tgoop.com/techzone_ethio/1520
Last Update:
ቴሌግራም አዲስ የማስታወቂያ ሥርዓት በሚቀጥለው ዓመት ዘረጋለሁ ብሏል‼️
↘️ የቴሌግራም መደበኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 500 ሚሊዮን መጠጋቱ ተገልጿል። እስካሁን ግን የገቢ ምንጩ ምን እንደሆነ የብዙዎች ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።
↘️ ከዛሬ ሰባትና ስምንት ዓመት በፊት በሁለቱ ወንድም አማቾች ኒኮላይ እና ፓቬል ዱሮቭ የተጀመረው ቴሌግራም በገቢ ምንጭነት እስካሁን የሚጠቀመው የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃብት ነው። በዚህም ፓቬል ዱሮቭ ለቴሌግራም ሥራ ማስኬጃ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ አድርጓል።
↘️ ሥራ አስፈጻሚው ዛሬ በቴሌግራም ቻናሉ እንዳሳወቀው ድርጅቱ ገለልተኛና ጥራቱን እንደጠበቀ እንዲቀጥል በመጪው ዓመት ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።
↘️ ቴሌግራም አንዳንድ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግም የገለጸ ሲሆን ተጠቃሚዎች እስካሁን በነጻ ሲያገኙ የነበሩትን አገልግሎት ያለ ክፍያ እስከመቼውም መጠቀም እንደሚችሉ አረጋግጧል።
↘️ ድርጅቱ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መሰብሰብ እንደሚጀምር ያስታወቀው ፓቬል ዱሮቭ የግላዊ መልዕክት ልውውጦች እንዲሁም በቡድን ልውውጦች ወቅትም ምንም አይነት ማስታወቂያ እንደማይለጠፍ ገልጿል።
↘️ ቴሌግራም ማስታወቂያ አሳያለው ያለው በቻናሎች ላይ ሲሆን ለዚህም ከመደበኛ መልዕክቶች ለየት ያለ እንዲሁም ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ የማስታወቂያ ስርዓት ዘረጋለውም ብሏል።
↘️ማስታወቂያዎቹ የሚነገሩበት ቻናል በተከታዮቻቸው ብዛት መሰረት ቻናላቸው ይበልጥ ተደራሽነቱ ከፍ እንዲል እድሉ ይመቻችላቸዋል ተብሏል።
@techzone_ethio
@techzone_ethio
C ልዩ መረጃ
BY ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ
Share with your friend now:
tgoop.com/techzone_ethio/1520