tgoop.com/techzone_ethio/1528
Last Update:
#ኦንላይን_ስራዎች_ለምትፈልጉ
#ሼር_ይደረግ
አንዳንዶቻችሁ ኮምፒውተርና ኢንተርኔት በመጠቀም ቤታችን ቁጭ ብለን ኦንላይን የምንሰራው ስራ ካለ ብትጠቁመን ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ፡፡
በዚህ ቴክኖሎጂ በተራቀቀበት ዘመን ሁሉም ስራዎች ኦንላይን እየሆኑ መጥቷል፡፡ ሰዎች በኮምፒውተርና ኢንተርኔት አማካኝነት ቤታቸው ቁጭ ብለው የተለያዩ ስራዎች ለተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በመስራት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ፡፡
ኦንላይን ስራዎች በጣም እየተለመዱ መጥቷል፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎች ብዙም ማሰላሰል የማይጠይቁ ስራዎች ለምሳሌ፡- ዳታ መመዝገብ፡ መፅሀፎችን ፊደል ማረም፤ድምፅን ወደ ፁሁፍ መገልበጥ፤ወዘተ ስራዎች በስፋት ኦንላይን ያሰራሉ፡፡
ኦንላይን ስራዎችን በመስራት ጥሩ ገቢ ማግኘት እያሰባችሁ ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ ኦንላይን ልትሰሯቸው የሚችሉ 3 ስራዎች ልጠቁማችሁ፡፡
1ኛ፡- Copy Editor
ጥሩ የእንግሊዘኛ ቋንቃቋ እውቀት ካላችሁ ይህ ስራ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ብዙ ኦንላይን ስራዎች አሉ፡፡
በዚህ ዘርፍ ከናንተ የሚጠበቀው ስራ የተለያዩ ፁሁፎች ይሰጣችኋል ። ከዚያ ያንን ፁሁፍ ፊደል ማረም ነው፡፡ፊደል ማረም ሲባል ፁሁፉ ላይ ቃላት የተገደፉ ካሉ ማስተካከልና ማረም የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡
በዚህ ዘርፍ ዌብሳይቶች፤መፅሀፍት፤መፅሔቶች እና የመሳሰሉትን እንድታርሙ ትጠየቃላችሁ፡፡
ጥሩ ስራ ይመስለኛል፡፡
እንዲህ ዓይነት ኦንላይን ስራ ከፈለጋችሁ
"copy editor online jobs" ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
2ኛ፤- Transcriber
ይህ ኦንላይን ስራ ሪከርድ የተደረገ ድምፅ ይሰጣችኋል፡፡ድምፁን እያዳመጣችሁ ወደ ፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ለምሳሌ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ንግግር ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ በተለይ እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ ያላችሁ ይህ ጥሩ ስራ ይመስለኛል።
የሚሰጣችሁ ድምፅ ንግግር፤ስብሰባ ላይ የተደረገ ንግግር፤ቪዲዮ ኮንፈረንስ ሊሆን ይችላል፤ትምህርቶች ሊሆን ይችላል፡፡ወዘተ
Online Transcriber Jobs ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
3ኛ፡- Data Entry
ይህ ኦንላይን ስራ የተለያዩ መልክ ያልያዙ ዳታዎችን መመዝገብ ነው፡፡ ለምሳሌ የትምህርት ቤቶች ወይም የሆስፒታል ትልልቅ ዳታዎችን ወደ Excel ማስገባት ወይም መመዝገብ ማለት ሊሆን ይችላል።፡
በተለይ ቁጭ ብሎ የመስራት ትዕግስት ያላችሁ ሰዎች ይህ ስራ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
እንደዚህ ዓይነት ኦንላይን ስራዎች ለመስራት ኢንተርኔትና ኮምፒውተር ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡
ከላይ ከገለፅኳቻው ስራዎች ውጪ ሌሎች ብዙ ኦንላይን ስራዎችን ብትፈልጉ ታገኛላችሁ፡፡ሞክሩ፡፡
@techzone_ethio
@techzone_ethio
Pliz comment on it
@samiiiiabcd
BY ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ
Share with your friend now:
tgoop.com/techzone_ethio/1528