tgoop.com/sturaelclinic/388
Last Update:
መንስኤ
የጆሮ ደግፍ በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰትና በተበከለ ምራቅ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ ህመም ነው። የጆሮ ደግፍ የያዘው ሰዉ የበላበትንና የጠጣበትን ዕቃዎች በጋራ መጠቀም ቫይረሱ ሊይዝዎ ይችላል።
ቫይረሱ ሊያመጣዉ የሚችላዉ የጎንዮሽ ጉዳት
በጆሮ ደግፍ ሊያመጣዉ የሚችለዉ የጎንዮሽ ጉዳት አምብዛም ባይሆንም ከተከሰቱ ግን አንዳንዶች ከባድ ሊሆን ይችላል። መምፕስ በአንዳንድ የሰውነት ክፍሎች ላይ እብጠትና መቆጣት ሊኣስክትል። ለምሳሌ
· አንጎል ላይ፦ እንደመምፕስ ቫይረስ ኢንፌክሽን ሲከሰት የአንጎል ላይ ኢንፌክሽንና መቆጣት እንዲከሰት ያደርጋል።
· የኡንጎልና ህብለሰረሰር ሸፋን ኢንፌክሽን፦ ይህ ሚንንጃይትስ( የማጅራት ገትር) ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።
· ቆሽት፦ የቆሽት መቆጣት እንዲከሰት ያደርጋል
· መስማት መቀነስ
· የልብ ችግሮች
· ዉርጃ አንዲከሰት ማድራግ ናቸዉ።
መከላከል
የጆሮ ደግፍን ለመከላከል ወሳኙ መንገድ ክትባት መዉሰድ ነዉ። ብዙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ከተከተቡ በኋላ የጆሮ ደግፍ በሽታን የመከላከል አቅም አላቸው።
የመምፕስ ክትባት ከሌሎች ክትባቶች ጋር በአንድነት የሚሰጥ ሲሆን ኤም ኤም አር (MMR) ይባላል። አንድ ልጅ ትምህርት ቤት ከመግባቱ በፊት ሁለት ጊዜ የ MMR ክትባት እንዲወስድ ይመከራል። ሕፃናት እነዚህ ክትባቶች በሚከተሉት መርሃግብር እንዲወስዱ ይመራል
· ከ12 እስከ 15 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ
· ከ 4 እስከ 6 አመት እድሜ መካከል
ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!
BY St. Urael Internal Medicine Clinic

Share with your friend now:
tgoop.com/sturaelclinic/388