Telegram Web
ስሜቶቻችንን ለመቀየር ወይም ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ በውስጣችን እንዲኖሩ መፍቀድ ነው ያለብን፡፡ ስንፈቅድላቸው አዕምሯችን ይረጋጋል፤ ስሜቶቻችንም ይስተካከላሉ፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
የማትደራደሩበት ነገር ምንድን ነው?
Anonymous Poll
20%
ራሳችሁን
14%
ቤተሰባችሁን
3%
ስራ
6%
ሀገር
52%
ሀይማኖት
5%
ሌላ
ነገሮች ሁሌምእኛ እደጠበቅናቸው አይሆኑም፡፡ መሆንም አይገባቸውም፡፡ ስለዚህ ለሁሉም ዝግጁ መሆን የኛ ስራ መሆን አለበት፡፡

ተመስገን አብይ Psychologist
የሙሉነት ስሜት ተሰምቷችሁ ያውቃል?
Anonymous Poll
44%
አወ
19%
አያውቅም
24%
ሰው ሙሉ አይደለም
12%
አላውቅም
3 አዕምራችን በተደጋጋሚ የሚያደርጋቸው ነገሮች፡

1️⃣ መጠቅለል፡ አንድ ሰው ላይ ያየነውን ነገር ሙሉ የኢትዮጵያ ሰዎች እንደሚያደርጉት አድርጎ ማሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ወጣት ሲሳደቡ የተመለከቱ አዛውንት አይ የዘንድሮ ወጣት እንዲህ ናቸው ቢሉ አዕምሯቸው ጠቅልሎ እንዲያስቡ ሆናል ማለት ነው፡፡

2️⃣ መሰረዝ፡ ከዚህ በፊት አድርገናቸው የምናውቃቸው ነገሮች ሊሰረዙና ልንረሳቸው እንችላለን፡፡ ይህም ብዙዎቻችን የሚገጥመን ነገር ነው በተለይ ለጅም ግዜ ከሆነው በኋላ፡፡

3️⃣ ማዛባት፡ የሆነው ጉዳይ ላይ ምናባዊ የሆነ እውነት የሚመሰል ሀሳብ ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ ፈጣን የነበረ ጓደኛችንን አሪፍ የማስታወስ ችሎታ አለው ብለን ልናወራ እንችላለን፡፡ በተለይ የልጅነት ታሪካችንን ስናወራ አንዳንዶቹ ያልሆኑ ነገሮች ነገር ግን ያደረግናቸው የሚመስሉ ናቸው፡፡ በቆይታ ሂደትም እውነት አድርገን እንቀበላቸዋለን፡፡

ተመስገን አብይ Psychologist
እንዲህም ይታሰባል ለካ......... አንብቡት

ለጓደኛዉ "ትናንት ማታ ባለቤቴ አንተ መቼም የማትቀየር ድንጋይ ነህ" አለችኝ:: "በሇላ ሳስበው ግን ልክ ነች" ይለዋል::

እንዴት?

አንተ መቼም የማትቀየር መሰረት ነህ:: በአቋምህ የፀናህ ነህ:: ታማኝ ነህ ማለቷ ነዉ ሲል ይመልስለታል::

ተመስገን አብይ Psychologist
ወሳኔ ቁርጠኝነት ነዉ::


ተመስገን አብይ Psychologist
ከሰሞኑ አንዱን ቀን ወደቤቴ ልገባ የግቢውን በር በመክፈት ላይ ሳለሁ "አባ አባቴ ወንድሜ" የሚል ድምፅ ሰማሁ:: ወደሰማሁበት አቅጣጫ ዘወር ስል ለካ እኔን ነው::
ልጁ ወጣትና ቆሸሽ ያለ ልብስ የለበሰ ነው:: ወደ እኔ እየመጣ ድምፁን ከፍ አድርጎ "የሚበላም አይደለም የምፈልገዉ ገንዘብም አይደለም የምፈልገዉ እያለ እየቀባጠረ ቆዬ::"
ጊዜዬን እንዳይወሰድብኝ አልኩና ምንድን ነዉ የፈለከዉ? የፈለከዉን ተናገር አልኩት:: ቀልጠፍ አለና "ሱሪ ነዉ የምፈልገዉ ሱሪ ካለህ" አለኝ:: ጠብቀኝ አልኩትና ቤት ገብቼ ከጠበቡኝ ሱሪዎች አንዱን አንስቼ ሰጠሁት:: ደስ ብሎት ስሞኝ መርቆኝ ሄደ::

በኃላ ሳስበዉ ሁለት ነገር ገረመኝ:: የመጀመሪያዉ የሚፈልገዉን በቀጥታ ከመናገር ይልቅ የማይፈልገውን ሲዘረዝር መቆየቱ ነዉ:: ይኸም ሰዎች አይረዱኝም የሚል ፍርሃት መሆኑ ነዉ::

