Telegram Web
"ያገኘውን ሁሉ የሚበላ ሰው ጤናማ እንደማይሆን ሁሉ የሰማውን ሁሉ የሚወስድ ሰው አይምሮ የተበላሸ ይሆናል ፤ አንድ ግለሰብ በምግብ ቢመረዝ ቢበዛ ራሱን ነው የሚገለው። በሀሳቡ ቢመረዝ ግን ራሱን ብቻ ሳይሆን አከባቢን ያጠፋል ። አከባቢን ከማጥፋት ራሱን ለመታደግ አእምሮውንና ውስጡን ማፅዳት ይኖርበታል ።
ቀስት ወደ ፊት ሊስፈነጠር የሚችለው ወደ ኋላ በተለጠጠበት መጠን ነው።


ችግር ሲያጋጥምህ ደስ ይበልህ ከበፊቱ ወደ ተሻለው ልትስፈነጠር ነውና።ሁሌም ኢላማህን በመልካሙና በተሻለው ነገር ላይ ያነጣጥር!በፍጥነትም ትደርሳለህ።

ምርጥ ቀን ይሁንላችሁ 🙏🙏
ሁሉንም ታልፋለህ!

በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው።

ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ አንተ ከዛ በላይ ከባድ ነህ! ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት!

ማራኪ ቀን ተመኘንላችሁ🙏
ደስ የሚል በቀል!

እልህ ይዞህ ያውቃል? የሚንቁህና የበታችነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሰዎች ህይወትህን የቀን ጨለማ አድርገውት ያውቃሉ አይደል?

እሳትን ስትፈልግ ንብረት ለማውደም ትጠቀምበታለህ ስትፈልግ ደግሞ ምግብ ታበስልበታለህ፤ ታዲያ ለናቁህ ሰዎች ማንነትህን ለማሳየት ጠንክረህ ሰርተህ ራስህን ለውጠህ በስኬትህ የያዘህን እልህ ለምን አትወጣም?! የምድራችን ጣፋጭ በቀል በናቁህ ፊት የሚያስከብር ስኬት መጎናፀፍ ነው!

አሰደሳች ቀን ይሁንላችሁ 🙏
መነቀፍ አይግረምህ !

ሰዎች አስተያየት መስጠታቸውን አያቆሙም ፣ ልክ ስላልሆንክ መታረም ስላለብህ ብቻ ሳይሆን ለእነርሱ ምቹ ስላልሆንክም ነው ለምን የሚሉህ ! ስለዚህ መገረም አቁም ለምን እንደዚህ አሉኝ አልረባም ልክ አልሰራውም ማለት ነው ብለህ አትጨነቅ ፈጣሪህን እያመንክ መንገድህን ቀጥል ! የሚጠቅምህን ግን አገናዝበህ ውሰድ !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
ለራስህ ቃል ግባ!

ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈን እናውቃለን ወደፊትም እናልፍ ይሆናል።

ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠህ ጥረትህን እንደማታቆም ለራስህ ቃል መግባት ነው!

ተስፋ የሞላበት ዉሎ ተመኘሁላችሁ🙏
በህይወት ስትኖር ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች

1. የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው።
2. ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ።
3. ስትፈልገዉ ያጣከውን ሲፈልግህ ታገኘዋለህ ።
      
ድንቅ ቀን ተመኘንላችሁ 🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
መነቀፍ አይግረምህ !

ሰዎች አስተያየት መስጠታቸውን አያቆሙም ፣ ልክ ስላልሆንክ መታረም ስላለብህ ብቻ ሳይሆን ለእነርሱ ምቹ ስላልሆንክም ነው ለምን የሚሉህ ! ስለዚህ መገረም አቁም ለምን እንደዚህ አሉኝ አልረባም ልክ አልሰራውም ማለት ነው ብለህ አትጨነቅ ፈጣሪህን እያመንክ መንገድህን ቀጥል ! የሚጠቅምህን ግን አገናዝበህ ውሰድ !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
ሳናውቅ አንፍረድ...

