SEWMEHONETH Telegram 247
የመፀዳጃ ቤት ወግ!
«ዘውድአለም ታደሠ»

መስሪያ ቤታችን ውስጥ ያሉት መፀዳጃ ቤቶች እንደብዙሃኑ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶቻችን ከመፀዳጃነት ባለፈ እንደሃሳብ መስጫ ሳጥንነትም ያገለግላሉ። በርና ግድግዳው ላይ የማይፃፍ ነገር የለም። የኛ ህዝብ ሽንት ቤት ሲቀመጥ ወደደራሲነት የሚለወጠው ታሪክ አለ። አረ ሁን ብሎ ፓርከር ይዞ ሚገባ ሁሉ አለ።
በርግጥ ሰው ከበላና ከጠጣ ሽንት ቤት መቀመጡ አይቀርም። ሞዴል ሆነች ታዋቂ ዘፋኝ ፣ ቄስ ሆነ ፓስተር፣ ሃብታም ሆነ ደሃ ሁሏም በቀን ለተወሰነ ደቂቃ ሸኖ ቤት ዱቅ ትላለች። አንዳንዴ ሳስበው ሰውን እኩል የሚያደርገው ሞትና ሽንት ቤት ይመስለኛል

የመፀዳጃ ቤት ግድግዳና ፌስቡክም አንድ ናቸው። ሁሉም በነፃነት ሃሳቡን እንደወረደ ተንፍሶ ውልቅ ይላል።
ያው እኔም በገባሁ ቁጥር ግድግዳና በሩ ላይ የሚፃፉትን ፅሁፎች እያነበብኩ ዘና እላለሁ። አንዳንዴም ፃፍ ፃፍ አረጋለሁ :)

ዛሬ መስሪያ ቤት ያሉት ሶስቱም መፀዳጃዎች በራቸው ተዘግቶ ደረስኩ። ሽንት ቤቱ የግሌ ይመስል በሌላ ሰው ሲያዝ ለምን እንደምበሳጭ አይገባኝም :) ደሞ ክፋቱ የቤት አከራይና ሸኖ ግዜ አይሰጡም :) ሁሉም እንደተያዙ ባውቅም ጠጋ ብዬ የመጀመሪያውን በር አንኳኳሁ። በሃበሻ ባህል የሽንትቤት በር ማንኳኳት ማለት «ሰው አለ ወይ?» ማለት ሳይሆን «ሰውዬ ቶሎ ውጣ» ማለት ነው። ደጋግሞ ማንኳኳት ደግሞ «ሰውዬ የሽንትቤቱ መቀመጫኮ ስልጣን አይደለም ምን ይጎልትሃል?» ማለት ነው :)

የመጀመሪያውን በር ሳንኳኳ አንድ ሰላላ ድምፅ «ሰው አለ» አለኝ። ማንነቱን በድምፁ አወቅሁት። ምክትል ስራ አስኪያጃችን ነው። ይሄ ሰውዬ አንዴ ከገባ አይወጣም። እንደውም ግድግዳው ላይ በቀይ እስክሪብቶ ረጃጅም ግጥም ሚፅፈው እሱ ሳይሆን አይቀርም። :)

የሚቀጥለውን በር ሄጄ አንኳኳሁ። «ሰው አለ» አለኝ ወፈር ያለ ሻካራ ድምፅ። እሱንም በድምፁ ለየሁት። የእቃ ግዢ ክፍሉ ሃላፊ ነው። ፀባዩ እንደድምፁ ሻካራ ነው። በዚያ ላይ በገንዘብ ብክነት ብዙ ግዜ ተገምግሟል። ሆኖም የቀድሞው ማኔጀር ዘመዱ ስለነበር በማስጠንቀቂያ ነበር ሚታለፈው። አሁን ግን ማኔጀሩ ከቦታው ስለተነሳ እየጨነቀው ነው መሰለኝ ሽንት ቤት መመላለስ አብዝቷል። በየትኛውም ሰአት ብትመጡ የምታገኙት እሱን ነው። ልክ እንደ ናይት ክለብ ሽንት ቤት ሁሉ እየቀያየረ ይቀመጣል :) (እኔ ደሞ ሳጋንን ለነገ አልልም)

ሶስተኛውን ክፍል ሳንኳኳ «አለን» የሚል የሴት ድምፅ ሰማሁ። ጆሮዬን ስላላመንኩ ደግሜ አንኳኳሁ። «አረ ሰው አለ ጌታው መቼስ ተጠጋግተን አንቀመጥ» አለችኝ። ገኒ ነች። የመስሪያ ቤታችን ክሊዮፓትራ!
የወንዶች ሽንት ቤት መጠቀሟ ስለገረመኝ «ገኒ በሰላም ነው እኛ ጋር የመጣሽው?» ስላት እየሳቀች
«ዜድዬ እና ልፈንዳልህ እንዴ? ሴቶቹ እንደው አንዴ ከተቀመጡ ሽንት ቤቱ ለልማት ካልተፈለገ አይነሱ! ቢቸግረኝ እናንተጋር መጣኋ! መቼስ እቺን ሰራች ብላችሁ አትገመግሙኝም» ስትል ምክትል ማኔጄሩ ጮክ ብሎ
«ደና ዋልሽ ገኒ» አላት። (ያው ሰምቼሻለሁ ለማለት ነው)
«ደና ዋሉ አቶ ታምራት» አለች ደንገጥ ብላ
«እግዚሐር ይመስገን ስራ ጥሩ ነው?» አላት
«ጥሩ ነው ይመስገነው» አለች።
«እንዴት ነው ባለፈው ያዘዝኩሽን ስራ ጨረስሽ?» ሲላት ትግስቴ አለቀ።
«ሰውዬ ምን ነካህ? ሽንት ቤት ውስጥ ብዙ ስትቆይ ቢሮህ መሰለህ እንዴ?» ልለው አሰብኩና ከእንጀራ ገመዴ እንደሳር ሲነቅለኝ ታይቶኝ ዝም አልኩ!

ወዲያው ገኒ ወጣች! በስመአብ ዛሬ ደሞ እንዴታባቷ ነው ያማረባት? የሆነ ከሽንትቤት ሳይሆን ከስቲም ቤት የወጣች ነው ምትመስለው። ደሞ ሽቶዋ!
እጇን እየታጠበች ፈገግ ብላ «ሰላም ነው?» አለችኝ። ድምጿ ራሱ ሰላም አለው። እጆቿ አጥንት ያላቸው አይመስሉም። አለ አይደል በደም ተሞልተው በለስላሳ ቆዳ የተወጠሩ ነው ሚመስሉት።
ገኒ ውብ ነች! ውበቷን እንደመሰላል ብትጠቀም የትና የት እንደምትደርስ እናውቃለን። የድሮው ማኔጃራችን በፍቅሯ ጠብ ብሎ ሊጠብሳት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በቀን አስር ግዜ ነበር በሰበብ አስባቡ ቢሮው ሚያስጠራት። ምንም ሴልስ ኦፊሰር ብትሆንም ቢሮው አስጠርቶ ስለማይመለከታት ጉዳይ ያወራታል። አንድ ሰሞን የሻይ ሰአት ላይ የሚላትን እየነገረች ታስቀን ነበር። ቢሮው ባስቸኳይ ያስጠራትና
«እኔ ምልሽ ገኒ! የሰሜን ኮሪያና የአሜሪካን ፍጥጫ ከሙያሽ አንፃር እንዴት ታይዋለሽ?» ይላታል።
ሌላ ግዜ ደግሞ ከመሬት ተነስቶ «እንዴት ነው ሰሞኑን ፊትሽ ጥሩ አይደለም ያስቀየመሽ ሰራተኛ አለንዴ?» ይላታል። አዎ ብላ አንዱን ብትጠቁመውኮ ያለማስጠንቀቂያ ሊጭረው ነው :)
ብቻ ያቅሙን በስልጣኑም በፍራንኩም ሊያሰምጣት ሞክሮ ሳይሳካለት መስሪያቤቱን ለቀቀ!
(አንዳንዴኮ ቆንጆ ሴቶችን እንደጉሊት እቃ ገንዘብ ያለው ሁሉ ሚሸምታቸው ይመስለናል እንጂ ከአይናቸው ይልቅ እይታቸው ከከንፈራቸው ይልቅ ንግግራቸው የተዋበ እልፍ ሴቶች አሉኮ የምር)
አልዋሻችሁም አንድ ሰሞን እኔም ገኒን ልጠብሳት ተፍ ተፍ ብዬ ነበር። በርግጥ ከገኒ በፊትም መስሪያ ቤታችን የምትሰራ ሌላ ልጅም ወድጄ ነበር (ጥሎብኝ ፍቅር ያጠቃኛል መሰለኝ :D )
የመጀመሪያዋ «አይ ዜድዬ ጥሩ እህትህ ብሆን ይሻላል» ብላ ጨጓራዬን ላጠችው! ሴቶች ግን ካልፈለጋችሁ ለምን አልፈልግም እንደማትሉ ግራ ይገባኛል። «እናቱ እኔ ያሉኝንም እህቶች በአደራ ሚረከበኝ እያፈላለግኩ ነው። የምፈልገው ተጨማሪ እህት ሳይሆን ፍቅረኛ ነው» ብዬ ነካሁት :)

