tgoop.com/sratebetkrstyane/9724
Last Update:
#ድንግል_ሴት_ትፈልጋለህ?
ምንም እንኳን ሰዎች ሁሉም ባይሆኑም ብዙ ሰዎች ግን የሚያገቧት ሴት ድንግል እንድትሆን ይፈልጋሉ አንዳንዶች ደግሞ መፈለግ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ መስፈርታቸው ያደርጉታል ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ አቋም ነው ምክንያቱም የኹሉም ሰው አቋም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ኹሉ በንጽሕና መኖርን ለወደፊት ትዳራቸው መቃናት ሲሉ ስለሚለማመዱት ነው።
ታዲያ ሚስቱ ድንግላዊት ሆና ቢያገኛት የሚመኝ ሰው እርሱም ድንግልናውን የጠበቀ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ለአፍታም እንኳን ቢሆን መዘንጋት የለበትም ስለዚህ ይህን የሚመኝ ራሱን ይጠብቅ ካላገባኻት ሴት ጋር አንሶላ መጋፈፍን አትሻ ልታገባ አንድ ቀን የቀረህ ቢሆን እንኳን ሳታገባት ይኽን መሞከር የለብኽም በሰዓታትና በቅጽበት ውስጥ በእቅፍኽ ያለች እጮኛህ ያንተ ሚስት መሆን የማትችልበት ሁኔታ ይፈጠር እንደሆነ አታውቅምና አንተ ራስህ ከነድንግልናህ የምትፈለግበት ጋብቻ ከፊተህ ይጠብቅሀል ።
#እርሷም_በምትሄድበት_ቦታ_ባሏ ከነ ሙሉ ክብሯ ይሻታል ታዲያ ካላገባሃት ሴት ጋር ለምን ትተኛለህ? ካላገቧት ሴት ጋር ምንጣፍ መጋራት በሰው ቤት መግባትና ከባለ ትዳር ሴት ጋር እንደ ማመንዘር ነው ያላገባች መሆኗ ልዩነቱ ባሏን መቅደምህ ብቻ ነው አንተ በሰው ትዳር እንዲህ የምተገባ ከሆነ ሌሎች ደግሞ አንተ የምታገባትን ሴት ከክብር አስንሰው ንጽሕነዋን ገፈው ያቆዪሀል አንተ ድንግል ሳትሆንና የብዙዎችን ሕግ አፍርሰህ ድንግል ሴት መፈለግህ አያስገርምም ?
ሰው የራሱን ድንግልና ቢጠብቅ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግልና የተጠበቀች ሚስት እንደ ፍላጎቱ ሊሰጠው ተስፋ ሰጥቷል ሰው የራሱን ዕቃ ቢጠብቅ ለእርሱ የሚገባውን ዕቃ እግዚአብሔር በክብር ይጠብቅለታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ዕቃ የሚባለው አባለ ዘርዕ (ኀፍረተ አካል )ነው።ቅዱስ ዳዊት በእውነት ከመጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሶስት ቀን ጠብቀናል የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆኗ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል 1ኛሳሙ 21:5 በማለት የተናገረው ቃል ኀፍረተ አካል ዕቃ እንደሚባል ያስረዳል።
#የራሱን ንጽሕና የጠበቀ ሰው ለእርሱ የምትሆነው ሚስቱ ከነቅድስነዋ ከነንጽሕነዋና ከነሙሉ ክብሯ(ድንግልነዋ)እንደሚያገኛት ማወቅ አለበት ሲል ሐዋሪያው"ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን እቃ(ሚስቱ የምትሆነውን ) በቅድስናና በክብር (ከነድንግልነዋ) ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ"በማለት ይናገራል።
#ዕቃ የሚለው ኀፍረተ አካል መሆኑ ከላይ በማያሻማ መልኩ ተገልጿል።ስለዚህ ድንግልን ማግባት የሚፈልግ ሰው የራሱን ክብር መጠበቅ ይኖርበታል።
#1ኛ_ተሰሎንቄ 4÷5🙏
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
BY ✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️

Share with your friend now:
tgoop.com/sratebetkrstyane/9724