tgoop.com/sturaelclinic/371
Last Update:
ድንገተኛ የጉበት መድከም
ድንገተኛ የጉበት መድከም ማለት ጉበት በቀናት ወይም ሳምንታት ዉስጥ ለሰዉነታችን የሚሰጠዉን አገልግሎት በሚያጣበት ወቀት የሚከሰት ነዉ። ይህ ችግር በብዛት በጉባት ቫይረስ ኢንፌክሽን ወይም በመድሃኒቶች አማካኝነት ይከሰታል። ድንገተኛ የጉበት መድከም ከፍተኛ የደም መፍሰስ እና በአንጎል ውስጥ ግፊት መጨመርን ጨምሮ ከባድ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።
የህመም ምልክቶች
❤ የአይን ነጩ ክፍልና የቆዳ ቢጫ መሆን
❤ በቀኝ የላይኛዉ የሆድዎ ክፍል ህመም መሰማት
❤ የሆድ ማበጥ(ዉሃ መያዝ)
❤ ማቅላሽለሽ
❤ ማስታወክ
ድንገተኛ የጉበት መድከም የሚከሰተው የጉበት ሴሎች በከፍተኛ ሁኔታ ሲጎዱና መሥራት ሲያቅታቸው ነው።
ከተለመዱት መንስኤዎች ዉስጥ
❤ ፓራሲታሞል( አሴታሚኖፌን) ከመጠን በላይ መዉሰድ፦ በጣም ብዙ አሲታሚኖፌን (Tylenolና , ሌሎችም) መውሰድ በጣም የተለመደው የጉበት መድከም መንስኤ ነው።
❤ መድሃኒቶች፦ ለህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች ( ፀረ-ባክቲርያዎች፣ለሚጥል በሽታና ነን ስቴሮይዳል አንቲ ኢንፈላማቶሪ ) የጉባት መጎዳት ሊኣይስከትሉ ይችላሉ።
❤ ባህላዊ መድሃኒቶች
❤ ቶክሲኖች
❤ በጉበት ዉስጥ ያሉ የደም መልስ የደምቧዎች ህመም
ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!
BY St. Urael Internal Medicine Clinic

Share with your friend now:
tgoop.com/sturaelclinic/371