በአንድ መንደር ውሰጥ ይኖር የነበረ አንድ ትልቅ አርቲስት ነበር ፤ ይኼም አርቲስት ስራዎቹን በመሸጥ የተሻለ ክፍያ ያገኛል። ታዲያ በአንድ ወቅት በአካባቢው የሚኖሩ ድሃዎች ተሰባስበው ወደ አንጋፋው አርቲስት ጋር በመሄድ እንዲህ አሉት፦
"አንተ ለምንድነው የአካባቢውን ሰዎች የማትረዳው? አንተ ከሁሉም የተሻለ ገቢ አለህ። ካንተ ያነሰ ገቢ ያላቸው ዳቦ ጋጋሪውና ባለ ልኳንዳው ስጋ ሻጩ ለአካባቢያችን ድሆች በነጻ ይሰጣሉ በማለት ጠየቁት?
    አርቲስቱም ፈገግ አለ በሁኔታው ሰዎቹ  ግራ ተጋብተውና  ተናደው ጥለውት ወጡ። ነግርግን ሌላ ቀን ወደ ውጭ ሲወጣ ጠብቀው ደበደቡት ፤ እድሜው የገፋ ነበረና በዚያው ታሞ አንድ ጠያቂ እንኳ ቤቱ ሳይመጣ በዚያው ሞተ።
    ሆኖም ከዚያም ቀን በኋላ ዳቦ ሻጩም ስጋ ሻጩም በነጻ መስጠት አቆሙ። የአካባቢው ሰዎች ግራ ቢገባቸው ምከንያቱን መጠየቅ ጀመሩ። ያገኙትም ምላሽ ያ አንጋፋው አርቲስት በየወሩ በነጻ እንድንሰጥ ብዙ ብሮችን ይሰጠን ነበር ፤ አሁን ግን ስለሞተ አገልግሎቱ መስጠት እንደማይችሉና  እንደተቋረጠ ተነገራቸው።
    ብዙዎቻችን በሰዎች ላይ በቂ መረ8ዳት ሳይኖረን የተሳሳተ ግንዛቤ ሊኖረን ይችላል።
  አንዳንዴ ነገሮች እንደምናየቸው አይደሉም በሰዎች ላይ ለመፍረድ አንቸኩል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
# ሚስት ባሏን ,,,,,,,,,

#ሚስት_ባሏን_ልትፈትን! ፈለገች ከእኔ ተለይቶ ሲያድር ወይም ድንገት ከቤት ሲያጣኝ ምን ይሰማቸዋል?የሚለውን ለማወቅ አቀደችና ባሌቤቷ ከስራ በሚመለስበት ሰአት ጠብቃ አልጋ ስር ተሸሸገች።በብጣሽ ወረቀት ቤተሰቦቼጋ ሄጃለሁ።አልመጣም አትጠብቀኝ  የሚል ማስታወሻ  ፅፋ ኮሚዲኖ ላይ አስቀምጣ አልጋ ስር ገባች።ባል ወደቤት ሲገባ ባለቤቱ የለችም።

ወረቀቱን አነበበና እሱም መልስ ጫር ጫር አድርጎ ወረቀቱን ያገኝበት ቦታ አስቀምጠው እና ልብሱን ቀይሮ እንደጨረሰ ሞባይሉን አንስቶ ሄሎ ሄሎ ፍቅሬ የእኔ ማር እዴት ነሽልኝ ዛሬ ምርጥ ጊዜ እናሳልፋለን።ባለቤቴ ቤተሰቦቿ ጋር ሄዳለች አትመጣም።......አንቺን ኮ ማር ነሽ .....እሷን ሳላገባ ባውቅሽ ኖሮ እሷን አላገባም ነበር....ከአምስት ደቂቃ በላይ አልቆይም ዝግጁ ሁነሽ ጠብቂኝ መጥቼ ወስድሻለሁ.......ባይ የኔ ጣፋጭ ብሎ ወሬውን ጨርሶ ተነስቶ ወጣ።ሚስት አልጋ ስር ሆና ቅጥል ብግንግን ብላለች ....ልክ እንደወጣች አፍናው የቆየችውን ለቅሶዋን አፈነዳችው .....ከዚያ ምንባቱ ነው ፅፎ ያስቀመጠው .....አለችና ወረቀቱን አንስታ ስታነበው ....ቂሎ ባንቺ ቤት መሸወድሽ ነው አይደል እግሮችሽን ገና ስገባ ነው ያየሁት .....በይ እራት ገዝቼ መጣለሁ እንባሽን ታጥበሽ ......እሽቅርቅር ብለሽ ጠብቂኝ  ።

#🙏🙏አሪፍ ቀን ተመኘሁ🙏🙏🙏
2025/02/06 06:27:19
Back to Top
HTML Embed Code: