Telegram Web
በየሳምንቱ እሁድ በጉጉት ከምጠብቃቸው ስራዎቼ አንዱ ይህ ነው፡፡

ራሳቸውን በመቀየር ሂደት ውስጥ ያሉ ሞዴሎች ናቸው፡፡ ዘወትር እሁድ አዲስ ሀሳብ እናነሳለን፤ በአዲስ ጥያቄም ይሞግቱኛል፡፡ ከሳምንት ቆይታቸውም ያስተምሩኛል፡፡ ያዘዝኳቸውንም ይሆናሉ፡፡ ሲላቸውም ያዙኛል፡፡ ብቻቻቻ ደስ ትላላችሁ……… ደግሞ ቶሎ የሚገባችሁ ነገርስ…..

የምወደውን እሁዴን ከእናንተ ጋር እያሳለፍኩ ስለሆነ ደስተኛ ነኝ፡፡


Legacy Modeling and art

ተመስገን አብይ Psychologist
መርሳትና መፍትሄዎቹ

መርሳት ምንድን ነው? ለምንስ እንረሳለን? 🤔

እኔ የመርሳት ችግር አለብኝ በጣም እረሳለሁ ይላሉ ሰዎች፡፡ ይህንን የሚሉት ሁሉን ነገር ማስታወስ እንዳባቸው ስለሚያስቡ ነው፡፡ ያየነውን ሁሉ፣ የሰማነውን ሁሉ፣ የዳሰስነውን ሁሉ፣ ያሸተትነውን ሁሉ ማስታወስ የለብንም፡፡ አንችልም ምክንያቱም ስራችን ማስታወስ አይደለም፡፡

በቀን ውስጥ በአማካኝ 60,000 ገደማ የሚሆኑ ሃሳቦችን እናስባለን፡፡ ከዚህ ሁሉ ሃሳብ የምናውቀው 5% አይሞላም፡፡ ማለትም ከ 95% በላይ የሚሆኑ ሃሳቦቻችንን አናውቃችውም ነገር ግን እኛው ነው የምናስባቸው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አይናችንን ቀኑን ሙሉ ሲመለከት የዋለውን ማወቅ አንችልም ከጥቂቶች በስተቀር፡፡ የማናውቀውን ማስታወስ ደግሞ ከየት ይመጣል፡፡

ስለዚህ መርሳት ወይም አለማስታወስ ችግር አይደለም፡፡ አዕምሯችን የሚሰራበት መንገድ እንደዚህ ስለሆነ ራሳችሁን መውቀስና ችግር አለብኝ ብላችሁ ማሰብ የለባችሁም፡፡

የምናስታውሰው ትኩረት የሰጠነውን ነገር ብቻ ነው፡፡ ትኩረት ያልሰጠነውን ጉዳይ በምንም ያህል ግዜ ብንደጋግመው ላናስታውሰው እንችላለን፡፡ ግርምት የጫረብንንና ከኛ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች በይበልጥ ትኩረት ስለምንሰጣቸው የማስታወስ እድላችን ከፍተኛ ነው፡፡

ሁሉንም ነገር ለማስታወስ ከመሞከር ይልቅ ጥቂት ዋና ጉዳዮችን ማስታስ ነፃ ሆነን እንድንኖር ያደርገናል፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
እድሜና ደስታ

እንደልጅነታችን አሁን ላይ ለምን ደስተኛ መሆን አቃተን? ለምን ይሆን እድሜያችን እየጨመረ ሲመጣ ደስታችን የሚቀንሰው?

