Telegram Web
🌻#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊው🌻
     ==================

⛪️🌻ዮሐንስ ማለት “የእግዚአንሔር ጸጋ ነው”፤ደስታ ማለት ነው፡፡ አባቱ ዘብዴዮስ፤ እናቱ ማርያም ባውፍልያ ትባላለች፡ ፡ቁጥሩ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረው፡፡ /ማቴ 4፥21፤ ማር 1፥20፤ማቴ 20፥20/ ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅም ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ /ዮሐ 1፥35/ ቅዱስ ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሣ በሚያጠምድበት በገሊላ ባህር ላይ መረቡን ሲያበጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራው፡፡ እሱም አባቱን ሌሎቹንና ታንኳን ትቶ ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ጌታን ተከተለው፡፡

✍️
#የዮሐንስ_ስሞች

✔️ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
✔️ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
✔️ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ
✔️ዮሐንስ ታኦሎጎስ
✔️ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
✔️ዮሐንስ ወንጌላዊ
✔️ዮሐንስ ዘንስር

⛪️🌻ቅዱስ ዮሐንስ ወንድሙ ያዕቆብ የሰማርያ ሰዎች በእሳት እንዲጠፋ ተመኝተዉ ነበር ፡፡በዚህ ዓይነት የችኩልነት ስሜታቸው የተነሣ ጌታ “ቦአኔርጌስ” የነጎድጓድ ልጆች ብሏቸዋል፡፡ /ማር 3፥17፤ ሉቃ 9፥54/
ለጌታችንን ከሚደርቡ ዐዕማደ ሐዋርት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ያዕቆብ ቅዱስ ዮሐንስ ቀዳሚው ነው፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት፣ ምሥጢረ መንግሥትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም “ጌታ ይወደው የነበረ ደቀ መዝሙር” ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ /ዮሐ 13፥23/፡፡

⛪️🌻ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ /ቁጽረ ገጽ/ ሆኖ ኖሯል፡፡

⛪️🌻ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አምልቶና አስፍቶ በመጻፉ /ታኦጎሎስ/ ተብሏል፡፡ ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር) ማለት ነው፡፡
ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ ትጉሙም የራእይ አባት ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በመጻፉ ወንጌላዊ ተብሏል፡፡

⛪️🌻በሥላሴ ስዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳ አንዱ ንስር ነው፡፡ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ ንስር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ ንስር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላዉያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል፡፡ ንስር አይኑ ንጹህ ነው ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ የታመልጠዉም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን) በቅድምና መኖር ተናግሯል፡፡ በዚህም ዮሐንስ ዘንስር ተብሏል፡፡

⛪️🌻ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በሕይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነው፡፡ ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ “ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?” /ዮሐ 21፥20/ ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነው፡፡ /በማቴ 16፥18/ ላይ “እውነት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ” ያለው ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነው፡፡

#የቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ_በረከቱ_ረድኤቱ_ከሁላችን_ጋር #ይሁን🙏🙏🙏

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
https://www.tgoop.com/tmhrteorthodox
“ሰላምየ አኀድግ ለክሙ ወሰላመ አቡየ እሁበክሙ፡- ሰላሜን እተውላችኋለሁ፥ የአባቴ ሰላምም እሰጣችኋለሁ” (ዮሐ.14፡27)

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነት ማስፈንን አስመልክቶ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤

ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና ደኅንነት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቀዳሚ ተልእኮዎች ናቸው፡፡ በሃገራችን ሰላምን ለማስፈን ቅድስት እናት ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞ ጀምሮ ብዙ ጥረት ስታደርግ ኑራለች፡፡ አሁንም ሊኖራት የሚገባውን ተግባራዊ ሚና መወጣት ይኖርባታል፡፡

በተለይም ሰላም በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊ፣ በግለሰብ፣ በተቋም፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ክበብ ውስጥ ያለውን የተሣሠረ ሁለንተናዊ ትርጉም ከግምት ውስጥ ያስገባ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡

ለሰላም መደፍረስና መታጣት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን በማንሳትና ያስከተሉትን የሰው ልጅ እልቂት፣ ሞትና ስደት፣ የአብያተ ክርስቲያናትና የመንፈሳዊ ቅርሶች ውድመት፣ የካህናትና የሊቃውንት ስደትና መከራ፣ የቋሚና የተንቀሳቃሽ ንብረቶች ውድመት፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት መናጋት፣ በዜጎች መካከል ጥላቻ መስፋት፣ መተማመን መጥፋት፣ የኑሮ ዋስትና ማጣት፣ በስጋት መኖር፣ የማያባራ መከፋፈል፣ የሰብአዊ ክብር ማጣት፣ የመብት ጥሰት፣ የኑሮ ውድነትና የሕዝቦች መፈናቀል በአደባባይ እየታዩ ያሉ ሰብኣዊ ሰቆቃዎች ናቸው፡፡
፩ኛ. የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር ፲፭ እስከ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤
 
፪ኛ. በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤ 

፫ኛ. በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

፬ኛ. በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር ፲፭ ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር ፳፩ ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

፭ኛ. በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

፮ኛ. በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

፯ኛ. ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤ 
 
፰ኛ. አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤   

፱ኛ. ይኽንኑ መልእክት መላው ዓለም እንዲውቀው፣ በተለይም የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎት እንዲያስቡን፣ የጸሎታችንና የምኅላችን መነሻ ምክንያቱ የሀገራችን ወቅታዊ ችግር ቢሆንም የምንጸልየው ለመላው ዓለም መሆኑ ተገልጾ በደብዳቤ እንዲላክ እንዲደረግ፣ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል፡፡ 

እግዚአብሔር አምላካችን በእንባና በንሥሓ የምናቀርበውን ጸሎተ ምኅላችንን በምህረቱ ተቀብሎ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሕዝባችንን ይጠብቅልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 
ቅዱስ ሲኖዶስ
...🥀🍃❤️እንኳን አደረሳችሁ❤️🙏
.............................................................
#ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል??
#ለምንስ_እንፆማለን?
................................................................

🥀ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 28 ይፈታል።

➡️🍃ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

🥀🌿ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

=>❤️ ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።

❤️⤵️
#ፆመ_ድህነት የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።

❤️⤵️
#ፆመ_ማርያም የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

❤️⤵️
#ፆመ_አዳም የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡

❤️⤵️
#ፆመ_ፊሊጶስ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

❤️⤵️
#ፆመ_ስብከት የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡

🌿ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።

።።።።
#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።።
#ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።።
#ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
🥀✝️አሜን🥀አሜን🥀አሜን🙏
ኪዳነ ምህረት

🤲
#ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡


  🤲
#እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎልጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ #ልጇ እና #ወዳጇ #ጌታችን_መድሐኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡


🤲 እንኳን
#የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ #አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ #እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
«
#ከመረጥሁት_ጋር_ቃል_ኪዳኔን_አደረግሁ።»_መዝ89:3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

🤲 ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

🤲 ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦
". . .
#ቀስቲቱም_በደመና_ትሆናለች_በእኔና_በምድር_ላይ_በሚኖር_ሥጋ_ባለው_በሕያው ነፍስ_ሁሉ_መካከል_ያለውን_የዘላለም_ቃል_ኪዳን_ለማሰብ_አያታለሁ። "_ኦሪት_ዘፍ.9:16

🤲 በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ
#ኪዳነ_ምህረት እያልን እንጠራታለ

እንኳን ለ«
#ኪዳነምህረት» ወርሀዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ። #የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!
      
የአብያተ ክርስቲያናት አርማ
| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.|

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አርማዋ መስቀል ነው:: "ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሠጠሃቸው" የሚለው ቃልም የሚፈጸመው በዚሁ መንፈሳዊ አርማ ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለአስተዳደር እንዲመች ደግሞ በአህጉረ ስብከት ተከፍላ እንደምታገለግል ይታወቃል:: ለዚህ መንፈሳዊ አስተዳደርዋ ደግሞ ለእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የራሱ መታወቂያ የሆነ አርማ (logo) እና ዓላማ (emblem) አለው:: ኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የየራሳቸው አርማ አላቸው:: አርማዎቹም ትርጉም ያላቸውና አብያተ ክርስቲያናቱን የሚገልጹ ናቸው::

የጥቂቶቹን እንመልከት :-

⛪️ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ

በአራቱም በኩል እኩል የሆነ መስቀል ሲሆን እያንዳንዱ ሦስት ቀስት ያለው መሆኑ ቅድስት ሥላሴን ይወክላል:: ሙሉው ሲቆጠር ዐሥራ ሁለት ቀስቶች መሆናቸው ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት በሰበኩት ወንጌል ላይ ቤተ ክርስቲያን መመሥረትዋን ያስረዳል:: በመስቀሉ ዙሪያ ያለው ቃል ደግሞ በኮፕቲክ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን "ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር" ማለት ነው::

⛪️ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ

ከላይ የሚታየው መስቀልና ከሥሩ ያለው አርዌ ብርት በሞቱና በትንሣኤው ለቤተ ክርስቲያንን ድል ነሺነትን የሠጠ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሲሆን አርዌ ብርቱ ደግሞ በፓትርያርኮች እጅ የሚያዘው "ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" የሚለውን ቃል የሚያስረዳ ያለ በደል ስለ እኛ ተሰቅሎ ያዳነንን ክርስቶስን የሚያሳይ ነው:: ከመስቀሉ ሥር ያለው ብርሃን በመስቀሉ ጨለማን ያራቀ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የማዳኑን ሥራ የሚያስረዳ ነው:: በመካከል ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ከሥር ባለው መጽሐፍ ቅዱስ ላይም የተጻፈው "ቃል ሥጋ ሆነ" የሚለውን የተዋሕዶ መሠረት የሆነ ቃል ነው::
በዙሪያ ያለው የስንዴና ወይን ዘለላ ደግሞ ምሥጢረ ቁርባንን የሚያሳይ ነው::

⛪️ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ

ከላይ የሚታየው የጳጳሳት አስኬማ ከሐዋርያት ጀምሮ በቅብብል የመጣውን የፓትርያርኩንና የሊቃነ ጳጳሳትን ሥልጣነ ክህነት የሚገልጽ ነው::

መስቀሉ በሞቱና በትንሣኤው ለቤተ ክርስቲያንን ድል ነሺነትን የሠጠ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሲሆን አርዌ ብርቱ ደግሞ በፓትርያርኮች እጅ የሚያዘው "ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" የሚለውን ቃል የሚያስረዳ ያለ በደል ስለ እኛ ተሰቅሎ ያዳነንን ክርስቶስን የሚያሳይ ነው:: ከታች ያለው "አምላኬ ጌታዬም" የሚለው የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያ የሆነው የቅዱስ ቶማስ ምስክርነት ቃል ነው:: (ዮሐ. 20:28

⛪️ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ

ከላይ የሚታየው የጳጳሳት አስኬማ ከሐዋርያት ጀምሮ በቅብብል የመጣውን የፓትርያርኩንና የሊቃነ ጳጳሳትን ሥልጣነ ክህነት የሚገልጽ ነው::

መስቀሉ በሞቱና በትንሣኤው ለቤተ ክርስቲያንን ድል ነሺነትን የሠጠ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሲሆን አርዌ ብርቱ ደግሞ በፓትርያርኮች እጅ የሚያዘው "ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" የሚለውን ቃል የሚያስረዳ ያለ በደል ስለ እኛ ተሰቅሎ ያዳነንን ክርስቶስን የሚያሳይ ነው::

ቁልፉ የአንጾኪያው የመጀመሪያ ፓትርያርክ ለሆነው ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሠጠውን ሥልጣነ ክህነት የሚያሳይ ሲሆን ቁልፎቹ ሁለት መሆናቸው በጴጥሮስ ብቻ ያልተወሰነ መሆኑን ያስረዳል:: ሚዛኑ ፓትርያርኩ በፍትሕ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያስተዳድሩ የተሾሙ እንደሆኑ የሚያሳይ ሲሆን ከሥር በዓረቢኛ የተጻፈው ደግሞ "የአንጾኪያና የመላው ምሥራቅ ፓትርያርክ" የሚል ነው::

