tgoop.com/sebeer_zena/2679
Create:
Last Update:
Last Update:
የታማሚዎች ሁኔታ ፦
- በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ (5) ከአዲስ አበባ ሲሆን አንድ (1) ከድሬዳዋ ነው።
- በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
- በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን የመጀመሪያው የ35 ዓመት ወንድ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጣ ነው። ሁለተኛው የ30 ዓመት ወንድ በተመሳሳይ ከዱባይ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም የመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሁለቱም አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የገቡ ናቸው።
- ሶስተኛው የ28 ዓመት ወንድ፤ አራተኛውም የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ ነው።
- ስድስተኛዋ ሰው የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት ነበራት።
@Sebeer_zena
BY ሠበር ዜና
Share with your friend now:
tgoop.com/sebeer_zena/2679