ለደስታችን መቀነስ ዋነኛው ምክንያት፡

ሃሳብ ይባላል፡፡ እድሜያችን ሲጨምር አብሮ ማሰባችን ይጨምራል፡፡ ማሰብ ለነገሮች ቅድመ ተከተል ማውጣትና መስፈርት ማስቀመጥ ስለሆነ ከደስታ ያርቀናል፡፡ ምክንያቱም ደስተኛ ለመሆን ምንም ቅድመ ተከተልና መስፈርት አያስፈልገውም፤ እንዲሁ መደሰት ብቻ ነው የሚያስፈልገን፡፡

ትምህርቴን ልጨርስና፣ ስራ ልያዝና፣ ስልክ ልያዝና፣ ላግባና፣ ልውለድና፣ መዝናኛ ቦታ ልሂድና ወዘተ. ደስተኛ እሆናለሁ ብላችሁ አታውቁም ፡፡ ደስታን በቀጠሮ ማግኘት አይቻልም፡፡ ደስታ ከእኛ ጋር ሊኖር የሚገባው የማንነታችን አካል ነው፡፡

ስለዚህ በሃሳብ ውስጥ ብቻ የሚኖር ሰው ደስተኛ መሆን አይችልም ማለት ነው፡፡ በተግባር የሚኖርን ሰው ግን ከደስታ መነጠል አይቻልም!


ተመስገን አብይ Psychologist
ከቤት የመውጣት ጥቅሞች

1️⃣ ብዙ አማራጭ እንዳለ ይገባናል፡፡
2️⃣ መጋፈጥ እንድንችል ያደርገናል፡፡
3️⃣ ደስተኛ ያደርገናል፡፡
4️⃣ አዳዲስ ነገሮችን እናገኛለን፡፡
5️⃣ ጤናማ እንሆናለን፡፡

ስለዚህ ቤት ውስጥ ብቻ ግዜያችሁን የምታሳልፉ ሰዎች ከቤት ወጥቶ የመንቀሳቀስ ልምድ ይኑራችሁ፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
ስሜትና ሃሳብ

ስሜታችንና ሃሳባችን ለምን አንድ አይሆንም?

ሃሳብ ከውጪ የሚገባ መረጃ ነው፡፡ ግዜ ሰጥተንም በማገናዘብ ቅርጽ እናስይዘዋለን፡፡ ስሜት ደግሞ ያሰብነውን በተግባር ስናደርገው ሰውነታችን ላይ የሚፈጠር ነው፡፡

ከተግባር ውጪ ያለ ስሜት ምንጩ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ሃሳባችን በራሱ የሚፈጥርብን ስሜት አለ፡፡ ይህም ቶሎ ቶሎ የሚቀያየር ነው፡፡ ሁለተኛው ከዚህ በፊት ተሰምቶን የሚያውቅ ስሜት ነው፡፡ ሰውነታችን ላይ የተመዘገበ ስለሆነ እንድናስታውሰውና አሁን ላይ እንዲሰማን ያደርገናል፡፡

ሃሳብና ሰሜታችን አንድ መሆን የሚችሉት በአንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ እሱም ተግባር ይባላል፡፡ ያሰብነውን ስንተገብረው የሚፈጠርብን ስሜት ከሃሳባችን ጋር ይገጣጠማል፡፡

የተግባር ሰው ካልሆን ሃሳብና ስሜታችን አንድ መሆን አይችልም!


ተመስገን አብይ Psychologist
የመረጋጋት ምስጢር

በእጥረትና በማጣት ውስጥ ያለ ሰው ያለው አማራጭ መቸኮል ብቻ ነው፡፡ ለምን አትሉም? ምክንያቱም ከተረጋጋሁ አጣለሁ ብለን ስለምናስብ ነው፡፡

ስለመረጋጋት የተሳሳቱ 4 ምልከታዎች፡

1️⃣ መረጋጋት መዘግየት ነው፡፡ ከተረጋጋሁማ ቶሎ አልደርስም፤ ቶሎ ካልደረስኩ ደግሞ የምፈልገውን አላገገኝም ብለወ የሚያስቡ ሰዎች ሁሌም በጥድፊያ ውስጥ ብቻ ይኖራሉ፡፡
2️⃣መረጋጋት ስንፍና ነው፡፡ አንዳንዶች ስራ መስራት ቶሎ ቶሎ ነው እንጂ የምን መረጋጋት ነው ይላሉ፡፡ ይህም ስህተት የሆነ እሳቤ ነው፡፡
3️⃣መረጋጋት ያደክማል፡፡ ከተረጋጋሁ እደክማለሁ ስለዚህ በፍጥነት ስራዎቼን ላከናውን የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህም በቂ እረፍት ስለማያገኙ ሰውነታቸው ላይ የተከማቸው ድካም ይጠራቀምና ሲረጋጉ ያስታውሳቸዋል፡፡ ላለመስማትም መረጋጋት ያደክማል ብለው ይደመድማሉ፡፡
4️⃣በሌሎች ተጽዕኖ ስር እንውድቃለን፡፡ በመጣደፍና በመቸኮል ውስጥ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ስለማይኖረን ሌሎች ሰዎች በቀላሉ ተጽዕኖ የሚያደርጉብንና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያራምዱብን ሰዎች እንሆናለን፡፡

የመረጋጋት 4 ዋና ዋና ጥቅሞች፡

1️⃣ለማስታወስ ይረዳናል፡ እርጋታ ብዙ ነገሮችን ለማስተዋል ስለሚያስችለን ንብረቶቻችንንና ያቀድናቸውን ነገሮች በተገቢው መንገድ እንድናስታውሰው ያደርገናል፡፡
2️⃣አማራጭ እናገኛለን፡ ማከናወን የምንፈልገውን ጉዳይ ለማድረግ ሌሎች ምርጫዎችን እንድናገኝና የተሻለ ውሳኔ እንድንወስን ይረዳናል፡፡
3️⃣ከራሳችን ጋር እንሆናለን፡ በእርጋታ ውስጥ ሆነን ያመንንበትን ብቻ ለማድረግ እድል እናገኛለን፡፡
4️⃣ስህተቶችን እንቀንሳለን፡ በእርጋታ ውስጥ የተሻለ ዘዴን ስለምናገኝ ትፋቶቻችን ይቀንሳሉ ውጠየታችን ይጨምራል፡፡

ተመስገን አብይ Psychologist
ምክር

ምክር ምንድን ነው?
ምክር ሰዎች የተሻለ የመሰላቸውን ሃሳብ ለሌሎች ማካፈል ማለት ነው፡፡ ሰዎች ይሆናል ያሉትን መፍትሄ፣ ጥያቄ ወይም ተሞክሮ ወይም ሌላ ሀሳብ ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ለምን ይመክራሉ?

1️⃣ ለመርዳት/ ለማገዝ፡ ምክር ሰዎች ያልገባቸው ጉዳይ ግልጽ እንዲሆንላቸው፣ ወዴት መሄድ እንዳለባቸው አቅጣጫ ለመጠቆም፣ የአንድን ነገር ጉዳትና ጥቅም ለመሳየት ወዘተ. ጠቀሜታ አለው፡፡
2️⃣ ግንኙነትን ለማስቀጠል፡ ሰዎች ያላዩትን ገጽ እንዲያዩት ምክር በመለገስ ግንኙነትን ለማስቀጠል ይጠቅማል፡፡
3️⃣ ተጽዕኖ ለማድረግ፡ በአሉታዊ ወይም በአዎንታዊ መንገድ ተጽዕኖ በማድረግ ያሰቡትን ለማሳካት ምክርን እንደ መሳሪያ ይጠቀሙታል፡፡ ጠቃሚነቱ እንደ ጉዳዩ ይወሰናል፡፡
4️⃣ ተቀባይነትን ለማግኘት፡ አዋቂነት ብዙ ማውራት የሚመስላቸው ሰዎች በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲሉ ለረባውም ላረባውም ጉዳይ መካሪ ይሆናሉ፡፡
5️⃣ አለመቻላቸውን ለመሸፈን/ ለመካስ፡ አንዳንድ ሰዎች ሳይሳካላቸው ሲቀር የተለያየ ምክንያትና ምክር በመደርደር ለመሸፈን ይሞክራሉ፡፡ ይህም የተሻለ ማወቃቸውን ወይም ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲሉ የሚያደርጉት ነገር ነው፡፡

ምክር ለምን ያስፈልጋል?

