tgoop.com/sebeer_zena/2770
Last Update:
የ4 ሰዎችን ህይወት ያጠፋው የፌዴራል ፖሊስ አባል!
ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረ ጊዜአዊ አለመግባባት የ4 ግለሰቦችን ህይወት በመሳሪያ ተኩሶ ያጠፋው የፖሊስ አባል ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽ አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪው የግድያ ወንጀሉን የፈፀመው መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጨርጨር ጊርጊሮስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ተጠርጣሪው ረዳት ሳጅን መልህቁ መኪ የተባለ የፖሊስ አባል ሲሆን ከባለቤቱ ጋር በትዳር ለሁለት አመት አብረው ሲኖሩ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ከ15 ቀን በፊት ባለቤቱ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ሄዳለች።
ከባለቤቱ እንዲሁም ከቤተሰቦቿ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል ለስራ የታጠቀውን ክላሽ ኮቭ መሳሪያ ይዞ ወደ ባለቤቱ ቤተሰቦች ቤት በመሄድ ፦
- የሚስቱን እናት ፣
- የእንጀራ አባቷን ፣
- የእህቷን ባል እና የቤት ሰራተኛን በአጠቃላይ 4 ግለሰቦችን ተኩሶ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል፡፡
የአዲስ አመት የበዓል አከባበር በሰላም እንዲከወን መላው የፖሊስ አባላትና የፀጥታ ሃይሉ ሌት ከቀን ሃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት ሲፈፅሙ ብለሹ ስብዕና ባለው አንድ የፖሊስ አባል በተፈፀመው ተግባር የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽ በእጅጉ ማዘኑን ገልጿል።
ድርጊቱ የፖሊስ አባላቱን እንዲሁም የፀጥታ ሃይሉን የማይወክል መሆኑንም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
BY ሠበር ዜና

Share with your friend now:
tgoop.com/sebeer_zena/2770