tgoop.com/proverbs_christians_tube/1039
Last Update:
ፍቅር ምንድን ነው?
1. ፍቅር ማለት አንዱ ሌላውን ለመርዳት. መሞከር ማለት ነው!!
- ፍቅር ማለት መስዋዕት መሆን ማለት ነው!!
2. ፍቅር ማለት መልካም ማለት ነው!!
√ ክፋት በፍቅር አለም ፈፅሞ የለም::
3. ፍቅር ማለት መልካም ቃላትን መለዋወጥ ማለት ነው!!
√ ፍቅር የሀጢዐትን ብዛት ይሸፍናል::
- 1ኛ ጴጥ. 4:8
4. ፍቅር ማለት በፍቅር(በትዳር) አጋር መካከል ያለ የይቅር ባይነት መንፈስ ነው::
√ ቂምን አይይዝም ብድር አይመልስም::
- 1ኛ ቆሮ 13:14-17
5. ፍቅር ማለት አንዱ ራሱን ለሌላው አሳልፎ መስጠትና መስዋዕት መሆን ማለት ነው!!
6. ፍቅር አንዱ ለሌላው ፈገግ ብሎ ደስታ ማሳየት ነው!!
7. ፍቅር ማለት አንዱ ሌላውን ማሞገስና ማመስገን ማለት ነው::
8. ፍቅር ማለት ስሜት ብቻ ሳይሆን አንዱ ለሌላው መልካም ነገሮችን ማሰብና ማድረግ ነው::
√ ፍቅር በስራ ይገለጣል!!
√ የባልና ሚስት ዋና ሀብታቸውና ንብረታቸው ወይም ቀሪ ገንዘባቸው በሞት እስኪለያዩ ድረስ የሚኖረው ፍቅር ነው!!
9. ፍቅር በጋብቻ ውስጥ ሆኖ አንዱ ሌላውን በግብረ ስጋ ግንኙነት ማስደሰትንም ያካትታል!
√ የግብረ ስጋ ግንኙነት ግን ፈፅሞ የፍቅር መለኪያ አይደለም::
10. ፍቅር ማለት አንዱ ሌላውን መታገስና ተስፋ አለመቁረጥ ነው::
√ ፍቅር ወደፊትም ተስፋ ያደርጋል!!
#ሼር
@proverbs_christians_tube
BY ProVerbS_Tube
Share with your friend now:
tgoop.com/proverbs_christians_tube/1039