tgoop.com/sratebetkrstyane/7149
Last Update:
አንዲት ሴት ወደ ንስሐ አባቷ ጋር በመሔድ ከዛሬ ጀምሮ ቃለ እግዚአብሔር ለመማር ወደ ቤተክርስቲያን አልመጣም አለቻቸው።
እኚህ አባትም ደንገጥ ብለው ለምን ልጄ❓ ብለው ጠየቋት
እሷም እንዲህ አለች" ለትምህርት የሚመጡ ሰዎች በስብከት ሰዓት ስልካቸው ላይ አፍጠው ፌስቡክናሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች እያዩ አንዳንዶች አፍ ለአፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ፣ ሰውን ያማሉ ሌሎቹ ደም በሀሳብ ሔደዋል ሁሉም አስመሳዮች ናቸው ስለዚህ ሁለተኛ አልመጣም" አለቻቸው።
አባም ዝም አሉ ፦ ከዚያ ትንሽ ቆይተው ውሳኔ ላይ ከመድረስሽ በፊት ለአንቺ የሚሆን አንድ ጥያቄ አለኝ አሉዋት
እሱዋም ጠይቁ አለቻቸው
አንድ ብርጭቆ ሙሉ ውሃ 💦 ይዘሽ በጉባኤው መሀል አቋርጠሽ መምጣት ትችያለሽ❓ አሉዋት
እሱዋም በሚገባ እችላለሁ ብላ አንድ ጠብ ሳይልባት እንዳለችው አደረገች።
አባም ጥያቆውን አቀረቡላት ውሀውን ስታመጪ ጉባኤው ላይ ስልክ የሚመለከት ወይም የሚንሾካሸክ አይተሻል ወይ❓ አሉዋት
ሴትዬዋም "አለ በፍጹም አላየሁም❗️ለሳቤ ሁሉ የብርጭቆው ውሃ💦 እንይፈስ ሀሳቤ ሁሉ እዛ ላይ አድርጌው ነበር" አለች
አባም እንዲህ አሉ፦ "አየሽ ሙሉ ትኩረትሽን ብርጭቆ ላይ ስለነበር ማንንም አላየሽም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጪ ማድረግ ያለብሽ ነገር ይህ ነው ሙሉ ትኩረትሽ እግዚብሔር ላይ መሆን አለበት አለበለዚያ ትወድቂያለሽ። አይኖችሽን ከሰዎች ላይ አንስተሽ ክርስቶስ ላይ አድርጊ።
እግዚአብሔር እኔን ተከተሉኝ እንጂ ክርስቲያኖችን ተከተሉ አላለም። አእምሮአችን ክርስቶስ የተናገረውን፣ ያደረገውን፣ ያሰበው ምን እንደነበር እንዲያሰላስል እናድርግ ከሰዎች ላይ አይናችንን አንስተን መስቀሉ ላይ አይናችንን እንትከል።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
BY ✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
Share with your friend now:
tgoop.com/sratebetkrstyane/7149