⛪️ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አርማ እና ትርጉም

፩ የአርማ ቅርፅ እና ይዘት

፩ . መደቡ ነጭ

፪ . ዙሪያው የስንዴ ዛላ እና የወይን ዘለላ

፫ . ከላይ ከአናቱ ከአክሊሉ ፣ ከታች ከግርጌው መሃል ለመሃል ወጥቶ አናቱ ከአክሊሉ ስር የደረሰና መስቀል ያለበት አርዌ ብርት

፬ . በግራ ሆኖ በቀኝ እጁ አርዌ ብረት በግራ እጁ ዘንባባ የያዘ መልዐክ ፣ በቀኝ ሆኖ በግራ እጁ አርዌ ብረት በቀኝ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ

፭ ከአርዌ ብርት ሥር "ነዋ ወንጌለ መንግሥት " ተብሎ የተጻፈበት መጽሐፍ ቅዱስ

፮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥር የ "ጸ" ፊደል ቅርጽ የሚመስል ሁለት ጫፎች ከመደቡ ወደ ውጭ የወጣ ሰበን

፯ የስንዴ ዘለላ እና የወይን ዘለላ በሚገናኙበት የዓለም ምስል ያለበት ይሆናል

፪ የአርማው ትርጉም
☞☞☞☞☞☞☞

ሀ / መደቡ ነጭ መሆኑ
ዘመነ ስጋዌ የምሕረት የደስታ የነፃነት ዘመን መሆኑን ያመላክታል

ለ / የአርማው ዙሪያ በስንዴ ዘለላ እና የወይን ዘለላ መሆኑ ምእመናን በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ፣ ስርየተ ኃጢአት የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ መሆኑን
(ዮሐ ፮ ፥፶፫-፶፰ ማቴ ፳፮፥፳፮- ፳፱ መዝ ፬፥፯)

ሐ / በአርማው መሃል ቀጥ ብሎ የቆመ የአርዌ ብርት ምስል ከበላዩ ላይ መስቀል ከዚያም ከፍ ብሎ አክሊለ ክህነት መኖሩ ሕዝበ እስራኤል አርዌ ብርቱን ባዩ ጊዜ ከእባብ መርዝ እንደዳኑ ሁሉ መስቀል ላይ በተሰቀለው ጌታችን በአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ከዲያቢሎስ ምክንያት የመጣባቸው ፍዳ ኃጢአት የሚድኑ መሆናቸውን መስቀሉም የቤተ ክርስቲያን የድኅነት አርማ መሆኑን ያሳያል
( ዘኁ ፳፮፥፰ ዮሐ ፫ ፥፲፬ )

መ / አክሊሉ
ቅዱሳን በሰማያዊ መንግስት የሚቀዳጁት አክሊል ክብር እና ማኅተመ ጽድቅን ያመላክታል
(ዘፀ ፴፱፥፱ ፩ተሰ ፪ ፥፲፱ ፪ጢሞ ፬ ፥፲ ፩ ጴጥ ፭፥ ፲፬ ራዕይ ፪፥፲ : ፲፥፲፬ )

ሠ / ሁለት መላዕክት የአርዌ ብረት እና የዘንባባ ዝንጣፊ መያዛቸው

ዘንባባ በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ደስታ ድኅነተ ነፍስን ያመላክታል:: ቅዱሳን መላዕክት የቤተ ክርስቲያን ጠባቂዎች እና የመልካም ዜና አብሣሪዎች መሆናቸውን ያሳያል የአርዌ ብርቱን ይዘው መቆማቸው ነገረ መስቀሉን አምኖና እምነቱን አጽንቶ ይዞ የሚኖር የዘላለም ድኅነት የሚያገኝ መሆኑን ያሳያል:: (መዝ ፺፥ ፲፩ ሉቃ ፲፫፥ ፮-፱ ዕብ ፩፥፲፬ )

ረ / በአርማ መሃል መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ በላዩ ላይ "ነዋ ወንጌለ መንግሥት" የሚል ጽሑፍ መኖሩ
የቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ቅኖና እና ትውፊት በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያመላክታል ( ማቴ ፳፬ ፥ ፲፬ )

ሰ / የስንዴ ዛላና ዘለላ በተገናኙበት ቦታ የሚታይ ክብ ነገር ዓለምን የሚወክል ሲሆን ዓለም በክርስቶስ መዳኑን ያሳያል:: ( ዮሐ ፫፥ ፲፯ )

ማስታወሻ :- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አርማ ጃንደረባው ሚድያ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ሠርቶታል:: ዛሬ ምሽት ከሰርክ ጸሎት በኋላ ይፋ ይሆናል::

#ወደዚህ_ሠረገላ_ቅረብ
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
.
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ደም ላነሳት ደም ልገሳ

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ እንደጻፉት

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ 12 ዓመት ታዳጊ የነበረችዋን የኢያኢሮስን ልጅ ከሕመሟ ለመፈወስ ሲጓዝ በመንገድ ብዙ ሕዝብ ያጨናንቀው ነበር። ከሚተራመሰው ሕዝብ የተወሰነው ተአምራት ሊያይ፤ ገሚሱ ሕብስት ሲያበረክት ጠብቆ ሊበላ፤ ሌላው መልኩን ሊያይ፤ ደግሞ ለበላይ አለቆች ያየና የሰማውን መረጃ ለማቀበል፤ የተቀረው ትምህርቱን ሊሰማ ይጋፋ ይዟል። ጌታችንም የሚጓዝ ይህ ሁሉ ሕዝብ እያጋፋው ነበር።

ይህ ሕዝብ እስከ ምጽዓት ክርስቶስን የሚከተሉ ሰዎችን የሚወክል ማሳያ ነው። ዛሬም በቤተክርስቲያን ለሆዱ ሲል ወይም በዚያ ያለው ሥርዓት ማርኮት፤ ደግሞም ትምህርት ለመስማት ብቻ፤ ተአምራት ለማየት ወይም ለተቃዋሚዎች ወሬ ለማቀበል የሚጋፋ አለ።

በጉዞው መካከል ጌታችን ድንገት ቆሞ "የዳሰሰኝ ማነው?" ሲል ጠየቀ። ደቀ መዛሙርቱ ይህ ሁሉ ሰው እያጋፋው ሳለ እንዲህ ብሎ መጠየቁ "መምህራችሁ ምን ማለቱ ነው?" ለሚል ትዝብትና ትችት እንዳይዳርጋቸው ቶሎ ብለው "አቤቱ ሕዝቡ ያጨናንቁሃል ያጋፉህማል፤ የዳሰሰኝ ማን ነው ትላለህን?" በማለት ያለበትን ሁኔታ ሊያስታውሱት ምከሩ። ዙሪያውን የተሰበሰበ ሁሉ አብሮት እንዳልሆነ የሚዳስሰውም ሁሉ ግንኙነት እንደማይፈጥር ከእርሱ ከራሱ በቀር የሚያውቅ የለም። ብዙዎች ዙሪያውን ቢያጋፉትና ቢያጨናንቁትም ከእርሱ ጋር በምሥጢር ግንኙነት መፍጠር የሚችሉ በጣም ጥቂት ናቸው። የማዳን ኃይል የፈውስ ኃይል ከእርሱ እንዲወጣ በእንባ፣ በጸሎት፣ በጾም፣ በስግደት፣ በሱባዔ፣ በምህላ፣ ወዘተ. . . ቀርበው የሚዳስሱት በእምነት የሚኖሩ ብቻ ናቸው።

ለአሥራ ሁለት ዓመታት ባለማቋረጥ ደም የሚፈሳት በዚህ ችግሯም ገንዘቧንና ትዳሯን ሁሉ የከሰረች ምስኪን ሴት ነበረች። በዘመናዊው ዓለም እንዳለው የሴቶችን ተፈጥሯዊ ክብርና የሥነ ልቡና ልዕልና እንዳይጎዳ፤ ያለ ምንም መሳቀቅም ዕለታዊ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያግዝ የንጽሕና አጠባበቅ መንገድ ባልነበረበት ዘመን እንደ ሰው መቆጠር ናፍቋት ትኖር ነበር። ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕጉ ራሱ "ማንም ሰዉ ከሥጋው ፈሳሽ ነገር ቢወጣ ስለሚፈስሰው ነገር ርኵስ ነው" "ሴትም ከመርገም ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፤ ወይም ደምዋ ከመርገምዋ ወራት የሚበልጥ ቢፈስስ፤ በመርገምዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ ርኵስነት ወራት ትሆናለች፤ ርኵስ ናት" በማለት ተፀይፏት፣ ገፍቷት፣ አግልሏት ኖረች። ዘሌ. 15

ይህን ጭንቅ የኖረው ብቻ ያውቀዋል፤ ታሪክንስ ከባለ ታሪኩ በላይ ሊተርከው ለማን ይቻለዋል? እነዚያን አሥራ ሁለት ዓመታት፤ መቶ አርባ አራት ወራት፤ ስድስት መቶ ሃያ አራት ሳምንታት፤ አራት ሺህ ሦስት መቶ ሰማንያ ቀናት፤ መቶ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰዓታት፤ ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ደቂቃዎች እንዴት አሳልፋቸው ይሆን? ስድብና ንቀትን ጠግባለች፤ የሚፀየፏትን ምራቅ መቀበል በእርሷ እንደ የዘወትር ሰላምታ ነው። ገንዘቧ አልቋል፤ የልጅነት ባልዋ ጥሏት ሄዷል፤ አብሮ አደጎቿና ቤተሰቦቿ በደም ኩሬዋ ውስጥ ጥለዋት ሸሽተዋል። እርሷ ከቆሙት በታች ሆና ብትሞትም፤ ተስፋዋ ግን አልምተም!!! "ሥጋዬ በተስፋ ያድራል" እያለች መቼና እንዴት እንደሚሰማትና እንደሚመልስላት ወደማታውቀው በለሆሳስ ትጣራላች። በቀናቱ ርዝማኔ ድምጿ ቢሰልልም በዝምታው እምነቷ ቢፈተንም ከመጣራት ግን አታርፍም። መዝ 15 (16)፥9

አንድ ቀን ድንቅ ከተደረገላቸው ሰዎች ወሬ ሰማች። የትኛውንም ዓይነት ደዌ ስለሚፈውሰው ለምፃሞችን ሳይቀር ስለሚዳስሰው ሰማች፤ ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ!!! የእርሷ ዓይነት ችግር ስለ ገጠማቸው ሰዎችና በምን መልኩ እንዳስተናገዳቸው ግን ምንም መረጃ ማግኘት አልቻለችም። ተመኘች . . . ደግሞ አመነታች:: ልታገኘው ፊቱ ልትቆምና ራራልኝ ልትለው ጓጓች . . . ግን ደግሞ ፈራች። ወደ እርሱ ለመቅረብ ለሚሻ ልብ የመንገዱ ጠባይ ይኸው ነው:: ፈውስ በደጇ ሲቀርብ የረሃብ ጠኔ ፀንቶበት ሳለ ምግብ እንደሸተተው ሰው የመዳን ናፍቆቱ አንገበገባት፡፡ ወደ ፊት የሚጠብቃትን እስካሁን ካሳለፈችው ሕይወት የባሰ አድርጎ፤ የኖረችበትን ውርደትም ገጥሟት የማያውቅ አስመስሎ ካለችበት እንዳትንቀሳቀስ ሊያስራት ታገለ። ወሰነች!!!

የመጀመሪያዎቹን ጥቂት እርምጃዎች ዝሆን ተሸክማ የምትሄድ እስኪመስላት ከብዷት ነበር። ኋላ ግን እንዴት እንደሆነ ልትገልጸው በማትችለው ተአምር ሕዝቡን ሁሉ ጣጥሳ አልፋ ቀሚሱን ልትነካ በሚያስችላት ርቀት ላይ ራሷን አገኘችው። በሥውር ቀሚሱን ዳሰሰች . . . ያለ መሳቀቅ ዳነች!!!

የነካኝ ማነው? ብሎ ሲጠይቅ ከእርሱ ልትሰወር እንደማትችል ውስጧ ሲነግራት ታወቃት። ቀስ ብላ ሰውነቷን ስታዳምጥ ከረዥም ጊዜ በፊት የምታውቀው ጥንካሬና ጤንነት ተሰማት። ከፊትና ከኋላ አንዳች ነውር እንዳይገኝባት ቀሚሷን ተመለከተች። የሚያሳቅቅ . . . የሚያሸማቅቅ ነገር የለም፤ ሁሉ ደኅና ሆኗል:: ለእርሱ እየተንቀጠቀጠች ሰገደች፤ ለሕዝቡ ቀና ብላ መሠከረች። መልስ ያገኘ ሕይወት ይህ ነው።

ለሕዝቡ ስለ አዲሱ ሙሽራዋ እንዲህ አለቻቸው :- የልጅነት ፍቅሬ ጥሎኝ ሄደ፤ የእርሱ ፍቅር ግን ከእርጅናዬ አደሰኝ። ንጹሕ ሳለሁ ያቀፈኝ ባሌ በሕመሜ ወራት ተፀየፈኝ፤ እርሱ ግን ከነ ደሜ አቀረበኝ። የራሄልን ዕንባዋን በአርያም የተቀበለ እርሱ የእኔን ደም ያደርቅ ዘንድ ወደ ምድር ወረደ። ደሜ አልቆ ወደ ሞት ጎዳና ስሄድ በመስቀል ላይ እጁን ዘርግቶ በችንካሩ ገመድ (tube) ደሙን ለገሰኝ፤ ወትሮም ደም አንሶት ሕይወቱ አደጋ ለተጋረጠበት የሚለገስ ደም ነውና። በሰው ፊት ይዞኝ ከመወጣቱ በፊት በምሥጢር ጫጉላችን ሰውነቴንና ቀሚሴን አጥቦ አዘጋጀኝ። ሕግ ገፋኝ ፍቅር ግን አቀፈኝ።

አንቺ ማን ነሽ? ሙሽራሽስ ማነው? ለምትሉኝ በዲያብሎስ የኃጢአት ሾተል ቆስዬ ደሜን ሳዘራ የኖርሁ፤ በአሕዛብ ተንቄ በእኔነቴ ተሳቅቄ የኖርሁ እኔ ቤተክርስቲያን . . . እኔ ምዕመን . . . እኔ ክርስቲያን ነኝ! ሙሽራዬም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!

በዕለተ ዓርብ ደሜን ያደረቀው መሸራዬ ከደፋው የእሾህ አክሊል በሚንዠቀዠቅ ደም ፊቱ ተሸፍኖ አየሁት። ከእርሱ ውጪ የአይሁድ ጥላቻም ሆነ የሮማ ወታደሮች ጭካኔ ሊታየኝ አልቻለም። እንዲዋጀኝ ቀሚሱን ለያዝኩት ለሙሽራዬ የፊት መሸፈኛ ክንብንቤን ፈትቼ ፊቱን ጠርጎ እንዲሰጠኝ አቀበልሁት። ሴት መሸፈኛዋን የምትገልጥ ሙሽራዋ ፊት ነውና። እኔና እርሱ በደም ተሳስረናል። ውዴ የእኔ እኔም የእርሱ ነኝ። የፊት መሸፈኛዬን በቆይታ ሳያው በልቤ የተሳለው የፊቱ መልክ በደም ታትሞበት ነበር፤ እስከ ወዲያኛው!!!

ማስታወሻ :- ቀሲስ ታምራት ውቤ የቴዎሎጂ ዲግሪና የሳይኮሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው::  ከክህነት አገልግሎታቸው በተጨማሪም ደራሲና የሥነ ልቡና ባለሙያ (Clinical Psycologist)  ናቸው:: ኤጲፋንያ በተሰኘ ቻናልም በቪድዮ ያስተምራሉ::
https://youtube.com/@EpiphaniaTube?si=PNTkqiTwsXLytMYL
ቀሲስ ታምራት የጃንደረባው ሚድያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ረቡዕ የሚነበቡ ይሆናል::
/ደም-ላነሳት-ደም-ልገሳ/

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው

#እነሆ_ውኃ
#ሰውማ_እናታችን_ጽዮን_ይላል

ሰው በምድር ላይ ያቃተው ነገር ቢኖር ሰው መሆን ብቻ ነው:: ብዙ ነገር መሆን ችሎአል:: እንደ አሣ በባሕር እንደ ወፍ በሰማይ በርሮአል:: እንደ እንስሳ መኖር ችሎአል እንደ አውሬም መጨከን ተሳክቶለታል:: እንደ ንስር ከሩቅ አይቶአል:: እንደ ውኃ ሰርጎ ብዙ ተመራምሮአል:: ለብዙ ሰው የከበደው ነገር ቢኖር ሰው መሆን ነው::

አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ  ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት።

ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ግን እኛም እንደርሱ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። 

ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።

ሰው በምድር ላይ ያቃተው ነገር ቢኖር "ሰው መሆን ነው"!  አዋቂ መሆን ቀላል ነው! ኃያል መሆንም ይቻላል:: ባለ ጥበብ መሆንና መራቀቅም ይቻላል:: ጀግና መሆንም እንዲሁ:: ሰው ያቃተው ሰው መሆን ብቻ ነው::

ሰው መሆን ትልቅ ዋጋ አለው:: ይህንን ዋጋ ስንዘነጋ በአርኣያ ሥላሴ ለተፈጠረው ሰው ሌላ ሚዛን እንፈልግለታለን:: ሰውነቱን ትተህ በሀብቱ በእውቀቱ በዘሩ በቋንቋው ከመዘንከው አንተም ሰውነትህን ታጣለህ::

ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ  ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው።  "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል? በውስጥዋም ሰው ተወለደ የተባለው ስለ ጌታ ነው:: እሱን የሚመስሉ እውነተኛ ክርስቲያኖችም  ሰዎች ናቸው::

ሰው ከሆንክ "እናታችን ጽዮን" ትላለህ:: ጽዮንን "እናታችን" ብሎ ለመጥራት ግን "ወንድሜ ወንድሜ" መባባል ይቀድማል:: ይህን ማለት ያልቻለ ግን ሰው አይደለም:: ጽዮንም እናቱ አይደለችም::

ነቢዩ በባቢሎን ሆኖ ስለ ጽዮን ሲያስብ መዝሙር ለመዘመር ተቸግሮ ነበር። "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን" ብሎ ነበር::

እኛም የአንዲትዋ የጽዮን ልጆች ሆነን በተለያየንበት ዘመናችን እንዲህ እንላለን :-

በዘረኝነት ወንዝ ውስጥ ሆነን አክሱም ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን

የማረኩን ኃጢአቶቻችን ሳንላቀቃቸው የዝማሬ ቃል ፈለጉብን

የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በጥላቻ ልብ እንዘምራለን?

የጽዮንንስ ዝማሬን ቂምና በቀል አርግዘን እንዴት እንዘምራለን?

ታቦተ ጽዮን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ
ከዘር ከነገዴ በላይ ቤተ ክርስቲያንን ባልወድድ!

እናታችን ጽዮን ሆይ እባክሽን አንቺን እናታችን ብለን ሰው ለመሆን አብቂን:: ከራሳችን ጠብቂን የጥላቻን ዳጎን ሰባብሪልን::  ፍልስጥኤማውያን በአንቺ ግርማ የተነሣ ፈርተው የዳጎን መድረክን እንዳልረገጡት እልቂትና ደም መፋሰስ በአማላጅነትሽ የኢትዮጵያን ምድር አይርገጥ:: እንደ ጣዖት በልባችን የነገሠውን ክፋት ሰባብረሽ ከእግርሽ በታች አድርጊልን::

https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze
​​ኅዳር 24

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አራት በዚች ቀን የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑበት ነው፣ የአቡነ ዜና ማርቆስ ልደታቸው ነው።

ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ

ኅዳር ሃያ አራት በዚህች ቀን በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው።

እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋርነ እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለእነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዙአብሔር አይቀርብም።

ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ። በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮች ላይም ሃያ አራት አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ።

ሁለተኛም እንዲህ አለ ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የወርቅ ጽንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይም የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት ። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐረገ።

የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም ። እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ።

እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆኑ በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእሱ ሰገዱለት ። አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው አቤቱ ፈጣሪያችን ኃይልና ምስጋና ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና ።

እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ሁነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ።

ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን በዚያው በሐይቅ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አክፍሎትንም በየሳምንቱ ያከፍላሉ፣ ከእሁድና ከቅዳሜ በቀር ምንም አይቀምሱም ነበር፡፡ በእነዚህም ዕለት የአጃ ቂጣ ወይም የዱር ቅጠል ይመጉ ነበር፡፡ ወዛቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድሪቷን እስኪያርሳት ድረስ እስከ 70 ሺህ ስግደትንም በመስገድ ራሳቸውን እጅግ አደከሙ፡፡ በእነደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ያቆማቸው፡፡

ከዚህ በኋላ ስለሆነው ነገር ራሳቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሲናገሩ ‹‹…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ ‹ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን› የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ…..›› (ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገጽ 216-223)

ይህንን ታላቅ በዓል ነው ዛሬ የምናከብረው፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት እንኳን አንደበታቸው የለበሱትም ልብሳቸውም ጭምር እግዚአብሔርን በሰው አንደበት እንደሚያመሰግን በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፏል።

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሼር አድርጉ
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
Daniel:
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል "*+

=>ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

+ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

+አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

+እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

+እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

+"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

+ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

+አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

+ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

+ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

+በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

+እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

+በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

+በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

+ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

+በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

+እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

+ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

+በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

+"ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

+ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:-
"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

+ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

+እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::
<<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>>

=>አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ኅዳር 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ)
3.ቅዱስ ሮማኖስ
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመአብ፣ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

“ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” ሮሜ 8፡35-36

ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራን፣ ሞትንና ስደትን፣ የመቀበል ታሪኳ ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ  ይኽንና መሰል መተኪያ የሌለው ሕይወት የሚያጠፋና ሥጋት ላይ የሚጥሉ ተፈጥሮአዊ፣ ሰብዓዊ ክብሩን የሚያራክስ ተግባራት እንዳይደገሙ ለማድረግ በሚጥርበት ዓለም ችግሩ በተለይም በሀገራችን እየተባባሰ መቀጠሉ እጅግ ያሳስበናል፡፡

በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶሌ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ሠላሳ ስድስት፣ እንዲሁም በሶሌዲገሉና ጢጆለቡ በተባሉ ቀበሌዎች ሃያ ስምንት ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው ተለቅመው ሰማዕትነትን ሲቀበሉ ከእነዚህም ሰባቱ ሴቶችና ሃያ አንዱ ወንዶች ናቸው፡፡ በዚህ ጥቃት የሰባ ዓመት አዛውንትና የሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት ይገኛሉ፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊትም በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን አምስት ምእመናን ሰማዕት ሲሆኑ የሦስት ምእመናን ቤት ተቃጥሏል። በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም አጥቢያ በዓለ ድንግል ማርያምን አክብረው በመመለስ ላይ የነበሩ ሦስት ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ገዳዮች ሰማዕትነት የተቀበሉ መሆኑን ከሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ደርሶን ከሐዘናችን ገና ሳንጽናና ይባስ ብሎ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት የጐንደር ዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት የአቋቋም መምህር የሆኑት መምህር ፍሥሐ አለምነው ባልታወቀ ግለሰብ በድንጋይ ተወግረው መገደላቸው እና ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሌሊቱ 11፡00 ላይ የማዕከላዊ ጐንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት በኲረትጉሃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተመተው መገደላቸው በእጅጉ ከማዘናችንም በላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያረጋግጥ አድራጐት ሆኗል፡፡ 

በዚህ መግለጫ በቅርብ የተፈጸመውን ለማቅረብ ተሞከረ እንጅ ተመሳሳይ ግድያና፣ ስደት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል የየዕለት ዜናችን ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ለአብነትም ያህል በወለጋ፣ በጐንደር፣ በጐጃም፣ በወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በመሳሰሉት እየተፈጸመ ያለው ድርጊት መንግሥትና ሕገ መንግሥት ባለበት ሀገር፣ የውጭ ወራሪና ድንበር ተሻጋሪ ጠላት ሳይኖርብን፣ እርስ በርሳችን በምናደርገው መጠፋፋት፣ ሃይማኖት ተኮር ጥላቻዎች፣ የንፁሐን ሕይወት መቀጠፉና የሀገርን ሀብት መውደሙ እኛንም ሆነ በመላው ዓለም መፍቀሬ ሰብእ የሆኑ የሰብዓዊ ክብር አስጠባቂ ተቋማትን ሳይቀር ማሳዘኑ ቀጥሏል፡፡ 

