tgoop.com/sturaelclinic/389
Last Update:
የደም ግፊት ማነስ
የአንድ ሰዉ የደም ግፊቱ ትክክለኛ/ ኖርማል ነዉ የምንላዉ የደም ግፊቱ የላይኛዉ ከ90 አስከ 120 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ ሲሆና የታችኛዉ ደግሞ ከ60 እስከ 80 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ ሲሆን ነዉ። የአንድ ሰዉ የግፊት መጠን የላይኛዉ ወይም ሲስቶሉ ከ90 ሚሊ ሜትር ሚርኩሪ በታችና የታችኛዉ ልኬት ደግም ከ60 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በታች ሲሆን የደም ግፊት ማነስ ችግር አለ እንላለን።
የደም ግፊት ማነስ አይነቶች
· ኦርቶስታቲክ( ፖስቸራል) ሃይፖቴንሽን
· ፖስትፕራንዲያል ሃይፖቴንሽን
· ከነርቭ ጋር የተያያዘ የደም ግፊት መቀነስ( ሃይፖቴንሽን)
· መልትፕል ሲስተም አትሮፊ ዊዝ ኦርቶስታቲክ ሃይፖቴንሽን
የህመም ምልክቶች
· አይን ላይ ብዥ ማለት
· ማዞር ወይም መግለፅ የሚከብድ የራስ ምታት
· ድንጋት ታዝለፍልፎ መዉደቅ( ፌንት ማድረግ)
· ድካም
· አትኩሮት መቀነስ
· ማቅለሽለሽ ናቸዉ።
በጣም ዝቅተኛ የደም ግፊት መከሰት ሾክ ( የደም ግፊት ከመጠን በላይ መከሰት) ዉስጥ ሊከተን ይችላል። የሾክ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
· እራስን መሳት በተለይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች
· ቀዝቃዛ ቆዳ
· የቆዳ ቀለም መገርጣት(Pallor)
· ከላይ ከላይ ቶሎ ቶሎ መተንፋስ
· ደካማና ፈጣን የልብ ምት ናቸው።
ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!
BY St. Urael Internal Medicine Clinic

Share with your friend now:
tgoop.com/sturaelclinic/389