Telegram Web
#PHYTON 🔍(part - one)🔍
​​
ሠላም ሠላም ውድ የ ethio tech ቤተሠቦች ዛሬ ይዘንላቹ የመጣነው ከ Programming language ሥለ ፓይተንን (phyton)

በተመለከተ የመጀመርያውን ክፍል ይዘንለቹ መተናል ተከታተሉን እውቀት እንደምታገኙበት ተሥፋ አናደርጋለን።                                                             
ፓይተን(phyton)      
  
ፓይተን ብዙ ግልጋሎት ያለው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ሢሆን ልክ እንደ ጃቫሥክሪፕት ተፋላጊ እና በጣም በማደግ 📈ላይ ካሉ ፕሮግራሚን ላንጉጅኦች አንዱ ነው።

ፓይተንን በአሁኑ ሠአት በአለማችን🌐 ላይ ብዙ ሠዎች ይጠቀሙታል ።ሦፍት ዌር ኢንጂንየርኦች፣ሣይንቲሥትዎች ፤
አካውንታትኦች እንዲሁም ታዳጊህፃናት እነዚህ ሁሉ ፓይተንን ይጠቀማሉ። ምክንያቱም ፓይተን ጀማሪዎች እንኳን በቀለሉ ሊረዱት የሚችሉት በመሆኑ ነው። ሥለዚህ የተለያዩ ሠዎች ማለትም የተለያየ ሥራ ላይ የሚገኙ ሠዎች ለሥራቸው ፓይተንን ይጠቀማሉ።
ተከታታይ (ተደጋጋሞሽ) ያላቸው ነገሮች መሥራት
like ፦   
📍 ፋይል ኮፒ ማድረግ           
📍 ማህደር (ፎልደር ) ክሬት ማድረግ
📍 ሥሙን መቀየር 
📍 ወደ ሠርቨር መጫን just የሚያሠለች ነገር ነው ። ነገር ግን ፓይተን ሥክሪፕት በመፃፍ ሁሉንም ነገር በቀለሉ መሥራት እና ጊዜአችንን መቆጠብ ይሥችለናል።
   ፓይተንን በመጠቀም   
🔌፦ዌብ አፕሊኬሽን 🔎
🔌፦ ዴሥክቶፕ አፕሊኬሽን🖥
🔌፦ ለሦፍትዌር ሙከራ 
🔌፦ለሃኪንግ ወዘተ...ሥለዚህ ፓይትን ብዙግልጋሎት
ያለው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ነው።ነገር ግን ከላይ የተጠቀሡትን ነገሮች ሌላ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ በመጠቀም መሥራት አንችልም እንዴ?🤔 ብላቹ ልትጠይቁ ትችላላቹ ። መልሡ እንችላለን ነው።

ሆኖም ግን ፓይተንን ሥንጠቀም 
1 📌ውሥብሥብ ( complex) ነገሮች በአጭር ጊዜ እና በጥቂት መሥመር ኮድ መፃፍ ያሥችለናል።

🖍ለምሣሌ 'hello world' ከሚለው ቃል ውሥጥ ሦስቱን(hel) ብቻ ፕሪንት ለማድረግ
🔹C#    str.substring(0, 3)
🔹phyton(py)    str[ 0,3 ]
ከዚህም ፓይተን(phyton) ምን ይህል እጭር እና ግልፅ እንደሆነ መረዳት እንችላለን።

2📌 አፃፃፋ (syntax)ቀላል በመሆኑ
ፓይተን ለመማርም ሆነ በራሣችን አንብቦ ለመረዳት ቀላል ነው።ፓይተንን ከሌሎች ጋር ብናነፃፅር like ከC++,C#,Php,java etc... ከሁሉም በላይ ግልፅ እና እጭር ኮድ መጠቀም ያሥችለናል።                                     
        🖍ለምሣሌ     
   🔹በጃቫ(java)
public class ethio technology {public static void main(String [ ]args)}               

💻                                                                               

🔹በፓይተን (phyton)
 print ('hello members')   
              
hello members 💻   
 በምሣሌው እንደተጠቀሠው በጃቫ 3 መሥመር ሢሆን በፓይተን ደግሞ አንድ መሥመር ብቻ በቂ ነው።በመጨረሻም ፓይተንን ለመማር ሶፍት ዌር ዴቨሎፐር መሆን አይጠበቅብንም።ፓይተንን ለመማር ጊዜው አሁን ነው።
 ለዛሬ በእዚህ እናበቃለን በቀጣይ በሚኖረን ቆይታ ቀጣዩን ክፍል ይዘንላቹ እንመጣለን እሥከዛው ግን መልካም ጊዜ።


@techzone_ethio
@techzone_ethio
#ለጠቅላላ-ዕውቀት

🌀 የአለማችን ትልቋ ሀገር ሩስያ ስትሆን 17.09 ሚሊየን km2 የሆነ የቆዳ ስፋት አላት::

🌀 በአለማችን ላይ በርሀማዋ ሀገር ሊቢያ ስትሆን ከአጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 99% የሚሆነው በረሀማነት የሚፈረጅ ነው::
🌀 በአለማችን ላይ ምንም አይነት ወንዝ የሌላት ሀገር ሳውድ አረቢያ ነች::
🌀ለሴቶች የመምረጥ መብትን ቀድማ የሰጠች ሀገር ኒውዝላድ ነች::

🌀አሜሪካ በአለማችን ላይ ብዙ ክርሰቲያኖች የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 245.9 ሚሊየን የሚሆኑት ክርሰቲያኖች ናቸው::

🌀ብዙ የሆነ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ህዝብ ያላት ሀገር ኢንዶኔዢያ ስትሆን ከ209 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊሞች ናቸው::

🌀በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀይቅ ብዛት ያላት ሀገር ካናዳ ስትሆን ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ሀይቆች ሲኖራት ይህም በአለማችን ላይ ካሉት የሀይቆች ብዛት 60% ይሸፍናል::

🌀በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የግድያ ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ኤል ሳልቫዶር ስትሆን በአማካኝ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 55.5% የሚሆኑት ግድያ ይፈፀምባቸዋል::

🌀በሀገሯ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሴቶች ቁጥር ያላት ሀገር ሩዋንዳ ስትሆን በፓርላማዋ ካሉት ጠቅላላ መቀመጫዎ ውስጥ 56.3% (50/80) የሚሆነው የተያዘው በሴቶች ነው::

🌀ዴንማርክ በአለማችን ላይ አነስተኛ የሆነ የሙስና ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ናት::

@techzone_ethio
@techzone_ethio
✳️ Laptop ስንገዛ #corei3#corei5 #corei7#corei9 ሲባል ምን ማለት ናቸው?


እነዚህ ነገሮች ስለ ላፕቶፑ ምን ይነግሩናል?

ኮምፒውተር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች መካከል #CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ #አእምሮ ማለት ነው።

ይህ #CPU ወይም #processor የተለያዩ ክንዋኔዎችን(Tasks) ተራ በተራ ማከናወን የሚያስችል የኮምፒውተሩ ዋና ክፍል ነው።

በሌላ አነጋገር #CPU ወይም #processor ላፕቶፓችን በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን በከፍተኛ ፍጥነት እንዲሰራ የሚያስችለው የላፕቶፑ ዋና ክፍል ነው።

ታስታውሱ እንደሆነ የመጀመሪያዎቹ ኮምፒውተሮች በአንድ ግዜ አንድ ሰራ ብቻ ነበር መስራት የሚችሉት።ለምሳሌ #Word ከፍታችሁ እየሰራችሁ ከሆነ ጎን ለጎን excel ወይም ሌላ ሶፍትዌር ከፍታችሁ መስራት አትችሉም ነበር።

እዚህ ጋር #Core የሚለው ቃል ይመጣል ።#Core ማት #አንድ ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።#CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ ትልቅ አእምሮ ብትሉት፤ #Core ማለት ትልቁ አእምሮ ውስጥ ያለ #አንድ_ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።

እንደምታውቁት የዘንድሮ ዘመናዊ #ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎች በከፍተኛ ፍጥነት ማከናወን ይችላሉ ።ለምሳሌ #Word ላይ እየሰራን ጎንለጎን #Excel ላይም ልንሰራ እንችላለን፤እንዲሁም ዩቲዩብ ከፍተን ልናይ እንችላለን።....ባጭሩ ብዙ ስራዎችን በአንድ ግዜ ማከናወን ይችላሉ ።

ታድያ #አንድ_core ሜለት #አንድ_አእምሮ ነው ካልን እና #አንድ_አእምሮ ደሞ በአንድ ግዜ አንድ ስራ ብቻ ከሆነ የሚያከናውነው፤የዘመኑ ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንዴት ቻሉ?

አሁን #corei3#corei5 #corei7#corei9 የተባሉት ነገሮች ይመጣሉ።

▫️ Corei3 ማለት 3 #processors ወይም 3 አእምሮች ማለት ነው።

▫️ Corei5 ማለት 5 #processors ወይም 5 አእምሮች ማለት ነው።

▫️Corei7 ማለት 7 #processors ወይም 7 አእምሮች ማለት ነው።

▫️ Corei9 ማለት 9 #processors ወይም 9 አእምሮች ማለት ነው።

#core ቁጥር እያደገ ሲመጣ ላፕቶፑ በአንድ ግዜ የሚያከናውናቸው ሰራዎች ከፍ እያሉ ይሄዳል ማለት።ፍጥነቱን ሳይቀንስ።እንደውም በከፍተኛ ፍጥነት።

በሌላ አነጋገር የ4ኛ ክፍል ተማሪ አእምሮ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪ አእምሮ አንድ ነው? አይደለም።

#core ማለት ይህ ነው።
@techzone_ethio
@techzone_ethio
ዛሬ ምሽት ጁፒተር እና ሳተርን በአንድ ላይ ይገጥማሉ ተባሉ‼️

↘️ ጁፒተር እና ሳተርን በአንድ ላይ ገጥመው አንድ ፕላኔት መስለው እንደሚታዩ ሳይንቲስቶች ጠቁመዋል።

↘️ ይህ የጁፒተር እና ሳተርን ጥምረት የሚፈጥረው ብርሃን ዛሬ ምሽት ሊታይ እንደሚችልም ተነግሯል።

↘️ ክስተቱ ‘ዘ ስታር ኦፍ ቤቴልሄም’ ወይም የቤቴልሄም ኮከብ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ፕላኔቶቹ ከቀን ቀን እየተቀራረቡ መጥተው ዛሬ ምሽት ደማቅ ብርሃን ሊፈነጥቁ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

↘️ ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰማይ ላይ እጅግ ደማቅ ብርሃን ታይቶ እንደነበር የሚናገሩት ሳይንቲስቶች ይህ ክስተት አሁን ሊፈጠር ይችላል ከተባለው ጋር ተመሳሳይነት ሳይኖረው አይቀርም ብለዋል።

