tgoop.com/shamilunkamil/2150
Last Update:
የተበደለ ሰው ዱዓእ
አንድ ንጉስ ቤተ መንግስት እንዲሰራለት አዘዘ,
ተሰርቶ ሲያበቃ እና ከለታት አንድ ቀን ሲወጣ አንድ ቤት አየ , ከዛም "የማን ነው ይሄ ቤት?" ሲል ጠየቀ, "ከቤተ መንግስትህ ጎን የምትኖር የአንዲት ሽማግሌ ሴትዮ ቤት ነው" አሉት, እሱም "አፍርሱት ምክኒያቱም ምቾት አይሰጠኝም" ብሎ አዘዛቸው, ከዛም አፈረሱት, ሴትዮዋም እዝን ብላ ከፈረሰው ቤቷ ላይ ቁጭ አለች, ንጉሱ በሷ በኩል ሲያልፍ "ምንድን ነው ምጠበቂ?" ብሎ ሲጠይቃት, "የቤተ መንግስትህን መፍረስ ነው ምጠብቅ" ስትል መለሰችለት, እሱም አሹፎባት ከወታደሮቹ ጋር አለፈ, ከዛም እሷ እጇን አንስታ "ጌታየ አምላኬ ሆይ እኔ ደካም ነኝ አንተ ደግሞ የሀይል ባለቤት ነህ ተበቀልልኝ (የስራውን ስጥልኝ)" ብላ ዱዐ አደረገች, ከዛም ወዲያውኑ አሏህ በዚህ ቤተ መንግስት ላይ መቅፀፍትን አውርዶ አወደመው, ከግድግዳዎቹ አንዱ ላይም እነዚህን የግጥም ቤቶች አገኙ
أتهزأ بالدعاء وتزدريه وما يدريك ما صنع الدعاء
سهام الليل لا تخطئ ولكن لها أمد وللأمد انقضاء
وقد شاء الإله بما تراه فما للملك عندكم بقاء
በዱዐ ታሾፋለህን ዱዐ ምን እንሚሰራ መች አውቀህ
የሌሊት ቀስት እኮ አይስትም ነገር ግን ጊዜ አለው ጊዜው ደግሞ ማለቁ አይቀርም
በርግጥ ጌታ የምታየውን ሽቷል ንግስና እኮ እናንተ ጋር ለዘላለም አይቆይም
ወዳጆቼ አደራቹህን የተበደለ ሰው ዱዐ እንዳያገኛቹህ ምክኒያቱም ዱዐውን ዳመናዎች ናቸው ሚወስዱት።
BY ሻሚል - shamil
Share with your friend now:
tgoop.com/shamilunkamil/2150