tgoop.com/sewmehonEth/407
Last Update:
"ዛሬ ወደ ራሴ የሚመልሰኘ አስገራሚ ታሪክ ገጠመኘ፡፡"
በእልፍ አእላፋት ጥልፍልፍ መስመሮች የተሞላውን የዕጣ-ፈንታ ሰንጠረዥ የሰው ልጅ እንዴት ሊረዳው ይቻለዋል?.....ጥቂቱን እንኳን መረዳት መቻል ትልቅ ስጦታ ነው፡፡
ከዚያ የላቀ መረዳት ግን ተዓምር ነው ሊባል ይገባል፡፡
ከወራት በፊት በነበረኘ ግንዛቤ "የሁሉም ነገር ዕጣ-ፈንታ በፈጣሪ መዝገብ ተከትቧል፡፡"
የሚለውን ነገር በከፊል ስቀበል በከፊል ደግሞ አይዋጥልኘም ነበር፡፡ "የአንድ ሰው ነፍሰ ገዳይነት ቀድሞውንም በዕጣ ፋንታ መዝገቡ ላይ ተፅፎ ከሆነ ፣ ያሰው ከመወለዱ በፊት የተፃፈውን ዓይነት ሰው ከመሆን ውጪ አማራጭ ላይኖረው ነው፡፡ ታዲያ በምንም ዓይነት መልኩ ነፍሰ-ገዳይነቱን ሊገታው ካልቻለና ከተፃፈው ውስጥ ጠብ የሚል ነገር ከሌለ፣ እንደምን 'ነፍሰ-ገዳይ' ተብሎ ከገሃነም ይጣላል?" ብዬ ነው ምሟገተው፡፡
ከዚህም ሌላ አንደ ሰው ሲሞት፣ እንዲህ ቢያደርግ ኖሮኮ!...ወይም ይሔን ቢያደርግ ኖሮ ይተርፍ ነበር፡፡ ሲባል ሁሌም ምላሹ 'አይ!....ምንር ቢደረግ ፈጣሪ ቀድሞ ከቆጠረለት ቀን አንዲትም ሰከንድ መጨመር አይቻል!" የሚል ነው፡፡
ይሄ አባባል የሚገልፀው፣ የሁሉም ሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተቆጠረና ከቀኗ ውልፍት አንደማትል ነው፡፡ ይሔም አንደማይዋጥልኘ ምክንያቴን አቅርቤ እሟገት ነበር፡፡
ምክንያቴም "እንደ ኢትዮጵያ ባሉት ደሃ ሃገራት የሰው አማካኘ እድሜ ከ40 አመት በታች ሲሆን፣ በስልጣኔ በገፋ ሀገራት ደግሞ የአማካኙ የሰው እድሜ 70 አመት ድረስ ይጠጋል፡፡ የሚል ነው፡፡ በደሃ ሃገራት በረሃብ ሳቢያ ሰው ያለዕድሜ ይረግፋል በቀላሉ ሊድኑ በሽታዎች በቂ ህክምና ባለመኖሩ ሳቢያ ብዙ ህዝብ ይጨርሳሉ፣ በዚህም ምክንያት የህዝቡ አማካኘ እድሜ አጭር ሊሆን ችሏል፡፡
በስልጣኔ በገፋ ሃገራት ደግሞ የተሟላ የምግብ አቅርቦት፣ በቂ ህክምና ማዕከል ስለሚገኘ፣ ህዝቡ በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች ሳቢያ ለሞት አይደርስም፣ ለዚህ ነው አማካኙ እድሜ ከፍ ያለው፡፡
ታዲያ የእያንዳንዳችን ዕድሜ አስቀድሞ ስለተወሰነ ነው?? ወይስ እድሜን ከፍና ዝቅ ሊያደርጉ የሚችሉ ኢኮኖሚ ከቴክኖሎጂ ጋር ቁርኘነት ያላቸው ምክንያቶች ስላሉ ነው ይሔ የሆነው?? በማለት የሰው ልጅ እድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ያለመሆኑን እሟገታለሁ፡፡
ፈጣሪ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ ለነፍሳችኝ በባህሪያት ከትቧል፡፡
እንደ ሕሊና አዕምምሮና ስሜት ሁሉን ፈቃድ የሚባል ባህሪን በነፍሳችን አትሟል፡፡
ይሔ ጥልፍልፍ ዕጣ-ፈንታ መዝገብ ጥልፍልፍ ጎዳና ቢሆንና እኛ ደሞ መኪና ብንሆን፣ ሹፌሩ ፈቃዳችን ነው፡፡
ይሔን መዝገብ የምንኖረው በፈቃዳችን በመረጥነው መስመር (ጎዳና) ይዘን በመጓዝ ነው፡፡
በፈቃዳችን ሹፌርነት የመረጥነውም መስመር(ጎዳና) ይዘን በመጓዝ ነው፡፡ በፈቃዳችን ሹፌርነት ከአንዱ ጎዳና ወደሌላው እየተጠማዘዝን ሁሉንም ጎዳናዎች በአንዴ መርገጥ ስለማንችል ከምንጓዝበት ጓዳና(ከመረጥነው መስመር) ውጪ ካሉት ሌሎች እልፍ አዕላፋት ሕይወት
ጎዳናዎች(ዕጣ-ፋንታዎች) ጋር ስንተዋወቅ ምን ሊመስሉ እንኳን እንደሚችሉ ፍንጣቂ ምስላቸው ሳይኖረን አልያ ከእነአካቴው መኖራቸውን እንኳን ሳናውቅ ተጀምረን እናበቃለን፡፡
በተከተልነውም ሆነ ባልተከተልናቸው የህይወት ጓዳናዎች ውስጥ የተለያዩ ገጠመኞች፣ የተለያዩ የዕድሜ ጣራዎች፣ የተለያዩ የሞት መንስኤውች ተፅፈዋል እላለሁ፡፡
ይሔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያመንኩበቶ መደምደሚያ ነው፡፡
እነዚህ ላይ "ከእኛ ፈቃድ ውጪ በሌሎች አስገዳጅነት ሳቢያ የሚገጥሙን ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
አንድ ሰው መኪና ሲያሽከረክር ፍፁም ጥንቃቄ ቢያደርግም አንዱ ተክለፍልፎ መቶ ሊወጣበት ይችላል፡፡
እንዲ ያለውስ ነገር ምን ሊባል ነው?" የእኔ መልስ ግን "አሁንም ቢሆን ያንን ጎዳና ተከትለን የተጓዝነው በፈቃጃችን ነውና በዚያ ጎዳና ውስጥ የሚገጥሙን መልካምም ሆነ መጥፎ ነገሮች ሁሉ እናስተናግዳለን፡፡" የሚል ነው፡፡
ስለዚህ ነገሩን ሳጠቃልለው ነፍሰ ገዳዩም፣ ነፍስ ገዳይ ከመሆኑ በፊት ላይሆኖ የሚችልበት ብዙ አማራጭ የሕይወት ጎዳናዎች ነበሩት፡፡ የተከተለው ጎዳና ግን ለዚህ አብቅቶታል፡፡ ሟቹም በህይወት ሊቆይ የሚችልበት ብዙ መንገዶች ሊኖሩት ይችሉ ነበር፣ ነገር ግን በመረጠው ጎዳና እና በዚያ ጎዳና ውስጥ በተከሰቱ ነገሮች ሳቢያ ያ ሳይሆን ይቀራል፡፡
ከፈቃጃችን ውጪ የሚሆኑ ነገሮች ግን አሉ እላለሁ፡፡ መወለዴ በእኔ ፈቃድ የሆነ አይደለም፡፡
ከማን እንደምወለድ፣ የትሀገር እንደምወለድ፣ እና መች እንደምወለድ እኔ አልወሰንኩምና፡፡
ዮቶር :- ዓለማየሁ ደመቀ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
ማንኛውንም አስተያየታቹን በ @hundaolN
የሰው ግማሽ የለውም ግን ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
@sewmehoneth
BY ሰው መሆን 🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/sewmehonEth/407