↘️ የአየር ሁኔታው አስተማማኝ አይደለም ያሉት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የአስትሮኖሚ ተቋም ምሁሯ ዶክተር ካሮሊን ክራውፎርድ በደመና መካከል በተገኘ ቀዳዳ ሁለቱ ፕላኔቶች ገጥመው የሚፈጥሩት ብርሃን ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል።
©BBC

@techzone_ethio
@techzone_ethio
ቴሌግራም አዲስ የማስታወቂያ ሥርዓት በሚቀጥለው ዓመት ዘረጋለሁ ብሏል‼️

↘️ የቴሌግራም መደበኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 500 ሚሊዮን መጠጋቱ ተገልጿል። እስካሁን ግን የገቢ ምንጩ ምን እንደሆነ የብዙዎች ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።

↘️ ከዛሬ ሰባትና ስምንት ዓመት በፊት በሁለቱ ወንድም አማቾች ኒኮላይ እና ፓቬል ዱሮቭ የተጀመረው ቴሌግራም በገቢ ምንጭነት እስካሁን የሚጠቀመው የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃብት ነው። በዚህም ፓቬል ዱሮቭ ለቴሌግራም ሥራ ማስኬጃ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ አድርጓል።

↘️ ሥራ አስፈጻሚው ዛሬ በቴሌግራም ቻናሉ እንዳሳወቀው ድርጅቱ ገለልተኛና ጥራቱን እንደጠበቀ እንዲቀጥል በመጪው ዓመት ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።

↘️ ቴሌግራም አንዳንድ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግም የገለጸ ሲሆን ተጠቃሚዎች እስካሁን በነጻ ሲያገኙ የነበሩትን አገልግሎት ያለ ክፍያ እስከመቼውም መጠቀም እንደሚችሉ አረጋግጧል።

↘️ ድርጅቱ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መሰብሰብ እንደሚጀምር ያስታወቀው ፓቬል ዱሮቭ የግላዊ መልዕክት ልውውጦች እንዲሁም በቡድን ልውውጦች ወቅትም ምንም አይነት ማስታወቂያ እንደማይለጠፍ ገልጿል።

↘️ ቴሌግራም ማስታወቂያ አሳያለው ያለው በቻናሎች ላይ ሲሆን ለዚህም ከመደበኛ መልዕክቶች ለየት ያለ እንዲሁም ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ የማስታወቂያ ስርዓት ዘረጋለውም ብሏል።

↘️ማስታወቂያዎቹ የሚነገሩበት ቻናል በተከታዮቻቸው ብዛት መሰረት ቻናላቸው ይበልጥ ተደራሽነቱ ከፍ እንዲል እድሉ ይመቻችላቸዋል ተብሏል።

@techzone_ethio
@techzone_ethio
C ልዩ መረጃ
🌀 PicsArt Colour: Draw & Paint
🎯 Version: v2.8.3 (Latest)
🔗 Playstore Link: click here

Features and Mod :
🔹Make awesome paintings easily
🔸Many types of brushes & tools
🔹Colour photos & backgrounds
🔸A easy professional drawing app
🔹Gold Pro unlocked by AjeethK

📌 Direct Download Link 👇
🔗 click here to download mod
🌀 TorrCrow Pro for Torrent
🎯 Version - v19.4.1 ( Latest )
🔗 Playstore Link: click here

Features and Mod :
🔹Best torrent search engine app
🔸You can find any file in torrent
🔹Premium Movies and tv shows
🔸Premium pc softwares & tools
🔹Paid Android apps and games
🔸Paid Ebooks available for free
🔹Mod: Paid app (100rs) for free

📌 Direct Download Link 👇
🔗 click here to download mod
🌀 WIFI Monitor Pro
🎯 Version: v2.4.4 (Latest)
🔗 PlayStore Link : click here

Features and Mod :
🔹Check wi-fi Security
🔸Check who is connected to wi-fi
🔹Find out vulnerabilities in wi-fi
🔸Detailed info of network
🔹No ads, Premium unlocked

📌 Direct Download Link 👇
🔗 click here to download mod
🌀 Call Recorder Pro: Cube ACR
🎯 Version: v2.3.192 (Latest)
🔗 Playstore Link : click here

Features and Mod :
🔹Best call recorder for Android
🔸Record your phone calls, more
🔹WhatsApp calls, Facebook calls
🔸Can also record telegram callls
🔹Many more amazing features
🔸Premium unlocked for free

📌 Direct Download Link 👇
🔗 click here to download mod
🌀 Express VPN Premium mod
🎯 Version - v9.3.0 (Latest)
📌 Instructions : click here

Features and mod :
🔹Latest stable version
🔸Best VPN app for android
🔹Secure all online activities
🔸Remain anonymous online
🔹More then 20+ countries servers
🔸Unlimited Premium free trials
🔹Must read Instructions first...

📌 Direct Download Link 👇
🔗 click here to download mod
🌀 Alight Motion Premium apk
🎯 Version - v3.6.1 (Latest)
🔗 PlayStore Link : click here

Features and Mod :
🔹One of the best video editor app
🔸Add graphics, animations, effect
🔹Visual effect and color correction
🔸Transections & slow motion effect
🔹Make professional videos easily
🔸Full Adfree, premium unlocked

📌 Direct Download Link 👇
🔗 click here to download mod
#የWiFi_ኮኔክሽናችንን_ፈጣን_ለማድረግ_የሚያስችሉ_ዘዴዎችን_ልጠቁማችሁ !

የWiFi ኮኔክሽናችን በጣም እየተንቀራፈፈ ሲያስቸግረን ኮኔክሽኑን ፈጣንና አስተማማኝ ለማድረግ የሚረዱ ብዙ ዘዴዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ዘዴዎች የተወሰኑትን ልንገራችሁ፡፡

1ኛ፦ #Speedfy የሚባል አፕሊኬሽን ዳውንሎድ አድርጎ መጠቀም

አንድ አንድ ግዜ የWiFi አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ሆን ብለው የDownload እና Upload ፍጥነቱን ሊቀንሱ ስለሚችሉ WiFi ኮኔክሽኑ ሊንቀራፈፍ ይችላል፡፡ በዚህ ግዜ #Speedfy አፕሊኬሽን ኮኔክሽኑን ፈጣን ያደርገዋል፡፡በተጨማሪ #Speedfy አፕሊኬሽን እንደ VPNም ስለሚያገለግል ኮኔክሽኑን ፈጣን ያደርገዋል፡፡

2ኛ፦ #Opera ብራውዘር መጠቀም

የWiFi ኮኔክሽናችን በሚንቀራፈፍበት ግዜ #Opera ብራውዘርን ስንጠቀም ኮኔክሽናችን ፈጣን ይሆናል፡፡ ምክንያቱም #Opera ብራውዘር ፈጣን ፕርፎርማንስ እንዲኖረው የራሱ Built-in features ስላሉት።

3ኛ፦ በአንድ ግዜ የከፈትናቸው ብዙ ታቦች(Browser Tabs) ካሉ እነሱን መዝጋት

የተከፈቱ ብዙ ታቦች ካሉ ኮኔክሽናችንን ዝግግግግ… ስለሚያደርጉት የማንፈልጋቸውን ታቦች መዝጋት ኮኔክሽኑን ያሻሽለዋል፡፡

4ኛ፦ ቦታ በመለዋወጥ የተሻለ ኮኔክሽን ልናገኝ እንችላለን።

5ኛ የላፕቶፕ ወይም የስልክ ቻርጀር መሰካት

የላፕቶፓችን ወይም የስልካችን ባትሪ እያለቀ ከሆነ ቻርጀር መሰካት ኮኔክሽኑን ሊያሻሽል ይችላል( ይሄ እንኳን Theory ነው፤ ላይሆን ይችላል)

6ኛ፦ ከጀርባ የሚሮጡ አፕሊኬሽኖችን መዝጋት።
#ኦንላይን_ስራዎች_ለምትፈልጉ

#ሼር_ይደረግ

አንዳንዶቻችሁ ኮምፒውተርና ኢንተርኔት በመጠቀም ቤታችን ቁጭ ብለን ኦንላይን የምንሰራው ስራ ካለ ብትጠቁመን ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ፡፡

በዚህ ቴክኖሎጂ በተራቀቀበት ዘመን ሁሉም ስራዎች ኦንላይን እየሆኑ መጥቷል፡፡ ሰዎች በኮምፒውተርና ኢንተርኔት አማካኝነት ቤታቸው ቁጭ ብለው የተለያዩ ስራዎች ለተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በመስራት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ፡፡
ኦንላይን ስራዎች በጣም እየተለመዱ መጥቷል፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎች ብዙም ማሰላሰል የማይጠይቁ ስራዎች ለምሳሌ፡- ዳታ መመዝገብ፡ መፅሀፎችን ፊደል ማረም፤ድምፅን ወደ ፁሁፍ መገልበጥ፤ወዘተ ስራዎች በስፋት ኦንላይን ያሰራሉ፡፡

ኦንላይን ስራዎችን በመስራት ጥሩ ገቢ ማግኘት እያሰባችሁ ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ ኦንላይን ልትሰሯቸው የሚችሉ 3 ስራዎች ልጠቁማችሁ፡፡

1ኛ፡- Copy Editor

ጥሩ የእንግሊዘኛ ቋንቃቋ እውቀት ካላችሁ ይህ ስራ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ብዙ ኦንላይን ስራዎች አሉ፡፡

በዚህ ዘርፍ ከናንተ የሚጠበቀው ስራ የተለያዩ ፁሁፎች ይሰጣችኋል ። ከዚያ ያንን ፁሁፍ ፊደል ማረም ነው፡፡ፊደል ማረም ሲባል ፁሁፉ ላይ ቃላት የተገደፉ ካሉ ማስተካከልና ማረም የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡

በዚህ ዘርፍ ዌብሳይቶች፤መፅሀፍት፤መፅሔቶች እና የመሳሰሉትን እንድታርሙ ትጠየቃላችሁ፡፡
ጥሩ ስራ ይመስለኛል፡፡

እንዲህ ዓይነት ኦንላይን ስራ ከፈለጋችሁ
"copy editor online jobs" ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

2ኛ፤- Transcriber

ይህ ኦንላይን ስራ ሪከርድ የተደረገ ድምፅ ይሰጣችኋል፡፡ድምፁን እያዳመጣችሁ ወደ ፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ለምሳሌ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ንግግር ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ በተለይ እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ ያላችሁ ይህ ጥሩ ስራ ይመስለኛል።

