tgoop.com/temuabiy/1149
Last Update:
ስሜት ምንድን ነው?
ስሜት ሰውነት ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ነው። አሁን ሰውነቴ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የማውቀዉ በሚሰማኝ ስሜት ነው። ብዙዎቻችን እንደምንለው ስሜት እንዲሁ የሚነዳን ወይም ጠላታችን አይደለም።
አሉታዊ ስሜቶች ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ የሚጠቁሙንና ማድረግ የሚገባን ነገር እንዳለ አመላካች ናቸው። አዎንታዊ ስሜቶች ላደረግነው ትክክለኛ ድርጊት ማረጋጫ ናቸወ።
ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ስራ ላይ የቆዬ ሰው የድካም ስሜት ይሰማዋል። ይህም ሰውነቱ እረፍት እንደሚፈልግ መልእክት ነው። ሰውነትም በቂ እረፍት ሲያገኝ የመነቃቃትና ዘና የማለት ስሜትን ይናገራል።
ነገር ግን ያለ በቂ እረፍት ስራችንን ብንቀጥል ሰውነት የድካም ስሜትን መንገር እየቀነሰ ይሄዳል በሇላም ዝም ይላል። ታዲያ በዚህ ግዜ አንዳንድ ሰዎች ምንም ያህል ብሰራ የድካም ስሜት አይሰማኝም፤ ሰርቼ አልጠግብም ይላሉ። ያልተረዱት ነገር ሰውነት መልስ መስጠት ሲያቆም እየደከመና እየሞተ መሆኑን ነው። ህመሞችን እያከማቸ መሆኑን አናውቅም።
የሰውነታችንን መልእክት ግዜ ሰጥተን ብናደምጠው ሰውነታችን በጣም ጤናማና ረጅም ግዜ የሚያገለግለን መሆን ይችላል።
ስሜትን ባለማድመጥና በመካድ ጤናማ መሆን አይቻልም። ስለዚህ ስሜት ጠቃሚና ቦታ ሰጥተን ልናደምጠው የሚገባን ነገር ነው!
ተመስገን አብይ_psychologist
https://www.facebook.com/inmotivation
BY ተመስገን አብይ _ Psychologist
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/cNy65YBYf9CNfXWru4FQA4OP0O_hmfuz8JfyGjJkVdE95i_SBgN3RXe_4Iu2xD33AaQnn0tz8BwZEestUbxgzouZr3_gh9aCH5Tfy_KCvcInKuuAAiLSLvm2K9lVXjC2oRYCTRws7GGlvxwZ0mXBtF9HUuxJ0kU0VhhRZmxXvswEgU218B6EkUMeyzsNEnpOS59iBUrimtlZetPJEE03sUGYmVGjWC45d343_VY39mldrfh4Nt4V83pV4Evdqz-C33bMc0ywF8bUQdyUPbwBS-fGUg7IXy-h4fI2P1qgsu9w1kT5Ejx_JIGxBp8Qw1ySXedaI7IsLNRB9OTOD8m1YA.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/temuabiy/1149