tgoop.com/taodocos1221/2105
Last Update:
❤ ጥንቃቄ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ❗️
#ሁሉም ኦርቶዶክስ_ሸር_ያድርግ!!!
❤ የቀበሌ መታወቂያ ጉዳይ ❗️
❤ ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት ከዚህ ከህዳር ወር ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ መሆኑን ተከትሎ መታወቂያ ለማሳደስ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከታች የምትመለከቱትን ፎርም አስቀድመው እንዲሞሉ በመደረግ ላይ ይገኛል።
❤ በሚሞላው ፎርም ላይ ከተካተቱት መጠይቆች አንደኛው " ሃይማኖት " የሚለው ነው። አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ባለማስተዋልና ትኩረት ባለመስጠት በዚህ መጠይቅ ሥር "ክርስቲያን" የሚለውን መጠሪያ መጠቀም ልምድ አድርጎት ይታያል።
❤ ሆኖም በዚህ ወቅት እንደ ወል ስም እያገለገለ በሚገኘው ስም መጠቀም ከኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ትልቅ ፈተና ይዞ የሚመጣ መሆኑን በማስተዋል ሐይማኖት በሚለው መጠይቅ ሥር " ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ " የሚለውን የሃማኖታችንን መጠሪያ ለይቶ በአግባቡ መሙላት ይገባዋል።
❤ በክርስትና ስም የሚጠቀሙ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች በመኖራቸውና ይህም የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር የተዛባና የተሳሳተ እንዲሆን ያደርጋል።
❤ በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ እንዳለው ኦርቶዶክሳውያን ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተገፉና እየተገለሉ እንዲሄዱ በማድረግ ቁጥራቸውን በማዛባትና ዝቅ አድርጎ በማሳየት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አይገባም።
❤ በተለይም በዕድሜ የገፉና የቀለም ትምህርት ያልቆጠሩ ወገኖቻችንን በማሳወቅ "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ" የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ በአግባቡ እንዲሞሉ ማድረግ ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
BY ✝️ ታኦዶኮስ ✝️
Share with your friend now:
tgoop.com/taodocos1221/2105