1️⃣ ለውሳኔ በቂ መረጃ ለማግኘት
2️⃣ ምርጫን ለማብዛት፡ ሌሎች እንዴት እንደሚኖሩ ለማወቅና አማራጮችን ለማግኘት ያስፈልገናል፡፡
3️⃣ አቅጣጫን መጠቆም መቻሉ እና
4️⃣ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
ብቻን የመሆን ችሎታ

ብቻን መሆን ብቸኛ መሆን አይደለም፡፡ ብቸኝነት ሰው ማጣት ነው፡፡ ብቻን መሆን ደግሞ ከራስ ጋር ለመሆን የሚወሰድ ግዜ ነው፡፡ ይህም በማንኛውም እኛን በሚመቸን ግዜ ልናደርገው እንችላለን፡፡ ሰፊ ግዜ መሆንም አይጠበቅበትም፡፡ እየተንቀሳቀስን ወይንም አረፍ ብለን ልናደርገው የምንችለው ጉዳይ ነው፡፡

ብቻችንን ስንሆን ምን ልናደርግ እንችላለን? 👇🏻

1️⃣እስካሁን ያሳለፍነውን ህይወት ልንቃኝ እንችላለን፡፡ እንዴት እንዳሳለፍን? ምን እንደተማርን? ምን ስህተት እንደሰራን? ከአሁን ህይወታችን ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው? ወዘተ ልናስብ እንችላለን፡፡
2️⃣ቅርብ የተፈጠሩ ጉዳዮችን ልናስብ እንችላለን፡፡ ያስገረመን ወይም ያበሳጨን ወይም አዲስ ነገር የሆነብንን ክስተት ልናስብ እንቸላለን፡፡
3️⃣ስለወደፊት ህይወታችን ልናስብ እንችላለን፡፡ ወደፊት ማድረግ፤ ማሳካት ስለምንፈልገው ጉዳይና አሁን ምን ላይ እንዳለን? ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ልናስቀምጥ እንችላለን፡፡
4️⃣ስሜታችንን ልናደምጥ እንችላለን፡፡ አሁን የሚሰማንን ስሜት በማድመጥ ሰውነታችንን መረዳት ማለት ነው፡፡
5️⃣ተፈጥሮን ማስተዋል፡፡ እንዲሁ ከራሳችን ጉዳይ ወጥተን በተፈጥሮ ልንደመምና ልንመሰጥ እንችላለን፡፡
6️⃣ዘና ልንል ወይም አረፍ ልንል እንችላለን፡፡

ብቻን መሆን ጤነኝነት ነው፡፡ ነገር ግን ብቻችንን ስንሆን የምናስባቸው ነገሮች አሉታዊ ብቻ ከሆኑ መልስ ያልሰጠናቸውን የግል ጉዳዮች መልስ መስጠት ወይም ወደ ባለሙያ መሄድ አለብን፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
የፍቅር ትርጉም ለወንድና ለሴት አንድ አይነት ነው?
Anonymous Quiz
17%
አወ አንድ አይነት ነው
59%
አይ ይለያያል
15%
ፍቅር ፍቅር ነው በቃ
8%
አላውቅም
የወንድና የሴት ፍቅር

የፍቅር ትርጉም ለወንድና ለሴት አንድ አይነት አይደለም፡
አንዲት ሴት ካፈቀረችው ወንድ የምትጠብቀው ፍቅር እንዲህ አይት ነው፡፡
መጫወት የሚችል፣ ትሁት የሆነ፣ ወንዳወንድ፣ ሁሌም የሚረዳኝ፣ የፍቅር ሰው የሆነ፣ አይኔን እያዬ ለእሱ ቆንጆ እንደሆንኩና ሙሉ እንዳደረኩት የሚነግረኝ፣ ልጅ የሚወድ እና እኔን ሳይጠይቀኝ ቤት ውስጥ ማድረግ ያለበትን የሚያደርግ፡፡ በተጨማሪም የሚያምር ተክለ ሰውነትና ብዙ ገንዘብ ያለው ወዘተ ወዘተ ወዘተ ነው፡፡

እንዲህ አይነት ፍቅር ከወንድ መጠበቅ ፍጹማዊነት ነው፡፡ የመሳካት እድሉም በጣም ጠባብ ነው፡፡

አንድ ወንድ ለሚያፈቅራት ሴት ፍቅሩን የሚገልፀው እነዚህን 3ት ነገሮች በማድረግ ነው፡፡

1️⃣ ፍቅረኛው (ሚስቱ) እንደሆንሽ ለሁሉም ሰው በይፋ ይናገራል፡፡በስምሽ ካስተዋወቀሽ ወይም ጓደኛዬ ናት ካለ ከዚህ ያለፈ ስላንቺ አያስብም ማለት ነው፡፡

2️⃣ የጎደለውን ሁሉ ያሟላል፡፡ ቤትሽ ውስጥ የሌለውን ሁሉ ሊገዛ ይችላል፡፡ ያስፈልገኛል ያልሽውን ነገር ያመጣል፡፡ ሲከፋሽም ይጋብዝሻል ወይም ያዝናናሻል፡፡ ይህን በማድረጉም ፍቅሩን ከመግለፁ ባሻገር የተሻለ የተፈላጊነት ስሜት ይሰማዋል፡፡

3️⃣ በተቻለው ሁሉ ከአደጋ ይጠብቅሻል:: በመጣላት ብቻ ሳይሆን እንዲህ አታድርጊ እያለ ይመክርሻል፡፡ ለምሳሌ ሰውነትሽን የሚያሳይ ልብስ ለብሰሽ ስትወጪ “ይበርድሻል፣ ያምሻል ቀይሪ” ሊልሽ ይችላል፡፡ ይህን እንደጭቅጭቅ ልታስቢው ትችያለሽ ነገር ግን አንቺ ምንም እንዳትሆኝበት ስለሚፈልግ ሲንከባከብሽ እንደሆነ መረዳት አለብሽ፡፡

ስለዚህ የወንድ ፍቅር እንደሴት በማቀፍ፣ በመንከባከብ፣ አብሮሽ በመዋል፣ ወዘተ. የሚገለፅ አይደለም፡፡ የወንድና የሴት ፍቅር ቋንቋ የተለያየ ነው፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
እምቢ የማለት ጥቅም

ለተማሪ ከሚሰጡ የጥያቄ ፈተና አይነቶች ውስጥ አንዱ ምርጫ ነው፡፡ አንዱ ጥያቄ ቢያንስ ሁለት ምርጫ ሊኖረው ይገባል፡፡ ታዲያ አንዱ ምርጫ ብቻ ነው ትክክለኛ መልስ ሊሆን የሚችለው፡፡ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት ደግሞ የግዴታ አንዱን መምረጥ ሌላውን ደግሞ መተው (እምቢ ማለት) አለብን፡፡

በተመሳሳይ መንገድ በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ብዙ ምርጫዎች አሉ፡፡ የስራ ምርጫዎች፣ የፍቅር ምርጫዎች፣ የመኖሪያ ቦታ ምርጫዎች፣ የልብስ ምርጫዎች፣ የሃሳብ ምርጫዎች፣ የንብረት ምርጫዎች፣ የትምህርት ምርጫዎች፣ ወዘተ. አሉን፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ ምርጫዎች ሁሉ ለእኛ የሚሆነውን ማግኘት የምንችለው ለእኛ የማይሆነውን ምርጫ እምቢ አልፈልግም ማለት ከቻልን ነው፡፡

አይሆንም እምቢ የምንለው ጉዳይ ከሌለን ምንም ቦታ ላይ የለንም፡፡
ሁሌ እሺ እያለ የሚኖር ሰው መኖር ያልጀመረ ሰው ነው፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የለውም፡፡

በሰዎች ዘንድ መታመን የምንችለው እምቢ ማለት ከቻልን ነው፡፡ ለመጣው ሁሉ እሺ የሚል ሰው ሃላፊነት ሊወስድ አይችልም፤ የሚሰራበት ግዜ የለውምና ነው፡፡

እምቢ ማለት ምርጫን የማጥበብና የውሳኔ ሰው የመሆኛ መንገድ ነው፡፡ ቅድሚያ የምትሰጡት እምቢ የምትሉት ጉዳይ ይኑራችሁ፡፡

ተመስገን አብይ Psychologist
ግጭትን ማስተናገድ መቻል

“እኔ ከማንም ሰው ጋር መጣላትም ሆነ መቀያየም አልፈልግም!” ሲሉ የምንሰማቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከሰዎች ጋር አብረን እስከኖርን ድረስ ደግሞ ከግጭት መራቅ አንችልም፡፡

ግጭት እንዳይፈጠር ከመታገል ይልቅ ግጭትን የምናስተናግድበትን አቅም መፍጠር ነው ያለብን፡፡

ግጭት ለምን ያስፈልጋል?

1️⃣ ግንኙነትን ለማደስ ያስፈልጋል፡፡
2️⃣ ልዩነትን ለማወቅና ለማክበር ያስፈልጋል፡፡
3️⃣ ያመንበትን ነገር እንድናሳይ እድል ይሰጠናል፡፡
4️⃣ መተማመንን ይፈጥርልናል፡፡
5️⃣ አቅማችንን ለመፈተሸ ይረዳናል፡፡
6️⃣ ሁሌም የሚፈጠር ጉዳይ መሆኑን እንድንረዳ ይጠቅመናል፡፡

ከግጭት ለመሸሽ ከመመሞከር ይልቅ ያመንበትን ነገር ለማሳየት መሞከር የተሻለ ደስታን ይፈጥርልናል፡፡

ግጭት ሁሌም ያለ መልካም ነገር ነው፡፡

ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት!

ተመስገን አብይ Psychologist
መኖርን የሚፈራ ሰው መሞትን ይፈራል፡፡ መኖሩን ትርጉም እየሰጠ ያለ ሰው ደግሞ ሞት ሌላ የመኖር ገፅ መሆኑን ይረዳል፡፡ በየትኛውም ሰዓት በሞት ውስጥ ያለውን ህይወት ለመኖርም ዝግጁ ነው፡፡ በምድር ያልተዘጋጀ እንዴት በሰማይ ይዘጋጃል?
እንድንኖር ተፈጥረን መኖርን የምንፈራው ለምንድን ነው?

ተመስገን አብይ Psychologist
ደስታችን ለምን ይቀንሳል?

ብዙዎች ደስተኛ መሆን እፈልጋለሁ ነገር ግን አልቻልኩም ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ደስተኛ መሆን የምችለው የሚል ጥያቄም በተደጋጋሚ ቀርቦልን ያውቃል፡፡ ቀጥሎ የጻፍንላቸሁ ማንኛውም ሰው ደስተኛ ሊያደርገው የሚችለውን መፍትሄ ነው፡፡
ደስተኛ ለመሆን፡

1️⃣ የግል ጥያቄዎቻችንን መመለስ አለብን፡፡ አንዳንዶቻችን ስለተፈጠርን እንጂ መኖራችን ትርጉም እንዳለው ገብቶን አይደለም የምንኖረው፡፡ ህይወት ለኔ ምንድን ነች? እኔ ምን አይነት ሰው ነኝ? የመጣሁበት መንገድ ምንድን ነው? ምን ተጽዕኖ አደረገብኝ? ወዴትስ ነው የምሄደው? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ መስጠት አለብን፡፡

ደስተኛ የምንሆነው ብዙ ቁሳቁስ ስላከማቸን ሳይሆን የውስጥ ጥያቄዎቻችንን ስንመልስ ብቻ ነው፡፡

2️⃣ በተግባር የምንኖር ሰዎች መሆን ይገባናል፡፡
ደስታ ከሃሳብ ይልቅ ከተግባር ይቀዳል፡፡ ነገሮችን መሞከር፣ መጋፈጥ፣ ማድረግ መቻል በጣም ደስተኛ እንድንሆን ብሎም ጤናችን የተጠበቀ እንዲሆን ያደርገናል፡፡

ስለዚህ ወሬያችንን ቀነስ እናድርግና በተግባር እንሞክር ከዛም ያደረግነውን እናወራለን፡፡


ተመስገን አብይ Psychologist
ሰውን ምን ብላችሁ ትገልፁታላችሁ?
Anonymous Poll
65%
ክቡር
3%
ክፉ
33%
የማይታወቅ
8%
አስመሳይ
8%
አልተጠቀሰም
2025/02/15 15:04:42
Back to Top
HTML Embed Code: