Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Audio
🔮የጁምዓ ኹጥባ
  ሙስሊም ለሆኑ እህቶች  መልዕክት
ወንዶች መልዕክቱን  አድርሱ
  

የሁለት አመት አካባቢ ኹጥባ
               
የዕለተ ጁሙዓ  19/7/1444 ዓ.ሂ

       ይደመጥ👂  ይደመጥ👂

በተለይ ለሴቶች መደመጥ ያለበት ነው
🔊በኡስታዝ  መሀመድ ኑር

   https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
ይደመጥ👂ይደመጥ👂

ወሳኝ ትምህርት ነው ሳታዳምጡ እንዳታልፉ
⚡️በዚች አለም ውስጥ ካሉት ነገሮች ሁሉ ጣፋጩ ተውሂድ ስለመሆኑ
⚡️ተውሂድ የሁለት ሀገር እርካታ ስለመሆኑ
⚡️ተዉሂድ አላህ ከባሮቹ የሚፈልገው አላማ ስለመሆኑ
⚡️እና ሌሎችም ነገሮች ተዳሰውበታል።
https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
💎 ስለ ወላጆች ሀቅ

በውስጡ ከተዳሰሱ ነገሮች👇👇

⚡️የወላጅ ሀቅ ከአላህ ሀቅ ቀጣይ ሁለተኛ ሀቅ ስለመሆኑ
⚡️በማሳደግ ላይ ምን አይነት መከራ እንዳሳለፉ
⚡️እነሱን መበደል ያለው መዘዝ
⚡️የናት ሀቅ ምን ያክል ከፍ ያለ እንደሆነ
⚡️ወላጆችን የሚተካ ለውጥ የሌለ ስለመሆኑ
⚡️ወላጆቹን የበደለ በአስቸኳይ መቶበት እንዳለበት እና ሌሎችም ተዳሰውበታል።

ይደመጥ👂ይደመጥ👂
https://www.tgoop.com/sunah123
ጠቃሚ መረጃዎች

1-
 የፆም ንያን ጀናባ በሆንበት ጊዜ ቢሆንኳ መነየት የምንችል ሲሆን ከንጋት ብኋላ መታጠብ እንችላለን።
2- የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ምሽት ላይ ያቆመላት ሴት ቀጣዩን ቀን ለመፆም መነየት ይኖርባታል። ጉሱል (ሙሉ ትጥበት) እስከ ንጋት ድረስ ማዘግየት ትችላለች። ነገርግን ሙሉ ትጥበቷን ከፈጅር ሶላት በፊት መፈፀም ይኖርባታል።
3- ፆመኛ ሰው ጥርሱን መንቀል ፣ ቁስሉን ወይም ጉዳት የደረሰበትን የአካል ክፍል ማከም ፣ የአይን ጠብታ መጠቀም ይችላል። ሆኖም የአይን ጠብታው ጣዕም በጉሮሮው ቢወርድ ፆሙ አይበላሽም።
4- ፆመኛ ሰው ሲዋክ ወይም የጥርስ ብሩሽ በመጠቀም ጥርሱን ማፅዳት ይችላል። ቀኑን ሙሉ ወይም ከሶላት በፊት ጥርስን በሲዋክ መፋቁ ሱና ነው።
5- ፆመኛ ሰው በሞቃት የአየር ንብረት ወይም በውሃ ጥም ቢቃጠል ይህን የሚያቀልለትን ነገር ማድረግ የሚችል ሲሆን ሰውነቱን ለማቀዝቀዝ ውሃ ወይም የአየር ማቀዝቀዣ መሳሪያ መጠቀም ይፈቀድለታል።
6- በጭንቀት ወይም በሌላ ችግር ምክኒያት የመተንፈስ ችግር ያጋጠመው ፆመኛ የአተነፋፈስ ስርአቱን ለማስተካከል አፉ ውስጥ የሆነ ነገር መርጨት ወይም መሳብ ይችላል።
7- አፍን መጉመጥመጥና አፍንጫን ወይም የደረቁ ከናፍሮችን በውሃ ማርጠብ ይፈቀዳል። ነገርግን እየፆመ በተጋነና መልኩ ብዙ ውሃ በጥልቀት ወደ አፍ ወይም ወደ አፍንጫ ማድረስ የተጠላ ነው።
8- ፀሐይ እንደጠለቀች ያለምንም ማዘግየት ወዲያውኑ ማፍጠር (ፆምን መፍታት) ሱና ነው።
9- በፆም ወቅት ብዙ መልካም ስራዎችን አብዝቶ መስራትና የተከለከሉ ነገሮችን ሁሉ መራቅ ሱና ነው።
10- ፆመኛ ሰው ዋጅብ (ግዴታ) የሆኑ ስራዎችን ሁሉ መስራት እና ከተከለከሉ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ የቀኑን አምት ስግደቶች በጀመአ መስገድ ይኖርበታል። ከተከለከሉ ነገሮች ደግሞ ለምሳሌ ሐሜት ፣ ውሸት መናገር ፣ ማታለል፣ አራጣ መብላት ወ.ዘ.ተ መከልከል ይኖርበታል። ይህን በተመልከተ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “ውሸት መናገርና መጥፎ ስራዎችን መስራት ያልተወ ሰው አሏህ ምግብና መጠጥ መተውን አይፈልግም” ብለዋል።
https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
ይደመጥ👂ይደመጥ👂

ወሳኝ ትምህርት ነው ሳታዳምጡ እንዳታልፉ
  
   በውስጡ ከተዳሰሱ ነገሮች
⚡️የሽርክ አደገኝነት
⚡️ሽርክ የሸይጧን መጥለፊያ ገመድ ስለመሆኑ
⚡️በምድር ውስጥ ካሉ ሙሲባዎች አደገኛው ምን እንደሆነ
⚡️የአንድ ሰው ተውሂዱ የሚስተካከለው ምን ሲያሟላ እንደሆነ
⚡️አሏህ በሙሽሪኮች ላይ ምን ፍርድ እንዳስቀመጠ
⚡️በምድር ላይ መጥፎ ፍጡሮች እነ ማን እንደሆኑ እና ሌሎችም ተዳሰውበታል።

ይደመጥ👂ይደመጥ👂
https://www.tgoop.com/sunah123
የፆመኛ ሰው ዱአ

የፆመኛ ሰው ዱአ በፍፁም ምላሽ የማያጣ ነው። ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው ፆመኛ ሙስሊም ከአሏህ ለለመነው ማንኛውም ነገር ከሚከተሉት ሶስት ነገሮች አንዱን ይቀበላል (ያገኛል)። የጠየቀውን ነገር በቀጥታ ያገኛል ወይም ባሰበው ነገር ፈንታ አሏህ ከመንገዱ መጥፎ ነገር ያስወግድለታል ወይም ደግሞ ለለመነው ነገር ምንዳ ለመጭው አለም ይቀመጥለታል ብለዋል።
ስለዚህ ያለ መሰልቸት ዱአ ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው። እሱን በማንኛውም ጊዜ ችላ ማለት ደግሞ ትልቅ እጦት ነው። አሏህ ለኛ ደህንነትና ጥቅም የሚሆነን ነገር ይሰጠናል። ዱአችን ተቀባይነት ባያገኝ እንኳ መለስ ብለን እራሳችነን ልንመረምርና ዱአችን ተቀባይነት የሚያገኝባቸውን ሁኔታዎች ልናጤን ይገባል። በሐራም ምግብ ፆሙን የሚፈታ ሰው ልክ መድሃኒትና መርዝ ቀላቅሎ እንደሚወስድ በሽተኛ ሰው ነው።

https://www.tgoop.com/sunah123
የወር አበባና የወሊድ ደም

⚡️ሴት ልጅ እነዚህ ሁለት ነገሮች ላይ እያለች መፆም ሐራም ነው። ነገር ግን በሌላ ጊዜ ቀዷ ማውጣት በእርሷ ላይ ግዴታ ነው። ለዚህም ማስረጃው ቡኻሪና ሙሊም እንደ ዘገቡት፦ ዓኢሻ (رضي الله عنها) እንዲህ አሉ፦
{ كنا نؤمر بقضاء الصوم، ولا نؤمر بقضاء الصلاة } البخاري الحيض (315) ، مسلم الحيض (335) ، الترمذي الطهارة (130) ، النسائي الصيام (2318) ، أبو داود الطهارة (262) ، ابن ماجه الطهارة وسننها (631) ، أحمد (6/232) ، الدارمي الطهارة (986) .
“ፆምን ቀዷ እንድናወጣ እንታዘዝ ነበር፤ ሶላትን ግን ቀዷ አውጡ ተብለን አንታዘዝም ነበር።” ይህን ሀዲስ የተናገረችው አንዲት ሴት ወደ አዒሻ መጥታ የሚከተለው ጥያቄ በማቅረቧ ነው፡ “ሴቶች ፆምን ቀዷ ያወጣሉ፤ ሶላትን ግን ቀዷ አያወጡም ይህ ለምንድነው?”በማለት ስትጥይቅ፡ ዓኢሻም ይህ መረጃ እንጅ ሚስጥራቸው ካልተገለፁት (አላህ ብቻ የሚያውቃቸው) ቁጥብነትን ከሚጠይቁ ውስጥ መሆኑን አብራራችላት።
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ያለመፆሟን ምክንያት መጅሙዑል-ፈታዋ 25ኛው ጥራዝ ገፅ 251 ላይ ሲያብራሩ፦ “በወር አበባ ጊዜ የሚወጣው ደም ከሰውነቷ ደም መጉደልን የሚያመጣ ደም ነው። ስለዚህ ይህ ደም በማይኖርበት ጊዜ መፆሟ ለሰውነቷ ጥንካሬ የሚያስፈልገው ደም በማይወጣበት በመሆኑ ፆሟ የተስተካከለ ይሆናል። ነገር ግን በወር አበባ ጊዜ የምትፆም ከሆነ ለሰውነቷ የሚያስፈልገው ንጥረ ነገር ከደም ጋር አብሮ ስለሚወጣ የአካል መዳከም እና የሰውነት መቀነስ ሊያስከትል ይችላል፤ ፆሟም የተስተካከለ አይሆንም። ስለዚህም ሲባል የወር አበባ ዘመኗ ሲጠናቀቅ እንድትፆም ታዘዘች።
2 እርግዝና እና ማጥባት
በእርግዝና እና በማጥባት ላይ መፆም በእናትዮዋ ወይም በልጇ ወይም በሁለቱም ላይ ችግር የሚያመጣ ከሆነ በእርግዝና እና በምታጠባ ጊዜ መብላት ይፈቀድላታል። ያፈጠረችው በህፃኑ ምክንያት ብቻ ከሆነ ያፈጠረችውን ቀዷ እያወጣች በየቀኑም አንዳንድ ድኻን (ሚስኪን) ትመግባለች። ነገር ግን ለማፍጠሯ ምክንያት ችግሩ ያለው በእርሷ ላይ ብቻ ከሆነ ቀዷ ማውጣት ብቻ በቂዋ ነው። ይህም ማፍጠራቸው የተፈቀደበት ምክንያት አጥቢዎች እና እርጉዞች ጭምር በአላህ ንግግር ስር ስለሚካተቱ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿ وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ ۖ ﴾ [ سورة البقرة: 184]
“በእነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድኻን ማብላት አለባቸው።” (አልበቀራህ፡ 184)
ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው 1ኛው ጥራዝ ገፅ 389 ላይ እነዚህ ህግጋት ከሚመለከታቸው ሰዎች ውስጥ፦በራሳቸው ወይም በልጃቸው ላይ የፈሩ አጥቢዎች እና ነፍሰጡር ሴቶች ይገኙበታል።
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦ “ነፍሰጡር ሴት በፅንሷ ላይ የምትፈራ ከሆነ ታፈጥርና ቀዷዕ ታወጣለች። ስለእያንዳንዱ ያፈጠረችበት ቀን አንዳንድ ሚስኪን መጠኑ አንድ ዋንጫ(መለኪያ) የሚሆንን ገብስ ትሰጣለች። (25/318)

ማስታዎሻ

1 የበሽታ ደም ያለባት ሴት፡


ከላይ እንዳሳለፍነው ያቺ ሃይድ ይሆናል ተብሎ የማይጠበቅ ደም የሚፈሳት ማለት ነው። ፆምን መፆም በእርሷ ላይ ግዴታ ነው። በበሽታ ደሙ ምክንያት ማፍጠር አይፈቀድላትም።
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑተይሚያህ መጅሙዑል-ፈታዋ 25ኛው ጥራዝ ገፅ 251 ላይ እንዲህ ይላሉ፦ "የወር አበባ ስላለባት ሴት ማፍጠር ሲያብራሩ እንዳሉት “የበሽታ ደም ሁሉንም ጊዜ የሚሸፍን(የሚይዝ) ስለሆነ ደም የማይታይበት ለፆም የምትታዘዝበት ጊዜ የላትም። ይህም እንደ ትውከት፣ በቁስል ምክንያት ደም እንደመፍሰስ፣ እንደ ብጉንጅ፣ በህልም ግንኙነት እንደማድረግ እና የመሳሰሉትን መጠንቀቁ የማይቻለው ክስተት ነው። ይህ የበሽታ ደም የታወቀ የጊዜ ገደብ ስለሌለው እና መጠንቀቁ ስለሚያስቸግር እንደየወር አበባ ፆምን የሚከለክል አልሆነም።”
2 ያፈጠሩ ሴቶች ባፈጠሩት ልክ ባለፈው እና በሚመጣው ሁለት ረመዳኖች መካከል ቀዷ ማውጣት በእነርሱ ላይ ግደታ ስለመሆኑ

የወር አበባ ላይ ያሉ፣አጥቢ እና እርጉዝ ሴቶች ከረመዳን ያለፋቸውን ፆም ባለፈው እና በሚመጣው ረመዳን መካከል ቀዷዕ ማውጣት በእነርሱ ላይ ግዴታ ነው።
የሚያጠቡ ሴቶች ረመዳን ወር ላይ ከበሉ በበሉት ቀን ልክ ባለፈው እና በሚመጣው ሁለት ረመዳኖች መካከል ቶሎ ቀዷ ማውጣቱ በላጭ ነው፤ይህም የሚሆነው የሚቀጥለው ረመዳን ከመግባቱ በፊት ያፈጠሩትን ቀን ያክል እስከሚቀር ድረስ ነው። ያፈጠሩትን ቀን ያክል ሲቀራቸው በእነርሱ ላይ ቀዷ ማውጣቱ ግዴታ ይሆናል። ምክንያቱም ያለፈው ረመዳን ፆም እያለባቸው አዲሱ ረመዳን እንዳይገባባቸው ነው። ነገር ግን ይህን ሳይሰሩ አዲሱ ረመዳን ቢገባባቸው እና ለማዘግየታቸው ሸሪዓዊ ምክንያት ከሌላቸው ቀዷ ከማውጣታቸው በተጨማሪ በየቀኑ አንዳንድ ሚስኪን ይመግባሉ። ያዘገዩት በሸሪዓዊ ምክንያት ከሆነ ቀዷዑን ከማውጣት ውጭ ምንም የለባቸውም።
እንደዚሁም በጉዞ ወይም በህመም ምክንያት አፍጥሮ ቀዷ ያለበት ሰው በወር አበባ ምክንያት እንዳፈጠረችው አይነት ዝርዝር ህግጋት ይመለከተዋል።

https://www.tgoop.com/sunah123
Audio
ይደመጥ👂ይደመጥ👂

ወሳኝ ትምህርት ነው ሳታዳምጡ እንዳታልፉ

ሁሉም አህለ ሱና ወለጀመዓ ነኝ ቢልም እንኳ በመገለጫቸው መለየት እንደት እንደሚቻል ተዳሶበታል።
https://www.tgoop.com/sunah123
2025/03/13 10:06:48
Back to Top
HTML Embed Code: