tgoop.com/sebeer_zena/2661
Create:
Last Update:
Last Update:
#COVID19
በቻይና በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተይዘዉ ካገገሙ ህሙማን 14 በመቶ የሚሆኑት ድጋሚ ሲመረመሩ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
የሃገሪቱ የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት ቀደም ሲል በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው አገግመዉ በወጡ ታማሚዎች ላይ ምርመራ ሲደረግ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህም የጤና ባለሙያዎችን አስደንግጧል፡፡
ባለሙያዎቹ እንዳሉት በቫይረሱ ተይዘዉ ከዉጭ በሚገቡና ቫይረሱ በሰዎች ላይ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ በመቆየት በሀገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ስጋታቸዉን እየገለጹ ነዉ፡፡
በዚህም በመጀመሪያ ወረርሽኙ የተቀሰቀሰባት የሁቤ ግዛት ነዋሪዎች የእንቅስቃሴ ገደቡ መነሳቱን ተከትሎ በስጋት አካባቢዉን ለቀዉ ወደ ሌላ ቦታ እየተሰደዱ መሆኑን ዴይሉ ሜይል ዘግቧል፡፡
More https://telegra.ph/COVID19-03-26
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም [ሙሉቀን አሰፋ]
BY ሠበር ዜና

Share with your friend now:
tgoop.com/sebeer_zena/2661