SEHKALIDERASHID Telegram 1063
╔═══════════════╗
ኢብራሂም አወድ ኢብራሂም አል-በድሪ
(አቡበክር አልባግዳዲ) ክፍል 2
╚═══════════════╝

ኮማንዶዎቹ የጨለማ መዋጊያ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ሮኬቶችና ሚሳይሎች ውሾችና ሮቦቶችን ጭምር ጭነዋል። የበረራ ግዳጃቸው በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በምትገኘው የባሪሻ መንደር እንደሆነም አውቀውታል። የተመረጡት የዴልታ ኃይል አባላት ከሁለት ሳምንታት በፊት ጀምሮ ልዩ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሄሊኮፕተሮቹ የሞት መልዕክተኛ ይመስል ወደ በሪሻ መንደር በረሩ። ጥቅምት 15 ቅዳሜ ምሽት 5:00 ሰዓት ግድም ሄሊኮፕተሮቹ ሞተራቸውን ሲያሞቁ አሜሪካ ለቱርክ ለሩሲያ ለሶሪያና ለኢራቅ በአየራችሁ ክልል ላይ እየበረርን ነውና እንድታውቁት የሚል መረጃ እያስተላለፈች ነበር። ሄሊኮፕተሮቹ የጦር መሳሪያ ጭነው ዝቅ ብለው በሚበሩበት ወቅት ያለእነዚህ ሀገሮች ፍቃድ ማለፍ አስቸጋሪ ነበር። ትራምፕም እነዚህን ሀገሮች እግዜር ይስጣቸው ሲሉ አመስግነዋቸዋል።
በሪሻ በሰሜን ምዕራብ የምትገኝ ትንሽ መንደር ናት። በአይኤስ ይዞታ ስር ቆይታ በኋላ የበሽር መንግስት ተቃዋሚ በሆነውና በአሜሪካ በሚደገፈው የሶሪያ ዲሞክራቲክ ጥምር ኃይሎች ይዞታ ስር ወድቃለች። ኩርዶችም በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ። ወታደሮቹ በሪሻ መንደር ደርሱ። በምዕራብ በኩል የሚገነጠለው አቧራማ መንገድ 5 ኪ.ሜ ፈንጠር ብሎ ከተሰራው ግንብ ቤት ያደርሳል። በጥብቅ ግንብ ቤት የተስራው ሰፊው ቤት በረጅም አጥር ተከቧል። ከቤቱ ጋር ተያይዞ የመሬት ውስጥ ዋሻ ተቆፍሯል። ከግንቡ ወጥቶ ወደ ዋሻው በመተላለፍ ከአየር እና ከሌላ ጥቃት ለመመከት እንዲቻል ታስቦ የተሰራ ነው። የባሪሻ መንደር ሰዎች ጭልል ባለ በረሃ ለፀሀይ የማይስብ አይነት ሆኖ በተሰራው ግንብ ቤት ውስጥ ማን እንደሚኖር አያውቁም።
የባሪሻ ምሽት ጨለማውን አንግሶ ፀጥ ባለበት ሰዓት ስምንቱ ሄሊኮፕተሮች አየሩን እየሰነጠቁ ወደዚያች መንደር እየገሰገሱ ነበር። የአሜሪካ ርዕሰ ብሄር መቀመጫ በሆነው የኋይት ሃውስ ቤተመንግሥት አነስተኛ ክፍል ውስጥ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከምክትላቸው፣ ከመከላከያ ሚንስትራቸውና ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጋር ተቀምጠው የሄሊኮፕተሮቹን በረራ ይከታተላሉ። በረቀቀ ቴክኖሎጂ ምስልና ድምጽ በሚያሰራጨው መሳሪያ ዘመቻውን ፊልም እንደማየት አይነት በትኩረት እየተከታተሉ ነበር። ዕለቱ ለነርሱ የቁርጥ ቀን ስለሆነ አይናቸውን ሳይነቅሉ የሚሆነውን ሁሉ ይከታተላሉ። ሄሊኮፕተሮቹ በተዋጊ ጀቶችና በጦር መርከቦች ሽፋን ተሰጥቷቸዋል።
ወደ ግቢው ደርሰው አዘቅዝቀው መውረድ ሲጀምሩ ግቢውን ከሚጠብቁ ታጣቂዎች ጥይት ተቀበላቸው። አሜሪካኖቹ የፈሪ ዱላ አፀፋዊ ምላሽ ሰጡ። በሄሊኮፕተሮቹ ላይ የተጫኑት ሮኬቶች ሲተኮሱ ግቢው በፍንዳታ ተሞላ። በዋናው መዝጊያ በር በኩል ልዩ ጥበቃና የፈንጂ አጥር ሊኖር ይችላል ብለው ስለገመቱ በኋላ በኩል አጥሩን ደረመሱና ወደ ውስጥ ዘለቁ። ልዩ ኮማንዶዎቹ ለዚህ ግዳጅ ያሰለጠኗቸውን ውሾች ይዘው አቡበከር አልባግዳዲ አለ ብለው በጠረጠሩት ክፍል ለመድረስ ተጣደፉ። ግቢውን የሚጠብቁት አጃቢዎችም በአልሞ ተኳሾች ተገለው ከጌታቸው ጋር ተገናኙ። በተኩሱ መካከል አቡበከር አልባግዳዲ ፈንጂ የተጠመደበትን ሰደርያውን ለብሶ በዋሻው ስር ጉዞ ጀመረ። ወታደሮቹ ወደ ዋሻው የዘለቀውን ሰው ከአነፍናፊ ውሾቻቸው ጋርና ፓውዛ በተገጠመላቸው አልሞ ተኳሾች ጋር ተከትለውት ገቡ። ከዋሻው ውስጥ መሬት የሚንጥ ድምጽ ያለው ፈንጂ ዋሻውን የላይኛውን ወደታችኛው እስኪገለባበጥ ድረስ አደበላለቀው። አቡበከር አልባግዳዲ ራሱ ላይ ባጠመደው ፈንጂ ራሱን ገደለ። በተኩሱ ልውውጥ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልተነገረ ተዋጊዎች ሞተዋል። አራት ሴቶችም ተገድለዋል። ኮማንዶዎቹ አካባቢውን ሲመረምሩ ለ2:00 ሰዓት ያህል ቆይተው ወደነበሩበት ለመመለስ ተዘጋጁ። ሲመለሱ ያን ቤትና አጥር ምን ላይ ነበር ተብሎ ደብዛው እስኪጠፋ ድረስ በሚሳኤል አወደሙት። አንዳችም ምልክት ሳይቀር የተደለደለ መሬት አደረጉት። ይህን ማድረጋችን ተከታዮቹ እንደ እምነት ቦታ አድርገው እንዳይዙት ነው በማለት ጀነራል ኬንዝ ተናግረዋል። አንድ አነፍናፊ ውሻ ጉዳት በማስተናገዱም ፕረዝዳንት ትራምፕ የቆሰለውን ውሻ በትዊተር ገጻቸው ፎቶግራፉን ለጥፈው ጀግና ሲሉ አወደሱት።
ለዘጠኝ አመታት ሲፈለግ የነበረው በተለይም ባለፉት ስድስት አመታት ከአፍሪካ እስከ አውሮፓ የሚኖሩትን ህዝቦች በእስልምና ሸሪዓ አስተዳድራለሁ በሚል መርሁ የሚታወቀው፣ የሶርያና የኢራቅ ግዛቶች ሉአላዊ የአገር ኸሊፋ ነኝ በማለት ያወጀው አቡበከር አልባግዳዲ በዚህ አይነት መልኩ ህይወቱ መደምደሙን በርካቶች ዘግበውታል።
የአይኤስ አዲሱ መሪ ኢብራሂም አልሐሺም እንደሚሰኝ እና ሁሉም ሙስሊሞች ታማኝነታቸውን እንዲያረጋግጡለት ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ስለ ሐሺም ማንነትና ስላለፈው ተግባሩ ግን ዝርዝር መግለጫን አልሰጡም።
አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው ያለፈ ወንጀሉንም ይማረው
ተ - ፈ - ፀ - መ

═════════════════
ይህ የዩቱዩብ ፔጄ ነው ሰብስክራይብ አድርገው የጀግኖችን ታሪክ ይከታተሉ
👇👇
https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA

ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንቴ ነው
👇👇👇
http://www.tgoop.com/sehkaliderashid
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like Comment Share
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት
╚═══════════════╝

tgoop.com/sehkaliderashid/1063
Create:
Last Update:

BY የሼኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች

Share with your friend now:
tgoop.com/sehkaliderashid/1063

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Clear Unlimited number of subscribers per channel For crypto enthusiasts, there was the “gm” app, a self-described “meme app” which only allowed users to greet each other with “gm,” or “good morning,” a common acronym thrown around on Crypto Twitter and Discord. But the gm app was shut down back in September after a hacker reportedly gained access to user data. Among the requests, the Brazilian electoral Court wanted to know if they could obtain data on the origins of malicious content posted on the platform. According to the TSE, this would enable the authorities to track false content and identify the user responsible for publishing it in the first place. With Bitcoin down 30% in the past week, some crypto traders have taken to Telegram to “voice” their feelings.
from us

Telegram የሼኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች
FROM American