ሁለተኛዉ የሚፈልገዉን ስጠይቀዉ በቀጥታ በአንድ ቃል "ሱሪ" ማለቱ አስገረመኝ:: እኔስ የምፈልገዉን በቀጥታ መግለፅ እችል የሆን...? ራሴን ጠየኩት::

አጋጣሚዉ ስላስገረመኝ ሼር አደረኳችሁ:: ከወደዳችሁት ለሚጠቅማቸዉ ሰዎች ሼር አድርጉት::


ተመስገን አብይ Psychologist
ራስን አንድም ከራስ አንፃር ደገግሞም በሌሎች አይን ማየት አስፈላጊና ጠቃሚ ነዉ::


ተመስገን አብይ Psychologist
📖 ልጆች በበጋው ወቅት ከሚማሯቸው ትምህርቶች እኩል ለህይወታችው ወሳኝ ከሆኑ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ የህይወት ክህሎቶችን መማርና ማዳበር ነው፡፡
🔊ምዝገባችን ሊጀመር ነው!

🚫 ያሉን ዉስን ቦታዎች ስለሆኑ ፈጥነው ልጅዎን ያስመዝግቡ !

🔐ልጆች በቅዳሜ ስልጠናችን፦

📌 በራስ መተማመናቸው ይጨምራል።
📌 እንደሚችሉ ይሰማቸዋል።
📌 ደጋግመው መሞከር ይችላሉ።
📌 አቅማቸው ይጨምራል።
📌 ጀምረው መጨረስ ይችላሉ።
📌 ሃላፊነት መውሰድ የሚችሉ ይሆናሉ።

🗓 ዘወትር ቅዳሜ 3:00-5:30 ሰዓት

ለበለጠ ማብራሪያ እና ለመመዝገብ

☎️ +251935 545452
+251970414243

@mindmorning
ለእስልምና ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።


ተመስገን አብይ Psychologist
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራና ለመስቀል በአል አደረሳችሁ።


ተመስገን አብይ Psychologist
Audio
🌘 ከግርዶሽ ጀርባ  

🔴 እናንተ ቶሎ ቶሎ ትናደዳላችሁ ወይስ አልፎ አልፎ ነው ቱግ የምትሉት ?

🖍 የተከማቸ ስሜት ካለን 🖍 ነገሮችን መቋቋም ሲያቅተን 🖍 እንዳይፈጠር የምንሰጋው ነገር ካለ 🖍 ሌላ አማራጭ የሌለን ሲመስለን

🌘 እያንዳንዱ ሰው በተለያየ ምክንያት ግርዶሽ አለው!

በጥያቄው ራስዎን ይፈትሹ!!

ማይንድ ሞርኒንግ የባህሪ ስልጠና ምርምርና ማማከር ከ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በመተባበር  ዘወትር ሰኞ ከ 8:00-10:00 ሰዓት በቀጥታ ይቀርብላችኋል፡፡

የዚህ ፕሮግራም አጋሮች

#አማራ_ባንክ
#ኮካ_ኮላ

@Mindmorning
ንጋት እና ህይወት

   🔗  አመክንዮ የበላቸው ተምሳሌቶች
        🤔  ምክንያት ወይንስ ምሳሌ ?

📆 ዘወትር ሰኞ ከ 8:00-10:00

  በ ኤፍኤም 97.1  ይከታተሉ !

ማይንድ ሞርኒንግ ( Mind Morning )
Telegram:@mindmorning
Facebook :https://www.facebook.com/mindmorning
YouTube :https://youtube.com/@mindmorning8895?si=kf-l6KGU52UoetK7
Audio
📻 ንጋትና ህይወት

እንጠየቅ

🤔 ሰዎች ስሜታቸውን መስማት የሚያቆሙት ምን ሲሆኑ ነው?

የሃሳብ መብዛት ስሜትን ይጋርደዋል።
♦️ ለስሜትም የበዛ ትኩረት መስጠት ሃሳብን ያጠፋዋል።

🎧 ያድምጡት በቂ ምላሽ ያገኛሉ!


ማይንድ ሞርኒንግ የባህሪ ስልጠና ምርምርና ማማከር ከ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በመተባበር  ዘወትር ሰኞ ከ 8-10 ሰዓት በቀጥታ የሚቀርብላችሁ የሬድዮ ፕሮግራም ነው።


+251970414243
+251935545452


Telegram: @mindmorning
Facebook :https://www.facebook.com/mindmorning
YouTube :https://youtube.com/@mindmorning8895?si=kf-l6KGU52UoetK7
2025/02/15 22:46:21
Back to Top
HTML Embed Code: