tgoop.com/slmatawahi/9983
Last Update:
አምላከ አበው
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ
"አብ" ማለት "አባት" ማለት ነው፥ "አበው" የአብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "አባቶች"ማለት ነው። እዚህ ጽሑፍ ላይ "አበው" ስል ጥንት የነበሩትን ነቢያት አብርሃምን፣ ይስሓቅን እና ያዕቆብ ወዘተ ለማመልከት ነው፥ "አምላከ አበው" ማለት "የአባቶች አምላክ" ማለት ነው።
አምላካችን አሏህ የጥንት አባቶች አምላክ ነው፥ ቁርኣን የአሏህ ንግግር ነው። አምላካችን አሏህ በሡረቱ አጥ ጧሀ ላይ "ቁርኣንን በአንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም" በማለት ዐውዱ ይጀምራል፦
20፥2 ቁርኣንን በአንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡ مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ
እዚህ ዐውድ ላይ አሏህ በሁለተኝም መደብ "አንተ" የሚላቸው ተወዳጁ ነብያችንን”ﷺ” ነው፥ በመቀጠል አሏህ ለተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” "የሙሣም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል" በማለት ይናገራል፦
20፥9 የሙሣም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ
አሏህም ሙሣን ጠራውና "የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ" አለው፥ ይህ የወረደለት የአሏህ ንግግር ሲሆን ይህም የወረደው ንግግር፦ "እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ" የሚል ነው፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሣ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ
20፥13 «እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህን አዳምጥ፡፡ وَأَنَا اخْتَرْتُكَ فَاسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰ
20፥14 እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
ሙሣን ጠርቶ "እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ" ብሎት እንደነበር ለተወዳጁ ነቢያችንን”ﷺ” በሁለተኛ መደብ የሚነግራቸው አሏህ እራሱ ስለሆነ "ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው" በማለት ይናገራል፦
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا
"ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" የሚለው መገሰጫ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” የወረደ እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት አበው የወረደ መገሰጫ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ
አንዱ አምላክ የጥንት አበው አሏህ እያሉ ይጠሩ እንደነበር የዐረቢኛ ባይብል ላይ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል። ለምሳሌ፦ አሏህ ለኢብራሂም፦ "አሏህ እኔ ነኝ" እንዳለው ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 5፥7 ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ አሏህ እኔ ነኝ" አለው።
وَقَالَ لَهُ: «أنَا هُوَ اللهُ الَّذِي أخْرَجَكَ مِنْ أُورِ الكِلْدَانِيِّينَ لِيُعْطِيكَ هَذِهِ الأرْضَ مِلْكًا.»
አሏህ ፈጣሪ ካልሆነ ለምን በዐረቢኛ ላይ "አሏህ እኔ ነኝ" እንዳለ ሰፈረ? ዐረብ ክርስቲያኖች "አሏህ" ሲሉ እውነት አሏህ የሚለው ቃል ፈጣሪን ለማመልከት ሳይገባቸው ቀርተው ነው? ለይስሐቅም አሏህ ተገለጠለት ይለናል፦
ዘፍጥረት 26፥2 አሏህ ተገለጠለት እና እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።
فَظَهَرَ اللهُ لِإسْحَاقَ وَقَالَ لَهُ: «لَا تَنْزِلْ إلَى مِصْرٍ. بَلِ امْكُثْ فِي الأرْضِ الَّتِي سَأقُولُ لَكَ عَنْهَا.
"መገለጥ" ማለት "መታወቅ" ማለት ነው፥ ለይስሐቅ "እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ" እያለው የሚያናግረው አሏህ እንደሆነ መገለጹ ስህተት ነውን? አሏህ ለያዕቆብ "የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ ነኝ" አለው፦
ዘፍጥረት 28፥13 አሏህም፦ "የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ ነኝ" አለው።
فَقَالَ اللهُ: «أنَا إلَهُ أبِيكَ إبْرَاهِيمَ، وَإلَهُ إسْحَاقَ.
ከተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በፊት አሏህ የሰበከ ከሌለ ለምን "አሏህ አለ" "እኔ አሏህ ነኝ" የሚል ቃል ባይብል ላይ ሰፈረ? አሏህ ሙሴን፦ እኔ አሏህ ነኝ" ብሎታል፦
ዘጸአት 6፥29 እርሱም ሙሴን፦ እኔ አሏህ ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር" ብሎ ተናገረው።
قَالَ لَهُ: «أنَا اللهُ. قُلْ لِفِرعَونَ مَلِكِ مِصْرٍ كُلَّ مَا أقُولُهُ لَكَ.»
በዚህ ሙግት ስናቆራጥጣቸው "የእኛ አሏህ እና የእናንተ አሏህ ይለያያል፥ የእኛ አሏህ አንድም ሦስት ነው፤ የእናንተ አሏህ አንድ ብቻ ነው" ይሉናል። ጥሩ!
፨ አንደኛ ሁለት አሏህ በህልውና የለም፥ ስለ አሏህ ሁለት ሰዎች የተለያየ መረዳት ቢኖራቸው አሏህ ሁለት ሆኖ ሳይሆን መረዳታቸው ብቻ ይለያያል።
፨ ሁለተኛ ከክርስቲያኖች በፊት ያሉ አይሁዳውያን ወጥ በሆነ አቋም አሏህ ጥንት የነበረው የአባቶች አምላክ መሆኑን ይቀበላሉ፥ በተጨማሪም "አሏህ አንድ ብቻ ነው" ብለው ሲያምኑ በተቃራኒው "አንድም ሦስት ነው" የሚለውን ክፉኛ ይቃወማሉ።
፨ ሦስተኛ አሏህ ፈጣሪ መሆኑን ከተቀበላችሁ እና ከጥንት ነቢያት ማስተማራቸውን መቀበላችሁ "ይበል" የሚያስብል ንግግር ነው፥ አሏህ የሚለው ስም ለጣዖት አገልግሎት የዋለበት አንድም የሐራዊ ሆነ የወጋዊ ዘገባ የሌለ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የባዕድ አምላክ ስም ቢሆን ኖሮ ባይብል ላይ ለነቢያት አምላክ ስም አርገው አይጠቀሙም ነበር።
አምላከ አበው አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY የሰለምቴዎች ቻናል
Share with your friend now:
tgoop.com/slmatawahi/9983