tgoop.com/temuabiy/1116
Last Update:
ብቻን የመሆን ችሎታ
ብቻን መሆን ብቸኛ መሆን አይደለም፡፡ ብቸኝነት ሰው ማጣት ነው፡፡ ብቻን መሆን ደግሞ ከራስ ጋር ለመሆን የሚወሰድ ግዜ ነው፡፡ ይህም በማንኛውም እኛን በሚመቸን ግዜ ልናደርገው እንችላለን፡፡ ሰፊ ግዜ መሆንም አይጠበቅበትም፡፡ እየተንቀሳቀስን ወይንም አረፍ ብለን ልናደርገው የምንችለው ጉዳይ ነው፡፡
ብቻችንን ስንሆን ምን ልናደርግ እንችላለን? 👇🏻
1️⃣እስካሁን ያሳለፍነውን ህይወት ልንቃኝ እንችላለን፡፡ እንዴት እንዳሳለፍን? ምን እንደተማርን? ምን ስህተት እንደሰራን? ከአሁን ህይወታችን ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው? ወዘተ ልናስብ እንችላለን፡፡
2️⃣በቅርብ የተፈጠሩ ጉዳዮችን ልናስብ እንችላለን፡፡ ያስገረመን ወይም ያበሳጨን ወይም አዲስ ነገር የሆነብንን ክስተት ልናስብ እንቸላለን፡፡
3️⃣ስለወደፊት ህይወታችን ልናስብ እንችላለን፡፡ ወደፊት ማድረግ፤ ማሳካት ስለምንፈልገው ጉዳይና አሁን ምን ላይ እንዳለን? ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ልናስቀምጥ እንችላለን፡፡
4️⃣ስሜታችንን ልናደምጥ እንችላለን፡፡ አሁን የሚሰማንን ስሜት በማድመጥ ሰውነታችንን መረዳት ማለት ነው፡፡
5️⃣ተፈጥሮን ማስተዋል፡፡ እንዲሁ ከራሳችን ጉዳይ ወጥተን በተፈጥሮ ልንደመምና ልንመሰጥ እንችላለን፡፡
6️⃣ዘና ልንል ወይም አረፍ ልንል እንችላለን፡፡
ብቻን መሆን ጤነኝነት ነው፡፡ ነገር ግን ብቻችንን ስንሆን የምናስባቸው ነገሮች አሉታዊ ብቻ ከሆኑ መልስ ያልሰጠናቸውን የግል ጉዳዮች መልስ መስጠት ወይም ወደ ባለሙያ መሄድ አለብን፡፡
ተመስገን አብይ Psychologist
BY ተመስገን አብይ _ Psychologist
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/HiWCpXrIylYPNcXCop8UlOHqiIAj490jQ8eueRbUJyxQpkt3SfqlzZkJSpaJkMel1OxYXxs7EyjMujctEqNM2rqCeyE1BCkaKoW8XVoel-BS-xfFkuHZbmLD_i13F2avlpaW1fUHHRFkx671jxfwqdNQ4jh5vQYAN4Wk3vyuFT9ajDKTRmKOK7qBAauRlMnsW1C6JmLbksBcTh89NoV64syla_8JLtcf_IcepH2HwmjsqoQwHzJIaQ8RnSDsPwG8mre4jplprH_jj8P5pzHvQp6XjulQic6fZiLIYdYMn4SSKvJRpwdK8cr5rUoCuwhy5HtWmZjkXr8g5N2_JG8W4g.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/temuabiy/1116