tgoop.com/sratebetkrstyane/6744
Last Update:
"አኩርፈው የተለዩንን ወደ እኛ እንመልሳቸው እኛም ከሚያስኮርፍ ነገር እንራቅ አንድነታችንን እናጠናክር።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ
ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ችግሮችን አጥንቶ ውሳኔ የሚሰጠው ምልዓተ ጉባኤ መከፈቱን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አበሰሩ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ቤተክርስቲያን ከፈተና አልተለየችም ወደፊትም አትለይም ያሉ ሲሆን የደረሰብን ጫና ምን ያህል እንደሆነ የሚታወቅ ነው አንድ መሆን አለመቻላችንም ፈተና ሆኖብን ክፍተትን ፈጥረናል ብለዋል።
የቀደምት አባቶቻችን የሰሩትን ልንደግም ይገባል ፤ ኃላፊነት አለብን ኃላፊነትታችንንም በሚገባ ልንወጣ ይገባል ፤ ለቤተክርስቲያን ክብር ከወገኝተኝነት የጸዳ እንከን የለሽ አንድነትን ልንፈጥር ይገባናል ነው ያሉት ቅዱስነታቸው።
በርካታ ተከታይ ያላት ቤተክርስቲያን ልጆቿን በቅዱስ ወንጌል ከገነባች ሀብቷን በሚገባ ከጠበቀች እንኳን ለገንዘቡ ለሕይወቱ የማይሳሳ ምእመናን አሏት ፤ ዘመኑ የሚጠይቀውን አሰራር በመጠቀም የምንሰራው አሁን ነው ብለዋል።
በመጨረሻም የሥራዎቻችን ዋስትና በሀገር እና በቤተክርስቲያን ዘላቂ ሰላም ሲኖረው ነው ፤ ቤተክርስቲያን ለሀገር ሰላም የአንበሳው ድርሻም እንዳላት ይታወቃል ድርሻዋንም ለመወጣት ትሠራለች ብለዋል ቅዱስነታቸው።
#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze
BY ✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
Share with your friend now:
tgoop.com/sratebetkrstyane/6744