ይህ ሁኔታ በታሪክ ከመመዝገቡ በላይ የዜጎች በሕይወት የመኖር፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት፣ የአካልና የንብረት ደኅንነታቸው መጠበቅ፣ የሃይማኖትና የእምነት ነፃነት መከበር፤ የዜጎች ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ ያለባቸውን አካላት በሙሉ በምድርም ሆነ በሰማይ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ነው፡፡ እየተፈጠረ ባለው አስከፊ መከራ፣ በጭካኔ የተሞላ ድርጊት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ማጣት የዜጎችን ሕይወት፣ አካልና ንብረት፣ የእምነት ተቋማትን፣ መተኪያ የሌላቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶችና መስሕቦችን ሲያወድም፣ በሀገር ሁለንተናዊ ደኅንነትና በሕዝቦች ትሥሥር ላይ የፈጠረው አለመተማመን በቀላሉ የማይመለስ አደጋ ነው፡፡ 

ይኽ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተከሰተው ረሀብ፣ ድርቅ፣ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነት በተጨማሪ በየቦታው በተፈጠሩ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች ምክንያት በርካቶች ቀያቸውን ለቀው፣ መነኰሳት ገዳማትን ትተው ተሰደዋል፤ ወላድ እናቶች፣ ሕሙማንና አረጋውያን በሕክምና እጦት እያለቁ ነው፣ ሕፃናትና ወጣቶች ከጤናማ እድገትና ከትምህርት ገበታ ተደናቅፈዋል፣ 

በመሆኑም

፩. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ከግጭትና ከጦርነት፣ ከርስ በርስ መገዳደል ወጥተው በውይይትና በምክክር፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት ስሜት የታላቋን ሀገር መልካም ስምና ክብር እንዲሁም የዜጎቿን ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ተግባር ቅድሚያ እንዲሰጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡  

፪. በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንፁሐን ምእመናንና ተቋማት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች  በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ መንግሥትና የሚመለከታችሁ ሁሉ ዋስትና እንድትሰጡ፣ ወንጀል ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ድርጊቱንም መላው ዓለም እንዲያወግዘው ቋሚ ሲኖዶስ በአጽንዖት ይጠይቃል፡፡ 

፫. ከቤተ ክርስቲያን አልፎ የሀገርና የዓለም ሀብት የሆኑ ቅዱሳን መካናት፣ እንደ ዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም፣ አሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም እና አካባቢው፣ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳምና አካባቢው የመሳሰሉ ሁሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት አደጋ የተጋረጠባቸው በመሆኑ ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን።

፬. በመጨረሻም በየቦታው የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለማስቀረት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራ ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብን ለቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራው መሳካትም  በየደረጃው ያላችሁ አህጉረ ስብከት የስጋት መረጃዎችን ለሚመለከተው ሁሉ በማሳወቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡   
 
ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ለሞቱት የተዋሕዶ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን አስበ ሰማእትታን እንዲከፍልልን፣ ለወገኖቻቸው ሁሉ መጽናናት እንዲሰጥልን፣ ስለስሙና ስለሰብዓዊ ማንነታቸው በመከራና ሥጋት ወስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ ጽናቱንና ብርታቱን እንዲሰጥልን፣ አጥፊዎችን እንዲገስጽልን፣ ስደትና አለመረጋጋትን እንዲያርቅልን፤ የሀገራችንን አንድነትና ሰላም፣ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሕልውና እንዲጠብቅልን የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ 

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
🗓ኢየሱስ ያሉትን ሁሉ የማንቀበለው ለምንድንነው?

ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በማለታችን ተገለልን ይላሉ

ኢየሱስ ያለን ሁሉ የምንቀበል ከሆነማ አጋንትንም በተቀብለን ነበር ። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ አጋንት እንድህ ሲሉ እንሰማ አለን
📕
(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 4)
----------
33፤ በምኵራብም የርኵስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፥ በታላቅ ድምፅም ጮኾ።

34፤ ተው፥
#የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ #አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ አለ።

35፤ ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም
#ውጣ ብሎ #ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ።
📕" አጋንንትም ደግሞ።
#አንተ ክርስቶስ #የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ ገሠጻቸውም ክርስቶስም እንደ ሆነ አውቀውት ነበርና #እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።"
(የሉቃስ ወንጌል 4:41)

💦ከላይ እንዳያችሁት አጋንንት አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ሲሉ ደስ ይላል አይደል ቃሉ 😄እውነትም የተናገረ ይመስላል አይደል አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ሲሉ ጌታ ኢየሱስ ግን እንድናገሩ እራሱ አልፈቀደላቸውም ምክንያቱም አጋንንት በእውነት የተሸፈነ ሀሰት ይናገራል እንጅ እውነትን ሊናገር አይችልም አጋንንት እውነትም ቢናገርም የሚናገረው በሰዎች ውስጥ ሁኖ ሰዎችን ለማጥፋት ነው
💧ጌታ ኢየሱስ ለጠየቀው ጥያቄ ጴጥሮስ እንድህ ብሎ
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 16)
----------
16፤ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
💧ጌታ ኢየሱስም እንድህ አለው
17፤ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

💦እዚህ እንግድህ እንደምናዬው አጋንንትም ጴጥሮስም የተናገሩት አንድ ሁኖ ሳለ ለአጋንንት ዝም ብለህ ውጣ ሲለው ለጴጥሮስ ግን ሥጋና ደም አልገለጠልህም ብፁዕ ነህ ብሎ ሲመሰክርለት እናይ አለን ።
💧ምክንያቱም አጋንንትና ጴጥሮስ የተናገሩበት መንፈስ ይለያያልና ነው ።
🗓እንግድህ ምን እንል አለን አጋንንትን ተቀብለን ቢሆንስ በጠፋን ነበር ።
🗓ስለዚህ ላለመጥፋት መናፍቃን ኢየሱስ ሲሉ ዝም ብለህ ውጣ እንል አለን ምክንያቱም መናፍቃን ኢየሱስ ሲሉ እውነተኛ ወንጌልን ለመስበክ ሳይሆን በኢየሱስ ስም የሚነግዱ አደገኛ የሰይጣን ልጆች ናቸው በውስጣቸው ክፋትን አስበው የሰው ልጆችን ከእውነተኛ የክርስቶስ አካልና መንገድ ለማስወጣት ስለሆነ ዝም ብለህ ውጣ አትለፍልፍ እንለው አለን እንጅ ኢየሱስ ስላለ የምንቀበል የሰይጣን ተባባሪዎች አይደለንም ሰይጣንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቅዱስ ..ይላልና ። ኢየሱስ ስላለ ሰይጣንን ብንቀበል እንደምንጠፋው ሁሉ ኢየሱስ ስላሉ ፕሮቴስታንትን መቀበል መጥፋት ነው።
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
❤️💸💲 Forex Trading መማር ለምትፈልጉ ከ ከመሰረታሚ ጀመሮ እስከ Intermediate level ድረስ ለ 3 ወር የተዘጋጀ Course አለ መማር ትችላላቹ ! 40% Discount አዘጋጅተውላችዋል @City_Forex_Ethiopia
እግዚአብሔርን አምናለሁ አከብራለሁ የሚል አንድ ሰው ነበር ከእለታት በአንደኛው ቀን አንድ እንግዳ ወደቤቱ ይመጣል እሱም እንደክርስትናው ሥርዓት ጓዙን ተቀብሎ 🍽የሚበላውንና የሚጠጣውንየሚተኛበትንም አዘጋጅቶ ሲያብቃ እግሩን ያጥበው ጀመር፡፡ ይህ ደግ ሰው የእንግዳውን እግር እያጠበ "ዛሬ አንተን ወደ ቤቴ ያመጣልኝ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው" ይላል:: እንግዳውም "እግዚርአብሔር ማነው?" ይለዋልእድሜህ በጥያቄው የደነገጠው እንግዳ ተቀባይ "ምን ማለትህ ነው እግዚአብሔርን አታውቀውምን?" ይለዋል "ኧረ በፍጹም ስሙንም ያለዛሬ ሰምቼ አላውቅም"ይላል እንግዳው፡፡ ለመሆኑ  ስንት ነው?ይላል የቤቱ ባለቤት። እንግዳውም ፷(ስልሳ) ይላል የቤቱ ባለቤት በጣም በመደነቅ በመናደድም ጭምር የእንግዳውን እግር ማጠብ አቋርጦ "60 ዓመትእንዴት ሙሉ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሰውማ እቤቴ አያድርም" ብሎ ያባርረዋል። የቤቱ ባለቤት እኩለ ለሊት ላይ ራእይ ያያል ልኡል እግዚአብሔር ተገልጾ "ዛሬ  ውለህ አመሸህ?" ሲለው የቀኑን ውሎ ተናግሮ ሲያበቃ "60 ዓመት ሙሉ አንተን የማያውቅ እንግዳ በቤቴ ሊያድር ሲል እኔ ያንተ ባርያ አባርርኩት" አለ።እግዚአብሔርም ይህንን ስህተቱን ሊያርም ነበርና መምጣቱ "ወዳጄ ሆይ እኔ ፷(ስልሳ) ዓመት የታገስኩትን አንተ አንድ ሌሊት መታገስ አቃተህን?" .....ብሎ መክሮት ተለየው

ብዙውን ጊዜ ሰው ከእግዚአብሔር ቀድሞ ፍርድ ለመስጠት ሲደክም ይታያል። እሱ እኛን በታገሰን ልክና መጠን ባይሆንም ምሳሌነቱን ወስደን ሰዎችን ይቅር ማለትና መታገስ አለብን
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
አንዲት ሴት ወደ ንስሐ አባቷ ጋር በመሔድ ከዛሬ ጀምሮ ቃለ እግዚአብሔር ለመማር ወደ ቤተክርስቲያን አልመጣም አለቻቸው።
እኚህ አባትም ደንገጥ ብለው  ለምን ልጄ ብለው ጠየቋት

እሷም እንዲህ አለች" ለትምህርት የሚመጡ ሰዎች በስብከት ሰዓት ስልካቸው ላይ አፍጠው  ፌስቡክናሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች እያዩ አንዳንዶች አፍ ለአፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ፣ ሰውን ያማሉ ሌሎቹ ደም በሀሳብ ሔደዋል ሁሉም አስመሳዮች ናቸው ስለዚህ ሁለተኛ አልመጣም" አለቻቸው።

አባም ዝም አሉ ፦ ከዚያ ትንሽ ቆይተው ውሳኔ ላይ ከመድረስሽ በፊት ለአንቺ የሚሆን አንድ ጥያቄ አለኝ አሉዋት

እሱዋም ጠይቁ አለቻቸው

አንድ ብርጭቆ ሙሉ ውሃ 💦 ይዘሽ በጉባኤው መሀል አቋርጠሽ መምጣት ትችያለሽ አሉዋት

እሱዋም በሚገባ እችላለሁ ብላ አንድ ጠብ ሳይልባት እንዳለችው አደረገች።

አባም ጥያቆውን አቀረቡላት  ውሀውን ስታመጪ  ጉባኤው ላይ ስልክ የሚመለከት ወይም የሚንሾካሸክ አይተሻል  ወይ  አሉዋት

ሴትዬዋም "አለ በፍጹም አላየሁም❗️ለሳቤ ሁሉ የብርጭቆው ውሃ💦 እንይፈስ ሀሳቤ ሁሉ እዛ ላይ አድርጌው ነበር" አለች

አባም እንዲህ አሉ፦ "አየሽ ሙሉ ትኩረትሽን ብርጭቆ ላይ ስለነበር ማንንም አላየሽም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጪ ማድረግ ያለብሽ ነገር ይህ ነው ሙሉ ትኩረትሽ እግዚብሔር ላይ መሆን አለበት አለበለዚያ ትወድቂያለሽ። አይኖችሽን ከሰዎች ላይ አንስተሽ ክርስቶስ ላይ አድርጊ።

እግዚአብሔር እኔን ተከተሉኝ እንጂ ክርስቲያኖችን ተከተሉ አላለም። አእምሮአችን ክርስቶስ የተናገረውን፣ ያደረገውን፣ ያሰበው ምን እንደነበር እንዲያሰላስል እናድርግ ከሰዎች ላይ አይናችንን አንስተን መስቀሉ ላይ አይናችንን እንትከል።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media


https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል....❤️

#ይቀላቀሉን!!
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
2024/11/12 18:17:07
Back to Top
HTML Embed Code: