ ከተማዋ በመቀሰር ጮኾ ተናገረ። <<ያለኝን ድምፅ ሁሉ አጠራቅሜ ዳቦ ስጡኝ ብያችሁ ነበር። እናንተ ግን ችላ አላችሁኝ። አሁን በጉልበቴ አገኘዋለሁ! በፍቅር እና በርህራሄ ስም ለምኜያችኋለሁ፤ ስብዕና ግን ዋጋ አልነበረውም። አሁን በርኩስ መንፈስ ስም አገኘዋለሁ!>>
ዓመታት ሲያልፉ ወጣቱ ዘራፊ፣ ነፍሰ-ገዳይ እና የነፍስ አጥፊ ሆነ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ያጠፋል፤ ጉልበቱን በመጠቀም ብዙ ሃብት ሰበሰበ። ከግብረ-አበሮቹ አድናቆትን አገኘ፣ በሌሎች ሌቦች ተከበረ፣ በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተፈሪ ሆነ።

ሃብቱና በጉልበቱ ያገኘው ተፈሪነቱ፣ አሚሩ የከተማዋ ባለስልጣን አድርጎ እንዲሾመው አበቃው- ብልህነት የጎደላቸው አገረ-ገዢዎች አሳዛኝ ሥራ። ከዚያ በኋላ ስርቆት ህጋዊ ስራ ሆነ፤ ጭቆና በስልጣን ይደገፍ ጀመር፤ ደካሞችን ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሆነ እናም ዙፋኖች ይፈሩና ይከበሩ ጀመር።
#ስለዚህ ስግብግብነት ነካ ያደረገው ስብዕና አይናፋሮችን ወንጀለኛ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ነፍሰ-ገዳይ ያደርጋል፤ ስግብግብነት የጎበኘው ስብዕና ያድግና መልሶ ስብዕናን አንድ ሺ እጥፍ ጊዜ ያጠፋዋል!

፨፨፨

ምንጭ ፦ እንባ እና ሳቅ(Tears and Laughter)
ደራሲ ፦ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ

...ዋጋ የነሱት(ያሳጡት)ነገር ዋጋ ያስከፍላል...!

ለማንኛውም ሃሳብ አስተያየትዎ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/SSR60

@phillosophy @phillosophy

tgoop.com/phillosophy/1563
Create:
Last Update:

BY ፍልሥፍናና የህይወት እውነታ

Share with your friend now:
tgoop.com/phillosophy/1563

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

During the meeting with TSE Minister Edson Fachin, Perekopsky also mentioned the TSE channel on the platform as one of the firm's key success stories. Launched as part of the company's commitments to tackle the spread of fake news in Brazil, the verified channel has attracted more than 184,000 members in less than a month. The optimal dimension of the avatar on Telegram is 512px by 512px, and it’s recommended to use PNG format to deliver an unpixelated avatar. 4How to customize a Telegram channel? Private channels are only accessible to subscribers and don’t appear in public searches. To join a private channel, you need to receive a link from the owner (administrator). A private channel is an excellent solution for companies and teams. You can also use this type of channel to write down personal notes, reflections, etc. By the way, you can make your private channel public at any moment. Today, we will address Telegram channels and how to use them for maximum benefit.
from us

Telegram ፍልሥፍናና የህይወት እውነታ
FROM American