tgoop.com/sratebetkrstyane/7074
Last Update:
🗓ኢየሱስ ያሉትን ሁሉ የማንቀበለው ለምንድንነው?
ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በማለታችን ተገለልን ይላሉ
ኢየሱስ ያለን ሁሉ የምንቀበል ከሆነማ አጋንትንም በተቀብለን ነበር ። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ አጋንት እንድህ ሲሉ እንሰማ አለን
📕
(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 4)
----------
33፤ በምኵራብም የርኵስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፥ በታላቅ ድምፅም ጮኾ።
34፤ ተው፥ #የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ #አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ አለ።
35፤ ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም #ውጣ ብሎ #ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ።
📕" አጋንንትም ደግሞ። #አንተ ክርስቶስ #የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ ገሠጻቸውም ክርስቶስም እንደ ሆነ አውቀውት ነበርና #እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።"
(የሉቃስ ወንጌል 4:41)
💦ከላይ እንዳያችሁት አጋንንት አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ሲሉ ደስ ይላል አይደል ቃሉ 😄እውነትም የተናገረ ይመስላል አይደል አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ሲሉ ጌታ ኢየሱስ ግን እንድናገሩ እራሱ አልፈቀደላቸውም ምክንያቱም አጋንንት በእውነት የተሸፈነ ሀሰት ይናገራል እንጅ እውነትን ሊናገር አይችልም አጋንንት እውነትም ቢናገርም የሚናገረው በሰዎች ውስጥ ሁኖ ሰዎችን ለማጥፋት ነው
💧ጌታ ኢየሱስ ለጠየቀው ጥያቄ ጴጥሮስ እንድህ ብሎ
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 16)
----------
16፤ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
💧ጌታ ኢየሱስም እንድህ አለው
17፤ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
💦እዚህ እንግድህ እንደምናዬው አጋንንትም ጴጥሮስም የተናገሩት አንድ ሁኖ ሳለ ለአጋንንት ዝም ብለህ ውጣ ሲለው ለጴጥሮስ ግን ሥጋና ደም አልገለጠልህም ብፁዕ ነህ ብሎ ሲመሰክርለት እናይ አለን ።
💧ምክንያቱም አጋንንትና ጴጥሮስ የተናገሩበት መንፈስ ይለያያልና ነው ።
🗓እንግድህ ምን እንል አለን አጋንንትን ተቀብለን ቢሆንስ በጠፋን ነበር ።
🗓ስለዚህ ላለመጥፋት መናፍቃን ኢየሱስ ሲሉ ዝም ብለህ ውጣ እንል አለን ምክንያቱም መናፍቃን ኢየሱስ ሲሉ እውነተኛ ወንጌልን ለመስበክ ሳይሆን በኢየሱስ ስም የሚነግዱ አደገኛ የሰይጣን ልጆች ናቸው በውስጣቸው ክፋትን አስበው የሰው ልጆችን ከእውነተኛ የክርስቶስ አካልና መንገድ ለማስወጣት ስለሆነ ዝም ብለህ ውጣ አትለፍልፍ እንለው አለን እንጅ ኢየሱስ ስላለ የምንቀበል የሰይጣን ተባባሪዎች አይደለንም ሰይጣንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቅዱስ ..ይላልና ። ኢየሱስ ስላለ ሰይጣንን ብንቀበል እንደምንጠፋው ሁሉ ኢየሱስ ስላሉ ፕሮቴስታንትን መቀበል መጥፋት ነው።
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
BY ✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
Share with your friend now:
tgoop.com/sratebetkrstyane/7074