tgoop.com/techzone_ethio/1519
Create:
Last Update:
Last Update:
ዛሬ ምሽት ጁፒተር እና ሳተርን በአንድ ላይ ይገጥማሉ ተባሉ‼️
↘️ ጁፒተር እና ሳተርን በአንድ ላይ ገጥመው አንድ ፕላኔት መስለው እንደሚታዩ ሳይንቲስቶች ጠቁመዋል።
↘️ ይህ የጁፒተር እና ሳተርን ጥምረት የሚፈጥረው ብርሃን ዛሬ ምሽት ሊታይ እንደሚችልም ተነግሯል።
↘️ ክስተቱ ‘ዘ ስታር ኦፍ ቤቴልሄም’ ወይም የቤቴልሄም ኮከብ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ፕላኔቶቹ ከቀን ቀን እየተቀራረቡ መጥተው ዛሬ ምሽት ደማቅ ብርሃን ሊፈነጥቁ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
↘️ ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰማይ ላይ እጅግ ደማቅ ብርሃን ታይቶ እንደነበር የሚናገሩት ሳይንቲስቶች ይህ ክስተት አሁን ሊፈጠር ይችላል ከተባለው ጋር ተመሳሳይነት ሳይኖረው አይቀርም ብለዋል።
↘️ የአየር ሁኔታው አስተማማኝ አይደለም ያሉት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የአስትሮኖሚ ተቋም ምሁሯ ዶክተር ካሮሊን ክራውፎርድ በደመና መካከል በተገኘ ቀዳዳ ሁለቱ ፕላኔቶች ገጥመው የሚፈጥሩት ብርሃን ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል።
©BBC
@techzone_ethio
@techzone_ethio
BY ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ

Share with your friend now:
tgoop.com/techzone_ethio/1519