ገኒ ግን እህት ምናምን የሚል ግርግር ሳታበዛ «ዜድ you can't be my future husband» አለችኝ።
“why” ስላት
“because i know that u'r not ready for marriage እኔ ደሞ በዚህ እድሜዬ ተቃቅፎ ካፌ ለካፌ መዞር ምናምን አልፈልግም?” አለችኝ። አልተከራከርኩም! ሂሴን ውጬ ተሸበለልኩ ;)

ወደመፀዳጃ ቤት ገብቼ እንደለመድኩት በሩ ላይ የተፃፉትን አዳዲስ ፅሁፎች ማንበብ ጀመርኩ። ህዝቤ በግዜ ፃፍ ፃፍ አርጎ ወጥቶላችኋል።
«ወገን! የፖለቲካው ሁኔታ አያሳስባችሁም ግን?»
ከሚል ፅሁፍ ስር «አንተ የደላህ ነህ ልጄ። እኔ ምለው ደሞዝ አይወጣም እንዴ ወይስ እሱንም እንደምርጫው ይራዘም ሊሉ ነው?» የሚል መልስ ተፅፏል።
«ጌታቸው አሰፋ ውስጤ ነው» ከሚል ፅሁፍ ስር ደሞ «አደራ እዛው ይኑር እኛ መስሪያቤት እንዳትፀዳዳው» ብሎታል አንዱ ተንከሲስ!

አንድ የተበሳጨ ሰራተኛ ደሞ «ስራ አስኪያጁን አንድ ቀን እደፈጥጠዋለሁ» ብሎ ከፃፈው ስር
«አንተ የሰርቪሱ ሹፌር በቀለ ነህ አውቄሃለሁ» ተብሏል። ወረድ ብሎ «እናቴ ትሙት እኔ አይደለሁም» ብሏል በቄ :)

ጥግ ላይ ደሞ አንዱ የዋህ በእርሳስ «እባካችሁ ወገኖቼ ንስሃ ግቡ» ብሎ ፅፏል ። ከሱ ጎን
«እስቲ መጀመሪያ በግዜ እንግባ» የሚል መልስ ተፅፏል። (ይሄን መልስ የፃፈው ዘገየ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። ዘገየ ቅምቀማ በጣም ከመውደዱ የተነሳ ቺክ ሲተዋወቅ ራሱ «ለምን ደብል ጅን በደረቁ እየጠጣን አናወራም?» ብሎ ነው ሚጀምረው)

ሌላ ሌላውንም ሳነብ ቆየሁ። ተረብ፣ ቀልድ ግጥም ሁሉም ነገር ተፅፏል። አንዳንዴ የስራ ባልደረቦቼ የባከኑ ደራሲዎች ሚመስሉኝኮ ለዚህ ነው። ጉዳዬን ጨርሼ ልወጣ ስል እኔም ስለተወሰወስኩ እስኪሪብቶዬን ከኪሴ አወጣሁና አንዲት ግጥም ፃፍኩ ..

ዶሮ ተወደደ
በጉ ተወደደ
በሬም ተወደደ
ብሎ ይተክዛል ፥ ሄዶ የጠየቀው
እኔን ምን ቸገረኝ ፥ ያገባ ይጭነቀው! :)
@sewmehoneth
Any comment 👉 @hundaolbot

tgoop.com/sewmehonEth/247
Create:
Last Update:

BY ሰው መሆን 🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/sewmehonEth/247

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

During the meeting with TSE Minister Edson Fachin, Perekopsky also mentioned the TSE channel on the platform as one of the firm's key success stories. Launched as part of the company's commitments to tackle the spread of fake news in Brazil, the verified channel has attracted more than 184,000 members in less than a month. How to Create a Private or Public Channel on Telegram? Select “New Channel” 2How to set up a Telegram channel? (A step-by-step tutorial) Deputy District Judge Peter Hui sentenced computer technician Ng Man-ho on Thursday, a month after the 27-year-old, who ran a Telegram group called SUCK Channel, was found guilty of seven charges of conspiring to incite others to commit illegal acts during the 2019 extradition bill protests and subsequent months.
from us

Telegram ሰው መሆን 🇪🇹
FROM American