Telegram Web
+• ጊዜው ገና ነው •+

አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ። በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት፥ ከዕለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል። ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ። ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ። ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ። 

አንዱ ተነሳና፥ “እኔን ብትልከኝ፥ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱ አይሠራም። ብዙዎቹ አያምኑህም። ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ። 

ሌላኛው ተነሳና፥ “እኔን ከላክኸኝ፥ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱም አይሠራም። ብዙዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ። 

ሌላው ደግሞ ተነሳና፥ “እኔን ላከኝ። ፈጣሪም አለ፥ ገነትም አለ፥ ሲኦልም አለ፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ለማሰብ ጊዜው አሁን አይደለም ብዬ አሳምናቸዋለሁ።” አለ። የአጋንንቱ አለቃም ደስ እያለው “ይህ ጥሩ መንገድ ነው!” በማለት አሳቡን ተቀበለና ላከው ይባላል።

ሰይጣን ማዘግየት ጥሩ ስልት መሆኑን ስለሚያውቅ፥ ለማዘግየት ይፋጠናል። በሐዲስ ኪዳን ላይ ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።” (1 ተሰ 2:18) ሲል እናገኘዋለን። ሰይጣን ላያስቀረን ይችላል፥ ግን ቢያንስ ሊያዘገየን ብዙ ይሞክራል።

እርሱ ዓለማዊ ጓዞቻችንን ለአፍታ ስንኳ አውርደን ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት እንድናስብ አይፈልግም። ስለ ጸሎት ብታስብ፥ "አሁን ደክሞሃል። ጊዜው አይደለም። ሌላ ጊዜ ትጸልያለህ" ይልሃል። ለመጾም ብትዘጋጅ "አሁን ጉልበት ስለሚያስፈልግህ ብላ። የምትጾምበት ጊዜ አይደለም፤ ሌላ ጊዜ ትጾማለህ።" ይልሃል። ለመስገድ ብትዘጋጅ "ኧረ ተረጋጋ፤ ጊዜው አይደለም፥ ጾም ሲገባ ትሰግዳለህ" ይልሃል። ንስሃ ልትገባ ብትዘጋጅ "ቆይ እንጂ፥ ዘልለህ ጨርሰህ አንዴ ብትታጠበው አይሻልም?" ለማለት የሚቀድመው የለም። ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ነው ካልክ "አንተኮ ገና ነህ፥ ለወደፊት ጣጣህን ስትጨርስ ቀስ ብለህ አመቻችተህ ትቆርባለህ" ብሎ ያዘናጋሃል።
🟢🟡🔴
በዚህ ሁሉ መዘግየት ውስጥ መልአከ ሞት መቼ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ለመንፈሳዊ ነገር ስንነሳ፥ ሰይጣን "ጊዜው ገና ነው" ማለቱ አይቀርም። እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል“ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ኛ ቆሮ 6፥2) እንደሚል እናስታውስ። ለመዳናችን ቀጠሮ አንስጥ።
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን

የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።

የብፁዕነታቸው ቡረከት ይደርብን



#ተዋሕዶ_ሚዲያ_ማዕከል

ቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
ዜና አበው
አባቶቻችንን ዕንወቅ
በወርቅ ቅቦች ሳንዋጥ ዕንቁዎችን
እናክብር።

ብጹዕ አቡነ አቡነ አትናቴዎስ
የደቡብ ወሎ ሐገረ ስብከት
ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
ዛሬም በእርጅና ከአገልግሎት ያልተለዮ ሐዋሪያ።

አባቶቻችንን በቁመተ ስጋ እያሉ የማክበር ልማድ ይኑረን የአገልግሎታቸው ዋጋ ከፋይ መድኃኔዓለም ቢሆንም በአባትነታቸው ጥላ የምንከለል በጸሎት በምርቃታቸው የለመለምን በትምህርት በተግሳጻቸው የተጠቀምን ልጆቻቸው ፍቅራችንን መግለጥ አርአያነታቸውን ማጉላት አለብን ሲሞቱ ዋዬ ወየው ለበጣ ነው መነኮሰ ሞተ ነውና
በክርስቲያን ሙስሊሙ የተወደዱ የሕዝብ አባት
የሐገር ሕሊና የግፉአን አንደበት አቡነ አትናቴዎስ
36,አመታት በሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል ልዮ ጸጋቸው የምዕመናን ፍቅር ነው እሳት በነደደበት ቤተክርስቲያን በተጠቃችበት ቦታ ቀድመው ከተፍ የሚሉ ልጆቼን አትንኩ ብለው ከነበልባል የሚገቡ አባት ናቸው ለዚህ ምስክር ከሚሴ ነው የዛሬን አያድርገውና በሕመም በእርግና ከቤት ሳይውሉ።
ለገዳማት ለአብነት ትምህርት ቤት ያላቸው ፍቅር ተነግሮ አያልቅም ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም ከምን አንስተው ምን ደረጃ እንደደረሰ እኛ ባንናገር ስራቸው ቆሞ ይመሰክራል።
የታላቁ ሊቅ የጌታ መምህር አካለ ወልድ ጉባኤ ቤት ቦሩ ሜዳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ጉባዔም ሕያው ቋሚ ስራ የሰሩበት ነው። በክህነት የሚገኙትን ደሞዝ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ነው የሚያውሉ።
ቅድመ ጵጵስና በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት በአቡነ ዮሴፍ አቅራቢነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሙሉ ድጋፍ እንዲያገለግሉ ተልከው ሰፊ ስራ ሰርተዋል በ19 77 ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ጵጵስና ከመናኙ ፓትርያርክ አቡነ ተክለሃይማኖት እስኪቀበሉ ድረስ ለክብረ አበውም በቅተው በሊቀጳጳስነት በኢየሩሳሌም እስከ 19 85 አገልግለዋል።
ሐብተ ልሳን የተሰጣቸው በእብራስጥ በዓረብኛ የተራቀቁ
በጣፋጭ አንደበታቸው ከሐዲስ ከቁርአን እየጠቀሱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በሐገረ ስብከታቸው የሚያስደምሙ ፍቅር የሚሰኩ አንድነት የሚያጸኑ እውነትን እውነት ውሸትን ውሸት የሚሉ ትጉኀ እረኛ ናቸውደ
ከ19 85 ጀምሮ እስከ ዛሬ የደቡብ ወሎን ሐገረስብከት በእረኝነት ይመራሉ በቅርቡ በእርጅናና በሕመም ምክንያት ከአስተዳደር ስራ ራሳቸውን ቢያገሉም ሐገረ ስብከቱ በብጹዕ አቡነ ኤርምያስ ይመራል።
አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ ቦታው ግሸን ደብረ ከርቤ ነው በወቅቱ ሆሳዕና አካባቢ አንድ ህንጻ ቤተክርስቲያን የሚያሰሩ አባት በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መውረጃ ጋር ቆመው ይለምናሉ የሐገረ ስብከቱ ሹማምንት ይቃወሟቸዋል የሰበሰቡትን ገንዘብም ይይዛሉ ሕጋዊ ማስረጃም ቢያሳዮ ሰሚ ጠፋ በቃ ብጹዕ አባታችን ጋር ውሰዱኝ ብለው ይማጸናሉ በብዙ ተማጽኖ አቡነ አትናቴዎስ ካረፉበት በዓት ይመጣሉ ጉዳዮን በዝርዝር ይሰማሉ ከተከሳሹ ከሳሾቹም አለ ሐገረ ስብከታቸው ከደቡብ መጥተው ይላሉ ይሄ አቡነ አትናቴዎስ ይቆጣሉ ደቡብ ሰሜን ምስራቅ ምዕራብ አትበሉ "የአንድ ገበቴ ውሐ ነን ቤተክርስቲያን አንዲት ናት።" ስለቦታውም የክፍሉ ሊቀጳጳስ ወንድሜ አቡነ መልከጼዴቅ ነግረውኝ ና በረከት ተቀበል እመቤታችን የተገለጠችበት ነው ብለው ጋብዘውኝ ሳልሄድ ሞት ቀደማቸው በሉ እንደውም በአውደ ምሕረቱ እንዲለምን ፈቅጃለው በቅዳሴ ቤት በዓልዋ መጥቼ አያታለሁ ብለው ከሳሾቹን አሳፍረው እራሳቸውም መባ ሰጥተው የተከሰሱትን አባት ይሸኛሉ እኛ ትሁት ሰው ግን አውደ ምሕረቱ ይቅርብኝ የቆምኩት ይፈቀድልኝ ብለው እጅ ነስተው ይወጣሉ።
አቡነ አትናቴዎስ እንዲህ ያሉ አብረሐማዊ ናቸው።
እኛ ትጉህ ምዕመን አባት ከምዕመናን እየለመኑ የሆሳዕና ቡሽና ደብረ ምጥማቅ ማርያምን ቤተክርስቲያን እና አንድ በታቦተ ኢየሱስ ሌላ ቤተመቅደስ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት አሳንጸው ለቅዳሴ ቤት አብቅተዋል።
በከንባታና ሐዲያ ሐገረ ስብከት ይገኛል።
የአባታችንን እድሜ ያርዝምልን ሙሉ ጤናን እግዚአብሔር ይስጥልን ታዛቢ አራሚ አባት አይንሳን አሜን አሜን አሜን
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
"አኩርፈው የተለዩንን ወደ እኛ እንመልሳቸው እኛም ከሚያስኮርፍ ነገር እንራቅ አንድነታችንን እናጠናክር።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ እና  መንፈሳዊ ችግሮችን አጥንቶ ውሳኔ የሚሰጠው ምልዓተ ጉባኤ መከፈቱን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አበሰሩ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ቤተክርስቲያን ከፈተና አልተለየችም ወደፊትም አትለይም ያሉ ሲሆን የደረሰብን ጫና ምን ያህል እንደሆነ የሚታወቅ ነው አንድ መሆን አለመቻላችንም ፈተና ሆኖብን ክፍተትን ፈጥረናል ብለዋል።

የቀደምት አባቶቻችን የሰሩትን ልንደግም ይገባል ፤ ኃላፊነት አለብን ኃላፊነትታችንንም በሚገባ ልንወጣ ይገባል ፤ ለቤተክርስቲያን ክብር ከወገኝተኝነት የጸዳ እንከን የለሽ አንድነትን ልንፈጥር ይገባናል ነው ያሉት ቅዱስነታቸው።

በርካታ ተከታይ ያላት ቤተክርስቲያን ልጆቿን በቅዱስ ወንጌል ከገነባች ሀብቷን በሚገባ ከጠበቀች እንኳን ለገንዘቡ ለሕይወቱ የማይሳሳ ምእመናን አሏት ፤ ዘመኑ የሚጠይቀውን አሰራር በመጠቀም የምንሰራው አሁን ነው ብለዋል።

በመጨረሻም የሥራዎቻችን ዋስትና በሀገር እና በቤተክርስቲያን ዘላቂ ሰላም ሲኖረው ነው ፤ ቤተክርስቲያን ለሀገር ሰላም የአንበሳው ድርሻም እንዳላት ይታወቃል ድርሻዋንም ለመወጣት ትሠራለች ብለዋል ቅዱስነታቸው።


#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 25  አጀንዳዎችን አጽድቆ ውይይት ጀመረ !

ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስአበባ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 25 አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ጀምሯል ።

ምልዓተ ጉባኤው ዛሬ ጠዋት ባደረገው ስብሰባ አጀንዳ አርቃቂ ሰባት ብፁዓን አባቶችን መሰየሙ የሚታወቅ ሲሆን ለምልዓተ ጉባኤው ቀርበው ከጸደቁት 25 አጀንዳዎች መካከል በቅዱስ ፓትርያርኩ መልእክት እና በ 42 ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በቀረበው የአቋም መግለጫ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

በቀጣይም ምልዓተ ጉባኤው የሚወያይባቸው አጀንዳዎች በየዕለቱ ለምእመናን እንደሚገለጹ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አሳውቀዋል።

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
ልሣነ ግእዝ
ዐረፍተ ነገር
ከመ = እንደ
ከመ እንስሳ = እንደ እንስሳ
ከመ ዮም = እንደ ዛሬ
ከመ ጽጌ = እንደ አበባ
ከመ ተፈጸመ = እንደ ተፈጸመ
ከመ ኀለየ = እንዳሰበ

ለ = የ

ልደታ ለማርያም
ቤቱ ለንጉሥ
ሀገሮሙ ለነቢያት

ወ = እና

አዳም ወሔዋን
ቃየል ወአቤል
ማርያም ወሰሎሜ

ምስለ = ጋር ፣ ጋራ

ሰብእ ምስለ ሰብእ  = ሰወ ከሰው ጋር
ዘመድ ምስለ ዘመድ = ዘመድ ከዘመድ ጋር
አንበሳ ምስለ አንበሳ = አንበሳ ከአንበሳ ጋር
ምስለ መንፈስከ = ከመንፈስህ ጋራ

ቅድመ = በፊት ፣ ከፊት

ቅድመ ሰብእ = ከሰው በፊት
ቅድመ ልደት = ከልደት በፊት
ቅድመ ሰዓት = ከሰዓት በፊት

ድኅረ = በኋላ

ድኅረ ዘመን = ከዘመን በኋላ
ድኅረ ልደት = ከልደት በኋላ
ድኅረ ትንሣኤ = ከትንሣኤ በኋላ

እንበለ = ያለ ፤ በቀር

እንበለ ንዋይ = ያለ ገንዘብ በቀር
እንበለ ዘመድ = ያለ ዘመድ
እንበለ ዐስብ = ያለ ደሞዝ

ቦ = አለ ፣ ነበረ /  አልቦ = የለም

ቦ ሰላም           አልቦ ዝናም
ቦ ፍቅር            አልቦ ፍቅር
ቦ ሕግ             አልቦ ንዋይ
ቦ ንዋይ
ቦ ሥርዓት

አኮ = አይደለም

አኮ ኤልያስ መምህር
አኮ ጸሓፊት ሐና = ሐና ጸሐፊ አይደለችም
አኮ ሰብእ = ሰው አደለም

ኢ = አፍራሽ

አወንታ             አፍራሽ

በልዐ               ኢበልዐ
ጾመ                 ኢጾመ
ሖረ                  ኢሖረ
ጸሓፈ               ኢጸሓፈ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Share share share share share share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
           
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍት ስብስብ 📚
💒 የአለማየሁ ዋሴ መፅሐፍት 📚
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

➱ 1, እመጓ
➱ 2, ዝጓራ
➱ 3, መርበብት
➱ 4, ሰበዝ
➱ 5, ሜተራሊዮን


➲ ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍ ማውጫ 📖
https://www.tgoop.com/+bmWacGGbXvJjOTQ8
.
🔔  ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች  🔔

🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ
የብዙ ዘማሪያንን መዝሙሮችን አዘጋጅተናል
በመቀላቀል የፈለጉትን መርጠው ያድምጡ‼️

🔔➯ የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔔➯ የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
🔔➯ የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
🔔➯ የቀዳሜጸጋ መዝሙር
🔔➯ የኪነጥበብ መዝሙር
🔔➯ የቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
🔔➯ የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
🔔➯ የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
🔔➯ የዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
🔔➯ የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
🔔➯ የዘማሪት አቦነሽ አድነው
🔔➯ የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
🔔➯ የዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ


በቻናላችን ላይ የእነዚህን ድንቅ ዝማሬ እና ሌላ
ብዙ መዝሙሮችን ያገኙበታል ይ🀄️🀄️ሉን።
➲ @Orthodox_mezemur

መዝሙሮቹን ለማግኘት ከስር
OPEN የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ !

ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስአበባ)

የጥቅምት 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለተከታታይ 6 ቀናት ማኅበራዊ ፣ መንፈሳዊ እንዲሁም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ  ውሳኔ በማሳለፍ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

ጉባኤው በዛሬ በ 6 ተኛ ቀን ውሎው አስተዳደራዊ ጉዳይን የያዘ የመሪ ዕቅድ ተመልክቶ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ተጨማሪ ግብዓት ተጨምሮበት ለግንቦት ርክበ ካህናት እንዲቀርብ ወስኗል፡፡


በጸደቁ አጀንዳዎች ላይ ላለፈው አንድ ሳምንት ሲወያይ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ በማድረግ መግባባት በሰፈነበት ሁኔታ ጉባኤውን ማጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን በማጠናቀቂያው በሕግ ፣ በመሪ ዕቅድ ትግበራ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ጥናት ላቀረቡ እና ማብራሪያ ለሰጡ ባለሙያዎች ብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ማቅረባቸውን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን አስመልክቶ ቅዱስነታቸው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

©EOTC TV

https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮችን
በድምፅ / በኦድዮ ለማግኘት ከስር
( ክፈት ) ሚለውን ይጫኑ።
ሰላም 👋

Forex Trading መማር ይፈልጋሉ ⁉️

ከ Beginner level ጀምሮ እስከ Intermediate level ድረስ ለ 3 ወር የተዘጋጀ Course አለ መማር ትችላላቹ ❗️

40% Discount አዘጋጅተውላችዋል
አሁኑኑ ተመዝገቡ 👇👇
@City_Forex_Ethiopia

.
ሰላም 👋

Forex Trading መማር ይፈልጋሉ ⁉️

ከ Beginner level ጀምሮ እስከ Intermediate level ድረስ ለ 3 ወር የተዘጋጀ Course አለ መማር ትችላላቹ ❗️

40% Discount አዘጋጅተውላችዋል
አሁኑኑ ተመዝገቡ 👇👇
@City_Forex_Ethiopia

.
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮችን
በድምፅ / በኦድዮ ለማግኘት ከስር
( ክፈት ) ሚለውን ይጫኑ።
ክርስቲያናዊ አለባበስ

         አንብቡት ይጠቅማቹሃን👇

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5

ስለ አለባበሳችን እንወያያለን ዛሬም እህቶቻችን ላይ እናተኩራለን አበዛኸው ምነው እኛን ብቻ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለው፡፡

ስለ አለባበስ መነጋገር ያስፈለገን እውነተኛ ክርስቲያን በአነጋገሩ፣ በአረማመዱ፣ በአመጋገቡ፣ በአለባበሱ፣ ብቻ በሁሉ ነገሩ የተለየ መሆን ስላለበት ነው ይኸውም ሁሉን በአግባብና በሥርዓት ስለማድረግ ነው እህቶቻችን ላይ ማተኮር ያስፈለገው ደግሞ በአብዛኛው በዚህ ረገድ ትችት የሚበዛው እነሱ ላይ ስለሆነ ነው፡፡

እነሆ ውድድሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረና እየከፋ ነው ለመልካም ነገር መወዳደር ባልከፋ ነገር ግን በከተማችን በተለይም በዋና ዋና መንገዶች ላይ የምናየው የእህቶቻችን አለባበስ አንዷ ከሌላዋ ልቃና በልጣ ለመታየት የሚደረግ ግብግብ እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ በእርግጥ እህቶቻችን በዚህ እንደማይስማሙ እናውቃለን አብዛኞቹም ስለተመቸኝና የምወደው አይነት አለባበስ ስለሆነ ነው እንዲህ የምለብሰው ይሉናል ይሁን እንጂ እውነታው ሌላ ይመስላል ምክንያቱም:-

* ብርድልብስ ለብሰን እንኳን በማንቋቋመው የብርድ ወቅት ሰውነትን በቅጡ የማይሸፍን ብጣሽ ጨርቅ ጣል አድርጎ መውጣት እንዴት ያለ ምቾት ነው?

*እጅግ አስጨናቂ ሙቀት ባለበት ሰዓት ሰውነት ላይ ተጣብቆ ሌላ ጭንቀት የሚፈጥር አለባበስ እንደምን ብሎ ያስደስታል?

ዓላማችን ምንም ይሁን እሱ ላይ የመከራከር ፍላጎት የለንም ነገር ግን አለባበሳችንን እንደ ክርስቲያን እንፈትሸው ዘንድ ይገባልና ይህ ተፃፈ

መሰልጠን ወይስ መሰይጠን?

አብዛኞቹ ሴቶች ይህን ተግባር ስልጣኔ እንጂ ስህተት ነው ብለው አያምኑም፡፡ ለነዚህ ሴቶች ከኃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከባህላችን ጭምር ያፈነገጠውን የምዕራባውያን አለባበስ መልበስ ዘመናዊነት ነው፡፡ ላንቺስ? መጽሐፍ ቅዱስስ ምን ይላል?

    ማንኛዋም ሴት የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ ወይም ክፍትፍት ልብስ ለብሳ መሄዷ የሁሉንም ወንዶች ስሜት መፈታተኗ እርግጥ ከመሆኑም በላይ በመንፈሳዊ ህይወት ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለኃጢያት አጋልጦ ይሰጣል፡፡ እዚህ ላይ የተሳሳተው በራሱ ደካማነት ነው ብሎ ምክንያት መስጠት አይቻልም እግዚአብሔር የሚጠይቀው በማን ተሰናከለ የሚለውን ጭምር ነውና በክርስትና ደግሞ ሰውን ማሰናከል እጅግ የከፋ ኃጢያት ነው፡-

“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር፡፡” ማቴ. 18፡6

አንዳንድ ሴቶች እግዚአብሔር ምን ሰራሽ እንጂ ምን ለበስሽ አይለኝም ይላሉ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል

“እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለው፡፡” ትን.ሶፎ. 1፡18

እንግዲህ የሴቶቹን እንቀበል ወይስ የእግዚአብሔርን ምርጫው ያንቺው ነው እህቴ መጽሐፍ ግን እንዲህ ይላል፡- “ከስው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል፡፡” የሐዋ. 5፡29

በሴቶችና በወንዶች መካከል የአለባበስ ልዩነት ሊኖር ይገባል

“ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5

ታዲያ ቀሚስን የወንድ ሱሪን የሴት ማን አደረገው? ይህ የሰነፍና ለስህተታቸው ምክንያትን የሚሹ ሴቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል አውቀን ልንፈፅመው እንጂ በቃሉ ላይ የምንፍቅና ጥያቄ እናነሳ ዘንድ ተገቢ አይደለም ግን ደግሞ ተፈጥሯችንን ብቻ በማየት ህሊናችን እራሱ ቢናገር ሱሪ የሴት ነውን? ቀሚስስ የወንድ ነው እንዴ “ተፈጥሮ እንኳን አያስተምራችሁምን? 1ኛ ቆሮ. 11፡14

ዳሩ ግን ማንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም፡፡” 1ኛ. ቆሮ. 11፡16

ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ስህተት መሆኑን መናገር እንጂ መከራከር አያስፈልግም ክርስትና በምርጫ ነውና፡፡

በፊትህ እሳትና ውሃን አኑሬአለው ወደ ወደድከው እጅህ ክተት፡፡” ሲራ. 15፡15

እዚህ ላይ ግን ቀሚስ ሲባል ከውስጥ ሱሪ የማይሻለውን ብጣሽ ጨርቅ እንዲሁም ቁመቱ ረዥም ሆኖ ከሰውነት ጋር የሚጣበቀውን አይነት አለባበስ ማለት እንዳልሆነ ልብ እንበል፡፡



እህቶቻችን ሆይ ማስተዋልን ትላበሱ ዘንድ እንለምናችኋለን መሰልጠንና መሰይጠንም ትለዩ ዘንድ ይሁን ሰውነትሽ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነውና ሁሉን በአግባብና በሥርዓት አድርጊለት፡፡

ደግሞም ክርስትና ራስ ወዳድነትን አብዝታ ትጠላለች ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላው ሰው ልናስብ ያስፈልገናል እኛስ ሰውን ወደ ዝሙት ሊያመራው ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨነቅን ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ወንድማችንን ስለማሰናከል ምን አለ

መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም፡፡” 1ኛ.ቆሮ 8፡13


እንግዲህ ክርስትና እዚህ ድረስ ነው ስለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ወንድሞችና እህቶቻችን የምናስብባት ለእነሱም መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን ሁሉን በአግባብና በሥርዓት የምናደርግባት፤ እምነታችንን በምግባር የምንገልጽባት ናት፡፡

በእውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን፡፡ ትን.ኤር. 13፡27

እህቴ ሆይ አንቺም ኤርሚያስ እንዳለው ኢትዮጵያዊነትሽን ጠብቂ የምዕራባውያን በዓል ከሆነው አለባበስም ሆነ የምንዝር ጌጥ ራስሽን አርቀሽ በሚያኮራው ኢትየጵያዊ ባህላችን ትዋቢ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡

ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡ አሜን!!!!

ሁላችን ምግባር ያለው እምነት እንዲኖረን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!!!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቀደመችው እውነተኛይቱ መንገድ!!!

      የቅዱሳን አምላክ ማስተዋል ይስጠን 🤲

ወ ስ ብ ሐ ት   ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ   ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ   ክ ብ ር   አ ሜ ን 

https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
ስቅለተ ክርስቶስ
#ሞት_ይሽረው_ዘንድ_የማይሞተው_ሞተ
ዕለተ አርብ አዳምና ሔዋን የተፈጠሩበት ፤ ከገነትም የተሰደዱበት ዕለት ናት ጌታም የሥነፍጥረት ስራውን እንደፈፀመ አሁንም የድኅነት ስራውን ፈፀመባት
የክብር ባለቤት ጭፍሮች ይዘው በሊቀ ካህናቱ ፊት አቆሙት "የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆንክ ንገረኝ" አለው ጌታም "አንተ አልክ .... የሰውልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመን በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላቹ" ቢለው ሊቀ ካህናቱን "ተሳደበ" በማለት ፊቱን ነጭ ልብሱን ቀደደ
አስራ ሁለት ሰዓት ሲሆን በፍጥረት ሁሉ ላይ የሚፈርደውን ሰማያዊ ንጉሥ በምድራዊ ንጉሥ ሊያስፈርዱበት በአደ ባባይ አቆመት ጲላጦስን መርምሮ ለሞት የሚያበቃ አንዳች አጣበት ህዝቡ ግን "ስቀለው ስቀለው" እያሉ አብዝተው ጮሁ የጲላጦስ ሚስትም ክፉ እንዳያደርግበት ለባሏ መልእክት ላከች ስለርሡ በህልሟ ስትሰቃይ አድራለችና ጲላጦስም ክርስቶስ የገሊላ ሰው መሆኑን ሲረዳ ወደ ሔሮድስ ሰደደው ጲላጦስና ሔሮድስም እኔ ልግዛ እኔ ልግዛ እያሉ ይጣሉ ነበር አሁን ግን ብጌታ ሞት ታረቁአንዱን በእስራኤልአውያን የፋሲካ በዓል ከስረኛ ሊፈታላቸው ልማድ ስለነበራቸው እርሱ እየሱስን ልፈታላቹ ወይስ በርባንን ቢላቸው ወንበዴውንእነርሱ በርባንን መረጡ
ሶስት ሰዓት ሲሆን ጲላጦስም ጥፋት ስላላገኘበት ቢገረፍ ልባቸው ይራራለት ይሆናል በማለት አስገረፈው ግን እንኳንስ ሊራሩ 40 ጅራፍ ብቻ መግረፍ ሲኖርባቸው እየተፈራረቁ ክንዳቸው እስኪዝል 6666 ጅራፍ ስጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር ገረፉት ስድስት ሰዓት ሲሆን ሱራፌልና ኪሩቤል ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑትን ክፉዎች አይሁዶች ዘበቱበት፤ መላዕክት በፍርሀት የሚሰግዱለትን ተፉበት በዘንግም እራሱን መቱት ለመዘባበት ያለበሱትን ቀዩን ግምጃ ገፈው ወደሚሰቀልበት ቀራንዩ ከባዱን እፀ መስቀል አሸክመው ወሠዱት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰውን አገኙትና አንተም የርሱ ወገን ነህ መስቀሉን ተሸከም ብለው አሸከሙት ወንበቤም እንዲመስል በግራና በቀኝ ወንቤዎችን አድርገው ሰቀሉት ኢሳያስም በትንቢቱ "ካመፀኞት ጋር ተቆጠረ" ያለውም ተፈፀመ
ጲላጦስም አይሁድ ተመቅኝተው ለሞት አሳልፈው እንደሰጡት ያውቅ ነበርና # የአይሁድ_ንጉስ_የናዝሬቱ_ኢየሱስ የሚል ፅሁፍ በፅርህ በእብራይስጥ በሮማይስጥ በመፃፋ አኖረ
ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 13 ሕማማተ መስቀል ከተቀበለ በኋላ የሰው ልጅ ያጣውን ሕይወቱን በሞቱ ለመካስ መራራ ሞትን በፈቃዱ ተቀበለ።
አፅርሐ መስቀል
1 ኤሎኼ ኤሎኼ ላማሰበቅታኑ/አምላኬ አእነሆ ለምን ተውከኝ 2 አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው 3 ዛሬ በገነት ትኖራለህ 4 አባት ሆይ ነፍሴን በጅህ አደራ እሰጣለሁ 5 እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ 6 ተጠማው 7 ውይቤ ተፈፀመ
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
2024/09/26 04:48:03
Back to Top
HTML Embed Code: