tgoop.com/tataafro_official/850
Create:
Last Update:
Last Update:
ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award 2024)
በሀገራችን እንቁ አትሌት የተሰየመው “ቢቂላ አዋርድ” ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሽልማት ተቋሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን እስካሁንም ለበርካታ የሀገር ባለውለታዎች እውቅናን በመስጠት ሲሸልም ቆይቷል። ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award) ከሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ከምንም አይነት ትርፍ እራሱን ባገለለ መልኩ በካናዳ ከ50 አመታት በላይ በኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው የተቋቋመው። ይህ ተቋም በትምህርታቸው፣ በንግዳቸው፣ በሙያቸው ብሎም በበጎ አድራጎት ስራ ተሰማርተው ልዩ ስኬት ያስመዘገቡ እና አርአያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ በመሸለም እውቅናን የሚሰጥ ትልቅ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።
በዚህ አመት አስረኛ (10) የምስረታ በአሉን የሚያከብረው የቢቂላ አዋርድ ተቋም፥ መስከረም 11 (21 September 2024) በሚያደርገው መርሃ ግብር ላይ በሙዚቃው ዘርፍ በዚህ አመት የሚሸልመው የግጥምና የዜማ ደራሲ ብሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነውን የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን መሆኑን በህጋዊ ድህረገጾቹ በይፋ አሳውቋል።
አርቲስቱም በዕለቱ በዚህ ግዙፍ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሽልማቱን እንደሚቀበል ተገልጿል።
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
BY ታታ አፍሮ -Tata Afro

Share with your friend now:
tgoop.com/tataafro_official/850