የሚሰጣችሁ ድምፅ ንግግር፤ስብሰባ ላይ የተደረገ ንግግር፤ቪዲዮ ኮንፈረንስ ሊሆን ይችላል፤ትምህርቶች ሊሆን ይችላል፡፡ወዘተ

Online Transcriber Jobs ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

3ኛ፡- Data Entry

ይህ ኦንላይን ስራ የተለያዩ መልክ ያልያዙ ዳታዎችን መመዝገብ ነው፡፡ ለምሳሌ የትምህርት ቤቶች ወይም የሆስፒታል ትልልቅ ዳታዎችን ወደ Excel ማስገባት ወይም መመዝገብ ማለት ሊሆን ይችላል።፡

በተለይ ቁጭ ብሎ የመስራት ትዕግስት ያላችሁ ሰዎች ይህ ስራ ጥሩ ይመስለኛል፡፡

እንደዚህ ዓይነት ኦንላይን ስራዎች ለመስራት ኢንተርኔትና ኮምፒውተር ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡

ከላይ ከገለፅኳቻው ስራዎች ውጪ ሌሎች ብዙ ኦንላይን ስራዎችን ብትፈልጉ ታገኛላችሁ፡፡ሞክሩ፡፡

@techzone_ethio
@techzone_ethio
Pliz comment on it
@samiiiiabcd
ሌሎች ቀጣም በርከት ያሉ የኦንላይን ስራዎች ስላሉኝ inbox @samiiiiabcd
ሃከሮች እንዴት መረጃዎቻችን ይጠልፋሉ/ይሰርቃሉ ??

🔅 ቸልተኝነት

በማወቅም ሆነ በመዘናጋት የምንፈጥራችው ክፍተቶች ለሃከሮች በቀላሉ ኢሜላችንን ወይንም ፌስቡካችንን ሃክ እንዲያደርጉ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ተጥቅመን ስንጨርስ ሎግ አውት ሳናደርግ ብራውሰሩን ክሎዝ አድርገን እንወጣልን፤ ይህ ማለት ቀጥሎ የሚመጣው ሰው ብራውሰሩን መልሶ ሲከፍተው እኛ መጨረሻ ላይ ዘግተን የወጣነውን ገጽ ነው የሚከፍትለት ይህም ፌስቡክ ወይንም አሜይላችን ቀጥታ ከፈተለት ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አካውንታችን ሎግ ኢን ስናደርግ ፓስዎርዳችንን ሴቭ ላድርግላቹ የሚል መልእክት ብቂ ሲል በቸልተኝነት ሳናነብ የስ እንለዋለን ይህም ማለት ዩሰር ኔማችን እና ፓስዎርዳችን ኮፒውተሩ ላይ ሴቭ ተደረገ ማለት ነው በሌላ አገላለፅ ከ ቆይታ በኋላ በቀላሉ ፓስወርዳችንን ሶስተኛ ወገን ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡፡

🔅 ግምት

ይህ መንገድ ብዙ ጊዜ በአቅራቢያችን በሚገኙ ለማጅ ሀከሮች የሚደረግ ነው፡፡ ይህም በቃላሉ ፓስዎርዳችንን በመገመት ኢሜላችንን ወይንም ፌስቡካችንን ሃክ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በእኛ አገር የተለመደው ፓስዎርዳችንን ስልክ ቁጥር እናደርጋለን ብዙ ጊዜ ላለመርሳት አናዳዴም እንደዚው ስለመጣለን እናደርገዋልን ወይንም የምንወደውን
ሰው ስም ወይንም ስልከ ቁጥራቸውን እናደርጋለን ይሄ ደገም በቀላሉ የሚገመት እና አጋለጭ ነው፡፡
የራስ ሰልክ ቁጥር፣ የፍቅረኛ ስልክ ቁጥር ወይንም ስም፤የእናት ስም የተለመዱ የሀገራችን ፓስዎረድ ናቸው፡፡

🔅 ማታለል

ብዙም ባያጋጥምም አንዳንዴ ከማናውቃቸው ላኪዎች በኢሜላችን ፓስወረዳችንን እንጠየቃለን አሳማኝ ለማስመሰልም በተደራጀ መልኩ የተዘጋጀ ቅፅ እንዲሁም ኢሜይሉ ከታማኝ ምንጭ ወይም ከታዋቂ ድርጅት እንደተላከ እና ፎረሙን በመሙላታችን ወይንም መልስ በመፃፉ ተጠቃሚ እንደምንሆን አድርገው ሊያታልሉን ይችላሉ፡፡ እንዲዚህ አይነት መልእክቶች ሲመጡ በጭራሽ መመለስ የለብንም፡፡አንዳዴ ፓስዎረዳችንን ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም የባንክ አካውንት ቁጥር ጭምር ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

🔅 ፒሺንግ

ይሄኛው መንገድ የፕሮገራሚንግ እውቀት የሚጠይቅ ሲሆን የተፈለገውን አካውንት ሃክ ለማድረግ ተመሳሰይ የሆነ ገፅ በመገንባት ዩሰር ኔም እና ፓሰዎረዳችንን ለሶስተኛ ወገን የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ ለምሳሌ
ፌስቡክን ሃክ ማድረግ ከተፈለገ ከፌስቡክ ጋር በጣም ተቀራራቢ የሆነ ካልተጠነቀቅን በጣም ተመሳሳይ የሆነ ዌብሳይት በመስራት እኛ ፌስቡክ መስሎን ኢሜልን አና ፓስዎረድ ስናስገባ የኛነን መረጃ ወደ ትክክለኛው ፌስቡክ እንደ መላክ ወደ ሀከሮቹ መረጃችንን ይለካል ማለት ነው፡፡
ፒሺንግን ለመከላከል ዋንኛው መንገድ የምንጎበኘውን ዌብሳይት እራስችን በቀቀጥታ በመጻፍ መከላከል አነችላለን፡፡ ለምሳሌ www.facabook.com ወይንም www.facbooc.com ወይንም ደግሞ አድራሻው ከፌስቡክ ጋር የማይገናኝም ሊሆን ይችላል www.newbook.nt78.net ሊሆን ይችላል፡፡ ምንጊዜም እኛ የምንፈልገው ፌስቡክ እነዳልሆነ ኢሜላችንን ከማስገባችን በፊት መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ፋጽሞ የማይገናኝ አድራሻ ወይንም ቀጥር (አይ ፒ አድሬስ) ሊሆን ይችላል ገፅታው ግን እኛ ከምናውቀው ፌስቡከ ወይንም ያሆ ጋረ ፈፅሞ ተመሳሳይ ሊሆን ሰለሚችል ምንጊዜም አድራሻውን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡
ጥንቃቄዎች በተቻለን መጠነ ፓሰወረዳችን ረዘም ማድረግ በቀላሉ የማይገመቱ ፐሰዎረዶችን መጠቀም የኛ ባልሆነ ኮምፒውተር ስንጠቀም ብራውዘሩ ፓስዋርዳችንን ላስታውስ (Remember your password) ብሎ ሲጠይቀን ምንጊዜም ክሎስ ማድረግ ወይንም No ማለት ይኖርብናል፤ በርግጥ እንደ ምንጠቀመው ብራውሰረ የሚጠይቀን ጥያቄ ሊለያይ ይችላል ሆኖም ቁምነገሩ ፓስዎረዳችንን የኛ ያልሆነ ኮምፒውተር ሴቭ እንዲያደርገው አንፍቀድለት፡፡ በከፍተኛ ባለሙያዎች የሚደረጉ ሃኪንጎችን ለመከላከል ፓስዎረዳችንን የተለያያ ካራክተሮች ቀላቅለን መጠቀም፡፡ ለምሳሌ ቁጥር እና ፊደልን አንድላይ መጠቀም በተጨማሪም ኪይቦርዳችን ላይ የሚገኙ ምልክቶችን መጠቀም ይቻላል ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ስንጠቀም ሎግ አውት ማድረጋችንን እርገጠኛ ሆነን መውጣት
የራስችን ኮምፒውትር ከሆነ ደግሞ በዩዘር አካውንት
መቆለፍ ፡፡ ሂንት መስጠት ካለበን ደግሞ የምንሰጠው
ሂንት ቀጥታ ፓስዎረዱን ሳይሆን ፓስዎረዳችንን ሊያስታውሰን የሚችል ብቻ ነው መሆን ያለበት፡፡
በተጨማሪም ምንጊዜም አንቲቫይረሳችንን በተቻለ
መጠን አፕዴት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

@techzone_ethio
@techzone_ethio
#ዌብሳይት_አድራሻ_ክፍሎች

አንድ ዌብሳይት አድራሻ አራት የተለያዩ ክፍሎች አሉት።
ለምሳሌ፦ https://facebook.com/Tvdotcomshow
የዚህ ዌብሳይት አድራሻ 4 ክፍሎች እንያቸው።

1ኛ፦ https ይህ ክፍል Scheme ይባላል

2ኛ፦facebook ይህ ክፍል Second Level Domain ይባላል

3ኛ፦ com ይህ ክፍል Top-Level-Domain ይባላል

4ኛ፦Tvdotcomshow Subdirectory ይባላል

እነዚህ አራት ክፍሎች እያንዳንዳቸው ትርጉም እና የሚሰሩት ስራ አላቸው።ነገርግን ዛሬ ልነግራችሁ የፈለኩት ስለ 3ኛው ክፍል(com) ነው።

የተለያዩ ኩባንያዎች ዌብሳይት አድራሻ ይኖራቸዋል።እነዚህ የተለያዩ ኩባንያዎች በተለያዩ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሊሆኑ ይችላሉ።

አንድ ዌብሳይት አድራሻን በማየት ብቻ የዌብሳይቱ ባለቤት የሆነው ኩባንያ በምን ዓይነት ስራ ላይ እንደተሰማራ ማወቅ ይቻላል።ይህንን መረጃ የሚሰጠን የዌብሳይቱ አድራሻ 3ኛው ክፍል ነው።

ይህ ክፍል( Top-Level-Domain )የተለያዩ ዌብሳይት አድራሻ ውስጥ 3 ፊደላት ቅጥያ የያዘው ክፍል ሲሆን የተለያዩ ኩባንያዎች የተሰማሩበት ዘርፍ የሚጠቁሙ የተለያዩ ባለ 3 ፊደላት ቅጥያዎች ያላቸው የዌብሳይት አድራሻዎች ላይ እናገኛለን።

ከነዚህ ባለ 3 ፊደላት ቅጥያዎች መካከል ለምሳሌ፦ .edu፣.gov፣.com፣.net፣.info፣net ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።

እነዚህ ባለ 3 ፊደላት ቅጥያዎች ስለኩባንያዎቹ የሚነግሩንን ትርጉሞች እንመልከት።

1ኛ፦ .com ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው በንግድ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ነው ማለት ነው።

com ማለት Commercial ለማለት ነው።

2ኛ፦.net ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው የቴሌኮሙኒኬሽን ወይም የቴክኖሎጂ ተቋም ነው ማለት ነው።

net ማለት Network ለማለት ነው።

3ኛ፦.gov ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው መንግስታዊ ተቋም ነው ማለት ነው።
gov ማለት Government ለማለት ነው።

4ኛ፦.info ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው መረጃ የሚያሰራጭ ተቋም ነው ማለት ነው።

info ማለት Information ማለት ነው።

5ኛ፦ .edu ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው የቴትምህርት ተቋም ነው ማለት ነው።ለምሳሌ ዩኒቨርሲቲዎች።

edu ማለት Education ማለት ነው።

6ኛ፦.biz ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው የቢዝነስ ተቋም ነው ማለት ነው።

biz ማለት Business እንደማለት ነው።

#ሼር_ይደረግ
@techzone_ethio
@techzone_ethio
#ለተማሪዎች_የሚጠቅሙ 4 #የአንድሮይድ_አፕሊኬሽኖች

#ሼር_ይደረግ

ተማሪዎች፤ የሃይ ስኩል እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደራራቢ አሳይመንቶች ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡
ተደራራቢ የቤት ስራዎች፣የግሩፕ አሳይመንቶች፣ፕሮጀክቶች፣ ተደራራቢ ጥናቶች ተማሪዎች ላይ ጫና ሊያበዛ ይችላል፡፡ ይሄ ጫና ደሞ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል፡፡

በትምህርት ወቅት ጫና እንዳይፈጠርባችሁ ዋናውና ቁልፍ መፍትሔ ለየአንዳንዱ ነገር ፕሮግራም ማዘጋጀት ነው፡፡

ቀጥሎ የምነግራችሁ 4 አፕሊኬሽኖች ተማሪዎች በትምህርት ወቅት ጫና ሳይፈጠርባቸው ትምህርታቸውን ባግባቡ በመከታተል በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ ዓለም ዓቀፍ እውቅናም የተሰጣቸው አፕልኬሽኖች ናቸው።

1ኛ፡- School Planner Application

ይህ አፕሊኬሽን የቤት ስራዎችን፣ የግሩፕና የግል አሳይመንቶችን፣ፕሮጀክቶችን፣የእያንዳንዱን ክላስ ሰዓትና ቀን…ማንኛውም ትምህርት ነክ አክቲቪቲዎቻችሁን ኦርጋናይዝ ያደርግላችኋል፡፡ ፕሮግራም ያወጣላችኋል።

ይህ አፕሊኬሽን በየቀኑ በፕሮግራማችሁ መመሰረት በየቀኑ መስራት ያለባችሁን ለምሳሌ ጥናት ወይም የቤት ስራ፣የግሩፕ አሳይመንት፣ የላብራቶሪ ሙከራ ….ባጠቃላይ ጠዋት ምን ማድረግ እነዳለባችሁ፡፡፡፡፡፡ ከሰዓት ምን መስራት እንዳለባችሁ…….ማታ ምን መፃፍ እንዳለባችሁ ያስታውሳችኋል….

የምታስረክቡት አሳይመንት ወይም ፕሮጀክት ካለባችሁ የምታስረኩብበት ቀን "በዚህ ቀን ነው፡፡፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው…" እያለ ያስታውሳችኋል፡፡

2ኛ፡- Brilliant

ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በተለይ በሂሳብ፣ በሳይንስና በኮምፒውተር ሳይንስ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በጣም የሚጠቅም አፕ ነው፡፡

ይህ አፕሊኬሽን እየሸመደዳችሁ እንዳታጠኑና በተለይ ረጃጅም ቃላት የሚበዙባቸው የትምህርት አይነቶችን ዘርዘር ያሉ ገለፃዎችን በመጠቀም ሳትሰለቹ ትምህርቶቹን በቀላሉ እንድታጠኗቸውና እንዲገባችሁ ይረዳል ።

3ኛ፡- Grammarly

ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ያሳድጋል፡፡

የተለያዩ ESSAY በእንግሊዘኛ ስትፅፉ የግራመር ስህተታችሁን ያርማል፣ትክክለኛ ቃላት እንድትመርጡ ይረዳል፡፡ ረጃጅም አረፍተ ነገሮችን ስትፅፉ የሲንታክስ ስህተታችሁን ያርማል፡፡

በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ቀስበቀስ ያሳድጋል፡፡

4ኛ፡- Mendeley

Research በምትሰሩበት ግዜ ለጥናታችሁ የሚሆኑ የተለያዩ ሪሶርሶች እንዴት እንደምታገኙ ይረዳችሃል፡፡

ለጥናታችሁ ወይም ለሪሰርቻችሁ የሚጠቅሙ መፅሃፎችን፣ጥናታዊ ፅሁፎችን፣ ምክረ ሃሳቦችን እንዴት እንደምታዘጋጁ ያስተምራቸኋል፡፡

ለሪሰርቻችሁ የተጠቀማችሁባቸውን የተለያዩ የጥናታዊ ፁሁፎች ፃሃፊዎችን፣የመፅሐፍት ደራስያን ፣ምሁራንን ስማቸውን በመጥቀስ ጥናታችሁ ላይ በማካተት እንዴት እውቅና ወይም ክሬዲት እንደምትሰጧቸው ያስተምራችኋል፡፡

#ሼር

@techzone_ethio
@techzone_ethio
Inbox me for the apps @samiiiiabcd
ሰላም ውድ የ ethio tech zone ቤተሰቦች ዛሬ ስለ ሳይበር ወንጀለኞች አጠር ያለች ማብራሪያ ይዤላቹ መጥቻለው።

🔻የሳይበር ወንጀለኞች በተለያዩ መንገዶች የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን ይፈፅማሉ። በሀገራችን የሳይበር ጥቃት ከተፈፀመባቸው ድርጅቶች አንዱ Ethio Telecom ነው።

🔻በ2020 በተደረገው ጥናት መሰረት የሳይበር ጥቃት የሚፈፀምበት አንዱ መንገድ የተለያዩ የ Mobile እና የ Computer Virus በማዘጋጀት የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
ምን አይነት ቫይረሶች ናቸው ለሚለው...

1⃣. Clop Ransomware

🔻ይህ ቫይረስ በጣም አደገኛ ቫይረስ ሲሆን በኮምፒውተራችን ከገባ ቡሀላ የተለያዩ መረጃዎችን በመዝጋት እንዳንጠቀም የሚያደርግ ነው። የተዘጉትን መረጃዎች ማገኘት የምንችለው የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎቹ የሚጠይቁንን ክፍያ ከፈፀምን ቡሀላ ነው። ለምሳሌ በዚህ ቫይረሰ የተጠቁ ድርጅቶች Ethio Telecom ልንጠቅስ እንችላለን።

2⃣ Hidden Ransomware

🔻ይህ ቫይረስ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር በEmail የሚላክና በየትኛውም Antivirus ሊታይ የማይችል ቫይረስ ነው። ይህም የተለያዩ መረጃዎችን በመዝጋት እንዳንጠቀም የሚያደርግ ነው። የተዘጉትን መረጃዎች ማገኘት የምንችለው የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎቹ የሚጠይቁንን ክፍያ ከከፈልን ቡሀላ ነው።

3⃣. Zeus Gameover

🔻ይህ ቫይረስ በኮምፕዩተራችን ከገባ ቡሀላ የተለያዩ ሚስጥራዊ መረጃዎችን (Email, Bank account detail Info bla bla) በመስረቅ ለተፈለገው ሰው መረጃዎችን Email የሚያደርግ አደገኛ ቫይረስ ነው።

4⃣. News Malware Attacks

🔻 ይህን ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችሁ እንዲገባ ለማድረግ የሚጠቀሙበት መንገድ አደገኛ ያደርገዋል።

‼️ማሳሰቢያ ‼️

⚠️በ Email የሚላኩ መልዕክቶችን ከማን እንደተላኩ ካላወቁ መልዕክቱን ይጠንቀቁት።

‼️ Join & Share...
📢 @techzone_ethio
@techzone_ethio
✳️ Tech News...

🔻በቅርቡ ስልካችንን በእየ ሶስት ወሩ ብቻ ቻርጅ ማድረግ ነው የሚጠበቅብን ምክንያቱም ከሰሞኑ ተመራማሪዎች እንድ ነገር ይፋ አድርገዋል።

🔻ተመራማሪዎችም እንዳሉት ከሆነ Magneto Electric Multiferroic ተብሎ የሚጠራ ከአዲስ ቁስ የተገኘ አዲስ የ Smartphone ባትሪ በአንድ ጊዜ በተደረገ ቻርጀ ለሶስት ወር ያህል እንዲቆይ የማድረግ አቅም ያለው ነው ተብሏል።

‼️ Join & Share...
@techzone_ethio
@techzone_ethio
✳️ ጄፍ ቤዞስ የአማዞን መስራች

◽️ January 12 1964 በNew Mexico ግዛት የተወለደው ጄፍ ቤዞስ ገና በለጋነቱ ነበር ወደ ቴክኖሎጂ ማዘንበል የጀመረው።
ከፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ በ ኮምፒውተር ሳይንስ እና በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተመርቋል።

◽️ ለአራት አመታት ተቀጥሮ ቢሰራም የራሱን ፈጠራ ለመፍጠር በማሰብ የመጀመሪያውን የመጽሃፉ መገበያያ ድረ-ገጽ ይፋ አደረገ። ስሙንም Amazon.com ብሎ ሰየመው። የስሙ መነሻም እንደ ግዙፉ የአማዞን ጫካ ግዝፈቱን ለማሳየት ነው።

◽️ ቀስ በቀስም ሌሎች እቃዎች በማገበያየት ባጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂ ለመሆን በቅቷል። በ2007 ያስተዋወቀው Kindle የዲጂታል መጻህፍት ማንበብያ በሰፊው ተቀባይነትን አስገኝቶለታል። በአሁን ሰአት እጅግ በጣም ሰፋፊ በሆኑት መጋዘኖች በ ሰከንድ እስከ 500 ትዕዛዛትን ይቀበላል። ሀብቱም ወደ 130 ቢሊዮን ዶላር እየተጠጋ ነው።

◽️ ከቴክኖሎጂው ባሻገር ወደ ሚድያው ዘርፍም በመቀላቀል በቅርቡ ለ 140 አመታት የዘለቀውን Washington Post ጋዜጣ በ250mln$ መግዛት ችሏል። እንዲሁም "Whole food" የተሰኘ ምግብ አቅራቢ ድርጅትን በ13.7bln$ በመግዛት የግሉ አድርጎታል።

◽️ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ውጪ በርካታ ፈጠራዎች ላይ እየሰራ ይገኛል። በ ሙከራ ላይ ያለው "Amazon prime air" የተለያዩ መልዕክቶችን በ ድሮን አማካኝነት ባጭር ጊዜ ማድረስ አንዱ ነው።

▬▬▬▬▬▬
@techzone_ethio
@techzone_ethio
2024/11/27 11:45:08
Back to Top
HTML Embed Code: